Bole Communication- ቦሌ

Bole Communication- ቦሌ

Share

ይህ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፣ በክፍለ ከተማው የሚከናወኑ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁነቶች መረጃ የሚሰጥበት ነው።

Photos from Bole Communication- ቦሌ's post 31/05/2026

በአዲስ አበባ የምርጫ ክልሎች የምርጫ የማስፈጸሚያ ቁሳቁስ ሥርጭት ተደራሽ በማድረግ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

በአዲስ አበባ የሚገኙ የምርጫ ክልሎች የምርጫ የማስፈጸሚያ ቁሳቁስ ሥርጭት ተደራሽ በማድረግ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

ነገ በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች በየምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ዝግጁ እየሆኑ ይገኛሉ።

በዚህም የኢዜአ ሪፖርተር በመዲናዋ በምርጫ ክልል 2 እና 14 በአካል ተዘዋውሮ እንደተመለከተው፣ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የማስፈጸሚያ ቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቋል።

በምርጫ ክልል 2 እና 14 ስር 14 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን የምርጫ ቁሳቁሶቹ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ በማድረግ ለምርጫው ሙሉ ዝግጅት መደረጉን መታዘብ ችሏል።
AMN

Photos from Bole Communication- ቦሌ's post 31/05/2026

ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያ ምርጫ ስኬት ከአፍሪካ ዲፕሎማቶች ጋር መከሩ

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ ነገ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ከ37 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 73 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን ያቀፈ ጠንካራ እና ስብጥሩ የሰፋ ቡድን እየመሩ ይገኛሉ።

ይህ የታዛቢ ቡድን ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን የምርጫ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና ታዋቂ የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎችን አካትቷል።

ልዑኩ በመንግሥት እና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተከናወኑ የመጨረሻ ዝግጅቶችን መገምገሙ ታውቋል።

ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጽ ለመስጠት በተመዘገቡበት በዚህ ጠቅላላ ምርጫ ሂደቱ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ እድገት ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

ይህ ለኢትዮጵያውያን የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጉዳይ የሆነው ምርጫ፤ ሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ሉዓላዊነቱን ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያሳይበት አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ለምርጫው የሎጂስቲክስ እና የፀጥታ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አረጋግጧል።

በኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የታዛቢ ቡድንም የግልጽነት እና የፍትሃዊነት መርሆዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ በመላ ኢትዮጵያ ተሰማርቶ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን ይከታተላል።

31/05/2026
31/05/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!

ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።

እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።

ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።

ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።

#ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

28/05/2026

ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታ
1. የምርጫ ኃላፊው የሚሰጠውን ትዕዛዞች ማክበር አለበት፣
2. የምርጫ ሂደቱን ከሚያውኩ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
3. አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መታወቂያውን ማሳየት አለበት፣
4. የምርጫ ሕጉን ማክበር አለበት፣
5. የምርጫውን ሂደት የመከታተል ተግባሩን ሲያከናውን መራጮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አስተያየት ከመስጠት ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር የለበትም፣
6. የምርጫ ቁሳቁሶችን መያዝ፥ ማንሳት፤ መነካካት ወይም በቁሳቁሶቹ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራትን መፈጸም የለበትም፣
7. የምርጫ ጣቢያውን ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ከማስፈራራት ወይም ሥራውን ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣
8. ወደ ድምፅ መስጫ ክፍሎች መግባት የለበትም፣
9. ቦርዱ የሚያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ መፈረም እና ማክበር ይገባዋል፡፡
ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 121

28/05/2026

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?
1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
👉የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
👉የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ
2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
👉የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
👉የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
👉ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"
የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 27/05/2026
27/05/2026

ከቃል በላይ...

"የቦሌ ትሩፋት በህዝብ አንደበት"

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Megenagna Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30