Lemi Kura wereda fourteen youth league

Lemi Kura wereda fourteen youth league

Share

prosperity for all

05/04/2024
05/04/2024

አይዴ ጫምበላላ
እንኳን ለሲዳማ ዘመን መለወጫ ለሆነው የፍቼ ጫምባላላ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

በዓሉ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በጋራ በመቆም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዳግም ቃል የምንገባበት እንዲሆንልን እመኛለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Ayide Cambalaalaa

Baga bara haaraa Sidaamaa kan ta'e Fiichee Cambalaalaa geessan, geenye!

Ayyaanichi tokkummaa sabdaneessummaa keenya cimsinee waliin dhaabbachuun fayyadamummaa uummata keenyaa mirkaneessuuf irra deebiin kan waadaa itti seennu akka nuuf ta'un hawwa.

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu

03/04/2024

"ለውጡ የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲከወን አድርጓል።"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

ሀገራዊ ለውጡ የህዳሴ ግድቡ ግንባታ የገጠሙትን ችግሮች በማረም ግንባታው በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲከወን አድርጓል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጅማሮ የታወጀበት 13ኛ ዓመት እና የለውጡ መንግስት 6ኛ ዓመት ምስረታ የሚታሰብበት ዕለት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ማማ ለማሸጋገር ፋና ወጊ ትልም ጅማሮ ‘ሀ’ ብሎ የተጠነሰሰበት የጠቅላይ ሚኒስትራችን የለውጥ ታሪካዊ መሰረተ ድንጋይ በፓርላማ የተቀመጠው የዛሬ ስድስት ዓመት ነበር ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፋይዳ እና ተምሳሌትነቱ ተፈጥሯዊ የወንዝ ውሃ ፍሰትን ለኢኮኖሚያዊ ብልጽግና የማዋል ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው፤ ሀብት እያላት በድህነት ለምትማቅቀው አህጉራችን አፍሪካ ድህነትን ማሸነፍ እንደሚቻል ተስፋን የፈነጠቀ የክፍለ ዘመኑ ስኬት ነው ብለዋል።
ለኢትዮጵያውያን ደግሞ በዓድዋ ድል የአፍሪካውያንን ነፃ መውጣት በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ትግላችው አባቶቻችን ትምህርት እንደሰጡ ሁሉ የህዳሴ ግድቡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ድህነትን በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ታግለን ማሸነፍ እንደምንችል ዳግም ትምህርት የሰጠንበት በመሆኑ ኮርተናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የለውጥ መንግስት የህዳሴ ግድቡ ግንባታ የገጠሙትን ችግሮች ፈጥኖ በማረምና ግንባታው በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲከወን ማድረጉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም እየተመራች ላስመዘገበችው ዕድገት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነታችንን እያጠናከርን "ብሔራዊነትን" በማጎልበት ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ሁሌም እንተጋለን ሲሉም አንስተዋል።

Photos from Lemi Kura wereda fourteen youth league 's post 03/04/2024

የረመዳን የጾም ወቅትን ምክንያት በማድረግ በወረዳ ደረጃ በነገው ዕለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር በወረዳው ለሚገኙ በቁጥር 900 ለሚሆኑ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት የበጎ አድራጎት ተግባር እንደሚከናወን ተገለፀ።

በወረዳው የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ተገኝ እንደገለፁት የረመዳን የፆም ወርን ምክንያት በማድረግ "ተካፍሎ የመብላት ወርቃማ ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት እሴትን" በሚያዳብር መልኩ የማዕድ ማጋራት ተግባሩ እንደሚከናወን በመጠቆም በዕለቱም በወረዳ አቅም ከበጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችና ተቋማት ድጋፍ ሰጭነትና በወረዳው አመራሮች ልዩ ጥረት የማዕድ በረከቱን ማሰባሠብ ተችሏል ብለዋል።

ሃላፊዋ አክለውም ማዕድ የማጋራት ተግባሩም በወረዳ ደረጃ በአንድ ማዕከል ብሎም በየክላስተሩ በትስስር ማዕድ የማጋራት ተግባሩ እንደሚከናወን በመግለፅ በዕለቱም በድምር ቁጥር 900 ለሚሆኑ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት የበጎ አድራጎት ተግባሩን ለማከናወን ሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት

Photos from Lemi Kura wereda fourteen youth league 's post 30/03/2024

ዛሬ 21/07/2016 ዓ/ም የአፍጥር ፕሮግራም በወረዳ 14 ከሁሉም ወረዳ የመጡት ሊግ ሰብሳብዎች ጋር በወጣት መሀመድ ጉቱ ቤት ተካሄዷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
❤️❤️❤️❤️❤️❤️

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ብልጽግና ወጣቶች ሊግ ከሙስልም እና ከክርስቲያን እህትና ወንድሞች ጋራ የአፍጥር ፕሮግራም በቤታችን አካሄደናል።በአፍጥር ፕሮግራሙ ላይ የ፣10ሩም ወረዳ ሊግ አመራሮችና የወረዳችን የሊግ ስራ አስፈፃሚ ና መሰረታዊ ፓርቲ ስብሰባዎች ተገኝተውበታል።
በወንድማማች እና በእህትማማች መገለጫ አፍጥር ላይ የተገኙትን ሁሉ ይህ ኢትዮጵያዊነት ባህላችንን በመተሳሰብ እና በመተባበር ልናሳልፍ ይገባል።አብሮ መብላትና መጠጣት አንድነትን ያደረጃል ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ብልጽግና ወጣቶች ሊግ
21/07/2016 ዓ.ም

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa