25/10/2025
ትምህርት ለትውልድ
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተጨባጭ ዉጤት ለማምጣት የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።
ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን
በኮልፌ ወረዳ 06 የማነብርሀን 1ኛና2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018ዓ.ም የተማሪዎችን የመማር ማስተማር ሂደትና በተማሪ ስነ ምግባር መሻሻል ዙሪያ ከተማሪ ወላጅና የትምህርት ቤት አመራር ጋር ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አንበሴ ነጋሽ እንደገለጹት ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለዉ ድጋፍ አመስግነው በ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን በትኩረት በመያዝ ብቁና የተሻለ ውጤት የሚያመጡ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልፀው፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተጨባጭ ዉጤት ለማምጣት ተማሪዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የተማሪ ውጤት ለማምጣት የሁላችንም ሀላፊነት ነው በማለት በ2017 በጀት አመት ከሌላ ጊዜ የተሻለ ውጤት ማምጣት ቢቻልም በተፈለገውን ልክ ውጤት ለማምጣት ባለመቻሉ የተነሳ ለቀጣይ ይህን ችግር ለቅሞ በማውጣት ሁሉም መምህራንና የተማሪ ወላጅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የተፈለገውን የተማሪ ውጤት ለማምጣት ከጀምሩ መስራት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስራዎችን በማጠናከር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል አኳያ በተማሪዎች ምቹና የተሟላ የመማር ማስተማር አካባቢ ለመፍጠር ከሚሰሩ ስራዎች ብዙ የቤት ስራ መኖሩን ያሳያል ብለዋል።
ወላጆች የልጆችን የትምህርት ክትትል እና ውጤት በየጊዜው መመልከትና ፈተናቸውን ማየት እና ከወዲሁ ጅምር ላይ መስመር ማስያዝ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልፀዋ ል::
25/10/2025
የወረዳ አስተዳደር የ120 ቀናት ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የፓርቲ ስራዎችና አፈፃፀም በጠቅላላ አመራር ተገመገመ።
በግምገማውም የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ ይርጋ እንደተናገሩት አመራሩ በ120 ቀን እቅድ ስራዎች የተሰጠውን ተልዕኮ በመውሰድ በትኩረት በመያዝ የስራ እድል ፈጠራ ፤የሌማት ትሩፋት ተግባራት ፣በተቀናጀ አግባብ በመስራት ውጤታማ ስራ ማከናወን ይገባል ብለው በተጨማሪ ሌሎች የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎችን በማስተሳሰር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ናተአ በበኩላቸው የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ120 ቀናት ዕቅድ ለማሳካት አመራሩ በሁሉም መስክ ተሰማርተው እየሰራ ያለዉ ስራና አጠናክሮ በማስቀጠል ስራ አጦችን ልየታና ምዝገባ ፣የስራ እድል ፈጠራን ማጠናከር፣ በሌማት ትሩፋት ተግባራትን በተመለከተ የቤተሰብ ቢዝነስ ላይ እንዲሁም ሞዴል ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 15/2018
25/10/2025
የሰንበት ገበያ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ተጠናክሮ ቀጥሏል
ጥቅምት 15/2017ዓ.ም
ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የሰንበት ሳምንታዊ ገበያ በቤተል ፓስታ ቤት እና በወይራ አደባባይ ተጠናክሮ መቀጠሉን በምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል።
ሳምንታዊ የሰንበት ገበያ የግብርና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት በማቅረብ ለሸማች ማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ወድነትን ለመቅረፍ እና ገበያውን ለማረጋጋት በኩል ጉልህ ሚና ስለአለው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።
በአደረገነው ምልከታም ሸማች ማህበረሰቡ በስፋት እየተገበያየ እንደሆነ የተመለክተን ሲሆን ሁሉም ሸማች ወደ ሰንበት ገበያ በመምጣት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ እና ከአላስፈላጊ ወጪ እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
25/10/2025
ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተናል። 589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል። ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ አካትቷል። የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ተከናውኗል። የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ ናቸው። የኮሪደር ልማቱ 50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችን አካትቷል። እንደዚህ ያሉት ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴን በማሻሻል፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠንከር ደማቅ ለእንቅስቃሴ ምቹ እና ዘላቂነት ያላቸው የከተማ ሥፍራዎች በመፍጠር ረገድ ዐቢይ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
25/10/2025
የተግባር ፣ የአመለካከት ጥራት በማስጠበቅ ፣ አመራሩ 7/24 እሳቤ ለውጤታማነት በመስራት ፣ ክፍለ ከተማችንን በውጤት በማስፈንጠር ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር የ 120 ቀናት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች በክፍለ ከተማው በሚገኙ ክላስተሮች ወረዳ 06 ወረዳ 05 እና ወረደዳ 01 አስተባባሪ ኮሚቴዎች በተገኙበት ተገመገመ::
በወረዳው የመንግስትና የፓርቲ የ 120 ቀን ተግባራት የስራ እድል ፈጠራ ፣ ሌማት ትሩፋት እና ተረጂነት ፣ የተቀናጀ ብሎክ እንድሁም ሌሎች ስራዎች የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች እና የየወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በተገኙበት ተገምግሟል።
አቶ አከበረኝ ወጋገን የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራ ክህሎት ኃላፊ እንደገለፁት የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት በታቀደላቸው ቀናት መጨረስ ያስችል ዘንድ በትጋትና በቁርጠኝነት በግዜ የለንም መንፈስ መስራት እንደሚገባ እንዲሁም አስተሳስሮ በመስራት እና መፈፀም ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ስራዎችን አቀናጅቶ በመስራት ወደ ውጤት መቀየር ይገባል በቀጣይም ለሚከናወነው የንቅናቄ ተግባራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ እና የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ጊዜ የማይሰጠው ቀጣይ ሰፊ የሆኑ የንቅናቄ መድረኮች ስላሉ በአግባቡ ከወዲሁ መጨረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
24/10/2025
የወረዳ 06 አስተዳር ካቢኔ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀመጠ።
ኮሙኑኬሽን
ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
በወረዳው ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የቀጣይ የስራ መመሪያና አቅጣጫዎች አስቀምጧል ።
ካቢኔው ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል የማህበረሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የህዝቡን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ አገሎግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እንዲሁም የልዩ ልዩ ተግባራት ማስፈጸሚያ በጀት ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል ።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ ይርጋ እንደተናገሩት ካቢኔው ተወያይቶ ያፀደቃቸው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ተፈፃሚ በማድረግ የህብረተሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አስጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የቀጣይ የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥቷል ።
24/10/2025
"ዴሞክራሲ ስርዓትን በመገንባት ሂደት የሲቪክ ማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው"!!
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የዴሞክራሲ ስርዓትና ባህል ግንባታን አስመልክቶ የሲቪክ ማህበራት ጋር በዛሬው እለት የውይይት መድረክ ያከናወነ ሲሆን፣ ልዩ ልዩ ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ የወጣቶች ማህበራት፣ የሴቶች ማህበራት፣ የእድሮች ማህበራት፣ የአረጋዊያን ማህበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት ማህበራት፣ ሌሎች የሲቪክ ማህበራት ተሳታፊ ሆነዋል።
በመድረኩ ላይ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የኢኒስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጄ ፍቃዱ እንዳሉት የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት የሲቪክ ማህበራት መጠናከር ስለሚያስፈልግ ሁሉም እስከ ወረዳ ድረስ የድርሻውን መወጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ የብዙ ዓመታት የመንግስት አስተዳደር ታሪክ ቢኖራትም ሁሉን አካታች የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አለመገንባቷን በማንሳት የብልጽግና ፖርቲ የሲቪክ ማህበራት መጠናከር ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳለው የተረዳ ገዢ ፖርቲ በመሆኑ ማህበራቱን በማጠናከር በጋራ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ለዚህም ተግባር መሳካት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
24/10/2025
#የአገልግሎት ቀን ለተገልጋዮች ብቻ!
ጥቅምት 14/2018 ዓ/ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር በሴክተር ተቋማት የባለጉዳይ ቀንን አስመልክቶ የአገልግሎት አሰጣጥ የባለጉዳይ ቀንን ምክንያት በማድረግ የሴክተሮችን አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተደርጓል ።
በምልከታው አመራሮች እና ባለሙያዎች ባለጉዳይ ቀን አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ተገልጋይ ዜጎቻችን እያገለገሉ ያለበትን አግባብ የተሻለ እንደሆነ ለመመልከት ተችሏል፤ ባለሙያው ማገልገል ክብር መሆኑን ተረድቶ በተቋም የሚሰጡ አገልግሎቶችን በስታንዳርድ መሰረት ለተገልጋዩ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ በቅንነት እና በታማኝነት ለተመደበበት የስራ ክፍል አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
24/10/2025
የ120 ቀናት ስራዎች እቅድ አፈጻጸም በወረዳው ተገመገመ።
ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
ኮልፌወረዳ 06 ኮሙኒኬሽን
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የ120 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ተግባራትን የወረዳው አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል።
በወረዳው በ120 ቀናት ውስጥ የተከናወኑ የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የሌማት ትሩፋት እና ሌሎች የንቅናቄ ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ ይርጋ እንደተናገሩት የነዋሪዎቻችንን ጥያቄ ለመመለስ የንቅናቄ ስራዎችን ከመደበኛ ስራዎች ጋር አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ በመግለፅ በ120 ቀናት የታቀደውን ለማሳካት አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የወረዳው የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ናተአ ስራዎች በቀን እቅድ በመሸንሸን በተደራጀ ስምሪት መሰራት እንዳለባቸው ገልፀው እስከ አሁን የመጡ ውጤቶችን በማስቀጠል በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስቧል።
23/10/2025
የክፍለ ከተማው አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና የ ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ቀጣይ ተግባራት ላይ ውይይት አካሄደ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው አስተዳደር በሚከናወኑ የትምህርት ለትዉልድ የንቅናቄ ስራዎችና የቀጣይ እቅድ እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ በንቅናቄ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሔዷል።
በውይይቱ በቀጣይ የትምህርት ለትዉልድ የሚከናወኑ የንቅናቄ ስራዎችና የሚመራበት የንቅናቄ ሰነድ በክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ገነነ ዘውዴ እና በንቅናቄ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ዙሪያ በክፍለ ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ኑሩ ባርጌቾ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሔዷል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በተመለከተ በሚካሄደው ንቅናቄ ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍና መወያየት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዉይይቶችም ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት እንደሚገባም ገልፀዋል።
በትምህርት ለትዉልድ የሚሰሩ የንቅናቄ ስራዎች ፈጥኖ ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ እና ይሄንንም አመራሩ ወደ ተጨባጭ መቀየር አስፈላጊ እንደሆነም አመላክተዋል።
ከህብረተሰቡ የሚሰበሰቡ ሀብቶችን አሰራሮች መጠበቅ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።
አቶ አሚ ሙሄ አሊ የክፍለ ከተማዉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ እንደገለፁት እነዚህ በንቅናቄ የሚሰሩ የልማት ስራዎች በአግባቡ በመፈፀም ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የምንፈታበት ነዉ ብለዋል።
እንደ ሀገር የተያዘዉን "ትምህርት ለሁሉም" የሚለዉን ንቅናቄ ማሳካት የሚቻልበት እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ሁሉንም ማህበረሰብ ያሳተፈ የንቅናቄ ስራዎችም መከናወን እንደሚገባም ገልፀዋል።
በንቅናቄዎችም በ16 ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና ፣መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ 229 ተጨማሪ መማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት እቅድ ተይዞዋል።
በህብረተሰብ ተሳትፎም የተለያዩ የአካባቢ ልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።
23/10/2025
የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት በወረዳ 6እና 9 ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
ጥቅምት 13/2018ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን
የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ኮልፌ ቅርንጫፍ ክላስተር 4 ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት በወረዳ 6እና 8 ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረገ።
ምግብና መዳኒት ክላስተር 4 ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ባለፉት በ1ኛ ሩብ አመት ያከናወናቸው በተለይም ደህንነቱና ጥራቱ የጠበቀ የምግብ፣ ጤና ነክ ተቋማት ለመፍጠር ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ የብቃት ማረጋገጥ እና የናሙና የመጠጥና ምግብ ምርመራዎች እንዲሁም ህገወጥ እርዶች ከመከላከል የሰራቸው ዝርዝር ስራዎች የጽ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደምስ ጓዳ በዝርዝር አቅርቧል፡፡
የክላስተር 4 ኃላፊ ሜሮን ኤልያስ እንዳሉት በቀጣይ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች በተመለከተ የህዝቡን መሰረታዊ ችግሮች በቀጠና እንዲሁም በጽህፈት ቤት ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት በቀጣይ ሊሰራበት እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተገልጸዋል።
በመጨረሻም ከተወያዮች ለቀረቡ አስተያየትና ጥያቄዎች የክላስተር 4 ኃላፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
23/10/2025
የአረጋውያን ቀንን በማስመልከት "ለአረጋውያን ደህንነትና መብቶች በመጠበቅ ሁለንተናዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ" በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከበረ።
ጥቅምት 13-2018 ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአረጋውያን ቀን አስመልክቶ " ለአረጋውያን ደህንነትና መብቶች በመጠበቅ ሁለንተናዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።
በፕሮግራሙ የተገኙት የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ታገሰች ኪባሞ አረጋዊያን በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እና ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማግኘት መብቶች እንዳሏቸው ገልፀው።
አክለውም አረጋውያንን መንከባከብ ሀገርን እንደ መንከባከብ ይቆጠራል ማንኛውም ዜጋ ከአረጋውያን ጎን በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመጨረሻም አረጋዉያን ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው ከመድረኩም ምላሽ ተሰጥቶበት ተጠናቋል።