Gullele woreda 9 communication

Gullele woreda 9 communication

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gullele woreda 9 communication, Government Organization, Addis Ababa.

05/06/2026
Photos from Gullele woreda 9 communication's post 04/06/2026

በሁሉም ፈጣሪ አምላክ ረድቶን 7ኛውን ዙር ምርጫ ባጠናቀቅንበት ማግስት ዛሬ 8ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ዛሬ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ባለ 7 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ 96 ተገልጋዮችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግዱ መስኮቶች ያሉት፣ በ22 ተቋማትና በ114 አገልግሎቶች ስራ አስጀምረናል።

ማዕከሉ ከፍ ባለ ጥራት እጅግ ውብ፣ ፅዱ፣ አካታች የሆነ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ፣ የህፃናት ማቆያ ያለው፣ ለሰራተኞችም ለተገልጋዮችም ምቹ ሆኖ የተገነባ ነው።

በቀጣይም በርካታ አገልግሎቶችን ወደ መሶብ ማዕከል በማስገባት ነዋሪዎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ እናደርጋለን።

የከተማችን ነዋሪዋች መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት ለዘመናት አስልቺ ከነበረውና ውጣ ውረድ ከበዛበት እና በእጅ መንሻ ከተማረራችሁበት ቢሮክራሲ የሚያላቅቃችሁ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! በማዕከላቱ በቦታ ሳትገደቡ በሚቀርባችሁ በየትኛውም ማዕከል በመገኘት ተገልገሉ።

ይህ ማዕከል ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር ያስተባበራችሁትን በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

04/06/2026

ጉለሌ የእንጦጦ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለቱሪዝም መስህብ የሆነና ዜጎችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ያደረገ ፤ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ፤አስደማሚ የእጅ አሻራዎች የስራ ውጤት የሆነውን የልማት ፕሮጀክችት ይጎብኙ!!

03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

Photos from Gullele woreda 9 communication's post 02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች !!

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚመራውን ሕጋዊ መንግሥት ለማቋቋም ያለው ጉጉት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ትልቅ አስረጅ ሆኖ በፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተመዝግቧል።

የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ህዝብ አስተሳሰብ ነው።

የጉለሌ ነዋሪውም በየአካባቢው ወደሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በማምራት የተለጠፉትን ውጤቶች በጉጉት እየተመለከተ ይገኛል።

Photos from Gullele woreda 9 communication's post 02/06/2026

የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች ፕሮጀክት በውስጡ ምን ይዟል፦

👉 597 ሄክታር ቦታ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት፤

👉 15 ሄክታር መሬትን በማልማት በአረንጓዴ ተሸፍኗል፤

👉 የ210 ቀፎ ዘመናዊ የንብ እርባታ፤

👉 የአበባ እና የእጽዋት ጋርደኖች ልማት፤

👉 የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ግንባታ፤

👉 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤

👉 8 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤

👉 6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፤

👉 4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ፤

👉 2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ግንባታ፤

👉 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች ዕድሳት ፤

👉 39 የውሃ መከላከያ ግድቦች ግንባታ (ቼክ ዳም) ወዘተ... በስጡ አጠቃልሎ ይዟል።

Photos from Gullele woreda 9 communication's post 02/06/2026

ዛሬ የተመረቀው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት (በምሥል)

02/06/2026
Photos from Gullele communication-ጉለሌ's post 02/06/2026
Photos from Gullele woreda 9 communication's post 02/06/2026

‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።

‎ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa