MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Share

ይህ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ነው።

This page is aimed at informing the public both in Ethiopia and the rest of the world about Ethiopia's foreign relations by focusing on the activities of the Federal Democratic Republic of Ethiopia's Ministry of Foreign Affairs.

05/06/2026

ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ እ.ኤ.አ. ጁን 3 ቀን 2026 ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ጋር ተወያዩ፡፡

ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ከሆኑት ክቡር OUE Sadamasa ጋር ተገናኝተው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አገራችን እያስመዘገበች ስላለው ከፍተኛ የልማት ዕድገት፣ ዕድገቱን ለማስቀጠል ስለተወሰዱ የሪፎርም ዕርምጃዎች፣ በሪፎርሙ ትኩረት ስለተሰጣቸው ጉዳዮች፣ የባህር በር ለማግኘት እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ የራስን ሃብት በማልማት የአገራችንን ብሎም የቀጣናውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ስለሚደረገው አፍራሽ እንቅስቃሴ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሃይሎች የኢትዮጵያን ብልጽግና ሰላም ወደኃላ በመጎተት ወደ ጦርነት ለማስገባት እያደረጉት ስላለው እኩይ እንቅስቃሴ እንዲሁም በአገራችን ስለተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በስፋት አስገንዝበዋል፡፡ ትንኮሳው በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች እንዲወገዝ የጃፓን መንግስት ድጋፍንም ጠይቀዋል፡፡

ልዩ አማካሪው በበኩላቸው የኢኮኖሚ እድገት የሚመዘገበውና የህዝቦች ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው ሰላምና ጸጥታ ሲጠበቅ እንደሆነ እና ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የምትጫወተው ሚና የሚደነቅ መሆኑን በመጠቆም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ጃፓን የምትደግፈው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ለመጠቀም እና የባህር በር ለማግኘት በሰላማዊ መንገድ የምታደርገውን ጥረት ጃፓን እንምትደግፍና በውይይቱ የተነሱ ጉዳዮችን ለአገሪቱ ክቡራን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር እንደሚያስረዱ ገልጸዋል፡፡

Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 04/06/2026

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት ለባቡል ኸይር ሀገር በቀል ድርጅት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን መሰረት ባደረገ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት የበጐ ድጋፍ ሰራዎችን በማከናወን ዜጐችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተግባራትን ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ በዛሬው እለት በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎትና የእርዳታ ተቋም በአካል በመገኘት ልዩ ልዩ የቁሳቁስ ድጋፎችን አድርጓል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽሕፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኡባህ መሀመድ በዕለቱ በተካሄደው የድጋፍ ስነ-ስርዓት ላይ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መርህ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች የተገኙ ቁሳቁሶች ለድርጅቱ አበርክተዋል።

የተደረገው የአይነት ድጋፍም አልባሳትን፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም ለተማሪዎች የሚሆኑ የትምህርት መገልገያ መሣሪያዎችን ያካተተ ሲሆን፤ ቁሳቁሶቹ በደቡብ ኮሪያ እና በህንድ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች የተገኙ መሆናቸውን የጽሕፈት ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኡባህ መሀመድ ገልጸዋል።

መንግስት ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም ሴቶችን፣ ህጻናትን እና አረጋውያንን ለመደገፍ የሚያደርገውን ሀገር አቀፍ ጥረት የሚደግፉ እንደ ባቡል ኸይር ያሉ የሲቪክ ማህበራት የሚያከናውኑት ተግባር እጅግ የሚደነቅና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ወ/ሮ ኡባህ በጉብኝቱና በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ገልጸዋል።

አክለውም ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ህይወት መለወጥ እና መደገፍ የአንድ አካል ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ትብብር የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አሳስበው፣ “መስጠት አያጎድልም፤ ሰጪና አመስጋኝ ትውልድ ሁልጊዜም አትራፊ ነው” ብለዋል።

የባቡል ኸይር የእርዳታ እና የእናቶች መልሶ ማገገም ድርጅት ለብዙዎች የስራ እድልን ከመፍጠር አንፃር ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ገልፀዋል።

ድርጅቱ ለአቅመ ደካሞች እና ለተማሪዎች ከሚያደርገው የምገባ ስርዓት በተጨማሪ፣ የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት ከተረጅነት ወጥተው የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ወይም በሰለጠኑበት ሙያ ተቀጥረው ራሳቸውን እንዲመሩ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።

Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 04/06/2026

"የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።"

ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

03/06/2026
Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 02/06/2026

"ከመ/ቤታችን ከፍተኛ አመራሮች፣ በመከከለኛው ምስራቅ፣ እስያና ፓሲፊክ አገሮች ከሚገኙ የሁሉም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚሲዮኖች መሪዎችና ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ጋር በመሆን የ9 ወራት የዜጎቻችን የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አፈጻጸምን በተመለከተ ውይይት አካሂደናል።

በውይይታችን በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚገኙ ዜጎቻችንን መብት እና ክብር አስጠብቆ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አንጻር ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሚሲዮኖችና ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቶች የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም በጋራ ገምግመናል።

በጋራ መድረኩ አገራችን በምትከተለው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ ስር በመካከለኛው ምስራቅና በሁሉም ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ዜጎቻችን በህጋዊ መንገድ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው፣ ክብርና መብታቸው ተጠብቆ እራሳቸውንና አገራቸውን መጥቀም እንዲችችሉ በተቋማችን፣ በሁሉም የኢፌዲሪ ሚሲዮኖችና ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቶች እንዲሁም በኢፌዲሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚደረጉ ቅንጂታዊ አሰራሮችን የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የገራ መግባባት ላይ ተደርሷል። "
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ

02/06/2026

"ማየት ማመን ነው - መጥታችሁ እዩ።"
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 02/06/2026

"‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።

‎ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።"
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

02/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 27/05/2026

"በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ዛሬ ተመርቋል።
‎በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57.6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው። ማዕከሉ የቦረናን ህዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።"
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Photos from MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር's post 27/05/2026

"ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦትፕሮጀክት ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ሕይወት እየቀየረ ይገኛል።

‎በብዙ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ የቧንቧ መስመሮችን፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየገነባን ሲሆን ይህም ድርቅን ከመመከት የላቀ ፋይዳ አለው።
‎የሕዝብ ጤናን እየጠበቅን፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም እያጠናከርን መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን።"
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Menelik II Avenue, P. O. Box Addis Ababa
Addis Ababa
393

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30