Amanuel mental specialized hospital

Amanuel mental specialized hospital

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amanuel mental specialized hospital, Addis Ababa ethiopia Addis ketema subcity at the vicinity of Mesalemeya, Addis Ababa.

Emmanuel mental specialized hospital is apionner one which provides mental health care and treatment for about people who are from all corners of the nation and mental health rehabilitation services since it has been established in 1938

Photos from Amanuel mental specialized hospital's post 04/06/2026

አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ የፓናል ውይይት አካሄደ
​አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም(አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) - አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በየዓመቱ በግንቦት ወር የሚከበረውን የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ሳሬም ሆቴል በፓናል ውይይትና ፕሬስ ኮንፍረንስ አክብሮ ዋለ።
የዘንድሮው የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር "አእምሮ ጤና ለሁሉም፤ ማህበረሰባዊ ኃላፊነትና የጋራ መፍትሄ" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ አጋር አካላት እንዲሁም የአእምሮ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይትና የፕሬስ ኮንፍረንስ ተከናውኗል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ በአእምሮ ጤና ጉዳዮች ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ አድልዎና መገለልን ለመቀነስ እንዲሁም በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶችን ለመቀየስ ያለመ ነው።
መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክብሮም ሃይሌ የአእምሮ ጤናችንና አካላዊ ጤናችን ፍፁም የተቆራኙ በመሆናቸው የአንደኛው ክፍል መጎዳት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሌላኛውን ሊጎዳው እንደሚችል ገልፀው አዕምሮ በጣም ረቂቅ ስለሆነ ልዩ የሆነ የጤና ክትትል ሊደረግለት የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም መላ ጤንነታችንን በሚገባ መጠበቅ ለአዕምሮ ጤና እጅግ ወሳኝ መሆኑንም አብራርተዋል።
​በሌላ በኩል በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች እንደገለጹት የአእምሮ ጤና ጉዳዮች እንደ አካላዊ ጤና ሁሉ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ መሆኑን በተለይም የአእምሮ ጤና እክል የደረሰባቸው ወገኖች ላይ የሚደርሰው ማህበረሰባዊ መገለል ችግሩን ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው ገልፀው ይህንን ተግዳሮት ለመቅረፍም የግንዛቤ ስራዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አመላክተዋል።
​በመጨረሻም የአእምሮ ጤና አገልግሎትን ተደራሽ እና ጥራት ያለው ለማድረግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የራሱን የአእምሮ ጤና ከመጠበቅና ከመንከባከብ ባሻገር የአእምሮ እክል ያጋጠማቸውን ወገኖች ልዩ ፍቅር፥ ድጋፍና ክብካቤ በመስጠት የአእምሮ ጤና ማጎልበት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በአጽንኦት ተመላክቷል።

27/05/2026
Photos from Amanuel mental specialized hospital's post 21/05/2026

በድንገተኛና ወሳኝ ክብካቤ ላይ ያተኮረ የፅንሰ-ሃሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጠ
​አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)፦ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለጤና ባለሙያዎቹ ያዘጋጀው በድንገተኛና ወሳኝ እንክብካቤ አያያዝና አተገባበር ላይ ያተኮረ የፅንሰ-ሃሳብና የተግባር ስልጠና በአዳማ ከተማ ሰጠ።
​ከግንቦት 10 እስከ 13/2018 ዓ.ም ድረስ በተሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ ከሆስፒታሉ የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የድንገተኛ ህክምና ዲፖርትመንት ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሚክያስ ጥላሁን እንደተናገሩት ድንገተኛ አደጋዎች አስቀድመው አይቀጠሩም። የአየር መተላለፊያ መዘጋት፣ ድንገተኛ የልብ መቆም፣ የደም ግፊትና የደም ዝውውር መዛባት በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶች ናቸው። በእንዲህ አይነት አስጨናቂ እና በሕይወትና በሞት መካከል ባሉ ደቂቃዎች ውስጥ ልዩነቱን የሚፈጥረው የሕክምና መሣሪያው መኖር ብቻ ሳይሆን መሣሪያውን በልበ-ሙሉነትና በጥራት መጠቀም የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖሩ ነው።
​ለዚህም ነው ይህንን ሥልጠና እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊ የሚያደርገው በማለት ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መኮንን አስፋው በበኩላቸው አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአገሪቱ የአእምሮ ጤና ሕክምና ላይ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም የአእምሮ ጤና እክሎችና ሕክምናዎች በራሳቸው ከተለያዩ ድንገተኛና አፋጣኝ የውስጥ ደዌ ወይም የአካል ጉዳት አደጋዎች ጋር የመገናኘት ዕድላቸው ሰፊ ነው በመሆኑም ማንኛውም ታካሚ ወደ ተቋማችን ሲመጣ የአእምሮ ጤና ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ሙሉና አስተማማኝ የሕክምና ዋስትና የመሻት መብት ስላለው ሆስፒታሉ በሰው ሃይልና በህክምና ቁሳቁስ የመደገፍና የማጠናከር ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል።

​ስልጠናው በዋናነት ባለሙያዎቹ ድንገተኛና አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የሚሰጡትን ምላሽ ይበልጥ ፈጣን፣ ስልታዊና ሳይንሳዊ ለማድረግ የታለመ ሲሆን
የአደጋ ጊዜ ታካሚዎችን ሁኔታ በፍጥነት መገምገምና የደም ዝውውር መዛባትን በፈጣን ህክምና ማረጋጋት፤ የመተንፈሻ አካል ችግር ላጋጠማቸው ታካሚዎች የላቀ የአየር መተላለፊያ መክፈቻ ዘዴዎችን መጠቀምና በመተንፈሻ መሳሪያ መደገፍ፤ መሰረታዊ የህይወት ድጋፍ ፣ የላቀ የልብና የደም ቧንቧ ህይወት ድጋፍ እንዲሁም አውቶማቲክ ውጫዊ ዲፊብሪሌተር (AED) መሳሪያን በመጠቀም የልብና የመተንፈስ ችግር ያጋጠማቸውን ታካሚዎች ህይወት ማዳን ላይ ትኩረት አድርጎ ተሰጥቷል። በተጨማሪም የስኳር በሽታ ኬቶአሲዶሲስ እና ሃይፐርኦስሞላር ሃይፐርግሊሴሚክ ሁኔታ ማለትም ከፍተኛ የሆነ የደም ስኳር መጠን መጨመር የሚያስከትሏቸው እና አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልጋቸው አደገኛ የስኳር በሽታ ውስብስብ ችግሮች ላይ ምልክቶችን ተረድቶ ስለሚደረግ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ የስልጠናው አካል ተደርጓል።
​ ስልጠናው ባለሙያዎቹ ያላቸውን የንድፈ-ሃሳብ እውቀት በተግባራዊ ልምምድ እንዲያበለጽጉ ያስቻለ ሲሆን በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ጥራትና ዝግጁነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተገልጿል።
conceptual andppractical trainingon eemergencyand ccritical care provided​Addis Ababa; May 13/2018 E.c (EMSH): Emmanuel Mental Specialized Hospital provided a concept and practical training on emergency and critical care management and implementation for its health professionals in Adama city.
​Health professionals from the hospital participated in this training, which was given from May 10 to 13/2018 E.c. At the opening of the training, Dr. Mikyas Tilahun, Head of the Emergency Department, said that emergencies are not planned in advance. Airway obstruction, sudden cardiac arrest, blood pressure and circulatory disorders are threats that can occur at any time and place. In such a stressful and life-and-death situation, the difference is not only in the availability of medical equipment, but also in the availability of trained personnel who can use the equipment with completeness and quality.
​That is why he said that this training is very important and timely.
The hospital’s cchiefof sstaff,Ato Mekonnen Asfaw, for his part, said that Emmanuel Mental Specialized Hospital is known to be a leading hospital in mental health treatment in the country. However, mental health disorders and treatments themselves have a high chance of being associated with various sudden and urgent internal diseases or physical injuries. Therefore, when any patient comes to our hospital, he said that he has the right to seek not only mental health support but also complete and reliable medical care, so the hospital will work to support and strengthen it with human resources and medical equipment.

​The training is primarily aimed at making the response of professionals to patients in need of emergency and urgent medical care more rapid, systematic and scientific.
Rapid assessment of emergency patients and stabilization of circulatory disorders with rapid ttreatment,use of advanced airway management and ventilator support for patients with respiratory pproblems,basic life support, advanced cardiovascular life ssupport, and the use of automated external defibrillator (AED) devices were focused on saving the lives of patients with cardiac and respiratory problems. In addition, the training focused on understanding the symptoms of diabetic ketoacidosis and hyperosmolar hyperglycemic state, which are dangerous complications of diabetes that cause high blood sugar levels and require urgent treatment.
​ The training has enabled the professionals to enrich their theoretical knowledge with practical experience and has contributed significantly to improving the quality and preparedness of emergency medical services provided at the hospital.

19/05/2026

አካላዊ ጤናችንን እንደምንከባከበው ሁሉ... የአእምሮ ጤናችንስ?
ጉንፋን ሲይዘን፣ ጥርሳችንን ሲያመመን ወይም ሰውነታችን ሲደማ ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድ አንገደድም። ታዲያ ለምን የአእምሮ ጫና፣ ከልክ ያለፈ ጭንቀት ወይም የስሜት መዋዠቅ ሲያጋጥመን ለብቻችን እንሰቃያለን?
​የአእምሮ ጤና ችግር የድክመት ወይም "የማሰብ አቅም ማነስ" ምልክት አይደለም። ልክ እንደ ማንኛውም የአካል ህመም ሁሉ የህክምና፣ የባለሙያ ምክር እና የማህበረሰብ ድጋፍ የሚያስፈልገው ተፈጥሯዊ ክስተት ነው።

​📌 ዛሬውኑ፦
• ​የሚሰማዎትን ስሜት ለሚያምኑት ሰው ያካፍሉ።
• ​ከመጠን በላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጭንቀት ካለ ባለሙያ ለማማከር አይቆጠቡ።


​እውነታ እና ህሊናዊ እሳቤ ስለ አእምሮ ጤና 🧐💡
​❌ የተሳሳተ እሳቤ (Myth): የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ሰነፎች ወይም ጠንካራ ስብዕና የሌላቸው ናቸው።
✅ እውነታው (Fact): የአእምሮ ጤና ችግር ማንም ሰው ላይ ሊደርስ የሚችል፣ ከባዮሎጂያዊ (ጂን)፣ ከህይወት ተሞክሮ እና ከአካባቢያዊ ጫናዎች ጋር የተያያዘ የጤና እክል ነው።
​❌ የተሳሳተ እሳቤ (Myth): የአእምሮ ጤና ችግሮች አይድኑም፣ አንዴ ከተከሰቱ ዘላቂ ናቸው።
✅ እውነታው (Fact): በቂ የባለሙያ ምክር፣ የስነ-ልቦና ህክምና እና ተገቢው ድጋፍ ከተደረገ ሰዎች ሙሉ በሙሉ አገግመው ንቁና ምርታማ ህይወት መምራት ይችላሉ።
​💬 እርስዎስ በአካባቢዎ በብዛት የሚሰማው የተሳሳተ እሳቤ የትኛው ነው? በኮሜንት ያጋሩን።

Photos from Amanuel mental specialized hospital's post 15/05/2026

የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቴሌ-ሳይካትሪ አገልግሎት ማስተግበሪያ ጋይድላይን ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለፀ
​አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2018 (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአእምሮ ጤና አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያስችለውን የቴሌ-ሳይካትሪ (Tele-psychiatry) የአሰራር መመሪያ (Guideline) አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ዶ/ር ሉሉ በቃና የሆስፒታሉ የስነ አእምሮ ህክምና አገልግሎት የዲፓርትመንት ሃላፊ እንደተናገሩት የቴሌ ሳይካትሪ አገልግሎት መጀመር የአእምሮ ጤናን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል። አክለውም ብዙ ሰዎች በአእምሮ ጤና ተቋማት በአካል ተገኝቶ መታየትን ሊፈሩ ይችላሉ። የቴሌ ሳይካትሪ አገልግሎት ታካሚው ባለው ምቹ ቦታ (ቤት ወይም የግል ክፍል) ሆኖ ህክምና እንዲያገኝ ስለሚያደርግ ሰዎች ሳይሸማቀቁ የባለሙያ እርዳታ እንዲጠይቁ ያበረታታል በማለት ገልፀዋል።
የአሰራር መመሪያው ተቋሙ ወደ ዲጂታል የአሰራር ስርዓት ለመሸጋገር ለጀመረው ጥረት ትልቅ እምርታ ሲሆን በተለይም በቦታ ርቀው ለሚገኙ ታካሚዎችና በአካል ሆስፒታል መገኘት ለማይችሉ ዜጎች ምቹ አማራጭን ይፈጥራል።
ሆስፒታሉ ያጠናቀቀው ይህ መመሪያ አገልግሎቱ በምን መልኩ መሰጠት እንዳለበት፣መሟላት ያለባቸው ቴክኖሎጅዎችና መሠረተ ልማቶች፥ የታካሚዎች የጤና መረጃ ሚስጥራዊነት አጠባበቅ፣ የክፍያ ስርዓት እና የባለሙያዎችን የስራ ድርሻ በግልጽ የሚያስቀምጥ ነው።
​አገልግሎቱ ሆስፒታሉ በቅርቡ በስፋት እየተገበረው ካለው የወረቀት አልባ (Paperless) አሰራር እና ከኤሌክትሮኒክ የህክምና መረጃ ስርዓት ጋር ተሳስሮ የሚሰራ ነው። ይህም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በቪዲዮ፣ በድምጽ ወይም በጽሁፍ መልዕክት የባለሙያ ምክርና ክትትል እንዲያገኙ መንገድ ይከፍታል።
በመጨረሻም መመሪያው ተጠናቆ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ በመሆኑ በቀጣይ የቴክኒክ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅና ለባለሙያዎች አስፈላጊውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት አገልግሎቱ በይፋ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

Photos from Amanuel mental specialized hospital's post 13/05/2026

የአለም የእጅ ንፅህና አጠባበቅ ቀን በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በልዩ ሁኔታ ተከበረ
​አዲስ አበባ፦ግንቦት 5/2018ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) የ2026 የዓለም የእጅ ንፅህና አጠባበቅ ቀን መሪ ቃል "Action saves lives" ''ድርጊት ህይወትን ያድናል''
''እጅዎን ይታጠቡ" በሚል መሪ ቃል በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ዋለ። ዕለቱ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከናወነ የእጅ መታጠብ ስነስርዓት እና በባለሙያዎች በተመራ የፓናል ውይይት ታስቦ ውሏል።
በዕለቱ የሆስፒታሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በተገኙበት የተግባር የእጅ መታጠብ ስነስርዓት ተከናውኗል።
ከንፅህና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ሰፊ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይም በአእምሮ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ኢንፌክሽኖችን የመከላከል ስልቶች፣ የእጅ ንፅህና አጠባበቅ በታካሚዎች ደህንነት ላይ ያለው ፋይዳ እና የጤና ባለሙያዎች በስራ ገበታቸው ላይ ሊከተሏቸው የሚገቡ የንፅህና መስፈርቶች ላይ ጥልቅ ትንተና ቀርቧል።

የሆስፒታሉ የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መኮንን አስፋው ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ንፅህናን መጠበቅ ከሙያዊ ግዴታ ባለፈ የታካሚዎችን ህይወት የመታደግ ስራ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። በተለይም እንደ አማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባሉ ልዩ ትኩረት በሚሹ የህክምና ተቋማት ውስጥ የኢንፌክሽን መከላከል ስራ ለጥራት አገልግሎት ቁልፍ ተግባር መሆኑንም አክለዋል።
በዓለማችን ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቀላሉ ሊከላከሏቸው በሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች ይጠቃሉ። በተለይም በጤና ተቋማት ውስጥ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች ለታካሚዎች ደህንነት ትልቅ ስጋት ናቸው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ እጅን በትክክል በሳሙና እና በውሃ መታጠብ እነዚህን ስጋቶች ከግማሽ በላይ የመቀነስ አቅም አለው።
በመሆኑም በጤና ተቋማት ውስጥ የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የእጅ ንፅህና ቀዳሚውና ውጤታማው መንገድ መሆኑን በአፅንኦት ተመላክቷል።

10/05/2026

የቤተሰብ መሰረት፣ የፍቅር ምንጭ ለሆናችሁ እናቶች ሁሉ መልካም የእናቶች ቀን ይሁንላችሁ!"

Photos from Mental wellness የአእምሮ ጤና's post 07/05/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

http://WWW.amsh.gov.et/

Address


Addis Ababa Ethiopia Addis Ketema Subcity At The Vicinity Of Mesalemeya
Addis Ababa