10/01/2024
ብሔራዊ ገዥ ትርክት በመፍጠር አብሮነታችንን ማጠናከርና አገራችንን መገንባት የሁላችንም ሃላፊነት ነው!
አቶ ድሪባ ዶጃ
*****************************
ታህሳስ 30/2016 ዓ/ም
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዱ 03 "ብሔራዊ ገዥ ትርክት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ምሽት አካሄደ። በኪነ ጥበብ ምሽቱ ላይ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የወጣትና ሴት አደረጃጀቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ያመንግስት ሰራተኞች፣ የወረዳው አመራሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ገዥ ትርክትን የሚያሰርፁ መነባነቦች፣ውዝዋዜዎች፣ ስነ ግጥሞችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ውጤቶች ቀርበዋል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዱ 03 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ድሪባ ዶጃ ብሔራዊ ገዥ ትርክት በመፍጠር አብሮነታችንን ማጠናከርና አገራችንን መገንባት የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል። ፓርቲያችን ብልፅግና በህብረ ብሔራዊነት አንድነቷ እንደ ብረት የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት አልሞ እሰራ ያለ ፣ ከጥላቻ ኪሳራ እንጅ ትርፍ እንደሌለ ለህዝባችን በልዩ ልዩ መድረኮች እየነገረ ብሔራዊነት እንዲገነባ እየታተረ ያለ እና ገዥ ትርክት የበላይነት እንንዲይዝ የኪነ ጥበብ ድርሻ አለው ብሎ ያምናል ብለዋል አቶ ድሪባ ባስተላለፉት መልዕክት።
የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ ወ/ሮ ሰመሃል ገ/መድህን በበኩላቸው ይህ በገዥ ትርክት የተዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት እንዲሳካ ላደረጉ የወረዳው አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ተሳታፊዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለመምጣት ብሔራዊ ገዥ ትርክት ግንዛቤ እንዲሰርጽና ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት የኪነ ጥበብ ምሽት መርሃግብሮች ውሳኝ ናቸው ብለዋል።

21/08/2021
21/08/2021
23/07/2021
18/12/2020
17/12/2020
10/09/2020