House of Federation of Ethiopia
unity in diversity for development
02/06/2026
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ የተከበሩ አቶ ትግሉ መለሠ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ተገንተው ድምጽ ሰጥተዋል
01/06/2026
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሐራ ሁመድ በአፋር ክልል ዱብቲ ምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሰጥተዋል
01/06/2026
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በጎንደር ድምጽ ሰጥተዋል
27/05/2026
ለአገር አንድነትና ለፌዴራል ሥርዓቱ ግንባታ የጎላ አስተዋፅኦ ያበረከቱት የቀድሞው የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት የተከበሩ አምባሳደር አቶ ያለው አባተ የ40 ቀን መታሰቢያ የፀሎት ሥነ ሥርዓት እና የሀውልት ምርቃት ዛሬ በምንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል
*******************************************
(ዜና ፌዴሬሽን)
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተው ለአምባሳደሩ ያላቸውን ክብርና መታሰቢያ ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች ባደረጓቸው ንግግሮች አምባሳደር ያለው አባተ ለሀገር አንድነት፣ ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አብሮነት፣ ለፌዴራል ሥርዓቱ መጠናከር እና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያበረከቱት አስተዋፅኦ በታሪክ የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በትህትናቸው፣ በአመራር ብስለታቸው፣ በመልካም ሰውነታቸው እና ለአገራዊ አንድነት ባሳዩት ጽኑ አቋም ለትውልድ ተምሳሌት ሆነው እንደሚቀጥሉ አስታውሰዋል።
አምባሳደር ያለው አባተ በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ላይ በቆዩባቸው ዓመታት አገራዊ ጥቅምን በማስቀደም፣ በሕዝቦች መካከል መግባባትና መከባበርን በማጠናከር እንዲሁም የውይይትና የሰላም ባህል እንዲዳብር ባደረጉት ጥረት ዘወትር የሚታወሱ መሪ እንደነበሩም ተጠቅሷል።
በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ የአምባሳደሩ ሀውልት በክብር የተመረቀ ሲሆን፣ በሃይማኖት አባቶች የፀሎትና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። በተጨማሪም ለቤተሰቦቻቸውና ለቅርብ ወዳጆቻቸው አጽናኝ መልእክቶች ተላልፈዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፣
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍሊከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia
አዲስ አበባ
26/05/2026
እንኳን ለ1447ኛው የአረፋ (ዒድ አል አድሃ) በዓል አደረሣችሁ!
**********************************************
እንኳን ለ1447ኛው የአረፋ (ዒድ አል አድሃ) በዓል አደረሣችሁ! አደረሠን ሲል የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአረፋ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት ለሕዝበ ሙስሊሙ ያስተላልፋል።
አረፋ የመታዘዝና የመስዋዕትነት በዓል ነው፤ ነብዩ ኢብራሂም የተጠየቁትን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ በመሆናቸው ለታላቅ ክብር በቅተዋል። ነብዩ ኢብራሒም ልጃቸው ኢስማኤልን ለመሰዋት ልባዊ ዝግጅት አድርገዋል ፤ አላህ የነብዩን ሀቀኝነትና ታዛዥነት አይቶ በምትኩ የሚሰዋውን በግ አዘጋጅቶላቸዋል። ስለሆነም ነብዩ ኢብራሒም በከፈሉት መስዋዕትነት ድል አድርገው ክብርና በረከትን ከፈጣሪያቸው ዘንድ ተቀብለዋል። ይህ ዓርዓያ የሆነ ተግባራቸውም በሕዝበ ሙሲሊሙ ዘንድ ትልቅ የሃይማኖት አስተምህሮ ስፍራ ይዟል፡፡
እምነት ፈተናዎችን በፅናትና በመስዋዕትነት ጭምር ማለፍን እንደሚጠይቅ ሁሉ አገርም የምትገነባው ሕዝቦቿ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሁሉ በጽናትና በመስዋዕት መሻገር ሲችሉ ነው፡፡ ፅናት በትጋት በመስራት፣ ሰላማችንና አብሮነታችን በመጠበቅ፣ ለአገራችን ብሎም ለቀጣዩ ትውልድ ያለንን ተቆርቋሪነት በማሳየት እና በተሠማራንበት ዘርፍ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣትና በመሰል ብዝሐ ዕምርታዎች የሚገለጥ ነው፡፡
መስዋዕትነትም ለተግዳሮቶች እጅ ከመስጠት ወይም ችግሮችን ከመሸሽ ይልቅ ወደዕድልና ድል ለመቀየር በሙሉ ልብ መነሳሳትን ይጠይቃል፡፡ ይህም በመሆኑ ለሀገራችን ሠላም፣ ልማትና ብልፅግና ሊኖረን የሚገባው ፅናትና መስዋዕትነት ከዚሁ በዓል የምንማረው ትልቅ ትምህርት ነው ።
የአሁኑ ትውልድ ከአባቶቹ የተቀበለውን የአገራችንን ሉዓላዊነት የመጠበቅ አደራ፣ የኢትዮጵያን ወደ ከፍታዋ የመመለስ እና የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ዳር የማድረስ ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳለበት ለአፍታም ያህል መዘንጋት የለበትም፡፡
አሁናዊ የዓለምም ሁኔታ አርቆ ማሰብን፣ ፈጥኖ መራመድንና ወደፊት መገስገስን እንጂ የነበረውን ብቻ ይዞ በመቆየት ወይም ያንኑ በማስቀጠል ተወዳዳሪ መሆን አይቻልም፣ ተግዳሮቶችን ማሸነፍም ይሳናል፡፡ ስለሆነም አሁን በአገራችን ላይ የተፈጠሩ አስቻይ ሁኔታዎችን እንደመደላድል፣ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችንና ተግዳሮቶችን ወደ ክብርና ብልፅግና መጎናጸፊያ በመቀየር የምናልማትን ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ሁለንተናዊ ርብርባችን በላቀ ግለት ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቤት የሆነው የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምንገኝበት ወቅት 7ኛው አገራዊ ምርጫ ድምጽ የሚሰጥበት ዋዜማ እንደመሆኑ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ነጋቸውን ለማሳመር፣ የተጀመሩ ስኬቶቻችን ለማስቀጠል፣ኅብረብሔራዊ አንድነታችን ለማጽናት ሕገመንግሥታዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው የሚበጃቸውን ለመምረጥ በድምጻቸው ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እንዲሁም የምርጫ ዕሴቶች ተጠብቀው ምርጫው እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን እንዲወጡ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
ምክር ቤቱ በድጋሚ በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጿል !
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photo/house of the Federation of.
20/05/2026
በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት ስም በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰት ሲሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ የሌለ መሆኑን እያገለጸን ይህን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩት አካላትን አጣርቶ ተቋሙ ለህግ የምናቀርብ መሆኑን ይገልጻል።
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት
11/05/2026
“የሴቶች በምርጫ መሳተፍ የፍትሐዊነት ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲና የሰብአዊነት መብትም ማረጋገጫ ጭምር ነው” ክቡር አቶ በላይ ወዲሻ
**************************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን)፣ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ፣
የሴቶች በምርጫ መሳተፍ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብትን ከማረጋገጥ ባለፈ ለምርጫው ተአማኒነትና ፍትሐዊነት ወሳኝ እንደሆነ በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ክቡር አቶ በላይ ወዲሻ ገለጹ፡፡
በምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ሕጻናት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት “ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ ሕጋዊ መሠረቶችና የታሪክ ሂደት” በሚል ርእስ ለምክር ቤቱ ጽሕፈት ሴት ሠራተኞች በአዘጋጀው ሥልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ በላይ ምርጫ በዴሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ የሕዝብ ፈቃድ የሚገለጽበት መንገድ ሲሆን፣ የሴቶች ተሳትፎ ደግሞ ለአገር ዘላቂ እድገት፣ ለፍትሕዊ የሀብት ክፍፍል፣ ለእኩልነትና ለፖለቲካ ውክልና መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል።
ከግማሽ የሚሆነውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚወክሉት ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት ያላቸው ተሳትፎ ለረጅም ጊዜ ዝቅተኛ እንደነበር ጠቁመው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተዋል ብለዋል፡፡
በጽሕፈት ቤቱ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ትንሣኤ ከተማ የመወያያ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የ1987 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ሕገመንግሥትም ለሴቶች እኩል መብት የሚሰጥ ሲሆን፣ በአንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን፣ በአንቀጽ 35 ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል መብት እንዳላቸው እና በፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ መደንገጉ ተጠቅሷል። በተጨማሪም አንቀጽ 38 ሁሉም ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።
ለተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photo/house of the Federation of.
08/05/2026
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ላይ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቅጽ አገልግሎትን በተመለከተ፣ የሰጠው የሕገመንግሥት ትርጉም፣
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን በ6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ የስራዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም የቅጽ አገልግሎትን በተመለከተ የሕገመንግሥት ትርጉም የሰጠ ሲሆን በመመሪያው መሰረት የሚሞሉ ቅጾች ዓላማቸው የቤቶቹን መረጃዎች መያዝ እንጂ የቤት ባለቤትነትና ቤቱ ስለመወረስ አለመወረሱ እንደበቂና ብቸኛ ማስረጃ የሚያገለግል ባለመሆኑ ቤቱ በመንግስት ከዛሬ 40 ዓመት በፊት በሕግ ስለመወረሱ ቅጽ አልቀረበም፤ ቅጽ አለመቅረቡ ደግሞ የቤቱን አለመወረስ ያመላክታል በማለት ቅጹን እንደበቂ እና የመጨረሻ ማስረጃ በመውሰድ የሚሰጥ ውሳኔ የተሳሳተ ነው በማለት በመዝገብ ቁጥር108/15 ዓ.ም አስገዳጅነት ያለው የሕገመንግስት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የዳኝነት ስልጣንን እና የቅጽ አገልግሎትን ውሳኔዎችን ተፈጻሚነት በተመለከተ በቀን 28/08/2016 ዓ/ም የተከበሩ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የፌዴራል ፍትሕ ተቋማት፣ የሁሉም ክልል እና የሁለቱ ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዝዳንቶች እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተደርጓል፡፡
በመድረኩ ከዚህ ቀደም አዋጅ 47/67 አስመልክቶ ምክር ቤቱ የአሳለፋቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ መሆን እንዳለባቸው ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለወደፊትም ፍርድ ቤቶች የምክር ቤቱን ውሳኔ በተሳሳይ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የቅጽ አገልግሎትን በተመለከተ በመዝገብ ቁጥር 108 የተሰጠው የሕገመንግሥት ትርጉም የሚከተሉት ናቸው፡፡
08/05/2026
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ላይ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የዳኝነት ስልጣንን በተመለከተ፣ የሰጠው የሕገመንግሥት ትርጉም፣
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት የመንግሥት ንብረት ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 47/67 ላይ የዳኝነትን ሥልጣንና የቅጽ አገልግሎትን በተመለከተ ከ29/01/2011 ዓ.ም ጀምሮ የሕገመንግሥት ትርጉም ሰጥቷል፡፡
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክርቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ የስራ አመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 113/16 በሰጠው ውሳኔ ለረዥም ጊዜ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ቤቶች ከአዋጅ ውጪ በሆነ አግባብ ተይዘዋል የሚል ክርክር ስልጣን ለተሰጠው አካል ቀርቦ እስካልተረጋገጠ ድረስ ቤቱ የመንግሥት እንደሆነ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑ አስገዳጅ የሕገመንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በአዋጅ 47/67 አስመልክቶ ምክር ቤቱ የአሳለፋቸው ውሳኔዎች በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆነወሉ፡፡
የዳኝነትን ሥልጣንን በተመለከተ በመዝገብ ቁጥር 113 የተሰጠው የሕገመንግሥት ትርጉም የሚከተሉት ናቸው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
20212/1000
