The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

Share

It is the Supreme Court of the federal state of Ethiopia. It is the highest court of all the regional and federal state courts.

29/05/2026

ስለ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ የዳኝነት ስልጣን

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚከተሉትን ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ይኖረዋል፡-

👉የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ ውሳኔ የሰጠባቸው፣

👉የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሰሚነት ስልጣኑ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው፣

👉የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ አይቶ ውሳኔ የሰጠባቸው፣

👉የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በይግባኝ ሰሚነት ስልጣኑ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሰጠባቸው፣

👉በሌሎች ህጎች የተጠቀሱ ጉዳዮችን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ (1-5)

26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 26/05/2026

‎ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

‎ግንቦት 18/2018 ዓ/ም (ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

‎የህጻናት ፍትህ አስተዳደርን ለማዘመን እንደሚያግዝ የተገለጸው ይህ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በተገኙበት ተከናውኗል።

‎ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑ እና ለህጻናት ምቹ ችሎትን ከመፍጠር አንጻር የሚሰሩ ስራዎች የዚሁ ግብ አካል መሆናቸው በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

25/05/2026

ስለ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች የወል የዳኝነት ሥልጣን

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚከተሉት ላይ የዳኝነት ሥልጣን ይኖራቸዋል፡፡
👉ሕገ መንግሥቱን፣ የፌዴራል መንግሥቱን ሕጎች ወይም ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸዉ እና ያፀደቀቻቸዉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሠረት በማድረግ በሚነሱ ጉዳዮች፣
👉በፌዴራል መንግሥቱ ሕግ ተገልጸው በተወሰኑ ባለጉዳዬች፤
👉በሕገ መንግሥቱ ወይም በፌዴራል መንግስት ሕግ በተገለጹ ቦታዎች፤
👉የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 9(2) እና 13(1) መሰረት የህገመንግስቱን ድንጋጌዎች ተግባራዊ ያደርጋሉ።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀጽ (1-2)

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 23/05/2026

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ ላይ የቫሊዴሽን ወርክ ሾፕ ተካሄደ

‎ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ፈዬራ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ህጻናት በፍትህ ስርዓት ውስጥ ሲያልፉ ተጎጂ የሚሆኑበትን አጋጣሚ በዘላቂነት ለመቅረፍ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ለሚያገለግሉ የሶሻል ወርክ ባለሞያዎች የስልጠና ማኑዋል መዘጋጀቱ አስፈላጊ መሆኑንና በከፍተኛ አመራሩ አቅጣጫ ተሰጥቶበት የተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

‎የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በማዋቀር ለህጻናት ተስማሚ የችሎት ማስቻያ ቦታ እንዲኖር፣ ችሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደራጁ፣ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት በተደራጀ የሰው ኃይል እንዲመራ ማድረግ እና መመሪያና ማንዋሎችን በማዘጋጀት በሁሉም ፍርድ ቤቶች ወጥነት ያለው የፍትህ አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ ሰፊ ስራ መሰራቱን አያይዘው ተናግረዋል።

‎የስልጠና ማንዋሉ የመጨረሻ ረቂቅ ላይ ከመጀመሪያው ረቂቅ ጀምሮ የተሰበሰቡ ግብዓቶችንና አስተያየቶችን በማካተት 11 ሞጁሎችን የያዘ ሰነድ መዘጋጀቱ ታውቋል። በቀረበው የስልጠና ማንዋል ላይ ከተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየቶች ተነስተው ውይይቶች ተካሂዷል።

‎ይህ የስልጠና ማንዋል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በተባበሩት መንግስታት የህዝብ ፈንድ (UNFPA) በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ‎ባለሙያዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ተሳትፈዋል።

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 20/05/2026

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወኑ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ጎበኙ

‎ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ መርሃ ግብሩ በሁለቱ አገራት የፍትሕ አካላት መካከል በዘርፉ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥና ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

‎ክቡር ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የዳኝነት ሥርዓቱን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ሂደት ውስጥ በርካታ ጠቃሚ ትምህርቶች መወሰዳቸውን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

‎በቆይታቸው በተለይ በምርጫ ነክ ክርክሮች አፈታት ዙሪያ ያሉ ተሞክሮዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ እና የሪፎርሙ አካል የሆኑት፤ የኢ-ኮርት (e-Court) ሲስተም፣ የበይነ-መረብ የክስ መዝገብ አስተዳደር ሥርዓት (ICMIS)፣ የኤሌክትሮኒክስ ክስ ማቅረቢያ (e-Filing)፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የቃለ-ጉባኤ ግልባጭ (AI Transcription) እና የበይነ-መረብ ችሎት (Vertual hearing) ሥርዓቶችን በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

‎ልኡካኑ በተቋሙ የተሰሩ ዋና ዋና የሪፎርም ሥራዎችን በአካል የተመለከተ ሲሆን፤ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀውን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዲስ ሁለገብ ሕንፃ ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

‎የልዑካን ቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የዳኝነት ሥርዓት ማሻሻያ እና የቴክኖሎጂ ትግበራ ሥራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው ለኬንያ የዳኝነት ሥርዓትም ትልቅ ልምድ ያገኙበት መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል።

‎***********************

‎Delegations from the Court of Kenya visit the ongoing reform initiatives at the Federal Supreme Court of Ethiopia.

‎May 20, 2026 (Federal Supreme Court)

‎A Kenyan delegation led by Supreme Court Justice and JCE Chairperson Honorable Lady Justice Susan Nyoki Ndungu concludes a three-day experience-sharing program at the Federal Supreme Court of Ethiopia.

‎Federal Supreme Court President His Excellency Tewodros Mehret welcomes the delegation, noting that the program plays a vital role in exchanging best practices and strengthening the strategic partnership between the judiciaries of the two countries.

‎During their stay, the delegation engages in extensive discussions on election-related dispute resolution practices. They also receive detailed briefings on the Federal Supreme Court's ongoing digitalization reforms, including the e-Court system, the Integrated Case Management Information System (ICMIS), electronic filing (e-Filing), AI-driven transcription, and virtual hearing systems.

‎The delegation observes key reform milestones firsthand and tours various departments, including the Federal Supreme Court’s new multipurpose building, which expects to begin full operations soon.

‎In their closing remarks, members of the delegation commend the judicial reform efforts and technological advancements underway at the Federal Supreme Court of Ethiopia, confirming that the platform provides valuable insights for Kenya's judicial system.

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 20/05/2026

የጉዳዮች ድልድል ለውጥ ማስታወቂያ

‎ቀድሞ በ2ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ሲታዩ የነበሩ የመፋለም፤ የንብረት፤ የቤት እና የሁከት ክርክር ያለባቸው ጉዳዮች ወደ 1ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት የተዛወሩ መሆናቸውን እየገለጽን በዚህ መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት መዝገቦች ከ2ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ወደ 1ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት የተዛወሩ መሆናቸውን እንገልፃለን፡፡

የፒዲኤፍ ፋይሉን ለማግኘት ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም በቴሌግራም ገጻችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የ‎ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 19/05/2026

‎በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

‎ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎ከፌዴራልና ከክልል ለተውጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት አመራሮች፣ ዳኞች እንዲሁም የሕግ ባለሙያዎች በመሰረታዊ የክስ መደራደር ( Plea bargaining) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ተሰጥቷል።

‎የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት አበባ እምቢአለ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የክስ መደራደር በኢትዮጵያ አዲስ በፀደቀው የወንጀል ህግ ስነ ስርዓትና ማስረጃ ህግ ውስጥ አዲስ እና ወሳኝ የሆነ ሃሳብ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጥንቃቄ የተላበሰ መረዳት፣ ትክክለኛ ትግበራ እና ተቋማዊ ዝግጁነት እንደሚፈልግ አስገንዝበዋል።

‎ዳኞች ህግን ብሎም የፍትህ ስርዓቱን ጠባቂ እና ተከላካይ ከመሆናቸው አንፃር፤ ራሳቸውን ከአዳዲስ ፅንሰ-ሃሳቦች እና ሂደቶች ጋር ማላመድ እንደሚጠበቅባቸውም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

‎የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፤ በስልጠናው መዝጊያ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በተለይም አዲሱ የወንጀል ህግ ስነ ስርዓትና ማስረጃ ህግ ከጸደቀ በኋላ በዳኝነትና በፍትህ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች ስልጠናውን መውሰዳቸው በህጉ ውስጥ የተካተቱ በህግ መደራደር ዙሪያ ያሉ ነጥቦች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል ሲሉ ተናግረዋል።

‎ስልጠናው በዘርፉ ከሚታወቅ ተቋም ሰፊ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች መሰጠቱ ለዳኞች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር በማንሳት፤ ከመሰል ተቋማት ጋር በአጋርነት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ክቡር ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልጸዋል።

‎ስልጠናውን በአግባቡ ለተከታተሉ ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

‎**********************

‎Training Conduct on Basics of Plea Bargaining

‎May 19, 2026 (Federal Supreme Court)

‎Trainers from Pepperdine University conduct a sensitization workshop on basic plea bargaining for judicial and justice leaders, judges, and legal professionals drawn from federal and regional institutions.

‎Her Excellency Abeba Embiale, vice president of the Federal Supreme Court, underscored that plea bargaining is a novel and critical concept within Ethiopia's ratified criminal law framework.

‎She added that the successful rollout of the system demands a precise and careful understanding, accurate implementation, and thorough institutional readiness across the legal sector.

‎She further noted as guardians and defenders of the law and the justice system, judges are expected to continually adapt to emerging concepts and procedural developments.

‎The President of the Federal Supreme Court, His Excellency Tewodros Mehret, in his closing remarks stated that the training provides a vital opportunity for judicial and justice sector professionals to understand the mechanisms of plea bargaining, particularly following the ratification of the new Criminal Code.

‎The president highlighted the critical importance of strategic partnerships with industry-leading organizations, noting that undergoing training conducted by highly experienced experts will significantly support the capacity of judges.

‎Certificates of recognition were presented to the professionals who successfully completed the training program.

Photos from The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት's post 18/05/2026

‎የኬንያ ፍርድ ቤት ልኡክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ እያደረገ ነው

‎ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት ክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የልምድ ልውውጥ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።

‎ክቡር ፕሬዚዳንቱ፤ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ ስላሉ ዋና ዋና የሪፎርም ሥራዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በምርጫ ነክ ክርክሮች አፈታት ዙሪያ በሁለቱም ወገኖች ያሉ ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይትም ተካሂዶባቸዋል።

‎የልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው በተቋማቱ ውስጥ የተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

‎***************************

‎A Kenyan court delegation is visiting and conducting an experience exchange at the Federal Supreme Court.

‎May 18, 2026 (Federal Supreme Court)

A delegation led by Hon. Lady Justice Susan Njoki Ndungu, CBS, judge of the Supreme Court of Kenya and chair of the JCE, is warmly welcomed at the Federal Supreme Court by Honorable Tewodros Miheret, president of the Supreme Court of Ethiopia.

‎The Honorable President provided a briefing on the ongoing major reform initiatives at the Federal Supreme Court.

‎In today's session experiences on election-related dispute resolution present on both sides and discussions held. In their stay, the delegation is expected to visit the reform works accomplished in the institutions.

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Sidist Kilo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30