15/05/2026
የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የሕግ መዝገበ ቃላት ተመረቀ !
(አዲስ አበባ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሕግ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው "ዋላቡ የኦሮሚኛ የሕግ መዝገበ ቃላት" (WALABU OROMO LAW DICTIONARY / WLAABUU GUUBOO JECHOOTA SEERAA AFAAN OROMOO) ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል።
ይህ ግዙፍ የሕግ መዝገበ ቃላት በፌደራል የሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት (FLJI)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት እና በጀስቲስ ፎር ኦል ፒኤፍ ኢትዮጵያ (JFA-PFE) የጋራ ትብብርና ጥረት ለህትመት የበቃ ነው።
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፍትሕ ተቋማት አመራሮች፣ የሕግ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፤ ይህ መዝገበ ቃላት በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የነበረውን የወጥነት ችግር ለመቅረፍ የሚኖረውን ፋይዳ በአጽንኦት ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት፤ እስከ ዛሬ የሕግ ባለሙያዎች የሕግ ቃላትን በየግላቸውና እንደተረዱት ወደ አፋን ኦሮሞ ይተረጉሙ የነበረው አሠራር፣ በፍትሕ አሰጣጥ ጥራት ላይ የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ነበረው። ይህ መዝገበ ቃላት ግን የተዘበራረቁ ትርጉሞችንና ጽንሰ-ሀሳቦችን በማስቀረት ወጥ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት ለመስጠትና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንደ ዋቢ መጽሐፍ የሚያገለግል ትልቅ ስኬት መሆኑን አስገንዝቧል ።
በመቀጠል በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የፌደራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ እንደገለጹት፣ መዝገበ ቃላቱ በሕግና በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የሚታዩ የቋንቋና የፅንሰ-ሀሳብ ልዩነቶችን በማጥበብ ረገድ የማይተካ ሚና ይኖረዋል። ሥራው በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገራችን አንጋፋ በሆነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪነት መዘጋጀቱና በዚሁ ግቢ ውስጥ መመረቁ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። ሥራው ረጅም ጊዜ ቢወስድም፣ ለቋንቋው ዕድገት ተቆርቋሪ በሆኑ የኦሮሞ የሕግ ምሁራንና የላቀ የቋንቋ ችሎታ ባላቸው ባለሙያዎች መዘጋጀቱ የጥራት ደረጃውን ከፍ እንዳደረገው አምባሳደሩ አስረድተዋል።
መዝገበ ቃላቱ ሲዘጋጅ የሁሉንም የኦሮሚያ አካባቢዎች የአነጋገር ዘዴና የቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ለማመጣጠን ከፍተኛ ጥረት መደረጉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ መዝገበ ቃላቱ ሙሉ በሙሉ መነሻውንና ማብራሪያውን አፋን ኦሮሞ ማድረጉ የቋንቋውን ትርጉም ይበልጥ ለመረዳት እንደሚያግዝ ገልጸዋል። አፋን ኦሮሞ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሦስቱም የመንግሥት አካላት የትምህርትና የሥራ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ እንደመገኘቱ መጠን ይህ መዝገበ ቃላት ለክልሉ የዳኝነትና ፍትሕ ተቋማት እንዲሁም ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ወጥ የሆነ የሕግ ትርጉም በመስጠት የሕግ የበላይነትና ፍትሕ እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
አምባሳደር ደግፌ አክለውም ፣ ሥራው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሚዲያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች የተጫወቱትን ሚና በማድነቅ፣ ሥራው በጥራት እንዲከናወን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትና በሙያቸው ቀንና ሌሊት ለለፉ ምሁራን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። መዝገበ ቃላቱ በፌደራል ደረጃም ቢሆን ቋንቋውን መናገር፣ መጻፍና ማንበብ ለሚችሉ የሕግ ባለሙያዎች እንደ ትልቅ ግብዓት እንደሚያገለግል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
07/05/2026
ለኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሕግ ባለሙያዎችና አመራሮች ሥልጠና ተሰጠ
(አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም)
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት የዳኝነትና የፍትሕ አካላት አመራሮችና ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው ለኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሕግ ባለሙያዎችና አመራሮች በፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት በተለይም የክስ አመሰራረትና የክርክር ክህሎት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
ይህ ሥልጠና ከግንቦት 12 እስከ 14/2018 ዓ.ም በአዲሱ የንግድ ሕግ ላይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
=================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
06/05/2026
የፌዴራል የሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት በምርጫ ፍትሕ ዙሪያ ያደረገውን የፖናል ውይይት በተመለከተ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘገባ
ለበለጠ መረጃ የፌስቡክ ቻናል፡- https://web.facebook.com/profile.php?id=100078423697131
ለድህረ ገታችን፡- Www.fjli.gov.et
ለቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/jlrtinet
ለሊንክድ ኢን፡- https://www.linkedin.com/.../federal-law-and-justice.../p
02/05/2026
በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ለአህጉራዊ መሪነት መሰረት ሆነዋል - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ለአህጉራዊ መሪነት መሰረት ሆነዋል
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2018 (ኢዜአ)፦በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተመዘገቡ ስኬቶች ለኢትዮጵያ የዘርፉ አህጉራዊ መሪነት መሰረት መ...
30/04/2026
ፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለረዳት ዳኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ጀመረ
(አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም) — የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ረዳት ዳኞች በዛሬው ዕለት በድሪም ላይነር ሆቴል ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች አንዱ የዳኝነትና የፍትሕ አካላትን አመራሮችና ባለሙያዎችን አቅም በሥልጠና መገንባት መሆኑን አብራርተዋል። ዶክተር ዘካርያስ አክለውም ሥልጠና በራሱ ግብ እንዳልሆነና ሰልጣኞች የቀሰሙትን እውቀትና ክሂሎት በተግባር ላይ በማዋል ሌሎችንም የማብቃት ሥራ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ክቡር ዳኛ አበበ ሰለሞን በበኩላቸው የሥልጠናውን አስፈላጊነት በማብራራት ተሳታፊዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ሲመለሱ ያገኙትን ልምድና ተሞክሮ ወደ ተግባር በመቀየር ለሀገሪቱ የዳኝነት ሥርዓት መዳበር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ይህ በሁለት ዙሮች የሚሰጥ ሥልጠና በመጀመሪያው ዙር በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 03/2017፣ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ (ሙግት) እንዲሁም በውጥረትና የሥራ ጫና አመራር (Stress management & resilience) ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
ዛሬ በተጀመረው በዚህ ሥልጠና የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አመክንዮ፣ ወጥነትና ትክክለኛነትን ከማረጋገጥ አንጻር የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ግምገማ፣ እንዲሁም የወንጀል ደረጃዎችን እንደክብደታቸው እና እንደአደገኛነታቸው ደረጃ በማውጣት ላይ የተመሰረተ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ይዘቶች በሰፊው እየተዳሰሱ ይገኛሉ። በተጨማሪም ከቅጣት ዓላማና ግብ እንዲሁም የቅጣት አወሳሰን የሚመራባቸው መሰረታዊ መርሆዎች ማለትም የሕጋዊነት መርህ፣ በሕግ ፊት እኩል መሆን፣ ሰብአዊ ክብርን የመጠበቅ መርህ፣ ተመጣጣኝነት፣ ወጥነት፣ አድልዎ የሌለበትና ግልፅነት ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን ሥልጠናው በነገው ዕለትም የሚቀጥል ይሆናል።
========================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት