04/06/2026
በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የተመራ የልኡካን ቡድን እድሳቱ የተጠናቀቀውን አዲስ የመድኃኒት ፋብሪካን ጎበኙ
___________
ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋራ በቅርበት በመሥራት፤ ጥራቱን፣ ደረጃውንና ደህንነቱን የጠበቀ ምርት ማምረት እንዲጀምር ይደረጋል ያሉት ወ/ሮ ፍሬህይወት: ድርጅቱ የጥሬ ዕቃና የግብዓት እጥረት እንዳይገጥመው የባለድርሻ አካላት ድጋፍ የማይለየው መሆኑ በመግለጽ፣ ምርታማነቱን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ያካተተው የልኡካን ቡድኑ ጁልፋር የመድኃኒት ፋብሪካን ጎብኝቷል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
03/06/2026
“ሰብአዊ ተግባር ሕይወት ይታደጋል፤ ብርሃን ይመልሳል”
ሰኔ 07 — የዓለም የደምና የዓይን ብሌን ለጋሾች ቀን
እንኳን ለዓለም የለጋሾች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
ሰኔ 7 ቀን በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው ክቡር ደማቸውን በመለገስ የሰውን ልጅ ሕይወት ለታደጉ እና የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል በመግባት ለወገኖቻቸው አዲስ ተስፋና የብርሃን ምንጭ ለሆኑ ውድ የሀገራችን በጎ ፈቃደኞች የላቀ ምስጋና የሚቀርብበትና ዕውቅና የሚሰጥበት ልዩ ዕለት ነው።
እያንዳንዱ የደም ልገሳ ውድ የሕይወት ማዳን ስጦታ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የዓይን ብሌን ልገሳ ደግሞ ለሌላው ሰው ዓለምን በደመቀ ሁኔታ እንዲያይ የሚያደርግ ታላቅ ሰብአዊነት ነው። በአንድነት በመረባረብ ዘላቂ፣ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የሕይወት አድን አቅርቦትን በሀገራችን ማረጋገጥ እንችላለን።
ዛሬውኑ ይወስኑ!
ደም በመለገስ ሕይወትን ይታደጉ፤ የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል በመግባት ብርሃን ይመልሱ!
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
03/06/2026
የዓለም አቀፍ የህክምና ሙከራ ቀን “አብሮነት ለተሻለ የህክምና ሙከራ ምርመራ” በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
_________
የዓለም አቀፍ የህክምና ሙከራ ቀን /International Clinical Trial Day/ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ተከብሯል፡፡
የህክምና ሙከራዎች አዳዲስ መድሃኒቶች፣ ክትባቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች ለሰው ልጅ ደህንነታቸውን የተጠበቁና ውጤታማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ሂደቶች መሆናቸውን የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ጠቁመዋል፡፡
የህክምና ምርምሮች የጤና ፍትሐዊነት፣ የሕዝብ አመኔታና የአገር ልማት ጉዳይ መሆኑን
በጤና ሚኒስቴር የፓሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር አስቴር ፀጋዬ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የህክምና ሙከራ ኔትዎርክ መኖርና ማደግ ትልቅ አገራዊ ምዕራፍ ነው ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚዋ በተመራማሪዎች፣ በላቦራቶሪዎች፣ በሥነ-ምግባር ኮሚቴዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በጤና ተቋማት፣ በኢንዱስትሪው፣ በማኅበረሰቡ እና በዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል የኢትዮጵያን የህክምና ሙከራ ሥነ-ምህዳር በትብብር ለማሳደግ የሚያስችል መድረክ ተፈጥሯል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሥነ-ምግባር የታነጸ፣ ሁሉንም ያካተተ እና ጥራቱን የጠበቀ የህክምና ሙከራ በማካሄድ ረገድ የቀጣናው መሪ መሆን ትችላለች ብለዋል።
በኢትዮጵያ የህክምና ሙከራዎች ቀን መከበሩ ህብረተሰቡ ስለ ሙከራዎቹ ሳይንሳዊ ሂደት፣ ስለ ተሳታፊዎች መብትና ደህንነት ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረውና የተሳሳቱ አመለካከቶች እንዲቀረፉ ያደርጋል ተብሏል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
03/06/2026
ለሰብአዊ ድጋፍ እና መድሃኒት አቅርቦት የሚያገለግሉ 28 የጭነት መኪናዎች እና ጥልቅ የከርሰ ምድር ውሃ መቆፈሪያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ
_________
በርክክብ መድረኩ ድጋፉን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ላደረገው ኤፍ.ሲ.ዲ.ኦ (FCDO)፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ሕዝብ እና መንግስት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የመድኃኒት አቅርቦትን የመጨረሻው ርቀት ላይ ለማድረስ ጠንካራ አጋር መሆኑን ገልጸዋል።
ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር ያለውን ጠንካራ አጋርነት ያብራሩት ሚስትሯ: ድጋፉ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥን ያጠናክራል ብለዋል። በተጨማሪም ድጋፉ ንጹህ ውሃ በማቅረብ የዋሽ (WASH) ፕሮግራምን እንደሚደግፍ አክለዋል።
ድጋፉ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ በኤፍ.ሲ.ዲ.ኦ (FCDO) እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር መካከል ያለውን ትብብር ያሳያል ያሉት በኢትዮጵያ የዩኬ አምባሳደር ዳረን ዌልች: ድጋፉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን አቅም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የተደረገው ድጋፍ በአደጋ ጊዜ የእርዳታ እና የህክምና አቅርቦቶችን ለማድረስ እንደሚረዳ አቶ አበራ ቶላ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዝዳንት የተናገሩ ሲሆን: የማህበሩን የሰብአዊ አገልግሎቶችን ያጠናክራል ብለዋል። ደጋፉ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ወቅታዊ የሰብአዊ እርዳታ መድረሱን ያረጋግጣል ብለዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
03/06/2026
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ማህበር 8ኛ ሳይንሳዊ፣ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል
______________
ጉባኤውን የከፈቱት በጤና ሚኒስቴር የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ አሀድ ጤና ክብካቤ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ እስራኤል አታሮ፣ የአካባቢ ጤና የማብረሰብ ጤና ዋና መሰረት መሆኑን ገልጸው የአየር ጥራት፣ የመጠጥ ውሃ፣ የምግብና የሳኒቴሽን ስርዓቶች የማህበረሰቡን ጤናና ደህንነት በቀጥታ እንደሚወስኑ፣ እነዚህ ሲደናቀፉ የበሽታ ጫናና የምርታማነት ችግር እንደሚከሰት አስታውቀዋል።
እንደ ሊድና ሜርኩሪ ያሉ ከባድ ማዕድናት እና ሌሎች ኬሚካላዊ ብክለቶች እያሳደሩ ያሉት ተፅዕኖ አሳሳቢ መሆኑን የተናገሩት አቶ እስራኤል የአካባቢ ጤናን መጠበቅ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ በWASH ስርዓቶች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለሰው ክብር፣ ለኢኮኖሚ እድገትና ለወደፊት ትውልድ ጠቃሚ መሆኑ አሰገንዝበዋል።
ጉባኤው ፖሊሲ አውጭዎችን፣ ተመራማሪዎችን፣ ምሁራንን፣ ባለሙያዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና የልማት አጋሮችን በአንድ መድረክ በማሰባሰብ ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን፣ ተግባራዊ ተሞክሮዎችን፣ ፈጠራዊ አሰራሮችን እና የፖሊሲ እይታዎችን ለመጋራት አስፈላጊ እድል የሚፈጥር ነው ያሉት የኢትዮጵያ የአከባቢ ጤና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አርጋው አምበሉ ከመድረኩ የሚወጡ ውይይቶች፣ ምክረ ሃሳቦች እና የትብብር ተነሳሽነቶች በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የአካባቢ ጤናና የውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የንፅህና (WASH) ስርዓቶችን ለማጠናከር ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
31/05/2026
በዶ/ር ቴድ ቤላንገር የተመራዉ የበጎ ፈቃደኛ የሀክሞች ቡድን 30 ውስብስብ የአከርካሪ አጥንት መዛባት ቀዶ ህክምናዎችን በተሳካ ሁኔታ አከናወነ
____________
በኮሪያ ሆስፒታል እየተካሄደ ባለዉ የአከርካሪ አጥንት ቀዶ ህክምና ዘመቻ እስካሁን 30 ውስብስብ የአከርካሪ አጥንት መዛባት ቀዶ ህክምናዎችን በተሳካ ሁኔታ ተከናዉኗል።
በጎ ፈቃደኛ የህክምና ቡድኑ በቀጣዩ ሳምንት ተጨማሪ 15 ቀዶ ህክምናዎችን ለማከናወንም አቅዷል።
በኮሪያ ሆስፒታል በመገኘት ቡድኑን ያበረታቱት የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የታካሚዎችን ተስፋ የሚመልሰውን፣ ህይወትን የሚለውጠውን እና የኢትዮጵያን የአከርካሪ አጥንት ህክምና አቅም ለቀጣዩ ትውልድ በሚሸጋገር መልኩ የሚያጠናክረውን ይህንን የረጅም ጊዜ አጋርነት JDC በማስተባበሩ አመስግናዋል።
ይህ የህክምና ዘመቻ በአሜሪካን ጁዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢዩሽን ኮሚቴ (JDC) አስተባባሪነት፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሀገር ውስጥ የጤና ተቋማት ጋር በቅንጅት የተዘጋጀ ሲሆን፤ እየተመራም የሚገኘው በታዋቂ የህክምና ባለሙያ በዶ/ር ቴድ ቤላንገር እና በቡድናቸው ነው።
A volunteer medical team led by Dr. Ted Belanger successfully performed 30 complex spinal deformity surgeries
______________
In the spinal surgery campaign currently underway at the Korea Hospital, 30 complex spinal deformity surgeries have been successfully performed so far.
The volunteer medical team also plans to perform an additional 15 surgeries next week.
In a message conveyed by the State Minister of Health, Dr. Dereje Duguma, who visited the Korea Hospital to encourage the team, he expressed gratitude to JDC for coordinating this long-term partnership that restores patients' hope, changes lives, and strengthens Ethiopia's spinal medical capacity in a way that transfers to the next generation.
This medical campaign was organized in collaboration with the Ministry of Health and local health institutions, under the coordination of the American Jewish Joint Distribution Committee (JDC); it is being led by the renowned medical professional Dr. Ted Belanger and his team.
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
30/05/2026
ፓን-አፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማህበር (PAHCS) የመመስረቻ ጉባኤ ተካሄደ
_________
የፓን-አፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማህበር (PAHCS) በአፍሪካ የኤችአይቪ እንክብካቤ እና ህክምናን ለማሻሻል የህክምና ባለሙያዎችን እና አጋሮችን በማስተባበር እየሰራ ይገኛል፡፡
ማህበሩ የአፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖችን አንድ ላይ በማስተባበር እና አብሮ ለመስራት እንደሚያስችል የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ያስረዱ ሲሆን፣ አፍሪካ በኤችአይቪ መከላከል እና መቆጣጠር ረገድ በርካታ ግቦችን አሳክታለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የኤችአቪ ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኗን ያረጋገጡት ዶ/ር መቅደስ: ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍን መግታት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የማህበሩ መመስረት አህጉራዊ ትብብርን በማጠናከር: ሀገራት ክልኒካዊ የትግበራ ሳይንስ እና ምርምሮችን እንዲጋሩ እንደሚያስችል አክለዋል።
ዶ/ር ሙሃንግዊ ሙላውዲ፣ የፓን አፍሪካ የኤችአይቪ ክሊኒሻኖች ማህበር (PAHCS) ሊቀመንበር በበኩላቸው ማህበሩ የተቋቋመው በኤችአይቪ ዙሪያ የሚሰሩ አፍሪካውያን ክሊኒሻኖችን አንድ ላይ ለማምጣት እና ድምፃቸውን ለማሰማት እንዲሁም አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
የማህበሩ በአዲስ አበባ መመስረት የአፍሪካ አንድነት ማሳያ ምልክት ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ምክንያቱም አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት (AU) መቀመጫ በመሆኗ ነው ብለዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
27/05/2026
ከጣሊያን አገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች ላከናወኑት 80 የሕፃናት የልብ ቀዶ ሕክምና የምስጋና እና አውቅና ፕሮግራም ተካሄደ
____________
በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎቹ ለረጅም ጊዜ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ለነበሩ 80 የልብ ሕሙማን ሕፃናት የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ባለፉት ስድስት ሳምንታት ውስጥ በሁለት ዙር የሰጡ ሲሆን 48 ሕፃናት በአዲስ አበባ ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል፣ 9 ሕፃናት በጂግጂጋ እንዲሁም 23 ሕፃናት በጎንደር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተሰጠው አገልግሎት በጤና ሚኒስቴር፣ በራሳቸው ስምና ከሁሉም በላይ በዚህ ሕክምና ተጠቃሚ በሆነው ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ መልካም ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረው የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጤና ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለዚህ ዓላማ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተለይም ለኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ የተባለው ግብረ-ሠናይ ድርጅት በገንዘብ እና በማስተባበር ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ45 ቀናት ለ175 ሕፃናት የልብ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት በጤና ሚኒስቴር፣ በኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ እና በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት መካከል የተደረገ ስምምነት አካል ነው።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB
26/05/2026
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__________
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥራችሁ ጋር አስተሳሰራችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት እየተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችሁም ተመዛኞች ከግንቦት 20 – 26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።
▪ ለብቃት ምዘና ፈተና የመፈተኛ ጣቢያ መምረጥ የምትችሉት ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች ብቻ ይሆናል፡፡
▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
▪ ለበለጠ ማብራሪያ በቴሌግራም ቻናል የተያያዘውን ቪዲዮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB