03/06/2026
የጅማ-ጭዳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኢመአ)፦በኦሮሚያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያሳድገው የጅማ - ጭዳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል ።
80 ኪሎሜትር በሚረዝመው የመንገዱ ግንባታ አፈፃፀም የአፈር ጠረጋ ፣ የውሃ ማስወገጃ ፉካዎችና የስትራክቸር ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን የፕሮጀክቱ 27.12 ኪሎ ሜትር የሚሆነው መንገድም በአስፋልት ንጣፍ ተሸፍኗል። ይህም አጠቃላይ አፈፃፀሙን 49.31 በመቶ አድርሶታል።
ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት የመንገዱ ግንባታ በቻይናው ቲሲጁ ሲቪል ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አማካኝነት በመከናወን ላይ ነው።
የፕሮጀክቱን የማማከርና የቁጥጥሩን ሥራ ደግሞ ኪዮንግዶንግ ኢንጅነሪንግ ፣ ኦረንትያል ኮንሰልቲንግ ግሎባል እንዲሁም ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ በጋራ በመሆን እያከናወኑ ይገኛሉ።
የግንባታው ሙሉ ወጪ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት (JICA) በተገኘ ድጋፍ የተሸፈነ ነው።
የወሰን ማስከበር ችግሮች፣ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እጥረት ፣ የሥራ ተቋራጩ የአፈፃፀም ውስንነት እና የነዳጅ እጥረት በግንባታው ሂደት ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሮችን ለመቅረፍ እና ግንባታውን ለማፋጠን በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የጅማ ጭዳ መንገድ ሲጠናቀቅ እንደ ቡና ፣ ሰሊጥና የተለያዩ ፍራፍሬዎች እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ ማዕከላት ለማድረስ የሚያስችል ነው።
እንዲሁም ወደ ኮይሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚደረገውን የተሽከርካሪ ጉዞ ለማቀላጠፍና በአካባቢው የሚመረተውን የድንጋይ ከሰል በቀላሉ ለማጓጓዝ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በተጨማሪም ለጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክና ለሃላላ ኬላ የቱሪስት መስህቦች አማራጭ መሄጃ በመሆኑ የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
26/05/2026
የአምቦ ወሊሶ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት ሥራው ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኢመአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው እና 63 ኪሎሜትር የሚረዝመው የአምቦ ወሊሶ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት ሥራው ተጠናቋል ፡፡
በመንገዱ የግንባታ ሂደት የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የሰብ ቤዝ እና የቤዝ ኮርስ፣የ 5 ድልድይ ግንባታ እንዲሁም 63 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ለማከናወን ተችሏል።
የመንገዱን ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች የስላብ ከልቨርትና የድሬኔጅ ስራዎች ፣ የመንገድ ምልክቶች እንዲሁም በአምቦ እና ወሊሶ ከተሞች የእግረኛ መሄጃ መንገዶች ስራን በዚሁ በጀት አመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ።
የመንገዱን ግንባታ ያከናወነው መንግስታዊ የልማት ድርጅት የሆነው መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥሩን ሥራ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን የትራንፖርት ዘርፍ ሰርቶታል ፡፡
የግንባታ ወጪው 3,857,936,611 (ሶስት ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ አስራ አንድ) ብር የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነዉ፡፡
ቀደም ሲል የነበረዉ መንገድ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ እና ጠባብ የነበረ በመሆኑ አሁን ላይ በገጠር እና በቀበሌ 7 ሜትር ፣ በዞን እና በወረዳ 14 ሜትር ፣ በከተማ ደግሞ 21 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረዉ ተደርጎ ተገንብቷል፡፡
ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘዉ አምቦ ከተማ ተነስቶ ወሊሶ ከተማ ላይ የሚያበቃ ነው፡፡
የመንገዱ መጠናቀቅ የምዕራብ ሸዋ(አምቦ) እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ(ወሊሶ) ከተሞችን እንዲሁም የጭቱ ወረዳን፣የዳርያን እና አልቱፋ ቀበሌዎችን በቅርበት በማስተሳሰር ቀድሞ ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜን ያሳጥራል፡፡
የአምቦ ወሊሶ መንገድ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍ ባሻገር በአካባቢዉ የሚመረቱ እንደ ጤፍ ፣ እንሰት ፣ ገብስ እና በቆሎ ምርቶችን በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲወጣ በማድረግ አምራችና ሸማቹን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም የቱሪዝም መዳረሻ የሆነው ‘’የወንጪ ሃይቅ’’ መንገዱ በሚያልፍበት በኩል የሚገኝ በመሆኑ ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
22/05/2026
የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ የአስፋልት መንገድ በይፋ ተመረቀ
ጅግጅጋ ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኢመአ)፦ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚታየውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በዘላቂነት ለመቅረፍ ታቅዶ ሲገነባ የቆየው የጅግጅጋ ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ፣ የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር የትምጌታ አሥራት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሃመድ አብዱራህማን (ኢንጅነር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በበኩላቸው፣ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ማህበራዊ ግንኙነታችንን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ብለዋል አያይዘውም የመሰረተ ልማቱ መጠናቀቅ በቀጣይ ለምናከናውናቸው ታላላቅ ስራዎች ከፍተኛ መነሳሳትን የሚፈጥር ስኬት እንደሆነም ገልጸዋል።
በግንባታው ሂደት ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ያሉ ሲሆን በክልላችን የሚከናወኑ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችም በተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃና የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአጽኖት ገልጸዋል።"
ዛሬ የምናከብረው የአንድ መንገድ መጠናቀቅን ብቻ አይደለም፤ ዛሬ የምናከብረው የሕዝባችንን የልማት ጥማት የመለሰ፣ የከተማችንን የኢኮኖሚ አቅም ያሳደገ እና የሁለንተናዊ ዕድገታችንን ማሳያ የሆነ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ያሉት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ አያይዘውም ጅግጅጋ የብዙ ባሕሎች፣ የፍቅርና የኢኮኖሚ መገናኛ መሆኗ ይታወቃል። ይህ መንገድ ደግሞ ይሄንን መገናኛ ይበልጥ ያሳለጠና ያቀላጠፈ ያደርገዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሃመድ አብዱራህማን በበኩላቸው፣ የፕሮጀክቱን ጥራትና ደረጃ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ከመንግሥት በተጣለበት አገራዊ አደራ መሰረት የሀገራችንን የመንገድ መሠረተ-ልማት ግንባታ ለማፋጠን እና የሕዝባችንን ተደራሽነት ለማሻሻል የሚያደርገውን ጉዞ ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ይህንን ዘመናዊ መንገድ ተንከባክቦ እና ጠብቆ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ኃላፊነት ደግሞ የሁላችንም ነው በተለይም ደግሞ የናንተ የነዋሪው ህዝብ ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈውል።
ይህ 7.3 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሰፊ መንገድ፣ የእግረኛ መሄጃዎችን ጭምር ያካተተ በመሆኑ ለከተማዋ ልዩ ውበትን ሰጥቷታል።
በተለይም ከቶጎ ጫሌ እና ከደገሀቡር የሚመጡ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች የከተማዋን መሃል ሳያቋርጡ እንዲያልፉ የሚያስችል አማራጭ በመሆኑ፣ በከተማዋ መግቢያና መውጫ ላይ ይታይ የነበረውን አድካሚ የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል ።
ለግንባታው 672 ሚሊዮን 98 ሺህ 730 ብር ከ28 ሳንቲም ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፣ ሀገር በቀሉ ይርጋለም ኮንስትራክሽን ግንባታውን ሲያከናውን፣ ኤልዳ እና ዳምራ አማካሪ ድርጅቶች ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን በጋራ አከናውነዋል።
ፕሮጀክቱ የጅግጅጋን ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው በምረቃው ወቅት ተመላክቷል።
መንገዱ ግንባታው ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
21/05/2026
የዩኒሳ - ቢሾፍቱ የመንገድ ግንባታ ሥራን ለማፋጠን እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኢመአ) በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር ከሚከናወኑ ዋና ዋና የመግቢያና መውጫ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የ 16 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የዩኒሳ - ቢሾፍቱ መንገድ ግንባታና ማስፋፊያ ሥራን ለማፋጠን እየተሰራ ይገኛል።
ይህ ግንባታ የዩኒሳ - ገላን - ቢሾፍቱ - በዩ የመንገድ ፕሮጀክት አካል ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የዚሁ ፕሮጀክት ክፍል የሆነው የዩኒሳ - ቢሾፍቱ ሎት 3 የመንገድ ግንባታ በይፋ ተጀምሮ ሥራው እየተካሄደ ነው።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የራስ ሀይል ኮንስትራክሽን አማካኝነት እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን የመከላከያ ዲዛይን ድርጅት ደግሞ የማማከሩንና የቁጥጥሩን ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ በጀት የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በጅማሬ ላይ በመሆኑ በአብዛኛው የአፈር ቁፋሮ እና የሙሌት ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው።
የመንገዱን መጨናነቅ በዘላቂነት ለመቅረፍ ታስቦ የሚገነባው ይህ መንገድ ቀደም ሲል ከከተማ ውጭ 7 ሜትር፣ በከተማ ውስጥ ደግሞ 14 ሜትር ብቻ የነበረው ስፋቱ ወደ 30 ነጥብ 5 ሜትር ከፍ እንዲል ተደርጎ የሚገነባ በመሆኑ የትራፊክ ፍሰቱን በከፍተኛ ደረጃ ያቀላጥፋል።
ግንባታው አዲስ አበባን እንደ ዱከም፣ ገላንና ቢሾፍቱ ካሉ የኢንዱስትሪ ማዕከላት ጋር በቀጥታ በማገናኘት፣ በመሃል አገርና በክልል ከተሞች መካከል ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ያሻሽላል ።
በተለይም እስከ ጅቡቲ ወደብ በሚዘልቀው ዋና መስመር ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ የትራንስፖርት ፍሰቱን ያቀላጥፋል።
ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ የሚገነባው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግቢያና መውጫ መስመር በመሆን የሚያገለግል ይሆናል።
በተመሳሳይ መልኩ ለቢሾፍቱ የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃትና ለአካባቢው መሠረተ ልማት መዘመን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑ ለአካባቢው ህብረተሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊና ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ ያደርጋል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
19/05/2026
የጊንጪ-ሽኩቴ ሎት 1፡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በዚህ አመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት11/2018 (ኢ መ አ):- 62 ነጥብ 2 ኪሎሜትር የሚረዝመው የጊንጪ - ሽኩቴ ሎት 1 አስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በዚህ አመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ።
አሁን ላይ 88 በመቶ የሚሆነው የግንባታ ሥራው የተጠናቀቀ ሲሆን 59 ኪሎ ሜትር የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የዉሃ ማፍሰሻና የፉካ ስራዎች ፣ የሰብቤዝ ፣ የቤዝኮርስ ስራ እንዲሁም 58 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተከናውኗል፡፡
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን በማከናወን ላይ የሚገኘው ሀገር በቀሉ ገምሹ በየነ ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭ ነው።
የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ፎርትረስ ኢንጂነሪንግ ኮንሰልታንትስ ከአሶሼትስ ማህበር ጋር በጥምረት እየሰሩት ናቸው።
የግንባታው 1,150,000,000 (አንድ ቢሊየን አንድመቶ ሀምሳ ሚሊዮን )ብር ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።
መንገዱ በወረዳ 18 ፣ በቀበሌ 14.2 ፣ በገጠር ደግሞ 10 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ የሚገኝ በመሆኑ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜን የሚያሳጥር ይሆናል።
የጊንጪ - ሽኩቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙትን ደንዲ እና ጀልዱ ወረዳዎችን እንዲሁም ሶስት ቀበሌዎችን ጨምሮ የጎጆ እና የሽኩቴ ከተሞችን በቀላሉ ለማስተሳሰር ያስችላል።
በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙትን የስንዴ ፣ የጤፍ ፣ የገብስ እና የቅባት እህል ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማውጣት ያግዛል ፡፡
እንዲሁም በዚሁ በአካባቢ የሚገኘው የጭልሞ ደን ለጎብኚዎች ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ለሀገራችን የቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
የዚሁ መንገድ አካል የሆነውን 63 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሽኩቴ - ጩሉጤ ቀጣይ ክፍል ወደስራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
15/05/2026
የቦኖሻ - አጫሞ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ዋና ዋና ሥራዎች በዚህ ዓመት ይጠናቀቃሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 07/2018 (ኢ መ አ):- የሃዲያ እና ስልጤ ዞኖችን የሚያገናኘው የቦኖሻ - አጫሞ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ዋና ዋና ሥራዎች በዚህ ዓመት ይጠናቀቃሉ ።
የመንገድ ፕሮጀክቱ 22 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ የ21 ኪ. ሜ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የ19 ኪ. ሜ ሰብቤዝ፣ የ7 ኪ. ሜ ቤዝኮርስ፣ የ4 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ እንደዚሁም የውኃ መፋሰሻ ቱቦ እና የከልቨርት ሥራዎች ተሠርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የ1 ድልድይ ግንባታ ተጠናቅቋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ አፈጻጸሙ 81 ነጥብ 72 በመቶ ደርሷል። የግንባታውን ዋና ዋና ሥራዎች በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቅቀዋል።
የመንገድ ግንባታውን ሀገር-በቀሉ ይርጋለም ኮንስትራክሽን ከፌደራል መንግሥት በተመደበ 682 ሚሊዮን ብር ወጪ በማከናወን ላይ ይገኛል። ጎንዱዋና ኢንጅነሪንግ የፕሮጀክቱን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራ ያከናውናል።
የመንገድ ግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መቀመጫ የኾነችው ሆሳዕና ከተማ ተነስቶ ወደ ሃላባ እና ሐዋሳ እንዲሁም በዙሪያው የሚገኙ ከተሞች በቀላሉ ለመንቀሳቀስ ያስችላል።
በአካባቢው በስፋት የሚገኙትን የበርበሬ፣ በቆሎ እንዲሁም መሰል የግብርና ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል።
ከዚህ ቀደም ከሆሳዕና ወደ ሃላባ ለመጓዝ በውልባራግ በኩል ይደረግ የነበረውን ረጅም እና አድካሚ ጉዞ በማስቀረት በአቋራጭ ለመጓዝ ያስችላል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
15/05/2026
የባህርዳር - ጢስ እሳት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀምን ለማሻሻል እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7 2018 ዓ.ም (ኢመአ):- 21 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የባህርዳር - ጢስ እሳት የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀምን ለማሻሻል እየተሰራ ይገኛል፡፡
እስካሁን ባለው የመንገዱ ግንባታ የዲዛይንና የቅየሳ ስራዎች ተጠናቀው 16.44 ኪሎ ሜትር የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ 5.02 ኪሎ ሜትር የሰብቤዝ፣ 4.8 ኪሎ ሜትር የቤዝ ኮርስ ንጣፍ እንዲሁም 4.5 ኪሎ ሜትር የሚሆን የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተከናውኗል።
ግንባታው በሀገር በቀሉ መልኮን ኮንስትራክሽን እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ጎንድዋና ኢንጅነሪንግ ከዋይ.ኤል.ኤስ ኢንጅነሪንግ ጋር በጥምረት የማማከር ሥራውን እየሰሩት ይገኛሉ።
ለግንባታው የሚውለው 957,930,208.44 (ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺህ ሁለት መቶ ስምንት ብር በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።
በመንገዱ ክልል ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች በወቅቱ አለመነሳት፣ የካሳ ክፍያ መዘግየት ፣የአካባቢው የፀጥታ ችግሮች እና የሥራ ተቋራጩ አፈፃፀም ማነስ በሥራው ላይ ጫና ፈጥሮ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ችግሮቹን ለመፍታት ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመሆን ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የአካባቢውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ከመሆኑ ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በማገናኘት የመጓጓዣ ጊዜንና እንግልትን በመቀነስ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡
በተጨማሪም እንደ ጤፍ፣ ሸንኮራ እና ሽንኩርት ያሉ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ለገበያ ለማቅረብ ከማስቻሉም በላይ የጢስ አባይ ፏፏቴን ለጎብኚዎች ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንደሚያሳድግ ይታመናል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
06/05/2026
የድሬዳዋ- ሸነሌ የመንገድ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ
ሱማሌ፣ ሸነሌ፣ ሚያዚያ 28 2018 ዓ.ም (ኢመአ):- ድሬዳዋ ከሸነሌ ከተማ ጋር የሚያገናኘው የድሬዳዋ- ሸነሌ የመንገድ ፕሮጀክት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራ፣ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ፣ የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ደኤታ የትምጌታ አሥራት (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሃመድ አብዱራህማን (ኢንጅነር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ተገኝተዋል።
በሸነሌ ከተማ በተካሄደው የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት፤ ዛሬ የድሬዳዋ – ሸነሌ መንገድ መጠናቀቅ በክልሉ ልማት ታሪካዊ ምዕራፍ እንደተከፈተ ግልጽ ማሳያ ያሉ ሲሆን መንገዶች አንድ ላይ ሲገናኙ የኢኮኖሚን እና የማህበራዊ እንቅስቃሴን በስፋት እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።
አያይዘውም ከመንገድ ባሻገር በክልሉ ውስጥ ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው ኢትዮጵያ በተግባር የተገነባ የትስስር እና የኢኮኖሚ ኮሪደር ስርዓት በመዘርጋት ወደፊት እየተጓዘች መሆኑን ተናግረዋል።
የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ዛሬ በሱማሌ ክልል የምናየው ልማት የተለየ ነው። ይህ የድሬዳዋ – ሸነሌ መንገድ ምርቃት በቃል ሳይሆን በተግባር የተፈጠረ ለውጥ ምስክር ነው ያሉ ሲሆን ይህ መንገድ ከተሞችን ብቻ አያገናኝም፤ ህዝብን ከህዝብ ጋር ያገናኛል፣ ንግድን ያበረታታል፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ እድገትን ያፋጥናል። አርብቶ አደሩም ሆነ ገበሬው ምርታቸውን ወደ ገበያ ማድረስ ያስችላል፣ ለወጣቶቻችን ዕድል ይፈጥራል፣ ለሕዝባችን አገልግሎትን ያቀርባል ብለዋል።
መንገዱ የድሬዳዋ እና የሸነሌን ህዝቦች በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ግንኙነት ይበልጥ በማስተሳሰር በሁለቱ ከተማዎች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና አብሮነት ከማጠናከሩም ባለፈ አንዱ አካባቢ ከሌላው ሳይነጠል በጋራ የማደግ ፍልስፍናችንን በተግባር የሚያሳይ ስኬታማ የመንገድ ልማት ነው ያሉት የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር የትምጌታ አስራት አክለውም የሃገራችን ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ ለኢንቨስትመንት ሳቢ እና ለንግድ እንቅስቃሴ ቀልጣፋ እንዲሆኑ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን በበኩላቸው
ይህ ስኬት መንግስታችን ለመሠረተ-ልማት ግንባታ የሰጠውን ልዩ ትኩረትና የማይለወጥ ቁርጠኝነት በተግባር የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህ ከፍተኛ የመንግስት መዋዕለ-ነዋይ ወጪ የሆነበት መንገድ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይችል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያደርግለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ የድሬዳዋ–ሽነሌ እና የድሬዳዋ ባይፓስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በፌደራል መንግሥት ወጪ ተደርጎበታል።
የድሬዳዋ አስተዳደርን ከሽነሌ ከተማ ጋር የሚያገናኘው ይኸው መንገድ 10.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው መንገዱ 7.5 ኪ.ሜ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ውስጥ ሲገኝ፣ ቀሪው ክፍል በድሬዳዋ አስተዳደር ስር ይገኛል
ዓለም - አቀፉ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የመንገዱን ግንባታ ያካሄደው ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራው በቤዛ ኢንጂነሪንግ ኬንያ ሊሚትድ ተከናውኗል።
መንገዱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያለው ሲሆን ከድሬዳዋ ተነስቶ ሽንሌን በማቋረጥ ሰፊውን የሶማሌ ክልል ከሀገራዊ የንግድ መረብ ጋር የሚያስተሳሰር ወሳኝ የልማት ድልድይ ነው።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/
29/04/2026
የጣፎ አደባባይ - ለገዳዲ - ኩራ ጅዳ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21/ 2018 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማን ከክልል ከተሞች ጋር ከሚያገናኙ አምስት ዋና ዋና መግቢያና መውጫዎች መካከል አንዱ የሆነው የጣፎ አደባባይ - ለገዳዲ - ኩራ ጅዳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል።
15 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ይህ የመንገድ ሥራ በኢመአ የራስ ኃይል (ዓለም ገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት) ፣በአሰር ኮንስትራክሽን እንዲሁም በዋይብ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጥምረት ነው እየተከናወነ የሚገኘው።
የማማከርና የቁጥጥሩን ሥራ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የትራንስፖርት ሴክተር እየሰራው ሲሆን ለመንገዱ ግንባታ የሚውለውን 19 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በፌዴራል መንግሥት የተሸፈነ ነው።
መንገዱ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙትን ኤካ ጣፎ እና ኩራ ጅዳ ወረዳዎችን አቋርጦ ያልፋል።
ቀደም ሲል የነበረው 7 ሜትር የጎን ስፋት የነበረው መንገድ አሁን ላይ በግራና በቀኝ 4 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ በሚችል መልኩ ወደ 28 ሜትር ስፋት እንዲያድግ ተደርጓል።
የፕሮጀክቱ ግንባታ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባለፈ 4 ሜትር የአረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም 14 ሜትር የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን ያካተተ ነው።
መስመሩ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ሲና፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ ለሚደረግ ጉዞ ዋነኛ መተላለፊያ በመሆኑ የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
ከዚህም በተጨማሪ በአካባቢው ከሚገኙ የኢንዱስትሪ ዞኖች የሚወጡ የኤክስፖርት ምርቶችን እንቅስቃሴ ከማሳለጡም በላይ የግብርና እና የወተት ውጤቶች ያለምንም መጓተት ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/