አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a

አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a

Share

ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ!!

03/11/2022

ጥቅምት 24
መቼም አንረሳውም

02/08/2022

የትምህርት ፍኖተ ካርታ የሚጀምሩ የመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የክ/ጊዜ ብዛት
👦👩 ቅድመ መደበኛ
👩👦 ከ1-6ኛ ክፍል
🧑👨🤵 ከ7- 8ኛ ክፍል
====================
😁አንድ ክ/ጊዜ 40 ደቂቃ አለው፡፡
😁በቀን 6 ክ/ጊዜ
😁በሳምንት 30 ክ/ጊዜ
😁የት/ት ሰዓት ከጥዋቱ 2:15-6:30 የጥዋት ሸፍት ከ6:45-11:00 የከሠዓት ሸፍት ሆኖ 15 ደቂቃ ዕረፍት አለው፡፡
😁የት/ት ሠዓት በየሸፍቱ 4ሰዓት ነው፡፡
በየት/ት አይነቱ የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
😁1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ እና የዓመቱ ሰዓት 104 ሰዓት ነው፡፡
😁2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ ክ/ጊዜ 3፣ በሳምንት 2ሠዓት እና በአመት78 ሠዓት አለው፡፡
😁3ኛ= እንግሊዘኛ የሳምንት ክ/ጊዜ 4 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ40ደቂቃ እና የአመቱ 104 ሰዓት አለው፡፡
😁4ኛ= ሂሳብ በሳምንት5 ክ/ጊዜ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት130ሰዓት አለው፡፡
😁5ኛ= አካባቢ ሳይንስ በሳምንት 5 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 3ሰዓት ከ20ደቂቃ እና በዓመት 130 ሰዓት አለው፡፡
😁6ኛ= የግብረገብ ት/ት በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁7ኛ= የሙያ ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
😁8ኛ= የሰውነት ማጎልመሻ ት/ት በሳምንት 3ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት እና በዓመት 78ሰዓት አለው፡፡
በአጠቃላይ በሳምንት 30 ክ/ጊዜ ወይም 20 ሰዓት እና በዓመት 780 ሰዓት አለው:: ስለሆነም የት/ት አመታዊ እቅድ በዚህ ስሌት መሠረት ይዘጋጀል፡፡
መልካም የት/ት ዘመን!!!

በት/ት ፍኖተ ካርታ ከቅድመ መደበኛ እስከ በመጀመሪያ መካከለኛ ት/ቤቶች በየክፍል ደረጃ የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-

😁= ቅድመ መደበኛ (KG) ለሁለት አመት የሚሠጥ:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አካባቢ ሳይንስ
3ኛ= ሙያ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡

😁በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ= እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= አካባቢ ሳይንስ
6ኛ= የግብረገብ ት/ት
7ኛ= ሙያ
8ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡

😁በመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= የአገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ=እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5= ሳይንስ
6ኛ= ህብረተሰብ
7ኛ= ስነ -ዜጋ
8ኛ= ሙያ
9ኛ= አይቲ (IT)
10ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው::

31/07/2022

በ8ኛ ክፍል በተመዘገበው ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛው መርሀ ግብር ለማስተማር ከተቀበላቸው ለፈተና የተቀመጡ ብዛት 317 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 244 ተፈታኞች 50% እና በላይ በማምጣት አፈጻጸም በመቶኛ 76.97% መሆኑና በ2013ዓ.ም ተፈትነው 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች 60% የነበረ ሲሆን በ16.97% የበለጠ አፈፃፀም ተመዝግቧል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ማርየ አክለው እንደገለፁት
በ2014ዓ.ም ከተፈተኑት መደበኛ ተማሪዎች ውስጥ ማለፊያ ነጥቡን በማግኘት ወደ 9ኛ ክፍል ማለፍ የቻሉ ተፈታኞች 305 ሲሆኑ አፈፃፀም 96.21% ሆኗል፡፡
በማታው ትምህርት መርሃ ግብር ፈተና ላይ የተቀመጡ128 ተማሪዎች ውስጥ 41 ተማሪዎች ወደ ቀጣይ የክፍል ደረጃ ተዛውረዋል። የማታና የግል ተማሪዎች ላይ አሁንም ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ነው። ሆኖም በዚህ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በብቃታቸው ለማለፍና ከኩረጃ በጸዳ ሁኔታ ለመፈተን ያደረጉትን እንቅስቃሴ እያበረታታን በቀጣይ ክፍሎችም ይህንን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አበክረን እንሰራለን፡፡
ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ለነበሩ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች: ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ወላጆች፣ የወላጅ ኮሚቴዎች እና በየደረጃው ያሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት
21/11/2014ዓ/ም

29/07/2022

የ2014 የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጣት ተመዘገበ

በ2014 የት/ት ዘመን የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 98 ፐርሰንቱ የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።
************************
የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በሰጡት መግለጫ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በግል መርሃ-ግብር ለፈተና ከተቀመጡ 6494 ተማሪዎች ውስጥ 4236 ተፈታኞች 50% እና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልፀው ይህም በመቶኛ 65.87% መሆኑና በ2013ዓ.ም ተፈትነው 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች 51.1% የነበረ ሲሆን የዘንድሮው ግን የ14.77% ብልጫ ያለውና የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በ2014ዓ.ም ከተፈተኑት መደበኛ ተማሪዎች ውስጥ ማለፊያ ነጥቡን በማግኘት ወደ 9ኛ ክፍል ማለፍ የቻሉ ተፈታኞች 5261 ሲሆኑ ይህም በፐርሰንት 98% ማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋልያሉት ሃላፊዋ ከነዚህም ውስጥ 90 የሚሆኑት የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች 100% ያለፉ ናቸው ብለዋል።

ተማሪዎች በብቃታቸው ለማለፍና ከኩረጃ በጸዳ ሁኔታ ለመፈተን ያደረጉትን እንቅስቃሴ እያበረታታን በቀጣይ ክፍሎችም ይህንን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ የጽ/ቤቱ ኃላዋ ገልጸዋል፡፡

ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ለነበሩ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ወላጆች፣ የወላጅ ኮሚቴዎች እና በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራሮች ምስጋናቸውን በማቅረብ በ8ኛ ክፍል የተመዘገበውን ውጤት በ12ኛ ክፍል ላይ ለመድገም ተማሪዎች በክረምት እየተሰጠ ያለውን ማጠናከሪያ ትምህርት አጠናክረው እንዲከታተሉ፤ ተማሪዎችን ጨምሮ የሚመለከታቸው የትምህርት ማህበረሰብ በሙሉ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሐምሌ 21-2014ዓም

26/07/2022

ቀን 18/11/2014 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ደግሞ 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛው ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡

ላለፉት 10 ቀናት በአሜሪካ ኦሪገን ሲካሄድ የሰነበተውን 18ኛውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡

በወንዶች እና ሴቶች ማራቶን እንዲሁም በ10ሺ እኛ 5 ሺ ሜትር ሴቶች 4 ወርቅ በማምጣት በሻምፒዮናው ከፍተኛ የሚባል ውጤት ተመዝግቧል፡፡

በ3ሺ ሜትር መሰናክል በሴት እና ወንድ እንዲሁም በወንዶች ማራቶን እና በ1500 ሜትር ሴቶች የብር ሜዳሊያ ተገኝቷል፡፡

ሁለቱ የነሐስ ሜዳያ የመጣው ደግሞ በሴቶች 3ሺ መሰናክል እና በ5ሺ ሜትር ነው፡፡

ኢትዮጵያ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ ፣ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛው ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡

ጎረቤት ኬንያ ደግሞ በ2 ወርቅ ፣5 የብር እና 3 የነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ በማግኘት በኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ ተበልጣ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a's post 05/07/2022

በክልል አቀፍ ደረጃ ከቀን 27- 29/10/2014ዓ/ም ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የዳግማዊ ብርሃን የፈተና ጣብያ 413 የመደበኛና የማታ ተማሪዎችን ያስፈተነ ሲሆን የፈተና ስርዓቱ ከኩረጃ የፀዳ ከት/ቤት ውስጥና ከትምህርት ቤት ውጪ ተማሪዎች በተለያዩ የፀጥታ ችግር እንዳይጠለፉ ከወረዳው ፖሊስ ጋር በመተባበር ግንዛቤ በመፍጠር; ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግና ተማሪዎች በቁርስና ምሳ ሰዓት ከት/ቤት ውጪ በመውጣት ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ መንግስት ለተማሪዎች ባመቻቸው ምገባ ሁሉም ተፈታኞች ቁርስና ምሳ እንዲመገቡ መደረጉ።
ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የሚገጥማቸው የጤና ችግር ካለ የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያ መመደቡ።
የትራንስፖርት እና የተለያዩ ግብዓቶችን የማቅረብ ስራ መሠራቱ:
በአጠቃላይ የፈተና ስርዓቱ ያለምንም ችግር በሰላም ተጀምሮ በሠላም መጠናቀቁ የሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ማለትም የት/ቤት አመራሮች: የፖሊስ አካላት: ፈታኞችና አስተባባሪዎች: ተማሪዎች እና የወረዳ አስተዳደሩ ሚና የጎላ እና በተቀናጀ መልኩ በመሰራቱ ነው።

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a's post 05/06/2022

ይቻላል!!
ማድረግ መቻል: መስራት መቻል: መፍጠር መቻል የልምምድና የትምህርት ውጤት ነው።

👉 የካቲት 23 ልዮ ፍላጎት የመ/ደ/ት/ቤት በዕለተ አርብ በቀን 26/09/2014ዓ/ም
# የሳይንስና ፈጠራ ስራ ኤግዚብሽን በማቅረብ በት/ቤት ደረጃ ማክበር ተችሏል።
በዕለቱ የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችም በሳይንስና ፈጠራ የተሠሩ ስራዎች፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ ፣ ስነ-ስዕልና ቅርፃ ቅርፅ ፣ ስነ ፅሁፉና በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስራዎቻቸውንና የፈጠራ ውጤቶቻቸውን አቅርበዋለ። ፕሮግራሙም በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a's post 05/06/2022

"እሩሳሌም ህፃናት ማህበረሰብ ልማት" የተሰኘ ግብረ ሰይይ ድርጅት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በሚገኘው ዳግማዊ ብርሃን ት/ቤት በ3.5 ሚሊዮን ብር ወጭ ያስገነባውን የህፃናት ማቆያ /ዴይኬር/ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ፡፡
****************************
ከዩኒሴፍ በጋራ የተገነባ ማዕከል መሆኑን የገለፁት የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ገብሩ የት/ቤቱ ማ/ህሰብ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ልጆች የማዕከሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የዋና ስራ አስፈፃሚ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪው አቶ ፈጠነ አበበ የነገ ሃገር ተረካቢ ህፃናትን መንገባከብ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ ይህ ተግባር እንደሞዴል በመውሰድ በሁሉም ተቋማት ማስፋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው ለህፃናት ልጆች ሁሉ ነገር የሚገባቸው መሆኑን ተረድታችሁ ይህንን የመሰለ ማቆያ ማዕከል በጥራት ገንብታችሁ ላስረከባችሁ በሙሉ ክብር ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡

በጥቅምት ወር የተጀመረው ግንባታ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በጀት በላይ የፈጀ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡
ግንቦት 25-2014ዓ.ም

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a's post 24/04/2022

እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በጤና አደረሳችሁ። በአሉ ፈጣሪያችን የሚታረቀን: የሰላም: የፍቅር: የመተሳሰብ እንዲሆን እመኛለሁ።
መልካም በአል!❤❤❤👏🤲🤲

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት Addisketema woreda8 Education office a's post 29/01/2022

ቀን21/05/2014ዓ/ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት የ6 ወር የትምህርት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ አደረገ።
# # #// # # # #
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት በ2014ዓ/ም በ6 ወር ውስጥ በትምህርት ሴክተሩ የተከናወኑ ተግባራትና እስካሁን ሳይፈቱ እየተንከባለሉ ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና በት/ቤት ውስጣዊና ውጫዊ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውኩ አዋኪ ጉዳዮችን : የባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ሚና የቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ቴዎድሮስ ማርየ በሪፖርት አቅርበዋል።
የትምህርት ኮማንድፖስት አባላቱ ከማህበረሰብ አባት: ከት/ቤት: ከሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣ ሲሆን በ6 ወር ዉስጥ የተከናወኑት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች: በተግባር ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬ የሚታዩ ሆነው ከተቋሙ አቅም በላይ የሆኑ በወረዳም በክፍለ ከተማ እንዲሁም በከተማ ደረጃ መፈታት ያለባቸው የመልካም አስተዳደርና የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን በትግል መፍታት እንደሚገባ ተገልጿል። ከዚህ አንፃር ሁሉም ለትምህርት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመራሮች ተናግረዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa