Addis Ababa city Auditor General

Directions Website

Addis Ababa city Auditor General we audit all addis ababa city government organization.
(1)

26/09/2026

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!

በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮዉ ሁሉ በአሉን ስናከብር እንደ ዳመራዉ በአብሮነት ተደምረን ፣በትብብር ፣በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።

በድጋሚ እንኳን ለደመራ እና መሰቀል በዓል በሰላም አደረሳቸሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !

Baga Ayyaana Daamaraa fi Masqalaaf Nagaan Geessan, Geenye!

Miidhagina magaalaa keenyaa kan ta'an ayyaana addabaabayii keessa tokko kan ta'ee fi Dhaabbata Barnoota, Saayinsii fi Aadaa Mootummoota Gamtoomanii UNESCO, hambaa killayyaatti kan galmaa'e ayyaana Masqalaaf baga nagaan geessan!!

Ayyaanichi duudhaa amantichaa eeggatee, uffata aadaa keenyaan miidhagee, hawwata turizmii ta'ee bifa fuula gaarii biyya keenyaa mul'isuun kabajama.
Akkuma durii ayyaana hunda wayita kabajnu akkuma Daamaraa waliin ida'amnee, tumsaan, waliif yaaduu fi jaalalaan akka kabajnu hawwii kiyya gaariin ibsa.
Irra deebiin baga ayyaana Daamaraa fi Masqalaa nagaan geessan!

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!

26/09/2026

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።
በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም

Baga ayyaana Masqalaatiin isin gahe!

Ayyaanni Masqalaa ayyaana karaa amantaafi aadaatiin guutummaa Itoophiyaatti kabajamudha. Ayyaanichi bifa maatummaafi hawaasummaa qaba. Maatiin kan itti walargudha. Mandarris kan itti walgahudha. Magaalaafi naannawaan gara Addabaabayii tokkootti yeroo itti yaa'udha. Walittiqabamuun mukaa hamma damaraatti jirus fakkeenya humna ida'amuu agarsiisudha. Wayita hunda ayyaanicha yoo kabajnu humnoota Itoophiyaa walittiqabneefi idaanee humna guddaa biyyaalessaa uumuuf haadhimmamnu.

Irradeebiidhaan ayyaana gaarii!

Itoophiyaan tattaaffii ijoolleesheetiin sodaatamteefi kabajamtee bara baraan haajiraattu!!

Uumaan Itoophiyaafi uummattootashee haaeebbisu!
Fulbaana 16/2019.

25/09/2026
የአብሮነት እሴቶች የመዲናችን ድምቀት! የብዝሀነታችን ውበት!የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻን የመሳሰሉ በዓላት ሚሊዮኖች በአብሮነት የሚደምቁባቸው፣ የህዝባችን ማህበራዊ መስተጋብር ከፍ ብሎ ለዓለም...
25/09/2026

የአብሮነት እሴቶች የመዲናችን ድምቀት! የብዝሀነታችን ውበት!

የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻን የመሳሰሉ በዓላት ሚሊዮኖች በአብሮነት የሚደምቁባቸው፣ የህዝባችን ማህበራዊ መስተጋብር ከፍ ብሎ ለዓለም የሚታይባቸው ፀጋዎቻችን በመሆናቸው የሀገራችንን መልካም ገፅታ ከፍ ያደርጋሉ፡፡

የአደባባይ በዓላት የሀገራችንን ጥንታዊ ታሪክ፣ ጥልቅ ባህሎች እና ዘርፈ-ብዙ ማኅበራዊ እሴቶችን የሚያንፀባርቁ የጋራ ሀብቶቻችን ናቸው፡፡ በዓላቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማይዳሰሱ ቅርሶች በመሆናቸው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ካበረከተቻቸው ድንቅ ስጦታዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚህም የመዲናችንን የቱሪስት መዳረሻነት ያሰፉ ሲሆን፣ የሀገራችንን የስዕበት ማዕከልነትም ከፍ አድርገዋል፡፡

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በተለያዩ ብሔረሰቦች፣ የሃይማኖት ተቋማትና የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ለዘመናት የቆዩትን የመቻቻል፣ የመከባበርና የሰላም እሴቶች በተግባር የሚያጸኑ ህያው መድረኮች ሆነው ዘልቀዋል።

ዜጎች የአደባባይ በዓላቱን በጋራ ደምቀው፣ በአብሮነት ተጋምደው ሲያከብሩ፣ የአግላይነት ኋላቀር እሳቤ ይወገዳል፤ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ይጎለብታል፡፡

የአደባባይ በዓላቶቻችን በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ የሚከበሩ የደስታ ቀናት ብቻ ሳይሆኑ፣በየጊዜው ሲላላ የቆየውን የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ትስስር በመጠገን አብሮነትን የሚያጠናክሩ፣ የጋራ ተስፋን የሚያፀኑ የወል ማንነቶቻችን ናቸው።

የሀገር ፍቅር ስሜትንና፣ የህዝብ ትስስርን ከማሳደግ ባሻገር እነዚህ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት የመዲናችንን እና የሀገራችንን የቱሪስት ፍሰት በመጨመር ለለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት አንቀሳቃሽ ሞተር የሚሆኑበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችና የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በዓላቱን በአካል ለመታደም ወደ ሀገራችን ስለሚገቡ፣ ከሚያመጡት የውጭ ምንዛሬ በተጨማሪ የኢትዮጵያን እና የህዝቦቿን ገናና ታሪክ አውቀው የሚያሳውቁበት ምቹ ሁኔታም ይፈጠራል፡፡

በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚጨምረው የቱሪዝም ፍሰት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን የመጎብኘት ተነሳሽነትን ከፍ ስለሚያደርግ፣ ሆቴል እና ትራንስፖርትን ለመሳሰሉ የአገልግሎት ዘርፎች እንዲሁም በባህል አልባሳት፣ የእጅ ጥበብ ውጤቶች እና በመሰል የንግድ ተግባራት ላይ ለተሰማሩ ዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

የሀገርን ታሪካዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለቀጣዩ ትውልድ በማሸጋገር፣ አዲሱ ትውልድ ቱባ ባህሉን እንዲያውቅ እና እንዲንከባከብ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩት የአደባባይ በዓላቶቻችን የወል ትርክታችን ማዕከል፣ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መስተጋብራችን ድምቀት፣ የዘላቂ ሰላማችን ፅኑ መሠረት መሆናቸውን በመረዳት እሴቶቻቸውን መጠበቅ ይገባል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተ...
25/09/2026

የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።

መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ/ም ረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች
• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች
• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ
• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ
• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ
• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።

ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የስራችን ስኬት የሚለካው ነዳጅ በፍጥነት አዲስ አበባ የሚገባበትን መንገድ በተግባር ስናመቻች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)**********************ህዝቦቻችን አዲ...
24/09/2026

የስራችን ስኬት የሚለካው ነዳጅ በፍጥነት አዲስ አበባ የሚገባበትን መንገድ በተግባር ስናመቻች ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**********************

ህዝቦቻችን አዲሱን የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ውጤት በተግባር ማየት አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ እና ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኘውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የማስጀመሪያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዳንጎቴ ግሩፕ የካፒታል አቅሙን፣ የኢንዱስትሪ ልምዱን እና በትልቅ ደረጃ የመፈጸም ከፍተኛ ክህሎቱን ይዞ ወደ ፕሮጀክቱ መግባቱ ለአህጉራዊ ትስስሩ ትልቅ አቅም ፈጥሯል ብለዋል።

አክለውም ይህ ኢንቨስትመንት በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ጠንካራ የልማት ታሪክ የበለጠ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ የአፍሪካ ካፒታል ለራሷ አህጉራዊ መሰረተ ልማት እና ለቀጣይ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚውልበት አህጉራዊ አጋርነት መሆኑን አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዳዲስ ይፋ የሚደረጉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ እምነትና ተስፋ የሚፈጥሩ ቢሆኑም፣ አስተማማኝ እምነት ሊገኝ የሚችለው ግን ፕሮጀክቶቹን በውጤታማነት አጠናቆ በተግባር ማስረከብ ሲቻል ነው ብለዋል።

በመሆኑም አሁን ዋናው ትኩረት የተገባውን ቃል ወደ ሚጨበጥ ተግባራዊ የስራ መስመር መለወጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

"ህዝቦቻችን የዚህን ታላቅ ፕሮጀክት ውጤት በተግባር ማየት አለባቸው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ነዳጅ በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ወጪዎችን መቀነስ፣ የነዳጅ ክምችት አቅምን ማሳደግ እና የንግድ እንቅስቃሴውን የበለጠ ተወዳዳሪ ማድረግ የእለቱ ዋና ቃል ኪዳንና ወደፊትም የስራችን ስኬት የሚለካበት ዋነኛ መስፈርት ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ላሳዩት መሪነትና ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ዘላቂና ጠንካራ አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለአሊኮ ዳንጎቴ በሀገራችንና በአህጉራችን ብሩህ ተስፋ ላይ ላላቸው ሙሉ እምነት ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ፕሮጀክቱ በፋይናንስ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኝ ላደረጉት ለአፍሬክሲም ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጆርጅ ኤሎምቢ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢ...
24/09/2026

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ ይታደማሉ።

Prime Minister Abiy Ahmed arrived in Djibouti and was welcomed by Djiboutian President Ismaïl Omar Guelleh. The two leaders will preside over the announcement of a joint project aimed at strengthening economic ties between Ethiopia and Djibouti.

24/09/2026

ቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ ተቀይፘል !

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Qixal Taraan gara "Ganda Baggoonnat Markaatootti" jijjiirameera!

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!

በአራት ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል?👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ  G+8 የሆኑ ዘ...
24/09/2026

በአራት ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል?

👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች

👉 በአራት ወራት ዉስጥ የተገነቡ 960 ቤቶች

👉 ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች

👉 በውስጡ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣

👉 የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥

👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ

👉 ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች

👉 ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤

👉 እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ: በአስከፊ የእሳት አደጋ የተጎዳ አካባቢ ነበር

👉 “መርካቶ የበጎነት መንደር “ አካባቢዉን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸውን እንደ ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ ያሉ ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።

ቅጠል ተራን ወደ ንፁህ አረንጓዴ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገንበቅጠል ተራ 960 ቤቶችን በአራት ወር  ዉስጥ ገንብተን ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች ...
23/09/2026

ቅጠል ተራን ወደ ንፁህ አረንጓዴ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገን
በቅጠል ተራ 960 ቤቶችን በአራት ወር ዉስጥ ገንብተን ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች መልሰን አስተላልፈናል።
ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ የነበረና የሰው ህይወትም ጭምር በአስከፊ ሁኔታ በእሳት አደጋ ያጣንበት አካባቢም ነበር።
ዛሬ ግን እጅግ ያማሩ ፣ ዘመናዊና ሁሉንም ነገር የተሟሉላቸው ባለ 9 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎች ላይ 960 ቤቶች ተገንብተው ወደ ምቹ መኖሪያ አካባቢ ተቀይሯል።
"የመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር" በ11, 000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች በአጠቃላይ 960 ቤቶች ያሉት ሲሆኑ፣ ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች በውስጡም የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ፥ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች በዘመናዊ መልክ ተሟልተው ተገንብተዋል።
ይህ በመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር የሰው ህይወትን የሚቀይር ፥ መርካቶ አካባቢን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸው ( ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ) ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።
ቃል በተግባር ማለት ይህ ነው፥ እንደዚህ ዓይነት የተወሳሰበ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለሰው ልጆች የሚመጥኑ፥ ነዋሪዎች የክብር ኑሮ እንዲኖሩ፥ ህይወታቸውን የሚቀይሩ ተግባራትን ያለ እረፍት 24/7 በመፈፀም ነዋሪዎች አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ማድረግ ነው ።
የስራዎቻችንን ማዕከል ሁሉ ሰው ተኮር አድርገን፥ ከተማችን ውብ ፅዱ፥ ለነዋሪዎቻችን የተመቸች ከተማ እንድትሆን ያለ እረፍት የመስራት ተግባራችን ይበልጥ አጠናክረን
እንቀጥላለን።
ካላችሁ አካፍላችሁ ከከተማ አስተዳደራችን ጎን በመሆን የበጎ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ፥ ዛሬም በቅጠል ተራ የበጎነት መንደር እንድንቀይር ያገዛችሁን በተለይ ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ፥ በግንባታው የተሳተፋችሁ ሁሉ በነዋሪዎች ስም ከልብ እናመሰግናለን ።
ቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ ተቀይፘል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa city Auditor General posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share