Eka Kotebe General Hospital

Eka Kotebe General Hospital

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eka Kotebe General Hospital, Government Organization, Addis Ababa.

08/12/2024

እንኳን ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አደረሳችሁ ። "አገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት"

06/12/2024

የፀረ ወባ ትንኝ መድሀኒት ርጭት በማካሄድ የወባ በሽታን ይከላከሉ ይህም እርስዎና ቤተሰብዎ በበሽታው በቀላሉ እንዳይጠቁ ይረዳል።

02/12/2024
Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 27/11/2024

በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ የሆኑት አዲስ አደራው በአደረባቸው ህመም በህክምናሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም አርፈዋል ።ሆስፒታሉም ፣ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹእንዲሁም ለአጠቃላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች መፅናናትን ይመኛል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 22/11/2024

የህልም ጉልበት፤ ለዕምርታዊ ዕድገት!በሚል መሪቃል ኤካኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች ለፌዴራል ተቋማት የመንግስት ሰራተኞችበተዘጋጀ የመወያያ ሰነድእና በሆስፒታሉ በ100ቀን የተከናወኑ ተግባራቶች ሪፖርት ቀርቦ በ13/3/2017 ጥልቅ ውይይት በሆስፒታሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።

የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት ሰነድ በዝርዝር በገለፃ ያቀረቡት የሆስፒታሉ ምክትል ስራ አስኪያጅአቶ ዳዊት ኪዳኔ ሲሆኑ በውይይቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ አስፈላጊነትን አስመልክቶ ሁሉንም አካታች ሃገራዊ ህብረብሄራዊ ፓርቲ የመመስረት፤ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችልና የሃገረመንግስት ቅቡልነትን ለማሳደግ የሚያስችል፤ የጋራ ህልምና ይህን የጋራ ህልም ዳር ለማድረስ የሚችል ፤ የሃገረመንግስትና የብሄረመንግስት ቅቡልነትን ለማፅናት የሚያስችል የወል ትርክት ለመገንባት የሃገራዊ ፓርቲ አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን አብራርተዋል፡፡አያይዘውም የብልፅግና ፓርቲ ትሩፋቶችና ተግዳሮቶች በፖለቲካዊ፤ ኢከኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በተመለከተ የህልም ጉልበትን ለእምርታዊ እድገት መጠቀም ላይ የመንግስት ሚና፤ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ሚና፤ የመንግስት ሰራተኛ ሚና ምን መሆን እንደሚገባው በማብራራት የተጀመረውን የፖለቲካ ሪፎርም ወደ እምርታ ማሸጋገርና የተቋም ግንባታ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተው በመጨረሻም ትኩረት ተሰጥቶ የተነሳውና የጋራ ህልም ሊሆን ይገባል ያሉት አገልጋይ አመራርና የሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ተጠናክሮ ሊቀጥልና የመልካም እሴቶቻችን አካል ሊሆን እንደሚገባተገልጿል፡፡የሆስፒታሉ100ቀን እቅድ አፈፃ
ፀም በዋና ስራ አስከያጅ ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋየ ቀርቧል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 06/11/2024

የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ በኤካኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ግቢ ለ ሰራተኞች ከየካ ወረዳ 12 ስቪል ምዝገባ እና ንዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር እየተሰጠ ይገኛል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 03/11/2024

26ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ በጋሞ የባህል አዳራሽ ኤካኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሰሩ ስራዎች በኤግዚቪሽኑ ተጎብኝተዋል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 29/10/2024

ሰላማችንን እያስጠበቅን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንሰራለን!🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ሰራተኞች በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ 100 ቀናት ሃገራዊ የሪፎርምና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ዙሪያ በሆስፒታሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ በ19/2/2017 ዓ.ም ጥልቅ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ለሆስፒታሉ አጠቃላይ ሠራተኞች የመጀመሪያ 100 ቀናት ሃገራዊ ሪፎርምና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ የውይይት መነሻ ሃሳብ ገለፃ ያቀረቡት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋየ ሲሆኑ ሀገራችን የያዘችውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርምና በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈፃፀም ያመጣውን ሁለንተናዊ እድገት አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡ አያይዘውም የሪፎርሙ አንዱ አካል የሆነው የውጭ ጉዳይ ግንኙነትን አስመልክቶ ሃገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነትና ተጠቃሚነቷ እየጎላ የመጣ መሆኑንና ከዶላር ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን የግብይትና ዋጋ ግሽበት ሌሎችን የግብይት መንገዶችንና አማራጮችን የቀየሰ ነው ብለዋል፡፡
በ2017 ዓ/ም የኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለይም በተመረጡ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፎች በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በአገልግሎት ዘርፎች ፤በኢንቨስትመንት እና አጠቃላይ የግብርና አገራዊ እድገት የአለም አቀፍ ሪፖርትን ዋቢ በማድረግ አብራርተዋል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 25/10/2024

የሀዘን መግለጫ የሆስፒታላችን የምርምርና ስልጠና ፀሀፊ የነበሩት ወ/ሮ በሰልፍ ዋይ ደርቤ በአደረባቸው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ኤካኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታልም የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቿ፣ለወዳጅ ዘመዶቿእና ለሆስፒታሉ ሰራተኞች መፅናናትን እንመኛለን::

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 17/10/2024

"በስራ ቦታችን ላይ የአእምሮ ጤናን ቅድሚያ የምንሰጥበት ጊዜው አሁን ነው!" በሚል መሪቃል ኤካኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታልየአለም የአእምሮ ጤና ቀንን በደማቅ ፕሮግራም አከበረ። በዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉ ቀን ተስፋየ እንደተናገሩት ሰራተኞች አብዛኛውን ጊዜያቸውን በስራቦታ የሚያሳልፉ በመሆናቸው የስራ ከባቢን ምቹ በማድረግ እና የሀላፊና ሰራተኞች መልካም ግንኙነት በመፍጠር ሰራተኞች የአእምሮ ጤናቸው ተጠብቆ ውጤታማና አምራች እንዲሆኑ ተደስተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሆስፒታሉ ለታካሚዎችና ለሰራተኞች ምቹ ከባቢ እንዲኖረው ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን ፅዱ የጤና ተቋማት ኢኑቤሽን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ እና እድሳቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ምቹ ሆስፒታል እና በተለያየ ቴክኖሎጅ የተደገፈ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ሀላፊው ተናግረዋል። በፕሮግራሙም ከጤና ሚኒስቴር፣ከአዲስ አበባ እና ፌደራል ሆስፒታሎች፣ ጤና ተቋማት ተወካዮች፣የአዲስ አበባ አእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበራትእና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌአካባቢ በሚገኘው ቸኪን ሆቴል ተከብሯል።

Photos from Eka Kotebe General Hospital's post 14/10/2024

"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ🇪🇹

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa