28/05/2026
ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት!
መልዕክትዎን ለመቀበል ቀላል መንገድ ከኢትዮጵያ ፖስታ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት (Virtual P.O. Box) በማንኛውም ጊዜ መልእክትዎን ለመቀበል ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል መዳረሻ ይሰጥዎታል።
ለግለሰቦች እና ንግዶች ተደራሽነትን የሚያሻሽል በሁሉ መልኩ የሚወዱት መተግበሪያ፡፡
ከ1000 በላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገር ውስጥ ቅርንጫፎች እና 194 የሚልቁ አለም አቀፍ መዳረሻዎች መልዕክቶችን ለመላክ እና ለመቀበል ዘመናዊ የፖስታ መፍትሄ ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት (Virtual P.O. Box)።
መተግበሪያውን በማውረድ ካሻዎትም app.ethio.post ላይ በመግባት በቀላሉ ይመዝገቡ ዲጂታል አድራሻዎትን ይያዙ፡፡
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም ያግኙን።
ሀሳብ ወይም አስተያየት ካልዎት https://forms.gle/7yw6mcxAi9tK2ean6
Follow us on our social media platforms
Facebook (https://www.facebook.com/EthiopianPostalService) | Telegram (https://t.me/Ethiopianpostal) | LinkedIn (https://www.linkedin.com/company/ethiopost) | Twitter (https://twitter.com/ethiopost) | Instagram (https://www.instagram.com/ethiopostal/) | Pinterest (https://pinterest.com/ethiopost) (Philately) | TikTok (https://www.tiktok.com/) |
27/05/2026
የኢትዮጰያ ፖስታ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል!
ኢድ ሙባረክ!
al Adha
Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok
25/05/2026
የኢትዮጵያ ፖስታ የደንበኞች እርካታ የዳሰሳ ጥናት።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሻሻል የደንበኞችን አስተያየት እየሰበሰበ ይገኛል።
የእርስዎ እውነተኛ ምላሽ ክፍተቶችን ለመሙላትና ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል ትልቅ እገዛ አለው።
በምስሉ ላይ ያለውን የQR ኮድ በስልክዎ በመቃኘት ወይም ይህንን ሊንክ በመጫን https://ee.kobotoolbox.org/x/vp1FgLhT በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አስተያየትዎን ያጋሩን።
የሚሰጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ ሲሆን ስምዎንም መጥቀስ አይጠበቅብዎትም። ውድ ጊዜዎን ስለሰጡን እናመሰግናለን!
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም ያግኙን።
25/05/2026
የኢትዮጵያ ፖስታ እና የፈረንሳዩ ላ ፖስት La Poste ልኡካን ውይይት አደረጉ።
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የሥራ አመራር ቡድናቸው ከፈረንሳዩ የፖስታ ድርጅት ላ ፖስት ግሩፕ La Poste ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ፖስታ ዋናው መሥሪያ ቤት ውጤታማ ውይይት አካሄዱ።
ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ከ2022 ጀምሮ በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የቴክኒክ ድጋፍ እየተገበረ ያለውን የዘመናት ትብብር ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ተብሏል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ፖስታ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ስር አስተማማኝ የገቢ ዕድገት ማስመዝገቡ፣ የአገልግሎት ዘመናዊነትን ማረጋገጡ፣ የፋይናንስ አካታችነትን ማስፋፋቱ፣ የብራንድ ማሻሻያ ማድረጉ እና ከጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ጋር ያደረጋቸው የፈጠራ ሥራዎች ትስስር ለዚህ አጋርነት መሳካት ትልቅ መሰረት እንደሆኑ ተገልጿል።
አዲሱ የትብብር ምዕራፍ የኢትዮጵያ ፖስታን አዲስ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በጥራት ለመቅረጽ፣ አተገባበሩን ለመደገፍ እና ቀጣይነት ያለው የልምድ ልውውጥ በማድረግ የሁለቱን ሀገራት አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።
ይህ ጥምረት ወደ ረጅም ዘመን የጋራ ታሪክ የሚወስድ ሲሆን 1894 ዓ.ም ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለፈረንሳይ መንግስት የመጀመሪያዎቹን ቴምብሮች እንዲነድፍ እና የመጀመሪያዎቹን የፖስታ አገልግሎቶች እንዲያስጀምር ጥያቄ ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ የዘለቀ ታሪካዊ ትስስር ነው።
Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |
18/05/2026
ሳምንትዎን በድል ያጠናቁ!
ይህ ቀን ጎልቶ ለመውጣት እና ሳምንትዎን በዓላማ ለመጨረስ ትልቅ እድል ነው። ጉልበትዎን በጥበብ ይጠቀሙ እና ፈተናዎችን ወደ እድገት ይቀይሩ።
ከእርስዎ የተሻለ አሸናፊ የለም፡፡
ሀሳብ ወይም አስተያየት ካልዎት https://forms.gle/7yw6mcxAi9tK2ean6
Follow us on our social media platforms
Facebook (https://www.facebook.com/EthiopianPostalService) | Telegram (https://t.me/Ethiopianpostal) | LinkedIn (https://www.linkedin.com/company/ethiopost) | Twitter (https://twitter.com/ethiopost) | Instagram (https://www.instagram.com/ethiopostal/) | Pinterest (https://pinterest.com/ethiopost) (Philately) | TikTok (https://www.tiktok.com/) |