28/05/2026
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን Ethiopian Maritime Authority -ema
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን Ethiopian Maritime Authority -ema, Government Organization, መስቀል አደባባይ ከማርዮት አፓርትመንትስ ጎን ሰንሻይን ህንፃ ቁጥር 4 ከ7/11 ወለል Meskel Square Next to Marriot Apartment Hotel, Sunshine building no 4, 7th/11th floor, Addis Ababa, Addis Ababa.
28/05/2026
26/05/2026
ለመላው #የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1447ኛው በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
25/05/2026
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል።
ግንቦት 17/2018 (ኢማባ ) ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የእቃ አስተላላፊነት ዘርፍን ለውጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት ለማድረግ ውሳኔ አሳልፏል።
ቀደም ሲል በደንብ ቁጥር 474/2012 የውጭ ባለሀብቶች የዕቃ አስተላላፊነት የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለለ ሲሆን የውጭ ባለሃብቶች የካፒታል የሽርክና ተሳትፎም በ49% ተገድቦ ቆይቷል። ከዚህም የተነሳ በዘርፉ የሚፈለገውን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ክፍተት ፈጥሮ የቆየ ሲሆን የቦርዱ ውሳኔም ይህን እና መሰል ችግሮችን የሚቀርፍ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በዘርፉ የተሰማሩ ነባር ባለሃብቶችንም ሆነ አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚገቡት ባለሃብቶች በሎጂስትክስ ዘርፉ ላይ ተጨማሪ እምነት እንዲያሳድሩም የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በውሳኔው መሰረት ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት፣ አገራዊ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት እንዲሁም የአገር ውስጥ ተዋናዮች አቅማቸውን አሳድገው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየሰራ ሲሆን ይህ ውሳኔም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑ ተጠቁሟል ሲል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
21/05/2026
በባቡር አገልግሎት ሎጂስቲክስን ለማቀላጠፍ የተፈጠረ ተጨማሪ አቅም
ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ብረታ ብረቶች፣ ጣውላ እና መሠል ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚያስችል ሴንትራል ቢም ዋገን (Central Beam Wagons) - የባቡር ፉርጎ ወደ ስራ ገባ
ለበርካታ ዓመታት ያለሥራ ቆመው የነበሩት የባቡር ፉርጎዎቹ አስፈላጊ የቴክኒክ ፍተሻ ተደርጎላቸው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።
ይህም ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር በሎጂስቲክስ ዘርፉ እያበረከተ የሚገኘውን ሀገራዊ የባቡር ጭነት አገልግሎት ላይ ተደማሪ አቅም እንዲኖረው አድርጓል።
እያንዳንዳቸው ሰባ (70) ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሃያ (20) ሴንትራል ቢም ዋገኖቹ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ያለስራ ቆመው የነበሩ ናቸው፡፡
አሁን ወደ አገልግሎት በመግባታቸው ብረቶችን ጨምሮ ረዣዥም ጣውላዎችና መሠል ቁሳቁሶችን በፍጥነት፣ በተወዳዳሪ ዋጋና በከፍተኛ መጠን በማጓጓዝ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አይነተኛ ሚና መጫወት ጀምረዋል።
በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ከፍተኛ የወጪና ገቢ ዕቃዎቸ ጭነት በባቡር የማጓጓዝ አማራጭን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ ጎንዶላ ዋገኖችን (Gondola Wagons (CW 3 እና CW 4)) ወደ ሥራ መግባታቸው ይታወሳል።
ጎንዶላ ዋገኖቹ የመንግሥት ሸቀጦች የጉምሩክ ቁጥጥርን በመዳረሻ ጣቢያ እንዲያገኙ በማድረግ የተሳለጠ የባቡር ምልልስ እንዲኖር ማድረግ መቻሉን ኢዲአር በገጽ አጋርቷል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇
በድረ ገጽ፡
www.motl.gov.et
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL
በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia
በዩቲዩብ
https://youtube.com/
በትዊተር
https://x.com/MoTLogestics
በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-93fuvA1twuuy
14/05/2026
በሎጂስቲክ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አካላት አሰራራቸውን በማዘመን የላቀ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ገለፁ፤
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ይህን የገለፁት ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ጋር የሚሰሩ፤
በጅቡቲ እና ኢትዮጵያ የሚገኙ የጉምሩክ አስተላላፊዎች፣ የመርከብ ወኪል ድርጅቶችና ትራንዚተሮች ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዘርፉ ተዋናዮች ያከናወኗቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል።
በገቢና ወጪ ጭነቶች የሚጠየቁ ሰነዶችን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አለመከወን፣ ወጥነት ያለው የሥራ ሰዓት አለመኖር፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚደረግ ጥረት ውስን መሆኑ ተብራርቷል።
የጭነት ሠነዶች በተገቢው መንገድ ተሟልተው ባለመቅረባቸው እና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ጭነቶች ባለመነሳታቸው የባቡር ጭነት ጉዞ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈ እንደሚገኝ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ ገልፀዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ የተቀናጀ አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ በመግለፅ ኢዲአር ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ በበኩላቸው በማሪታይም ዘርፉ መንግስት ያስቀመጣቸው ስታንዳርዶች መኖራቸውን ጠቁመው የመርከብ ወኪሎችና የጭነት አስተላላፊዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።
አቶ ፍራኦል ዘርፉ የሚገጥሙትን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በመገንዘብ ተጨማሪ የስታንዳርድ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎቹ መድረኩ መዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በተነሱ ክፍተቶችና ውስንነቶች ላይ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ከመድረኩ ጠቃሚ ግብአቶች መገኘታቸውን በመግለፅ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የግምሩክ አስተላለፊዎች፣ ትራንዚተሮችና የመርከብ ወኪል ድርጅቶች በሎጂስቲክ ዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን በመገንዘብ በላቀ ትጋት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አስተማማኝ የሥራ ትስስር መፍጠር፣ ጠንካራ የእርስበርስ መተማመንን ማጎልበት፣ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመንና መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያመቻቸውን ዕድል አልቆ መጠቀም እንደሚገባ በመግለፅ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
14/05/2026
በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የመሶብ (MESOB) የአገልግሎት ማዕከል ስለሚሰጡ አገልግሎቶች
የመሶብ (MESOB) የአንድ ማዕከል የአገልግሎት ስርዓት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ዘመናዊ እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ የተዘረጋ የአገልግሎት ማዕከል ነው።
ማዕከሉ ተገልጋዮች በተለያዩ ቢሮዎች መዘዋወር ሳያስፈልጋቸው በአንድ ቦታ ፈጣንና የተቀናጀ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል የጊዜና የወጪ ቁጠባ እንዲኖር አድርጓል።
የመሶብ (MESOB) የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
1. የንግድ የመንገድ የህዝብ ትራንስፖርት ኦፕሬተርነት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት
ይህ አገልግሎት በህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ ለመስራት ለሚፈልጉ ኦፕሬተሮች የሚሰጥ ሲሆን፣ ድርጅቱ ወይም ግለሰቡ በህግ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልቶ መገኘቱን ያረጋግጣል።
2. የንግድ የመንገድ የህዝብ ትራንስፖርት ኦፕሬተርነት ፈቃድ እድሳት
የተሰጠ ፈቃድ የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ ተገልጋዮች ፈቃዳቸውን በወቅቱ እንዲያድሱ የሚያስችል አገልግሎት ነው።
3. የንግድ የመንገድ ጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀትና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት
በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ኦፕሬተሮች በህጋዊ እና በቴክኒክ መስፈርቶች መሰረት ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፈቃድ ነው።
4. የንግድ የመንገድ ጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር ፈቃድ እድሳት
ነባር የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች የፈቃዳቸውን ትክክለኛነት በመጠበቅ በህጋዊ ሁኔታ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
5. የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት መግቢያ ፈቃድ መስጠት
በዓለም አቀፍ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ስራ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች የሚሰጥ ፈቃድ ነው።
6. የድንበር ተሻጋሪ መግቢያ ፈቃድ እድሳት
የተሰጠው የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ በጊዜው እንዲታደስ የሚያስችል አገልግሎት ነው።
የመሶብ (MESOB) አገልግሎት ጠቀሜታዎች
1. ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት
ቀደም ሲል ቀናት ወይም ሳምንታት ይወስዱ የነበሩ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል በፍጥነት እንዲጠናቀቁ በማድረግ የጊዜ ፣ወጪ እና ጉልበት መቆጠብ አስችሏል፡፡
2. ግልጽነትና ተጠያቂነት
ተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት የሚያስፈልጉ ሰነዶች፣ የአገልግሎት ሂደቶች እና ክፍያዎችን አስቀድመው እንዲያውቁ በመደረጉ ግልጽ የአሰራር ስርዓት ተፈጥሯል።
3. የዲጂታል አሰራር መዘርጋት
የወረቀት ስራዎችን በመቀነስ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋቱ የመረጃ አያያዝ ቀላልና ዘመናዊ ሆኗል።
4. የደንበኞች እርካታ ማሳደግ
የደንበኞች አቀባበል ስርዓት እና የእንግዳ ማረፊያ ቦታዎች እንዲሻሻሉ በመደረጉ ተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።
5. የኦንላይን አገልግሎት ተደራሽነት
በቴክኖሎጂ የታገዘ ስርዓት በመሆኑ ተገልጋዮች በአካል ሳይገኙ መረጃ ማግኘት፣ ቀጠሮ መያዝ እና አንዳንድ አገልግሎቶችን በኦንላይን ማከናወን ይችላሉ።
የመሶብ (MESOB) አላማ
የሞስብ አገልግሎት ዋና አላማ በትራንስፖርት ዘርፍ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተጠያቂ የአገልግሎት ባህል በመፍጠር ለተገልጋዮች ቀላልና ፈጣን አገልግሎት ማቅረብ ነው።
14/05/2026
የዳታ ኢንኮደር ስልጠና የሰለጠኑ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሰራተኞች በሥራችን ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ አበርክቶ አለው አሉ
ግንቦት 6/2018 ዓ.ም (ትሎሚ)፡- በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በ“EthioCoders” እና በ“5 Million Coders” ተነሳሽነት ማዕቀፍ የዳታ ኢንኮደር (Data Encoder) ስልጠና የወሰዱ ሰራተኞች፣ ስልጠናው በየዕለቱ የሥራ ክንውናቸውን የሚያዘምንና ውጤታማ የሚያደርግ ጠቃሚ ክህሎት እንዳስገኘላቸው ገልጸዋል።
ሰራተኞቹ እንደገለጹት፣ የዳታ ኢንኮደር ስልጠናው በዋናነት ከ“Digital Ethiopia 2025” የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር በቅርብ የተሳሰረ ሲሆን፣ መረጃዎችን በትክክል የመመደብ፣ የማደራጀት፣ የማውጣትና የማጣራት (Sorting and Filtering) ክህሎት እንዲያዳብሩ አግዟቸዋል። በተጨማሪም የዳታ አያያዝና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲጠናከር ማስቻሉን ጠቁመዋል።
በተለይም በቴክኒክ ክህሎት ማዳበር እና በጽሕፈት ፍጥነትና ጥራት (Typing Speed & Accuracy) ላይ ያገኙት ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ መረጃዎችን ያለ ስህተት የመመዝገብ ብቃት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል ብለዋል። ይህም በተቋሙ ውስጥ ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ መሠረት መሆኑን አክለዋል።
ስልጠናው በዲጂታል ዓለም ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባሻገር፣ የሥራ ዲሲፕሊንን የሚያጠናክር፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ አሠራርን የሚያስፋፋና ቀልጣፋ የሥራ ባህል እንዲጎለብት ያግዛል ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም እንደ Microsoft Excel፣ Google Sheets እና የተለያዩ የዳታቤዝ (Database) ማስተዳደሪያ ሶፍትዌሮችን በጥልቀት የመጠቀም ክህሎት እንዳገኙ ጠቁመው፣ ይህም በመንግስት ተቋማት ውስጥ የዲጂታል አገልግሎት ሽግግርን ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ሰራተኞቹ በሥራ ላይ ስልጠና (On-the-job Training) በማግኘታቸው በቀጣይ በመንግስት ተቋማትም ሆነ በግል ዘርፉ ያላቸውን ተፈላጊነት እንደሚያሳድግ ገልጸው፣ ስልጠናው ለሙያ እድገታቸው ጭምር ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል።
የዳታ ኢንኮደር ስልጠናው የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ጉዞ ለማፋጠን ያለመ የሰው ኃይል ልማት ኢንቨስትመንት ሲሆን፣ ከ“EthioCoders” እና “5 Million Coders” ተነሳሽነት ጋር ተጣጥሞ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ የቴክኖሎጂና ዲጂታል ፈጠራ ማዕከል ለማድረግ የታለመ ትልቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ መሆኑ ተጠቁሟል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት👇👇👇
በድረ ገጽ፡
www.motl.gov.et
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL
በቴሌግራም:
https://t.me/ministryoftransportethiopia
በዩቲዩብ
https://youtube.com/
በትዊተር
https://x.com/MoTLogestics
በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-93fuvA1twuuy
06/05/2026
ያለጠንካራ የእርስ በርስ ትስስር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ማስፋፋት አይቻልም(አቶ ፍራኦል ጣፋ)
=========================
ሚያዚ27/2018 ዓ.ም(ኢሚ) በጠንካራ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የእርስ በርስ ትስስር የውስጥ አቅምን መገንባት በሚል ርዕስ ፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
የፓናል ውይይት መርሀግብሩን በንግግር የከለፈቱት የኢትዮጵያ ማሪ ታይም ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ ያለ ጠንካራ የእርስ በእርስ ትስስር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ማስፋፋት እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡
አቶ ፍራኦል ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማስፋፋት በአነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና በከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን የእርስበርስ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ዕሴት በመጨመር የኤክስፖርት መዳረሻዎችን የማስፋት ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ዋና ዓላማ ብዙ ምርት ማምረት መቻል ብቻ ሳይሆን በጥራት ከተመረቱ ምርቶች ላይ ዕሴት ጨምሮ የኤክስፖርት መዳረሻዎችን ማስፋት ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ምቹ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ መዘጋጀቱንና መንግስትም የግሉን ዘርፍ ለማበረታታት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የዓለም ሀገራት ከተኪ ምርትና ከኤክስፖርት አንጻር ያላቸው ተሞክሮ፣በኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ ያሉ አስቻይ ነባራዊ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች፣ ያደጉ ሀገሮች የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ይጠቀሟቸው የነበሩ ስትራቴጅዎች በተመለከተ በከፍተኛ ምሁራን ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም በውስጥ አቅም ለመተካት የተለዩ 96 ምርቶችን ከመተካት በተጨማሪ ለኤክስፖርት መር ኢንዱስትራላይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ እና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች ከማሳ ወደ ፋብሪካ በሚጓጓዙበት ወቅት የምርት ጥራት ችግር እንዳያመጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት በአጽንኦት ተጠቁሟል፡፡
ፓናሊስቶች ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ(ከተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ድርጅት ማዕከል)፣ፕሮፌሰር ታደለ ፈረደ(የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ምሁር)፣ዶ/ር ተስፋቸው ታፈረ(የቶኒ ብሊየር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አማካሪ) እና ዶ/ር መላኩ ደስታ(ከአፍሪካ የኢኮኖሚ ፎረም) ነበሩ፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እስከ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
29/04/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
መስቀል አደባባይ ከማርዮት አፓርትመንትስ ጎን ሰንሻይን ህንፃ ቁጥር 4 ከ7/11 ወለል Meskel Square Next To Marriot Apartment Hotel, Sunshine Building No 4, 7th/11th Floor, Addis Ababa
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 17:00 |
| Sunday | 08:00 - 17:00 |
