03/09/2024
Mr. Moges Balcha was appointed as the Chairman of the Board of New Media Network!!
Mayor Adanech Abebe has appointed the head of the Addis Ababa branch of the Prosperity Party, Mr. Moges Balchan, as the chairman of the board of Addis Media Network (AMN).
The mayor Ato Moges Balcha sincerely fulfills the responsibilities assigned to him. He urged them to come out with honesty and hard work.
Ato Moges Balcha replaced the former AMN board chairman Mrs. Hikma Hayredin and took over the position.
(I am where the message is)
21/06/2024
ከ83 ዓመታት በኋላ በ105 ዓመታቸው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት ብርቱ ሴት
*****************************************
የ105 ዓመቷ ሴት ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ ይባላሉ። በ1940ዎቹ የትምህርት ህይወታቸውን የጀመሩት እኚህ ሴት ከ83 ዓመታት ቆይታ በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት ቀጥለዋል።
በጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የተገደዱት ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ ከስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተው ነበር::
የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በመቀስቀሱ የመመረቅ እቅዳቸውን አከሸፈባቸው።
በወቅቱ ፍቅረኛቸው የነበሩት ጆርጅ ሂስሎፕ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ሀገራቸውን ለማገልገል መጠራታቸው አዲስ ነገር እንዲፈጠር ምክንያት ሆነ።
እናም የያንጊዜዋ ወጣት ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ ፍቅረኛቸውን ማግባት ነበረባቸው እና ትምህርታቸውን ማቋረጥ ግድ ሆነባቸው። ይህ ብቻም አይደለም፤ ቤተሰባቸውን የመምራት ሀላፊነትም በእርሳቸው ላይ ወደቀ።
ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ ሁለት ልጆችን፣ አራት የልጅ ልጆችን እና ዘጠኝ የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተው ከቤተሰባቸው ጋር ሲኖሩ ያኔ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያቋረጡትን ትምህርት ለመቀጠል ወሰኑ።
በእርግጥ ዋሽንግተን ስቴት ትምህርት ቤት የተማሩበት ብቻ ሳይሆን በስራ ሕይወታቸውም ለአስርት ዓመታት ያገለገሉበት ነው።
እናም ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ አቋርጠውት የነበረውን የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በማምሻ እድሜያቸው ላይ ሆነውም ቢሆን በመቀጠል በስኬት አጠናቀው ለመመረቅ በቅተዋል።
ቨርጂኒያ ሂስሎፕ ጄኒ ከጉድ ሞሪንግ አሜሪካ (Good Morning America) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፥ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቁት የነበረው ሕልም በመሳካቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"ይህ ነገር እንደሚገባኝ ይሰማኛል፣ ማስተርሴንም በማግኘቴ ተደስቻለሁ” ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ኢቢሲ
27/04/2024
የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የምግብ ግብዓት ድጋፍ ተደረገ፡፡
የካ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት ሚያዚያ 19/2016
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ምክር ቤት ሴት ኮከስ አባላት አስተባባሪነት በወረዳው ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለበዓል መዋያ የሚሆን የምግብ ግብዓት የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ ፣ የወረዳው ሴቶች ህጻትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አበባዬ እጀታ እንደዚሁም ይህንን ድጋፍ በማስተባበርና ለውጤት እንዲበቃ ያደረጉት የሴት ኮከስ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዙፋን ገብረእግዚአብሔር በተገኙበት የድጋፍ ተደርጓል፡፡
በድጋፊም ላይ የተገኑት የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት አበራሽ ቡቼ ሴቶች ቁጠባን ባህል በማድረግ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች እንዲተርፉ የማድረግ ስራ በየግዜው እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም በዛሬው እለት የሴት ኮከስ አባልና ሰብሳቢ ከሆኑት ዙፋን ገብረእግዚአብሔር አማካኝነት ለባዕል መዋያ የሚሆን የምግብ ግብዓት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
የወረዳው ሴቶች ህጻትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አበባዬ እጀታ በበኩላቸው የሴቶችን አቅም ለማጎልበት የቁጠባ ባህላቸውን ለማሳደግ ሴቶች በመሀበር እየተደራጁ ከሚያገኙት ገቢ እየቆጠቡ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደ ጽ/ቤታችን ድጋፍ ለማድረግ እሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
05/04/2024
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ11 ምክር ቤት ጽ/ቤት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2ና3 ምክር ቤት ጋር ልምድ ልዉዉጥ አደረገ።
የየካ ክፈለ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት
መጋቢት 27/2016ዓ/ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2ና3 ምክር ቤት ጽ/ቤት የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ልምድ ልዉዉጥ አካሂዷል።
በልምድ ልዉዉጡ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መኮንን ተከስቴ ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ብንያም ሀይሉ ፣ የ3ቱ ወረዳዎች የምክር ቤት ፀሀፊዎችና የምክር ቤቶቹ ባለሙያዎች ተገኝቷል።
በልምድ ልዉዉጡ ማጠቃለያዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2ና3 ወደ የካ ወረዳ 11 ድረስ በመምጣታችሁ እጅግ ደስተኞች መሆናቸዉን ገልጿል። አፈ ጉባኤዋ አክለዉም በ2016ዓ:ም ግማሽ አመት ወረዳዉ የተሻለ አፈፃፀም ያለዉና በእርካታ ስራዎችን የሰራንበት በመሆኑ ልምድ ሊወሰድባቸዉ የሚገቡ የሚችሉ ስራዎችን ዘርዝሯል።
የአዲስ ከተማ ክፈለ ከተማ ወረዳ 2 ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መኮንን ተከስቴ ዛሬ ከየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ከምክር ቤት መደበኛ ስራ አንፃር በርካታ ልምድ የሚወሰዱ ተሞክሮ የሚሆኑ ሞዴል ስራዎች መኖራቸዉን የለየን ስሆን ቀጣይ ወደ እኛ ወረዳ ወስደን ተሞክሮ ቀምረን ለቀጣይ ስራዎቻችን አቅም የሚሆንበት ሁኔታ ይፈጥራል ብሏል።
04/04/2024
የአቅመ ደካማ ወገኖች የቤት እድሳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የየካ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት መጋቢት 26/2016ዓ/ም
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤትና በወረዳው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የ3 አባወራ ቤቶች ሙሉ እድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ የተከበሩ አቶ ታደሰ ወርቁ፣ የወረዳዉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ የተከበሩ አቶ አብዱልፈታህ እስማኤል፣ የወረዳዉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼን ጨምሮ ሌሎች የወረዳዉ አመራሮች እንዲሁም ባለሀብቶችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝቷል።
የማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረጉት የወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ የተከበሩ አቶ ታደሰ ወርቁ እንደተናገሩት መንግስት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ለሰዉ ተኮር ተግባራት ቅድሚያ በመስጠት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደምገኝ ገልፀዋል። በወረዳው አስተዳደርም በበጋ የበጎ ፍቃድ መርሀ ግብር 42 ቤቶች ለማደስ አቅደው ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ቤቶች በማደስ ላይ እንደሚገኝ በመጠቆም በዛሬው እለት የተጀመሩት የ3 አባወራ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎችም የጀመርናቸዉ በፍጥነት እድሳታቸው ተጠናቅቆ ለባለቤቹ የሚናስረክበዉ ይሆናል ብሏል።
ኃላፊው አያይዞም በዚህ ተግባር ላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉትን በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችን ልባዊ ምስጋና በማቅረብ ድጋፋቸዉን አጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፏል።
04/04/2024
በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሴት ኮከስ አባላት በሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ተሳትፎ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክርቤት በ2016 በጀት ዓመት የሴት ኮከስ አባላት የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በተመለከለተ፣ ፆታዊ ጥቃትን በሚመለከትና የሴቶች በኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ሁሌንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ በማረጋገጥ ሴቶች ከራሳቸው አልፈው ለሀገር እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆን እንደምገባ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን አዘጋጅቶ የሰጡት የወረዳው የምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ ሲሆኑ ከስልጠናው በርካታ ልምዶች እና ተሞክሮዎች እንዲሁም ተነሳሽነትን የፈጠረ ስልጠና እንደነበር ተገልፀዋል።
የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን መጋቢት 25/2016
22/03/2024
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክርቤት 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት ሊያካሄድ ነው።
የካ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት መጋቢት 13/2016ዓ/ም
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት የ11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት መጋቢት 14/2016ዓ/ም የሚያካሂድ መሆኑን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ አስታውቀዋል።
በጉባኤው ላይ የ11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ተወያይቶ ማፅደቅ፣ የወረዳ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ተወያይቶ ማጽደቅ ፣የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ማፅደቅ እንደዚሁም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች የሚያስቀመጡ እንደሆነ ተገልፀዋል።
21/03/2024
የምክር ቤት የጉባኤ የቅድመ ጉባዔ ውይይት ተካሄደ፡፡
የካ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት
መጋቢት 12/2016 ዓ.ም
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የምክር ቤት የጉባኤ ቅድመ ጉባዔ ውይይት ተካሂዷል። በቅድመ ጉባዔው መድረክ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሴ ወርቁ ጨምሮ ሌሎች የወረዳው አመራሮች እንዲሁም አስተባባሪ ኮሚቴና ጥሪ የተደረገላቸው ባለ ድርሻዎች ተገኝተዋል ።
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የቅድመ ጉባዔ ውይይት በማስመልከት የወረዳ 11 ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ የ2016 ዓ.ም 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን በዚሁ መሰረትም የወረዳው የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ በአቶ አብዱ ሰይድ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከዚህ በማስቀጠልም የተከበረው የምክር ቤት ጽ/ቤት አስተባባሪ ኮሚቴ በ2016 ዓ/ም በ6 ወራት ባደረጉት የመስክ ምልከታና የተገኙ ግኝቶች በተከበሩ በአቶ አዱኛ አጫ የወረዳ 11 ምክር ፀሀፊ ቀርቧል።
በቀረበው ሪፖርት መሰረት በማድረግ ኮሚቴዉ አባላት ሀሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ዙሩያ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ወርቁ ምላሽ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የ2016ዓ/ም የ6 ወር የምዘና ውጤት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ጽ/ቤቶች የእውቅናና ሽልማትን ተሰጥተው መድረኩ ተጠናቋል።
29/02/2024
አስደሳች ዜና !!
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በ6 ወራት የስራ አፈጻጸም በክ/ከተማው ካሉት ከ13ቱ ወረዳዎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ 3ኛ ደረጃ በውጣት የምስክር ወረቀት በማገኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!!
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት
የካቲት 21/2016ዓ/ም
ለዚህ ለላቀ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ የምክር ቤቱ ባለድርሻ አካላት ፣ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሙሉ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለቀጣይም ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሙሉ መተማመንን ጋር ነው!!
ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ
22/02/2024
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት አባላት ጉብኝት አደረገ።
የየክ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት የካቲት 14/2016ዓ/ም
በዋና አፈ ጉባኤዋ ክብር ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ የተመራዉ የጉብኝት መርሃ ግብር በወረዳ 11 ስር በሚገኘዉ ሰላም ቴክንክና ሙያ ማሰልጠኛ ግቢ ዉስጥ የተሰራዉን ሞዴል የከተማ ግብርናና ሌማት ትሩፋት ስራ ተዘዋዉሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ መርሃ ግብር ላይ የየካ ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ምክር አባላት ተገኝቷል።
22/02/2024
የተከልናቸው ችግኞች በመንከባከብ የአረንጓዴ አሸራ እቅዳችን እናሳካለን።
የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት
የየካ ክ /ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ጽ/ቤት አስተባባሪነት "የተከልናቸው ችግኞች በመንከባከብ የአረንጓዴ አሸራ እቅዳችን እናሳካለን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ የመንከባከብ ንቅናቄ ተደረገ።
በመረሀግብሩ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ የከተማ ውበት አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እየሩሳሌም ዘነበ ፣የየካ ክ ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኪታራው በጋሻው ፣ የወረዳ 11 አመራሮች ፣ በየቀጠና የተወጣጡ ነዎሪዎች ታድሞዎል።
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አበራሽ ቡቼ እንደገለፁት በክረምቱ የተከልናቸው ችግኞች ተመልሰን እንከባከባለን ብለን በገባነው ቃል መሰሠረት ዛሬ ሰላም ህፃናት መንደር በመገኘት የችግኝ መንከበከብ እየተሰራ መሆኑ ገልፀው ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ የተተከሉት ችግኞች ፀድቀው ፍሬ እስከሚያፈሩ ኃላፊነታችን መወጣት እንደሚገባ አሳስቦዎል።