19/05/2026
Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia
Telegram: https://t.me/MinTEthiopia
Website: https://mint.gov.et/
Email: [email protected]
Ministry of Innovation and Technology (MInT) former Ministry of Science and Technology is a governmental institution that established for the first time in December 1975 by proclamation No.62/1975 as a commission. Following the change in government in 1991 and with the issuance of the new economic policy, the Commission was re-established in March 1994 by Proclamation No.91/94. The commission went
19/05/2026
19/05/2026
ሚኒስቴሩ የንግድና የመንግስት አገልገሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች ናቸው። የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ
=============
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል።
በግምገማው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የንግድና የመንግስት አገልገሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የሰው ሀብት ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ገልጸዋል።
ተቋሙ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ካከናወናቸው ጉልህ ተግባራት መካከል በቴክኖሎጂ የታነጸ የሰው ሀብት ለማፍራት ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች መካሄዳቸው፣ በስፔስ ሳይንስና በጂኦ ስፓሻል ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬ የሚታዩ አፈጻጸሞች መሆናቸውን የተከበሩ ነገሪ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
በተመሳሳይም በቴክኖሎጂ ታግዞ የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተደረገው ጥረት እንዲሁም የፈጠራ ስራዎች የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት ሰርተፊኬት መሰጠታቸው በአዎንታዊ ከሚታዩ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የሀገሪቱን ልማቶች ለማፋጠን የሚያግዝ ሳተላይት ለማምጠቅ እና የመንግስት አገልግሎቶችን ይበልጥ ለማሳለጥ የጥሪ ማዕከል ለመገንባት በእቅድ ተይዘው በዘኝ ወራት ውስጥ ያልተፈጸሙ ተግባራት መሆናቸውን የተከበሩ ነገሪ(ዶ/ር) ጠቁመዋል።
መንግስት የጀመረውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለማሳደግ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በሚገባ እንዲሳካ እንዲሁም በስፔስ ሳይንስና በጂኦ ስፓሻል ዘርፍ ችግር ፈቺ ጥናቶች እንዲካሄዱ ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አሳስበዋል።
አክለውም የፈጠራ ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዲችሉ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አተገባበር እና ውጤታማነት አኳያ እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ተደራሽነት አንጻር ጥያቄዎችን አንስተዋል።
በተመሳሳይም በሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች የተካሄዱ ጥናትና ምርምሮች ከሸልፍ ባለፈ ለሀገሪቱ ያመጡት ተጨባጭ ውጤት ምንድን ነው የሚል ጥያቄም ተነስቷል።
የኢኖቬሽንና ተክኖሎጂ ሚኒስትሩ ክቡር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ሲሆን በተለይም የሳይበር ሴኩሪቲን በምሳሌነት አንስተዋል።
በዲጂታል 2030 በሀገሪቱ ጠረፋማ አካባቢዎች የሀይል እና የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ተቋሙ ራዕይ አንግቦ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።
የጥናት እና ምርምር ዘርፎች ለሀገሪቱ ዘርፈ- ብዙ ጥቅሞች እንዲያስገኙ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የእስታርት አፕ አዋጁ ከወጣ በኋላ ለመተግበርና የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆን፤ እንዲሁም ደንብና መመሪያዎችን ለማውጣት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂን በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ስታርትአፕ ሊንኬጅን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
19/05/2026
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገለጸ
==============
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየገመገመ ይገኛል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደቻለ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ልማት የዓለም አንገብጋቢ ችሮች መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆናቸውንም አንስተዋል።
ዘርፉ የኢትዮጵያን የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲሁም የ2063 አጀንዳን ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገንዝቦ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
የተቋሙን የሰው ሀይል በእውቀትና ክህሎት ለመገንባት ታስቦ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ የተቋሙን አሰራሮች በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ ተሰርቶ አመርቂ ውጤቶች መታየታቸውንም አንስተዋል።
ክቡር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዘጠኝ ወራት ውስጥ በኢኖቬሽን ዘርፉ 1714 የጥናትና ምርምር ስራዎች ተካሂደው የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ያሉ ሲሆን በተመሳሳይም 25 የጂኦ ስፓሻል ጥናቶች ተካሂደው የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንደተቻለ ነው ያብራሩት።
ሚኒስትሩ አክለውም ባለፉት ዘጠን ወራት ውስጥ በሁሉም ስታርታአፖች 6424 የስራ እድሎች መፈጠራቸውንም ለምክር ቤቱ ገልፀዋል።
#ፓርላማ
18/05/2026
''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቼ የተመለከትኩት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው።
ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
18/05/2026
"የአሁኑ ትውልድ ብዙ እድል ያለው ነው"ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው..የሰው ልጅ የእውቀት ገደብ አግማሱን አጠቃላይ በጣም እያስፋፋ የመጣበት፤ የሰውን ልጅ ህይወት ለማቅለል ብዙ ቴክኖሎጂዎች ወደፊት እየመጡበት ያለበት ዘመን ነው።
የዚህ ዘመን ትውልድ የሚመች ፖሊሲ ስትራቴጂ መንግስታቶች እስከቀረጹ ድረስ....ወደኛ ሀገር እንምጣና ይህን ትውልድ ያለውን አቅም ወደ ኢኮኖሚ ለመለወጥ ለማስቻል ተገቢ ፖሊሲ እና እስትራቴጂዎች በየዘርፉ ተቀርጸው እነሱ ከተተገበሩ ትውልዱ በጣም ሰፊ እድል አለው ፤የማወቅ የመፈጸም የመሆን የመምረጥ እድሉን ያበዛለታል።
ስራ የመፍጠር ፤ ሀብት የመፍጠር በሀገሩ የኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋጽኦ የሚያበረክትበት ሰፊ እድል አለው።በዛው ልክ ተግዳሮቱ ደግሞ ከፍተኛ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ #ከኢቲቪ የመዝናኛ ፕሮግራም ጋር ከነበራቸው ቆይታ ላይ የተወሰደ
ቴክኖሎጂ እና የሰው ልጅ
==========
ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ነገን በተሻለ ለመተንበይ ዛሬን በተሻለ ለማወቅ ከዛሬ ለመጠቀም የሚያስችለውን እድል የፈጠረ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ #ከኢቲቪ የመዝናኛ ፕሮግራም ጋር ከነበራቸው ቆይታ ላይ የተወሰደ
06/05/2026
በሐረር ከተማ ለ12 አረጋውያንና አቅመ ደካሞች የተገነቡ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ።
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሐረር ከተማ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በምርቃት አስረክቧል።
ይህ የበጎ ፈቃድ ፕሮጀክት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ካለበት ሀገራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የአቅመ ደካማ ዜጎችን የኑሮ ሸክም ለማቅለል ካለው ቁርጠኝነት የመነጨ ነው።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ተገኝተው የዜጎችን ሕይወት የሚቀይር ሥራ በማጠናቀቃቸው የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አክለውም አረጋውያንን መደገፍና መጠለያ ማበጀት ቀዳሚው የሞራልና የሰብዓዊነት ተግባር መሆኑን በአፅንዖት አመልክተዋል።
የተገነቡት 12 አዳዲስ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ለእያንዳንዱ አባወራ እና እማወራ አስፈላጊ የሆኑ የቤት ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው በመሆናቸው፣ ተጠቃሚዎች በክብር እንዲኖሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ከመኖሪያ ቤቶቹ በተጨማሪ ተጠቃሚዎቹ ኑሯቸውን በዘላቂነት መደጎም እንዲችሉ የፈሳሽ ዘይት ማምረቻ፣ የዶሮ እርባታ፣ የዳቦ መጋገሪያና የመሸጫ ሱቆች ተገንብተው ሥራ እንዲጀምሩ መደረጉን ክቡር ሚኒስትሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። ይህም ፕሮጀክቱ ከመጠለያ ባሻገር ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።
በተያያዘም ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሂንስኔ ኮንስትራክሽን፣ ስፔስ ላብ አማካሪ ድርጅት፣ ለሐረሪ ክልል መንግሥትና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና ቀርቧል።
በመጨረሻም መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራት የአንድነታችን መገለጫ በመሆናቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ምርቃቱም በደስታ ተጠናቋል።
04/05/2026
የኢኖቬሽንና ኢንዱስትሪ ፖሊሲዎች ቅንጅት ለሀገራዊ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተወዳዳሪነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
==================
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የ"ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018" መድረክ ላይ በመንግሥትና በግል ዘርፍ መካከል የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞውን ለማፋጠን የሚያስችል ስልታዊ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
ይህ የፓናል ውይይት የገቢ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካትና የወጪ ንግድን በማጠናከር ላይ ያተኮሩ የጊዜ ገደብ የተቀመጠላቸው የፖሊሲ እርምጃዎችን በመለየት የኢትዮጵያን መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማገዝ ያለመ ነው።
በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራሩ የተናበና በዲጂታል ስርዓት ውስጥ ማለፍ እንዳለበት በአፅንዖት ገልፀዋል።
የኢኖቬሽንና የኢንዱስትሪ ስትራቴጂዎችን በማጣጣም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድግና የኢንቨስትመንት መተማመንን የሚፈጥር ወጥ የሆነ አሰራር መዘርጋት እንደሚቻልም በመድረኩ ላይ አመላክተዋል።
ዲጂታላይዜሽን የማምረቻ ሥርዓቶችን በማዘመን ወጪን ከመቀነሱም በላይ ኢንዱስትሪው ያልተጠበቁ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዎችን የመቋቋም አቅም እንዲኖረው በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና ይጫወታል።
የዲጂታል ኢኮኖሚ እንገነባለን ካልን ብቁ የሆነ የተዘጋጀ በዲጂታል ዘርፉ ላይ ተፅኖ የሚፈጥር አካል እንዲኖር በሰው ሀብት ልማት ላይ በትኩረት መሰራትና መጠቀብ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የመንግስትና የግል ዘርፍ ተዋናዮች በጋራ ግቦች ላይ እንዲሰለፉ በማድረግ ለውጤት ተኮር የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የፋይናንስ እጥረትና የተቋማት ቅንጅት ማነስ የግል ኢንቨስትመንትን መጉዳታቸውን ጠቅሰው፣ በዲጂታል ክትትልና በተቀናጀ አሰራር አማካኝነት እነዚህን የአሰራር እንቅፋቶች በማስወገድ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ቁርጠኝነት እንዳለ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የታለመ የቴክኖሎጂ ሽግግር አምራቾች ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ምርቶችን እንዲያቀርቡና የገበያ አማራጮቻቸውን በማስፋት በተወዳዳሪ ገበያዎች ውስጥ ተደራሽ እንዲሆኑ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
30/04/2026
የሪፎርም ስራዎቻችን የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጡ መሆን እንዳለባቸው ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ።
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ተግባራት የደረሱበትን የክንውን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፥ የሚከናወኑ የሪፎርም ስራዎች በሙሉ የዘርፉን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት በተጨባጭ የሚያረጋግጡ መሆን እንዳለባቸው በአፅንኦት ገልፀዋል።
በተጨማሪም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተገበረ ያለው የሪፎርም ስራ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑንና ተጨባጭ መሻሻሎች እየታዩበት እንደሚገኝ አንስተዋል።
ተቋማዊ አሰራርን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ጥረቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም በግምገማ መድረኩ ላይ በስፋት ተመልክቷል።
በሪፎርም እቅዱ የተካተቱና እስካሁን ያልተጠናቀቁ ቀሪ ተግባራት በሙሉ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በጥራት እንዲከናወኑ ግልጽ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህ ግምገማ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰነቁ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት በጋራ እንዲረባረቡ አዲስ መነሳሳትን የፈጠረ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://www. Google. Com/maps/place/Ministry+of+Science+and+Technology/@9. 0238105, 38. 7528862, 780m/data=, 3m1, 1e3, 4m5, 3m4, 1s0x0:0x2dc416a9b5ac4ac4, 8m2, 3d9. 0238105, 4d38. 7550749?hl=en-US
Addis Ababa
000000
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |
