የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

Share

Perform procurement of public organization common user items and nationally strategic utilities; render efficient and effective property disposal service;

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ሐምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሲቋቋም ዓላማዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን የመንግስት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡

26/05/2026
Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 25/05/2026
Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 24/05/2026

በዘመናዊ የመረጃ ልውውጥና የሰነድ አስተዳደር ስርዓቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
*******************************************
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በዘመናዊ የመረጃ ልውውጥና የሰነድ አስተዳደር ስርዓት (E-Office Document Management system) ዙሪያ ለሪከርድና ማህደር እና ሰነድ ያዥ ሠራተኞች በትናንትናው ዕለት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በአገልግሎቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢቲሳ ደሜ (ዶ/ር) እንዳሉት የመንግስት ግዥ አገልግሎት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ዲጂታል ፒፒኤስ (Digital PPS) የሚል ዕቅድ አዘጋጅቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ፤ የዛሬው ስልጠናም ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥና የሰነድ አስተዳደር ስርዓቶችን (E-Office Document Management system) ተግባራዊ በማድረግ ፣ የተቋሙ ስራ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆን ለማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል ።
ይህን ለማሳካት የፈፃሚዎችን የዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ፤ የዚህ ዓይነት የክህሎት ስልጠናዎች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ስልጠናው ተግባር ተኮር በመሆኑ እና ከስልጠና ስትመለሱ ወደ ስራ የምትገቡበት በመሆኑ በትኩረት ልትከታተሉ ይገባል ሲሉ ሰልጣኞችን አሳስበዋል።
ስልጠናው ከኢኖቬሽን ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን የተሰጠውን ተግባር ተኮር ስልጠና መሠረት በማድረግ ከተሳታፊዎች በአፈፃፀም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ችግሮች እና በስርዓቱ አተገባበር ዙሪያ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያዎች ተደርጎባቸዋል።

Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 19/05/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት የማኔጅመንት አባላት የመረጃ ሉአላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት ሀገራዊ ጉባኤና ኢግዚቢሽንን ጎበኙ
ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በጋራ በመሆን በአዲስ ኮንቬሽን ማዕከል የተዘጋጀው "የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት" ሀገራዊ ጉባኤና ኢግዚቢሽን ከግንቦት 10 - 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትናንትናው ዕለት በይፋ ተከፍቷል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ ያከናወነቻቸውን ተቋማዊና ቴክኖሎጂካዊ ለውጦች ለመታዘብ የሚያስችል ከመሆኑ ባሻገር የመንግስት የልማት ዕቅዶችን በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ቀረፃና የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ግንዛቤ እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
የመንግስት ግዥ አገልግሎት የማኔጅመንት አባላትም "የመረጃ ሉአላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሀገራዊ ጉባኤና ኢግዚቢሽንን በዛሬው ዕለት በቦታው በመገኘት ጉብኝት አካሂደዋል።

Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 19/05/2026

በዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ
******************
ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች በአገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርገዋል።
የአገልግሎቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ረድኤት ተክሉ በዝርዝር ቀርቧል ። የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግም ከተሳታፊዎች ግብዓት የሚሆኑ ሀሳብና አስተያየት ቀርቦ ማብራሪያ ተደርጎባቸዋል ።
በውይይቱ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ እንደገለፁት ፤ ባለፋት ዘጠኝ ወራቶች በማዕቀፍና ስትራቴጂክ ግዥዎች ትልቅ ውጤት መፈፀሙን ተናግረዋል።
በንብረት ማስወገድ ዘርፍም በየጊዜው እያደገ የመጣ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀው ፤ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙም ከመቶ ፐርሰንት በላይ መሆኑን ክቡር አቶ አስማረ አስገንዝበዋል ።
የአገልግሎቱ የበጀት አፈፃፀም ጥሩ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው በቀጣይ በጥንቃቄና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል ።
ክቡር አቶ አስማረ አክለውም ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ በተለይ ሠራተኛው ሌሎችን የመርዳትና የመደገፍ ባህሉ እያደገ መሆኑን ገልፀው ፤ በቀጣይም ይህ በጎ ተግባር ተቋማዊ ባህል ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል ።
በአጠቃላይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸማቸው የሚያበረታታ እና ጥሩ መሆኑን ገልፀው ፤ አንዳንድ ወደኃላ የቀሩ ስራዎችን በተቀመጠው ጊዜ መፈፀም እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 11/05/2026

የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን እና የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማትን ጉበኙ
***************
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን እና የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማትን በዛሬው ዕለት ጉብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱን ዋና ዓላማ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክ ለትውልድ ለማስተላለፍ፣ ዓድዋ የአንድነታችንና የነፃነታችን ምልክት ሆኖ እንዲዘለቅ፣ እንዲሁም የጀግኖች አርበኞችን መስዋዕትነት በዘመናዊ መንገድ ለማስታወስ ታስቦ የተገነባውን ታሪካዊ ሙዚየም ከመጎብኘት ባሻገር፤ እኛም የአገልግሎቱ አመራሮችና መላው ሰራተኞች የዓድዋ ጀግኖች አባቶቻችን ህይወታቸውን ሰውተው ያስረከቡንን ሀገራችን በየተሰማራንበት የስራ መስክ በርትተን በመስራት እና ውጤታማ በመሆን የአባቶቻችን ድል በውጤት ለመድገም የሀገር ፍቅርና የሥራ ተነሳሽነት እንዲኖረን ለማስቻል ነው፡፡
በተጨማሪም አመራርና ሠራተኞች የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማትን የጎበኙ ሲሆን ቀን ከሌሊት በመስራት አዲስ አበባ እንደ ስሟ አበባ እንድትሆን ላደረጉ የከተማዋ አመራሮችና ሰራተኞች ምስጋናቸውን በማቅረብ በቆሻሻ እና ጥሩ ባልሆነ ሁኔታ የነበሩት ወንዞቿ ዛሬ አምረው እና ተውበው ከተማዋን ዘመናዊ ከማድረጋቸው ባሻገር የልማት ማዕከል መሆናቸውን በማየታቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አመራርና ሰራተኞቹ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምንም ሆነ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማትን መጎብኘታቸው በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰራ ያለውን ውጤታማ ስራ ማየት እንዳስቻላቸው እና ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Photos from የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS's post 07/05/2026

በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ጉብኝት ተካሄደ
***************
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የዘንድሮውን የ4ኛው ዙር የ"ኢትዮጵያ ታምርት" አለም አቀፍ ኤክስፖን በዛሬው ዕለት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ዋና ዓላማ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማበረታታትና ምርታቸውን ለዓለም አቀፍ ገበያ ማስተዋወቅ ነው።
አገልግሎታችንም የሀገር ውስጥ ምርትና አምራቾችን በማበረታታት እና ህጉ በሚፈቅደው አግባብ ልዩ አስተያየት በማድረግ ምርታቸውን በጥራት እና በብዛት አምርተው እንዲያቀርቡ በማስቻል በየዓመቱ የጋራ መጠቀሚያ እና ስትራቲጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ግዥዎች በቢሊየን ብር ግዥ በመፈጸም የሀገር ውስጥ ምርት እና አምራቾችን ከማበርታታት ባለፈ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ጉብኝቱ አገልግሎታችን የሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶችን በማበረታታት ምርታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል፡፡
በተጨማሪም የቴክኖሎጅ ፈጠራና ትስስርን በመፍጠር በቴክኖሎጅ የታገዙ በርካታ ዘርፎች በአንድ ማዕከል እንዲታቀፉ መደረጉ ለሀገር ሁለተናዊ እና ፈጣን እድገት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑ፤ ይህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስራን ማዘመን በሁሉም ተቋም እንደ ትልቅ ተሞክሮ ሊወሰድ እንደሚገባ በጉብኝቱ የተሳተፉት አመራሮች እና ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡

06/05/2026

አገልግሎቱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን፣ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን በሽያጭ ሊያስወግድ ነው
*************************
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ10 መ/ቤቶችን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች፣ የ18 መ/ቤቶችን ያገለለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የ5 መ/ቤቶችን ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች:-
• ሚያዝያ 20፣ 23 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ፣
• በአገልግሎቱ የቴሌግራም ገፅ (Federal Public Procurement Service –FPPS)
• በአገልግሎቱ የፌስቡክ ገጽ (Federal Public Procurement Service –FPPS)
• በአገልግሎቱ ድረ -ገጽ (www.pps.gov.et) በተጫነው የጨረታ ማስታወቂያ
የተቀመጡ ዝርዝር መስፈርቶችን በመመለከት በጨረታው ላይ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
የፌዴራል መንግሥት ግዥ አገልግሎት
አዲስ አበባ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
Addis Ababa