01/05/2017
በሰሜን ጎንደር ዞን የመስክ ምልከታ እና የነዋሪዎች ምክክር . . .
ሃሳብ፥ ፅንሰ~ሃሳብ እና መልካም አስተሳሰብ ይመረታሉ፤
ዕውነ
01/05/2017
በሰሜን ጎንደር ዞን የመስክ ምልከታ እና የነዋሪዎች ምክክር . . .
01/05/2017
"በአመራሩና በማህበረሰቡ መካከል የሚደረግ የገፅ ለገፅ ውይይት ለላቀ የዕድገት ጉዞ ወሳኝ ነው!"
ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰሜን ጎንደር ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ መንግስት የህዝቡን የልማት አምሮት ለማርካት በዕቅድ ዘመኑ በትኩረት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አቶ ደመቀ ጠቁመው ህዝብ እና መንግስት በየደረጃው ተቀራርበው መወያየት መቻላቸው ለላቀ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
የየወረዳው ነዋሪዎች በውይይቱ ላነሱት የመሰረተ ልማት እና የልማት ጥያቄዎች የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በየደረጃው በአመራሩና በማህበረሰቡ መካከል የሚደረግ የገፅ ለገፅ ውይይት ለላቀ የዕድገት ጉዞ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ~ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
30/04/2017
Gonder ~ "City Of Camelot"
28/04/2017
በ~አብይ ኤፍሬም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠገዴ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ። ውይይቱ ከጠገዴ ወረዳ ወሰን መካለል እና ከአካባቢው ልማት ጋር በተያያዙ ዓበይት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
ነዋሪዎቹ ወሰን የመካለል ሂደቱ ጊዜ መውሰዱን በማስታወስ በአሁን ጊዜ መንግስት በሰከነ አግባብ የአከባቢውን ማህበረሰብ በማወያየት ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት እያደርገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል። በተለይ በውይይቱ ላይ የጠገዴና የአከባቢው ወረዳዎች በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር በመንግስት በኩል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የወሰን መካለል ሂደት በመንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩን ለመቛጨት ድንበሩ የሚካለልባቸው ማህበረሰቦችን የዘላቂ መፍትሄው አካል ለማድረግ በቅርበት ማወያየት ጠቃሚ መሆኑን አስረድተዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መሰል የውይይት መድረኮች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ደመቀ ተናግረዋል። የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በዕቅድ መሰረት በአፅንኦት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።
05/11/2015
Designing a presentation without an audience in mind is like writing a love letter and addressing it "to whom it may concern."
Ken Haemer
08/08/2015
Let's experience....
03/07/2015
የዘንድሮ የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ-ፈቃድ አገልግሎት ከሐምሌ 1 እስከ ጳግሜ 5፤ 2007 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ መርሃ ግብሩ "የወጣቶች በጎ-ፈቃድ አገልግሎት ለማህበረሰብ ዕድገት!" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ-12 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
(አብይ ኤፍሬም)
29/06/2015
“. . .ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን የማስቀረት አጀንዳ ከሚያስከትሉት ከባድ ጉዳት እና ከሚያስከፍሉን ያልተገባ ዋጋ አንፃር በተግባር እያዳበርን የመጣነውን ህብረታዊ ቅንጅት አጥብቀንና ጠብቀን ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡”
የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን
18/06/2015
Good Morning!