Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office

Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office, Government Organization, Addis Abeba, Addis Ababa.

Photos from Addis ketema woreda 8 communication አዲስ 8's post 09/07/2025
Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 21/06/2025

ዜና ማህበር

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር መደበኛ የስራ አስፈፃሚና የዘርፍ አመራሮች ስብሰባውን በማድረግ የክረምት መርሃ ግብር እቅድ ውይይት አካሄደ።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር መደበኛ የስራ አስፈፃሚና የዘርፍ አመራሮች ስብሰባውን በዛሬው እለት በማካሄድ:-በዋናነት

# #የ2017 ዓ.ም የመጨረሻ 4ተኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ስራዎች ላይ በሰፊው ለመወያየት የተቻለ ሲሆን አባላት ምልመላ፣ የወጣቶች ተጠቃሚነት ፣ የትምህርት እድል፣ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ፣ ክበባትን ማጠናከር፣ የሰላምና ፀጥታ ስራውች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለው የስራ መስተጋብር እንዲሁም ጥቅል የማህበሩ ስራዎች በሰፊው በወረዳዎች ቀርቦ ለመወያየት የተቻለ ሲሆነ የ2017/18 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ፣የ90ቀናት እቅድ ውይይት እና ወቅታዊ የማህበሩ ስራዎች ላይ እንዲሁም ትኩረት ተሰቷቸው መሰራት ያለባቸው ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግና መግባባት ላይ በመድረስ ከወረዳ አመራሮች ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በክ/ከተማው ኮር አመራሮች ምላሽና የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት የእለቱ ውይይይ ተጠናቋል ።

ሰኔ-13-2017 ዓ.ም

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 20/06/2025

በ6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የባህል ስፖርቶች የቤት ውስጥ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበላይነት ተጠናቀቀ።

ሰኔ 13 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በ6ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ጨዋታ የባህል ስፖርቶች የቤት ውስጥ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበላይነት ተጠናቆል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4ወርቅ በ2ብር እና በ2 ነሐስ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኦሮሚያ ክልል በ3 ወርቅ በ3ብር እና በ2 ነሐስ ሁለተኛ አማራ ክልል በ1ወርቅ በ3ብር እና በ4 ነሐስ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የባህል ስፖርቶች ከቤት ውጭ ጨዋታዎች ነገም ቀጥለው የሚካሄዱ ሲሆን በቀስት እና በኩርቦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጨማሪ የወረቅ ሜዳልያዎችን ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

19/06/2025

በ2017በጀት ዓመት ለ65 ወጣቶች በቋሚ እና ለ11 ወጣቶች በጊዘውነት ስራ ዕድል መፍጠረሩ በአዲስ ከተማ ክ/ተማ ወረዳ 9 ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

ሰኔ12/2017ዓ/ም
በአዲስ ከተማ ክ/ተማ የወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት

የወረዳ 9 ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሊድያ ፈጠነ በሰጡት ማብራሪያና ባስተላለፉት መልእክት እንደገለፁት አገራች ኢትዮጵያ ስፖርት ሀገራዊ ክብርን ሀገራዊ መቀራረብን የሚያረጋግጥ አንድ አካል እንደሆነ በመረዳት ስፖርት ለሁሉም በሚል መርህ ሀገራዊ አንድነትና የህዝቦች ወንድማማችነትና ህትማማችነት ለማጠናከር ባህላዊ ሆነ ዘመናዊ ስፖርት ተቋማዊና ህዝባዊ ሆኖ እንድያድግ በወጣቶች ተጠቃሚነትን በተለያዩ ዘርፎች ተሳትፎ የጎፍቃደኝነት ባህል በማድረግ እኩልነትና ፍታሃውነት ለማረጋገጥ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም አብሮነት፣መደጋገፍ፣ መተማመን እና ማስተሳሰር በመሳሰሉት እሴቶች በማካተት ድህነትን ለማስወገድ እና መሰረታዊ ጤናን እና ትምህርትን ለማሻሻል እና በቂ የንፅህና አጠባበቅ፣ የአካባቢ ጉዳዮችን እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ፤ ማህበራዊ ደረጋፍ ለማድረግና ግጭትን ለመቀነስ የወረዳ 9 ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ከወረዳው ወጣት ማህበር ሌሎች ወጣቶችን በማስተባበር እንዲሁም ሌሎች ተቋማት በጋራና በቅንጅት በ2017በጀት ዓመት ዕቅድ አቅዶ በዕቅድ መሰረት ፤
በወጣቶች ተጠቃሚነት ዙሪያ ለ65 ወጣቶች በቋሚ እና ለ11 ወጣቶች በጊዘውነት በተለያዩ ዘርፎች ስራ ዕድል መፍጠሩ፣

2 የዓቅመ ደካሞችን በመለየት መታደሳቸው

ስፖርት በብቃት ለማሰልጠን ለ25 አሰልጣኞች የአሰልጣኝ ስልጠና መሰልጠናቸው

480 ወጣቶች በበጎፍቃድ መሳተፋቸው፤

2400 በአረንጓዴ አሸራ መሳተፋቸውና ችግኞች መትከላቸውና መንከባከባቸው፤
600 ታዳጊ ወጣቶች በስፖርት ዙሪያ መሰልጠናቸው

350 ወጣጦች ማይንድ ሰት መሰልጠናቸው፣40 በሱስ ተገላጭነት ፣35 ወጣት ሴቶች በህይወት ክህሎት ዙሪያ መሰላጠነቸው፤

በወቅታዊ ሁነታ በተደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ከወረዳ እስከ ከተማ 12792 መሳተፋቸው፣

በማሕበረሰብ አቀፍ ስፖርት/ማስ ስፖርት ከወረዳ እስከ ከተማ በድግግሞሽ 40,000 ወጣቶችና ማህበረሰብ መሳተፋቸው፤

በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ፈስቲቫሎች 36325 ወጣጦች መሳተፋቸውና

በስብእና መገንብያ ማዕከል 37688 ወጣቶች በተለያዩ ዘርፍ መሰልጠናቸው እንዲሁም በማዘውተርያ ሜዳ 15000 ወጣቶች ስልጠና ወስደዋል፤

በማዘውተርያ ሜዳው የነበሩ የውሃ፣ የመብራትና መሰል ችግሮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች በፍታት ወጣጦች ወደ ተግባር አስገብተናል ብለዋል፡፡

የወረዳው የወጣቶች በተለያዩ በጎ ፍቃድ ያከናወኑዋቸው ተግባራት ጉልበት ወደ ብር ስተመን 1.8ሚለዮን በመሆን የመንግስትና የህዝብ በጀት ከወጪ በማዳን ፍትሓዊ ልማት አረጋግጠናል ብለዋል ወ/ሮ ሊድያ

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 16/06/2025

ቢሮው በቀጣይ 90 ቀናት ትኩረት አድርጎ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

የከተማው ወጣቶች ጥያቄ መመለስ ቁጥር አንድ አጀንዳው መሆኑንም አሳውቆል።

ሰኔ 09 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በቀጣይ 90ቀናት ትኩረት አድርጎ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አመራሮች፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እና ከአዲስ አበባ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በቀጣይ 90 ቀናት የከተማውን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የቢሮው ቁጥር አንድ አጀንዳ ነው ብለዋል።

የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ከከተማ እስከ ብሎክ የተካሄዱ ውይይቶች ፍሬያማ ውጤቶች የተገኙበት እንደነበር የተናገሩት አቶ በላይ በወጣቶች ለተነሱ ጥያቄዎች ሁሉም አካል ደረጃ በደረጃ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል ።

ቢሮው በቀጣይ 90 ቀናት የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማውን የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የበጎ ፍቃድ ስራም ትኩረት ተደርጎበት እንደሚሰራ ተመላክቷል።

ከብሎክ እስከ ከተማ ከወጣቶች ጋር የተካሄዱ መድረኮች እንዲሳካ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በዛሬው ቀን እውቅና ሰጥቷል።

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 15/06/2025

ስፖርት ለሁሉም ፤ ስፖርት ለፍቅር ፤ ስፖርት ለሰላም ፤ ስፖርት ለአብሮነት !!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር የማስ ስፖርት ንቅናቄ ተካሄደ::

በወረዳው በተካሄደው የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የስፖርት ቤተሰብና የስፖርት አፍቃሪያን ፣ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

በማስ ስፖርቱ ላይ የተገኙት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም ወጣቱ ጊዜውን ለስፖርት በመስጠቱ ከጤናማነት ባሻገር ማህበራዊ አንድነታችንን የሚያጠነክር ትልቅ ተግባር በመሆኑ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የዳበረ አዕምሮ፣የጠነከረ ቁመና እና በስነ ልቦና የተገነባ ዜጋን ለማፍራት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዲሳ አራርሳ ስፖርት ለሁሉም፤ ስፖርት ለፍቅር፤ ስፖርት ለሰላም፤ ስፖርት ለአብሮነት በሚል መሪ ቃል የማስ ስፖርቱ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀው፤ ስፖርት ለጤናችን ወሳኝ በመሆኑ ሁልጊዜ በየአካባቢያችን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አዘውትሮ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰውነት በላይ ስፖርት ለጤንነት፣ ለአንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት ማጎልበት ሰፊ ሚና ስላለው ነዋራዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣አመራሮችና ተማሪዎች ዛሬ ያሳያችሁት ህብረትና አንድነት መቀጠል አለበት ብለዋል::

14/06/2025

🙏🙏🙏🙏🙏

ፕሬስሊዝ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አስተባባሪነት በኳስ ሜዳ በቀን ሰኔ 01/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የማህበረሰብ ስፖርት/ማስ ስፖርት ይካሄዳል።
ግንቦት29 /2017ዓ/ም
አ/ከ/ክ/ከ/የወረዳ 9 ኮ/ጽ/ቤት

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሊድያ ፈጠነ ባስተላለፉት የጥሪ መልእክት እንደገለፁት ስፖርት ለሁሉም በማድረግ ስፖርት ባህል ያደረገ ጤናማ መህበረሰብና ወጣት በመፍጠር ማህበረ ኢኮኖሚ በመተሳሰር የህዝቦች አንድነትና ሰላም ለማረጋገጥ በኳስ ሜዳ የስፖርት መዘውተሪያ ሜዳ በተለያዩ መንግስተዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የወረዳው ማህበረሰብ የሚሳተፍበት የማህበረሰብ ስፖርት/ማስ ስፖርት ለማከሄድ በዕቅድ መሰረት ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁ በመግለፅ ስፖርት የቅድመ መከላከል የጤነ ፖሊስያችን መሰረት ስለሆነ ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ በነቂስ በነገው ዕለት ሰኔ 01/2017ዓ/ም በፕሮግራሙ በንቃት ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

14/06/2025

ተጋብዛችዋል👯‍♂️👯‍♀️👯‍♂️👯‍♀️👯‍♀️👯‍♂️👯‍♂️👯‍♂️👯‍♂️👯‍♂️

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 13/06/2025

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ጋር በ11 ክፍለ ከተማ የጸረ ሙስና ንቅናቄ ስልጠናዎችን አስጀመረ።

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 13/06/2025

የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አባላት በ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጅያዊ እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል አባላት በ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጅያዊ እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

በአዲሱ በጀት ዓመት የወጣቶችን ማሕብራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማውን የስፖርት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በስፋት እንሚሰራ ያስታወቁት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በላፈው በጀት ዓመት የነበሩብንን ጥንካሬዎች በማስቀጠል እና ክፍተቶችን ለማረም ከወዲሁ ስራዎች እንዲጀመሩ ጥሪ አቅርበዋል

በዝግጅት፣በተግባር እና በማጠቃለያ ምዕራፋች ስራን በመከፋፈል በወጣት እና በስፓርት ዘርፍ ስራዎችን ማከናወን ይገባል ያሉት አቶ በላይ ተቋማዊ አስራርን በመዘርጋት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል

የ2018 ስትራታጂክ ዕቅድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የዕቅድ በጀት ድጋፍ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ ቢሮ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና፣ በወጣቶች ማብቃት፣ በማህበረሰብ አቀፍ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በከተማ አቀፍ ስፓርታዊ ውድድሮች፣ በስፓርት ማዘውተርያ ስፍራዋች፣ በክረምትና በበጋ በጎ ፍቃድ እና በታዳጊዎች ስልጠና የሚሰሩ ስራዎች ትኩረት እንደሚሹ አመልክተዋል

አቶ በላይ ደጀን በማጠቃለያ ንግግራቸው ሰባት 24 አሰራር መሰራት በየደረጃው የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በየደረጃው ያለው አመራር እና ባለሙያ ቅንጅት እንዲሰራ አመላክተዋል።

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 13/06/2025

"የድህረ እውነት ዘመንን በእውነትና በእውቀት"

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ከሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነትና ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን "ድህረ-እውነት ዘመንን በእውነት እና በእውቀት" በሚል መሪ ቃል ለበጎ ማህበረሰብ አንቂዎችና አባላት ስልጠና ሰጠ ።

የወረዳው የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ሲትራ ሙራድ በስልጠናው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገራዊ አንድነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ አሉታዊ ትርክቶችንና የተሳሳቱ ሃሰተኛ መልዕክቶችን በእዉቀትና በእዉነት የመታገል ተግባር የበጎ ማህበረሰብ አንቂዎችና አባላት ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ተመስገን ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና በመተግበር የፓርቲውን ስኬት የሚያጎሉ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በትጋት መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ይጠበቅባቹአል ብለዋል።

በመጨረሻም የቀረቡ ሀሳቦች ላይም ውይይት የተደረገ ሲሆን ማጠቃለያ ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል።

Photos from Addis Ketema sub-city woreda 9 youth&sport office's post 03/06/2025

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በክፍለ ከተማው የተገነቡ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው::
****************
ግንቦት 26-2017ዓም

"የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ባለው ጉብኝት የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ቱኩን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እያስጎበኙ ይገኛሉ::

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ቱኩ እንዳሉት የተጀመረው ሐገራዊ ለውጥ እውን እንዲሆንና ፍሬያማ ሆኖ እንዲቀጥል ወጣቶች ከፍተኛ ሚና እየተወጡ መሆናቸውን ጠቅሰው የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ እንዲፋጠን ወጣቶች የሚያደርጉትን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዘይነባ ጣሃ በበኩላቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የከተማዋን መልካም ገፅታ የሚያሳድጉ ሆነው እየተገነቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል::


የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ወጣቶች በበኩላቸው ለውጡ የዜጎችን የረጅም ጊዜ ጥያቄዎች በሚከተለው ሰው ተኮር የልማት ፕሮግራም እየመለሰ መሆኑን የተሰሩ የልማት ስራዎች ማሳያ ናቸው ብለው የበለጠ ስራ እንዲሰራ ከመንግስት ጎን ሆነን የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ገልፀዋል።

በጉብኝት መርሐግብሩ ከላይ ከተጠቀሱ የስራ ሃላፊዎች በተጨማሪ የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም እና የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተባባሪ አቶ ያሬድ አሰፋ ተገኝተዋል::

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa