Justice ፍትሕ

Directions

Justice  ፍትሕ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Justice ፍትሕ, Government Organization, Ethiopian, Addis Ababa.

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያለሕግ ባለሙያዎችና ሕግ ምሩቃን👇👇👇👇👇👇👇👇!መልካም ዕድል!
29/09/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ለሕግ ባለሙያዎችና ሕግ ምሩቃን
👇👇👇👇👇👇👇👇
!መልካም ዕድል!

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ ...
09/09/2026

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤
👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡
በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡
ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

10  በህግ ክርክር ወቅት የሚያጋጥሙ የላቲን ቃላትና አማርኛ ትረጉማቸው። ⚖️ክፍል 11. Audi alteram partem 🎯እንግሊዝኛ: Hear the other side / Listen to th...
06/09/2026

10 በህግ ክርክር ወቅት የሚያጋጥሙ የላቲን ቃላትና አማርኛ ትረጉማቸው። ⚖️ክፍል 1

1. Audi alteram partem
🎯እንግሊዝኛ: Hear the other side / Listen to the other side
🎯⚖️አማርኛ: የሌላኛውን ወገን ሀሳብ/መከራከሪያ ስማ
በኢትዮጵያ ህግ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 (ፍትሕ የማግኘት መብት) እና በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ውስጥ የተካተተ፣ ማንኛውም ወገን ሳይሰማና የመከላከል እድል ሳይሰጠው ሊፈረድበት እንደማይችል የሚደነግግ የመሰማት መብት መርህ ነው።

2. Res ipsa loquitur
🎯እንግሊዝኛ: The thing speaks for itself
🎯አማርኛ: ነገሩ ራሱ ይናገራል
በኢትዮጵያ ህግ ከውል ውጭ ተጠያቂነት (ፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 2027 እና ተከታዮቹ) የጥፋተኝነት ግምት በሚወሰድባቸው አጋጣሚዎች ድርጊቱ እራሱ የቸልተኝነት ወይም የጉዳት መኖርን በግልጽ እንደሚያስረዳ የሚቆጠርበት መርህ ነው። የበሽተኛው ሆድ ውሰወጥ
መቀስ የረሳ ዶክተር ቸልተኛ ለመሆኑ የመቀሱ በሆድ ውሰጥ መገኜት ብቻ በቂ ነው።

3. Stare decisis
🎯 እንግሊዝኛ: To stand by things decided
🎯 አማርኛ: የቀደመው ውሳኔ ለዚህ ይሰራል።
በኢትዮጵያ ህግ: በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1) መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅነት አለው።

4. Mens rea
🎯እንግሊዝኛ: Guilty mind
🎯አማርኛ: የወንጀል ሀሳብ / ህገ-ወጥ አላማ
በኢትዮጵያ ህግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 57 እና 58፤ 59 አንድ ሰው በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው በህግ የተከለከለውን ድርጊት ለማድረግ ያሰበ (Intent) ወይም በቸልተኝነት (Negligence) የፈጸመ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

5. Actus reus
🎯እንግሊዝኛ: Guilty act
🎯አማርኛ: «የወንጀል ድርጊት»
በኢትዮጵያ ህግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 መሰረት አንድ ሰው ወንጀለኛ እንዲባል ከሀሳብ በተጨማሪ በድርጊት የተገለፀ አካላዊ የወንጀል ድርጊት ወይም ማድረግ የሚገባውን አለማድረግ (Omission) ሊኖር ይገባል።

6. Bona fide
🎯እንግሊዝኛ: In good faith / Genuine
🎯አማርኛ : ቅን ልቦና
በኢትዮጵያ ህግ: በፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 1161 በቀንልቦና ንብረትን ስለመያዝ እና በውል ሕግ ውስጥ ያለምንም ተንኮል ማታለል ወይም ህገ-ወጥ አላማ በእውነተኛና በቅን ልቦና የተደረገ ድርጊትን ወይም ስምምነትን የሚጠበቅ መርህ ነው። በንብረት ውርስ ህጎችም የቅን ልቦና ባለንብረቶች መብት የተጠበቀ ነው።

7. Prima facie
🎯እንግሊዝኛ: At first sight / On the face of it
🎯 አማርኛ: በመጀመሪያ እይታ ወይም ከቀረበው ማስረጃ አንፃር የሌለኛውን ወገን
ማስረጃ ሳይሰሙ ነገሩ ስለመደረጉ የቀረበ ማስረጃ።

በኢትዮጵያ ህግ: በሥነ-ሥርዓትና በማስረጃ ሕግ መርህ መሠረት ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ በመጀመሪያ እይታ አሳማኝና በቂ ሆኖ የሚቀርብ ማስረጃ ወይም የክስ መሠረት ነው።

8. Habeas corpus
🎯እንግሊዝኛ: You shall have the body
🎯አማርኛ: ሰውየውን ለምን ያዝከው።
• በኢትዮጵያ ህግ: በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 19(4) መሠረት ማንኛውም የታሰረ ሰው በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ እና የእስሩ ሕጋዊነት በመመርመር እንዲለቀቅ የመጠየቅ መሠረታዊ መብት ነው። ፍርድ ቤት ሰውን ያለሕጋዊ መሠረት እንዳይታሰር የሚያደርግ የፍርድ ቤት ጥበቃ።

9. Caveat emptor
🎯እንግሊዝኛ: Let the buyer beware
🎯አማርኛ: ገዢ ቢጠነቀቅ ይሻለዎል
በኢትዮጵያ ህግ: 1 መሠረት የሽያጭ ውል ከተፈጸመ በኋላ ገዢ የተረከበውን ዕቃ ሁኔታ እና ጉድለት ወዲያውኑ የመመርመርና የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት።

10. Volenti non fit injuria
🎯እንግሊዝኛ: To a willing person, injury is not done
🎯አማርኛ: «በፈቃደኝነት ጉዳትን የተቀበለ ሰው የካሳ መብት የለውም»
በኢትዮጵያ ህግ: በፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ 2091 መሠረት ተጎጂው አደጋውን ወይም ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አውቆና ፈቅዶ የተቀበለው ከሆነ የካሳ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም። አጩለኝ ብሎት ቢያጮለው አጮለኝ አይሰራም። የወንጀል ህግ አንቀፅ 70 ፤ ይህን ሀሳብ ሊያካትቱ ይችላሉ የሚባሉ የፍታብሔር አንቀፆች 2038 ፣2067፣ 2068 ፣ 2098

በሚከተለው ሊንክ በቅን ልቦች አዎርድ ላይ ደምፅ በመስጠት ያበረታቱን።

⁠ ⁠ ⁠ ⁠ ⁠ ⁠ ⁠ ⁠ ⁠

የአማራ ክልል አዲሱ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 310/2018፡ ዋና ዋና 9 መሠረታዊ ለውጦችየአማራ ክልል መንግሥት የነበረውን አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሻር አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳ...
05/09/2026

የአማራ ክልል አዲሱ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 310/2018፡ ዋና ዋና 9 መሠረታዊ ለውጦች

የአማራ ክልል መንግሥት የነበረውን አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሻር አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 310/2018 በሥራ ላይ አውሏል። ይህ አዋጅ ከፌደራል የገጠር መሬት ሕግ (1324/2016) ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ የባለይዞታዎችን መብት የሚያሰፉ 9 ዋና ዋና ነጥቦችን ይዟል።

1️⃣ የአዋጁ ተፈጻሚነት ወሰን (Scope of Application - አንቀጽ 3)

በገጠር መሬት ላይ፡ በክልሉ በሚገኝ ማንኛውም የገጠር መሬት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

በከተማ አስተዳደሮች ሥር ባሉ የገጠር ቀበሌዎች፡ በከተማ አስተዳደር ሥር ቢሆኑም የገጠር ይዘት ባላቸው አካባቢዎች ላይ ተፈጻሚነቱ ይመራል።

ርክክብ ባልተፈጸመባቸው ቦታዎች፡ ወደ ከተማ ወሰን ገብተው ነገር ግን የይዞታ ርክክብ እስካልተፈጸመ ድረስ በዚህ አዋጅ መመራታቸውን ይቀጥላሉ።

በሁሉም የይዞታ ዓይነቶች፡ በግል፣ በወል (በጋራ) እና በመንግሥት የገጠር መሬት ይዞታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

ልዩ ሁኔታዎች፡ ለደን፣ ለዱር እንስሳት እና ለማዕድን ተከልለው የተያዙ መሬቶችን በተመለከተ ለዘርፉ ልዩ ሕጎች (Specific Laws) ቅድሚያ ይሰጣል።

2️⃣ የመሬት ማግኘት መብትና ተጠቃሚነት (አንቀጽ 4-8)

ነፃ መሬት፡ በግብርና መተዳደር የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ (ዕድሜው 18+) መሬት በነፃ የማግኘት መብት አለው።

ቅድሚያ የሚሰጣቸው፡ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና ወጣቶች ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

የመብት ቆይታ፡ የአርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮችና የሃይማኖት ተቋማት መብት የጊዜ ገደብ የሌለው (ለዘላለም) ሲሆን፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን ለሥራቸው አስፈላጊ እስከሆነ ጊዜ ብቻ ይፈቀድላቸዋል።

3️⃣ የይዞታ ዝውውር - ኪራይ፣ ስጦታና ውርስ

ኪራይ (አንቀጽ 9)፡ ባለይዞታው ከግማሽ የማይበልጥ ይዞታውን ማከራየት ይችላል (አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ግን ሙሉውን ማከራየት ይችላሉ)። የጊዜ ገደብ፦ ለቋሚ ተክል እስከ 30 ዓመት፣ ለሰብል እስከ 10 ዓመት።

ስጦታ (አንቀጽ 11)፡ ለሥጋ ዘመድ ወይም "በይጦረኛል" ውል ለማንኛውም ሰው በጽሑፍ መስጠት ይቻላል።

ውርስ (አንቀጽ 12)፡ ማንኛውም ሰው (የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ) በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ በፍትሐ ብሔር ሕጉ መሠረት መሬት መውረስ ይችላል። ይህም ቀደም ሲል የነበረውን ገደብ ያነሳ ትልቅ ለውጥ ነው።

4️⃣ ንብረት መሸጥና በጋራ ማልማት (አንቀጽ 13-19)

የንብረት ሽያጭ፡ በመሬት ላይ የለማን ቋሚ ንብረት (ቤት ወይም ቋሚ ተክል) መሸጥ ይቻላል። ቋሚ ተክል ከሆነ ሙሉ በሙሉ ከለማ ግማሹን፣ በከፊል ከለማ ግን የለማውን ማሳ መሸጥ ይፈቀዳል።

ከባለሀብት ጋር ማልማት፡ ባለይዞታው የመጠቀም መብቱን እንደ ካፒታል በመጠቀም ከባለሀብት ጋር በጋራ ማልማት ይችላል።

5️⃣ የብድር ዋስትና (አንቀጽ 15)

የመሬት የመጠቀም መብትን (Usufruct right) ለፋይናንስ ተቋማት ለብድር ዋስትና ማስያዝ ይቻላል።

የዋስትና ዘመኑ ቢበዛ እስከ 10 ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ ተበዳሪው ካልከፈለ አበዳሪው መሬቱን ለተወሰነ ጊዜ በመጠቀም ዕዳውን ያስመክሳል።

6️⃣ ዲጂታል ምዝገባና የይዞታ ማረጋገጫ (አንቀጽ 61-62)

ዲጂታላይዜሽን፡ የመሬት መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ በዲጂታል ሥርዓት መመራት እንዳለበት በአስገዳጅነት ተደንግጓል።

የምስክር ወረቀት፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በመሬት ላይ ያለን መብት የሚያረጋግጥ "የመጨረሻና ፍጹም" ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል።

7️⃣ ይርጋና የግጭት አፈታት (አንቀጽ 14 እና 73)

የይዞታ ክስ ይርጋ፡ መሬት ያለአግባብ የተወሰደበት ሰው በ15 ዓመት ውስጥ ክስ ማቅረብ አለበት (ቀደም ሲል 10 ዓመት የነበረው መሻሻሉን ልብ ይሏል)።

የወርስ ይርጋ፡ ውርሱ ከተከፈተ በ3 ዓመት ውስጥ መጠየቅ አለበት።

ሽምግልና፡ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶችና ሽምግልና እንደ አማራጭ የመፍትሔ መንገድ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

8️⃣ የተጋላጭ ወገኖችና የአንድ በላይ ሚስት መብት (አንቀጽ 25)

አንድ ባል ከአንድ በላይ ሚስት በሚኖረው ጊዜ፣ የሴቶችን መብት ለመጠበቅ ሲባል የጋራ መሬቱ ተከፋፍሎ በየስማቸው እንዲመዘገብና ባልየው አዲስ በሚመሠርተው ትዳር ላይ በራሱ ድርሻ ላይ ብቻ እንዲመዘገብ ይደረጋል።

9️⃣ የአጠቃቀም ገደቦችና ግዴታዎች (አንቀጽ 33-35)

መሬትን የመንከባከብና የአፈር መሸርሸርን የመከላከል ግዴታ ተጥሏል።

ተዳፋትነቱ ከ60% በላይ የሆነ መሬት ለሰብል እርሻ መጠቀም የተከለከለ ሲሆን ለዛፍ ልማት ብቻ መዋል አለበት።

ግዴታን አለመወጣት ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ የመጠቀም መብትን እስከ ማጣት የሚያደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ያስከትላል።

አዲሱን የገጠር መሬት አዋጅ በተመለከተ ግንዛቤ እንዲጨብጡ መረጃውን ለሌሎች አካፍሉ (LIKE & SHARE)!
Justice ፍትሕ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ! https://t.me/Ayunews

በአዲስ አበባ ሰማይ ስርየቴሌግራም ቻናልችን፣ https://t.me/Ayunews
05/09/2026

በአዲስ አበባ ሰማይ ስር
የቴሌግራም ቻናልችን፣ https://t.me/Ayunews

ሙዚቃው ከእስር ቤት ቢያስወጣውም   ትዳሩን አፈረሰበት!ያኔ ዘመኑ ከበድ ያለ ነበር፡፡ ወጣቶች ኢህአፓ ናቸው ተብለው ጥርስ የገቡበት ዘመን፡፡ ታዲያ መስፍን ተመቻቸላቸው። ጠጉሩን አጎፍሮ፣ ያ...
05/09/2026

ሙዚቃው ከእስር ቤት ቢያስወጣውም
ትዳሩን አፈረሰበት!

ያኔ ዘመኑ ከበድ ያለ ነበር፡፡ ወጣቶች ኢህአፓ ናቸው ተብለው ጥርስ የገቡበት ዘመን፡፡ ታዲያ መስፍን ተመቻቸላቸው። ጠጉሩን አጎፍሮ፣ ያንን ቦክስ ጊታሩን መሳሪያ አስመስሎ ሲጓዝ “መሳሪያ የያዘ ጸረ ህዝብ እጃችን ገባ!” ብለው ያዙት፡፡ ለሶስት ወርም እስኪጣራ እስር ቤት ሰነበተ፡፡ ታዲያ ለመፈታት ምክንያት የሆነው የመጀመሪያው ካሴቱ ህዝብ ወዶለት መነጋገሪያ በመሆኑ ነው፡፡

“ከተማውን እሱ በሙዚቃው ተቆጣጥሮታል እናንተ እሱን እዚህ አስራችሁታል!” በሚል ስሞታ ተለቀቀ፡፡ በአንድ ሰአት ተቀርጾ በማራቶን ሙዚቃ ገበያ ላይ የዋለው ካሴቱ ነበር ያስፈታው፡፡
⬇️⬇️

እንዲህ ነው ነገሩ፡፡

መስፍን ዝነኛ በሆነበት አፍላ ዘመኑ በምሽት ክበብ ይሰራ ነበር፡፡ ባለቤቱም መስፍን ስራውን ሲሰራ የማየት ፍላጎትዋ ከፍ እያለ ይመጣል፡፡ አንድ ምሽትም ከቅርብ ጓደኛ ዋ ጋ ይጋብዛታል፡፡ ከፊት ለፊት ቁጭ ብላ የውድ ባለቤቷን ድምጽ በጊታሩ ድምጽ ታጅቦ ሲንቆረቆር ታዳምጣለች፣ ትመለከታለች፡፡ በችሎታው ኩራት ቢሰማትም አንድ ነገር ውስጧን ይፈታተናታል። ቅናት፡፡
በመስፍን ሙዚቃ የተማረኩት ወንዱም፣ሴቱም እየወጡ ሲሸልሙት፣ሲያቅፉት፣ሲስሙት ትታዘባለች፡፡ ይባስ ብሎም አጠገቧ የተቀመጠችው ባልንጀራዋ ከመቀመጫዋ ተነስታ መስፍንን ስትስመው ታያለች፡፡ በቃ ለእሷ ባሏ የህዝብ መስሎ ተሰማት፡፡ ትዳሯ የሚበረክት አልመስል አላትና ከእዚያ ምሽት በኋላ በገዛ ፍቃዷ ከመስፍን ተለየች፡፡ አለቀ፣ ደቀቀ!
ሃያ ሁለት አልበም ያሳተመው አንጋፋው ድምጻዊ፣የቦክስ ጊታር ተጫዋች፣የግጥም እና ዜማ ደራሲው መስፍን አበበ በ63 ዓመቱ ነበር በድንገት ያረፈው፡፡ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት የነበረው መስፍን ቀብሩ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን በ2008 ዓ/ም ነበር የተፈጸመው፡፡

ነፍስ ይማር፡፡
ክብር ሙያዊ ዋጋ ለከፈሉ የጥበብ አርበኞቻችን!!

ውድነህ ክፍሌ

የቴሌግራም ቻናልችን፣ https://t.me/Ayunews

ስለ አማርኛ ቋንቋአማርኛ ዓለማቀፍ ቋንቋ ሆኗል!የአማርኛ ቋንቋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በበርካታ ሀገራት በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የቋንቋ ማዕከላት ውስጥ በጥናት፣ በም...
05/09/2026

ስለ አማርኛ ቋንቋ
አማርኛ ዓለማቀፍ ቋንቋ ሆኗል!

የአማርኛ ቋንቋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በበርካታ ሀገራት በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የቋንቋ ማዕከላት ውስጥ በጥናት፣ በምርምር እንዲሁም በዲግሪና በሰርተፊኬት ደረጃ ይሰጣል።

ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፣

ጀርመን፡-
በሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ (University of Hamburg)፣ በፍራንክፈርት ዩኒቨርሲቲ እና በላይፕዚግ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ጥናት (Ethiopian Studies) እና በሴማዊ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል ሥር።

ሩሲያ፦
በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Moscow State University - ISAA) እና በሴንት ፒተርስበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ጥናት ክፍሎች።

ጣሊያን፡-
በናፖሊ ዩኒቨርሲቲ (University of Naples "L'Orientale") እና በሮም ሳፒየንዛ ዩኒቨርሲቲ (Sapienza University of Rome)።

እንግሊዝ (ብሪታንያ)፡-
በለንደን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና ምስራቅ ጥናት ትምህርት ቤት (SOAS - School of Oriental and African Studies)።

ፈረንሳይ፡-
በፓሪስ ከንቲባ የውጭ ቋንቋዎች እና ሥልጣኔዎች ተቋም (INALCO)።

ፖላንድ፡-
በዋርሶ ዩኒቨርሲቲ (University of Warsaw) በአፍሪካ ቋንቋዎችና ባህሎች ክፍል ውስጥ።

አሜሪካ (ዩናይትድ ስቴትስ)፡-

- በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Harvard University)

- በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ (Columbia University)

- በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ (Stanford University)

- በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ (Indiana University)

- በፎሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ (University of Florida)

- በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Michigan State University)

እስራኤል፡-
በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ እና በኢየሩሳሌም ዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ (Hebrew University of Jerusalem)።

ጃፓን፡-
በኦሳካ ዩኒቨርሲቲ እና በቶኪዮ የውጭ ሀገራት ጥናት ዩኒቨርሲቲ (TUFS)።

ቻይና፡-
በቤጂንግ የውጭ ሀገራት ጥናት ዩኒቨርሲቲ (Beijing Foreign Studies University)።

ኬንያ፡-
በናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎች የቋንቋ ማዕከላት።

ጂቡቲ፡-
በጂቡቲ ዩኒቨርሲቲ እና በባህል ማዕከላት።

ደቡብ አፍሪካ፡-
በኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ (በአፍሪካ ጥናቶች ሥር በተለያዩ ጊዜያት)።

አሟርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ከምትኮራባቸው የማይዳሰሱ ሀብቶች አንዱ ነው።

የአፍሪካ ሀገሮችና ዋና ከተማዎቻቸው በቁጥር፦1. አልጄሪያ — አልጀርስ2. አንጎላ — ሉዋንዳ3. ቤኒን — ፖርቶ-ኖቮ4. ቦትስዋና — ጋቦሮኔ5. ቡርኪና ፋሶ — ዋጋዱጉ6. ቡሩንዲ — ጊቴጋ7....
05/09/2026

የአፍሪካ ሀገሮችና ዋና ከተማዎቻቸው በቁጥር፦

1. አልጄሪያ — አልጀርስ
2. አንጎላ — ሉዋንዳ
3. ቤኒን — ፖርቶ-ኖቮ
4. ቦትስዋና — ጋቦሮኔ
5. ቡርኪና ፋሶ — ዋጋዱጉ
6. ቡሩንዲ — ጊቴጋ
7. ኬፕ ቨርዴ — ፕራያ
8. ካሜሩን — ያውንዴ
9. ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ — ባንጉዊ
10. ቻድ — ንጃሜና
11. ኮሞሮስ — ሞሮኒ
12. ኮንጎ ሪፐብሊክ — ብራዛቪል
13. ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ — ኪንሻሳ
14. ኮት ዲቯር — ያሙሱክሮ
15. ጅቡቲ — ጅቡቲ
16. ግብፅ — ካይሮ
17. ኢኳቶሪያል ጊኒ — ሲውዳድ ዴ ላ ፓዝ
18. ኤርትራ — አስመራ
19. ኢስዋቲኒ — ምባባኔ
20. ኢትዮጵያ — አዲስ አበባ
21. ጋቦን — ሊብሬቪል
22. ጋምቢያ — ባንጁል
23. ጋና — አክራ
24. ጊኒ — ኮናክሪ
25. ጊኒ-ቢሳው — ቢሳው
26. ኬንያ — ናይሮቢ
27. ሌሶቶ — ማሴሩ
28. ላይቤሪያ — ሞንሮቪያ
29. ሊቢያ — ትሪፖሊ
30. ማዳጋስካር — አንታናናሪቮ
31. ማላዊ — ሊሎንግዌ
32. ማሊ — ባማኮ
33. ሞሪታኒያ — ኑዋክሾት
34. ሞሪሸስ — ፖርት ሉዊስ
35. ሞሮኮ — ራባት
36. ሞዛምቢክ — ማፑቶ
37. ናሚቢያ — ዊንድሆክ
38. ኒጀር — ኒያሜ
39. ናይጄሪያ — አቡጃ
40. ሩዋንዳ — ኪጋሊ
41. ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ — ሳኦ ቶሜ
42. ሴኔጋል — ዳካር
43. ሲሼልስ — ቪክቶሪያ
44. ሴራሊዮን — ፍሪታውን
45. ሶማሊያ — ሞቃዲሾ
46. ደቡብ አፍሪካ — ፕሪቶሪያ፣ ኬፕ ታውን እና ብሎምፎንቴን
47. ደቡብ ሱዳን — ጁባ
48. ሱዳን — ካርቱም
49. ታንዛኒያ — ዶዶማ
50. ቶጎ — ሎሜ
51. ቱኒዚያ — ቱኒስ
52. ኡጋንዳ — ካምፓላ
53. ዛምቢያ — ሉሳካ
54. ዚምባብዌ — ሀራሬ

  የማይኖራቸው ጉዳዮች1. የጉዲፈቻ (Adoption) ውልየኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ቁጥር 194 የጉዲፈቻ ውል በፍርድ ቤት ካልጸደቀ የሕግ ውጤት አያስከትልም።ምሳሌ፦ አቶ አበበ እና ወ/ሮ አል...
04/09/2026

የማይኖራቸው ጉዳዮች
1. የጉዲፈቻ (Adoption) ውል
የኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ቁጥር 194 የጉዲፈቻ ውል በፍርድ ቤት ካልጸደቀ የሕግ ውጤት አያስከትልም።
ምሳሌ፦ አቶ አበበ እና ወ/ሮ አልማዝ ልጅ ጉዲፈቻ ቢያደርጉም ፍርድ ቤት ካላጸደቀው ልጁ በሕግ ልጃቸው አይቆጠርም።
2. በጋብቻ ውስጥ የሚደረግ የስጦታ (Donation) ውል
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2447–2448 በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ አንዳንድ የስጦታ ውል በፍርድ ቤት መጽደቅ ያስፈልገዋል።
3. በጋብቻ ውስጥ የግል ንብረት ስምምነት
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57–60 ባልና ሚስት ንብረትን በተመለከተ የሚያደርጉት ስምምነት በፍርድ ቤት መጽደቅ አለበት።
ምሳሌ፦ ቤቱ የባል ብቻ ንብረት ነው ብለው ቢስማሙ ፍርድ ቤት ካላጸደቀው በሦስተኛ ወገን ላይ አይተገበርም።
4. የጋብቻ ውልን ማሻሻል
የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 61 የጋብቻ ውል ማሻሻያ በፍርድ ቤት ሳይጸድቅ ሕጋዊ ውጤት አያስከትልም።
5. ፍቺ (Divorce)
የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 76 እና ተከታዮቹ ባልና ሚስት በራሳቸው ስምምነት ብቻ ትዳርን ማፍረስ አይችሉም፤ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያስፈልጋል።
6. የወራሽነት ማረጋገጫ
የፍትሐብሔር ሕግ ከአንቀጽ 947 በኋላ ያሉ ድንጋጌዎች የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የውርስ ማረጋገጫን የሚመለከቱ ሂደቶች ወራሽነት በፍርድ ቤት ተረጋግጦ የወራሽነት ማስረጃ እስኪሰጥ ድረስ በሕግ አይረጋገጥም።
7. ውል ማሻሻል
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1675 እና ተከታዮቹ ሕጉ የፍርድ ቤት ፍቃድ እንዲያስፈልግ በግልጽ በደነገገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ማሻሻያው ያለ ፍርድ ቤት ጸደቃ ውጤት አያስከትልም።
8. የግል ወይም የቤተሰብ ስም መቀየርየፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 32 እስከ 46 ሰዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችየፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የፍርድ ቤት ማመልከቻ ሂደትየስም ለውጥ በፍርድ ቤት ከተፈቀደ በኋላ ብቻ በመንግስት መዝገቦች ይመዘገባል።
9. ውክልና (Agency)
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2199 እና ተከታዮቹ በመሠረቱ ውክልና የፍርድ ቤት ጸደቃ አያስፈልገውም። ነገር ግን ሕጉ በልዩ ሁኔታ የፍርድ ቤት ፍቃድ ወይም ሹመት የሚጠይቅበት እንደ ሞግዚትነት ወይም አሳዳሪነት ያሉ ጉዳዮች ይለያሉ።
10. መክሰር (Bankruptcy)
የንግድ ሕግ የመክሰር ድንጋጌዎች አንድ ነጋዴ መክሰሩ የሚታወጅው በፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።
11. የመጥፋት ውሳኔ (Declaration of Absence)
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 154 እሰከ 173 ሰዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች አንድ ሰው እንደጠፋ ወይም እንደሞተ በሕግ የሚታወቀው በፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።
12. የልጅ ሞግዚት መሾም (Appointment of Guardian)
የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ 255 ጀምሮ ያሉ የሞግዚትነት ድንጋጌዎች ለሕፃን ሞግዚት የሚሾመው በፍርድ ቤት ብቻ ነው።
ምሳሌ፦ የሕፃን ወላጆች ከሞቱ በኋላ አጎቱ ራሱን ሞግዚት ብሎ መቀጠል አይችልም፤ በፍርድ ቤት ሹመት ማግኘት አለበት ::
የቴሌግራም ቻናል፣ https://t.me/Ayunews
Justice ፍትሕ

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Justice ፍትሕ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share