01/01/2021
አዲስ በተቋቋመው በሲዳማ ብሄራዊ ክልል የአሃዳዊ ዋሽ ፕሮግራም /One WASH National Programm ይፋዊ የአጀማመር ስነ-ስረዓት የፌዴራል ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ዴታ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ፡፡
ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Federal Democratic Republic of Ethiopia, Water Development Commission-WDC, Government Official, Addis Ababa.
The Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia established the Water Development Commission (WDC) which is accountable to the Ministry of Water, Irrigation and Energy with Proclamation No. 1097/2011
01/01/2021
አዲስ በተቋቋመው በሲዳማ ብሄራዊ ክልል የአሃዳዊ ዋሽ ፕሮግራም /One WASH National Programm ይፋዊ የአጀማመር ስነ-ስረዓት የፌዴራል ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ዴታ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ፡፡
ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም
27/08/2020
የውሃ ልማት ኮሚሽን ሠራተኞች እና አመራሮች "ገበታ- ለሀገር" ለተሰኘው አገራዊ የድጋፍ ጥሪ ሙሉ ድጋፋቸውን ገለጹ፡፡
የውሃ ልማት ኮሚሽን ሠራተኞች እና አመራሮች በአገር አቀፍ ደረጃ ለቀረበው አገራዊ የልማት ጥሪ በዛሪው ዕለት ባካሂዱት ስብሰባ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት እና ያለውን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ብሎም የገጽታ ግንባታ ላይ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በሸገር ማስዋብ ላይ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር ለሠራተኞች በክቡር ኮሚሽነሩ ዶ/ር በሻህ ሞገሴ ተገልጿል፡፡ በቀጣይም ይህንን አገራዊ ጥሪ እንዴት መደገፍ እንደሚቻል እና የታሪክ አሻራ ማሳረፍ እንደሚቻል ከሠራተኛው ጋር በተደረገው ውይይት በርካታ ገንቤ የሆኑ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ልማቱን እንደሚደግፉ እና ይህንን እድል በማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸው የተጠየቁትን ድጋፍ ለማድረግ ሙሉ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በዚሁ መሰረት ገበታ ለሽገር ወደ ገበታ ለሀገር ተቀይሮ ሀገራዊ የልማት ጥሪ ለሁላችንም ሲቀርብ በመጭው አመት ፡-
በአማራ ክልል ጣና ሀይቅ ምዕራባዊ ዳርቻ የሚገኘው ጎርጎራ
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የሚገኘው ወንጪ
በደቡብ ክል ኮንታ የሚገኘው የኮይሻ የተፈጥሮ ገጸበረከቶችን የማልማትና የማስዋብ ስራ ለማሰራት አገራዊ የድጋፍ ጥሪ መቅረቡን በመቀበል የኮሚሽኑ ሠራተኞች እና አመራሮች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለፕሮጀክቶቹ ማስተግበሪያ በልግስና መስጠታቸውን በሙሉ ድምጽ አረጋግጠዋል፡፡
13/08/2020
የውሃ ልማት ኮሚሽን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር አመራሮች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባባር በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራወችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ላይ የኮሚሽኑ የስራ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የሸገር የወንዝ ዳር ማስዋብ አካል የሆነውን የመጀመሪያ ዙር ፕሮጀክት በተለምዶ ፖሊስ ጋራዥ እየተበለ የሚጠራውውን ቦታ በመልሶ ማልማት እየተሰራ የሚገኘውን የመዝናኛ ቦታ መጎብኘት ችለዋል። በቀጣይም የእንጦጦ የጤና ፓርክ የተጎበኘ ሲሆን በፓርኩ ውስጥ ተፈጥሮን በመከባከብ የአካባቢን አየር ሁኔታ ከማስተካከል ባለፈ የቱሪስት ፍሰቱን እና የቆይታ ጌዜውን እንዲት ማራዘም እንደሚቻል ታስቦ የተሰሩ ስራዋች በጎብኝዋች በኩል አድናቆትንና ከፍተኛ እርካታን ፈጥሯል። ከጉብኝቱ በኋላም የተቋሙ አመራሮች የዘንድሮው የአሰንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን ባማከለ መልኩ ቀጤና ፖርኩ ውስጥ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
29/06/2020
የውሃ ልማት ኮሚሽን ሠራተኞችና አመራሮች የችግኝ ተከላ አከናወኑ፡፡
ሰኔ22/2012 ዓ.ም
የውሃ ልማት ኮሚሽን ሠራተኞችና አመራሮች ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት በሱሉልታ ወረዳ ደርባ አካባቢ የችግኝ ተከላ አከናወነዋል፡፡ የዘንደሮው የችግኝ ተከላ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ5 ቤሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘው ዕቅድ አካል ሲሆን ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው አለም አቀፍ የኮሮኖ ወረርሽኝ ስጋት በሆነበት ሰዓት ራሴን ጠብቂ አገራዊ የአረንጓዴ ልማትን እውን አደርጋለሁ በሚል መርህ ሰራተኛው እና አመራሩ በተራራቀ ሁኔታ ችግኝ መትከል መቻላቸው ብቻ ሳይሆነ ለልማት ስራ ምንም አይነት ወደኃላ የሚጎትት ምክንያት እንደሌለ ማሳያ መሆኑ ነው፡፡
11/06/2020
የውሃ ልማት ኮሚሽን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የደም ልገሳ እና የችግኝ ተከላ አከናወነ፡፡
በዛሬው ዕለት ሰኔ 04/2012 ዓ.ም የውሃ ልማት ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የበላይ አመራሮች እና ሰረተኞች በተጨማሪ ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በመሆን የደም ልገሳ እና የችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡ በስነስርዓቱ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅ. ስለሺ በቀለ ‘’ በአሁኑ ሰዓት አገራችን አለም አቀፍ የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በስፋት እያጠቃት እንደሚገኝ በመግለጽ በዚህ ወቅት እራስን እና ሌሎችን ከበሽታው መጠበቅ የሚቻለው በተደጋጋሚ በሳሙናና በውሃ በመታጠብ እንዲሁም አፋና አፍንጫን በመሸፈን መሆኑን አስታውሰው እጃችንን ስንታጠብ ውሃን በቁጠባ መጠቀም ለቀጣዩ ሰው ከኮሮና ቫይረስ ጥቃት እንዲከላከል ማስቻል በመሆኑ በዚህ ረገድ ትኩረት ልንሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ በሽታ ለሚደረስው የኢኮኖሚ፣ማህበራዊ ተጽዕኖ የሚደረጉ ድጋፎች እንዳሉ ሆኖ ሰራተኛው በራስ ተነሳሽነት ደም ለመለገስ በመገኘቱ አመስግነው ይህም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው በዘንድሮ ዓመት የተራቆቱ አካባቢዎችን ብቻ ሳይሆን በደጃፋችን ችግኞችን መተከል መስረት አድርጎ የሚካነውነው የአረንጓዴ ልማት አሻራ መስቀመጥ ስራ ከሰውች ንኬኬ በጸዳ መልኩ እየተከናወነ የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ በዛሬው ዕለትም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ይህንን ስራ በተቋሙ ቅጥር ግቤ ውስጥ እንዳከናወነ ተናግረዋል፡፡‘’
10/06/2020
የውሃ ልማት ኮሚሽን ከአስራ አራት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አበረከተ፡፡
ኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን በማስፋት ከቀን ወደ ቀን የተጠቂ ሰዎች ቁጥር እና ሀገራት ከመጨመር ያገደው ነገር እስከ አሁን እምብዛም አልታየም፡፡ በአገራችንም በሽታው መግባቱ ከተገለጸበት ቀን ጀመሮ በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከመቶዎች አልፎ በሽዎች መቁጠር ከጀመርን ወል አደር ማለት ተጀምሮል ፡፡ ይህንን አይነት ድንበር የለሽ ወረርሽ ለመከላከል ብሎም የሚያደርሰውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጫና እንዲሁም የሰው ልጆችን እልቂት ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ እና የተባበር ጥረት ወሳኝ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር/ የውሃ ልማት ኮሚሽን/ እና ተጠሪ ተቋማት በተቋም ደረጃ እያንዳንዱ ሰራተኛም ሆነ ለስራ ጉዳይ ወደ መ/ቤቱ የሚገቡ እንግዶች እጃቸውን በውሃና በሳሙና እንዲታጠቡ በሁሉም የመግቢያ በሮቸ በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት በማደረግ ወደ ስራ ገብቶል ፡፡ እንደዚህ አይነቱን የበሽታ ቅድመ መከላከል ዘዴዎችን በሌሎች አካባቢዎች ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ አዲስ አበባ ላይ በሚገኙ የፓሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም በዋና ዋና ቦታዎች ላይ ሮቶዎችን በማስቀመጥ እና ውሃ እንዲሞሉ በማደረግ እንዲሁም በለይቶ ማቆያ ሳይቶች ላይ ውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎችን በማስቀመጥ እcና በርካታ መጠን ያላቸው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማሰራጨት በሽታውን ‘’ እጅን በሳሙና በመታጠብ እንከላከል ለሌሎችም እንትረፍ ‘’ በሚል መርህ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር መጠነ ሰፊ የሆነ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ኮሚሽኑ ካለው በጀት ላይ በማብቃቃት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ብዛታቸው ሰላሳ አራት /34/ የሆኑ የተለያዩ መጠን ያላቸው ፕምፓችን ግዥ በመፈጸም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት አጋርነቱን ለመግለጽ በድጋፍ መልኩ ለክልሎች ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል ፡፡ በኮሚሽኑ እና በልማት አጋሮች ትብብር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እና ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፓለቲካዊ ጫናዎችን ለመቀነስ ይረዳ ዘንድ በዋነኝነት እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ድጋፎች አድርጓል፡-
1. በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ የለይቶ ማቆያዎች/ የካ ኮተቤ፣ቦሌ ጨፋ፣ባሻውልዴ ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ከ አምስት ሚትር ኩብ አስከ ሀያ አምስት ሚትር ኩበ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 16 የውሃ ማጠራቀሚያዎችን 544,490 ብር ወጭ በማድረግ ግዥ በመፈጸም ተክሎ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
2. በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በተቀመጡ ሮቶዎች የውሃ አቅርቦት እንዳይቆረጥ ለማድረግ ይቻል ዘንድ 10 የውሃ አቅራቢ ተሸከርካሪዎችን በመከራይት አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል፡፡
3. 11 ሰርፊስ ፓምፖች፣ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሰባት ሚትር የሚደርሱ መጠን ያላቸው ቦንቧዎች እና ፊቴንጎች፣አስር የኤሌክትሮ መካኒካል መለዎወጫዎች፤ ሰላሳ አራት የተለያዩ መጠን ያላቸው የጥልቅ ጉድጓድ ሰርፊስ ፓምፖች፤ አስር በእግር የሚሰሩ የእጅ መታጠቢያዎች፤ አንድ የሰርፊስ ፓምፕ መለዎወጫ እና አስር የኢሌክትሪክ ሲዊች ኪብሎች በድምሩ 13,624,834 ብር ወጭ በማድረግ ገዝቶ አሰራጭቶል፡፡ በለይቶ ማቆያዎች ላይም የቦንቧ ዝርጋታዎችን አከናውኗል፡፡
4. ብዛታቸው አራት መቶ ሀያ/420/ ባለ አምስት መቶ ሚሊ ፈሳሽ ሳሙና እንዲሁም ባለ አምስት መቶ/500 ሚሊ/ የሆኑ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሳኒታይዘሮች/ hand sanitizers/ በአጠቃላይ 24,401.84 ብር ወጭ በማድረግ ገዝቶ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች እና ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰራተኞች አሰራጭቶል፡፡
5. ከዚህ ባሻገር በአሁኑ ሰዓት በሁለተኛው የከተሞች ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አማካኝነት ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ 17 አዳዲስ ከተሞችና 12 የፕሮግራሙ ከተሞች በጥቅሉ ለ29 ለሚሆኑ ከተሞች የጥልቅ ጉድጓድ ፓምፕ፣የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ስራ ለመስራት የጀነሬተር፣የባንቧ መገጣጠሚያዎች ግዢ ለማድረግ ከ አንድ መቶ ሀምሳ ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ እየተሰራ ይገኛል፡፡
6. በሌላ በኩል ደወሌ ተርሚናል አካባቢ ከጅቡቲ ከሚገቡ መኪኖች ጋር ተያይዞ ውሃ ለማቅረብ ስራዎች በመስራት ላይ እንገኛልን፡፡
በአጠቃላይ የውሃ ልማት ኮሚሽን ከተሰጠው ሃላፊነት እና የስራ ድርሻ አንጻር የተለያዩ ስረዎችን ከመስራት ባሻገር ሀገር አቀፍ ብሎም አለም አቀፍ የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተለይ በዋነኝነት የመከላከያው መሳሪያ እጅን በውሃ በደንብ አድርጎ መታጠብ መሆኑን መሰረት በማድረግ እና ኮሚሽኑም ሳኒቴሽን ዋነኛ ስራው እንደመሆኑ መጠን ለዚህ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እና ከህዝባችን ጎን ለመሰለፍ ባደረገው ጥረት ለተለያዩ እቃዎች ግዥ በጥቅሉ ከአስራ አራት ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፉን አሳይቷል፡፡ ይህ አይነቱ ድጋፍ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የውሃ ል ማት ኮሚሽን ከአስራ አራት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለኮሮና ቫይረስ
ስርጭት ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አበረከተ፡፡
የግሉ ዘርፍ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ ድጋፉን እያሳየ ነው፡፡
ኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን በማስፋት ከቀን ወደ ቀን የተጠቂዎች ግለሰብ ቁጥር እና ሀገራት ከመጨመር ያገደው ነገር እስከ አሁን አልታየም፡፡ በአገራችንም በሽታው መግባቱ ከተገለጸበት ቀን ጀመሮ በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከአስር በላይ ከፍ ብሏል፡፡ ይህንን አይነት ድንበር የለሽ ወረርሽ ለመከላከል ብሎም የሚያደርሰውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጫና እንዲሁም የሰው ልጆችን እልቂት ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ እና የተባበር ጥረት ወሳኝ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተቋም ደረጃ እያንዳንዱ ሰራተኛም ሆነ ለስራ ጉዳይ ወደ መ/ቤቱ የሚገቡ ሰዎች እጃቸውን በሳሙና እንዲታጠቡ በሁሉም የመግቢያ በሮች በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን እንደዚህ አይነቱን የበሽታ ቅደመ መከላከያ ዘዴ በሌሎች አካባቢዎች ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ይገኛል ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በመላው አዲስ አበባ በሚገኙ የፓሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም በዋና ዋና ቦታዎች ላይ ሮቶዎችን በማስቀመጥ እና ውሃ እንዲሞሉ በማደረግ በሽታውን ‘’ እጅን በሳሙና በመታጠብ እንከላከል ለሌሎችም እንትረፍ ‘’ በሚል መርህ ከ GTB-engineering/ ጂቲቢ- ኢንጂነሪንግ ከተባለ የኮንስትራክሽን ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ጂቲቢ-ኢንጂነሪንግ ሮቶዎችን በየቦታዎቹ እየተከለ ሲሆን የውሃ ልማት ኮሚሽን/ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር/ ደግሞ የውሃ ትራኮችን በመከራየት በየተቋማቱ የተተከሉ ሮቶዎች ውሃ ስርጭት በማይኖርበት ጊዜ ውሃ እንዲደርስ የሚያደርስ ይሆናል፡፡ ከዚህ ባሻገር ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከዋሽ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል፡፡