04/05/2026
ወጥ የሆነ የዱር ሕይወት ህግ ማስከበር ስራዎችን ለመስራትና ውጤታማ ለመሆን የተቋማት ቅንጅታዊ ስራ በእጅጉ ወሳኝ ነው ።
አቶ ኩመራ ዋቅጅራ
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በአገራችን የዱር ህይወት ጥበቃ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂ መንገድ ለመፍታት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እና የህግ ማስከበር ተግባራትን ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ነው።
በዛሬው ዕለት ለኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር በመከላከያ ጠቅላይ መምራያ ለተለያዩ የስታፍ ከፍተኛ አመራሮች በዱር ህይወት ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ሠጥቷል።
በስልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የዱር ህይወት ህልውናን ለመጠበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ መሆኑን አንስተው ወጥ የሆነ የዱር ሕይወት ህግ ማስከበር ስራዎች ለመስራትና ውጤታማ ለመሆን የተቋማት ቅንጅታዊ ስራ በእጅጉ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የመከላከያ ግብርና ልማት ዘርፍ መካናይዜሽንና ግብዓት ድጋፍ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል እሸቴ አራጌ የሉአላዊነት አካል የሆነውን የተፈጥሮ ሀብት የመጠበቅ እና የመከላከል ስራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም በእጅጉ ወሳኝ እንደሆነ እና ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በቅርበት ለመስራት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ብርጋዴር ጀኔራል እሸቴ አራጌ አያይዘው ገልፀዋል።
በስልጠናውም የኢትዮጵያ ዱር ሕይወት ጥበቃ ታሪክ ፣ የዱር ህይወት ጥበቃና አጠቃቀም፣ የዱር ሕይወት የህግ ማዕቀፎች፣ አዋጅና ደንቦች እንዲሁም የዱር ህይወት የህግ ማስከበርን የተመለከቱ ፅፎች በዘርፉ ባለሙያዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው የጋራ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም ተሳታፊዎች ስልጠናው የዱር ህይወት ጥበቃ ስራን በትኩረት ለመስራት እንደሚያግዛቸው ገልፀው በቀጣይ መተካ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሀብት በጋራ ለመጠበቅ ተቋማዊ የጋራ ስምምነትን በመፍጠር ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባ፤ ጥበቃ ቦታዎች አካባቢው አሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የጥበቃና ቁጥጥር ስራ መሠራት እንዳለበት እንዲሁ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበትና በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ገልፀዋል ።
በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ በመከላከያ ጠቅላይ መምራያ የተለያዩ የስታፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
02/05/2026
የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ልማትና ጥበቃ ለማጠናከር ትኩረቱ ያደረገ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሔደ።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ጎንደር
የኢትዮጵያ የዱር እንሳሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከAWF ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮች፣የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም አጋር ድርጂቶችና የብሔራዊ ፓርኩ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የስሜን ተራራዎችን ብሔራዊ ፓርክ ጥበቃ ለማጠናከር ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ የተለያዩ አደረጃጀቶች መኖራቸውን አንስተው ፓርኩ ካለበት ሠው ሠራሽ ችግር ለመታደግ ከትናንቱ የተሻለ ቅንጅታዊ ስራ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
አቶ ኩመራ አያይዘው የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ግንባር ቀደምና የመጀመሪያው የሀገራችን የአለም ቅርስነት የተመዘገበ ሀብት መሆኑ ጠቅሠው ብ/ፓርኩ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለሀገር እየሰጠ ያለውን ፍይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ያሉበትን ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶች ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካል በዕቅዱ አካቶ ሊተገብር ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የስሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዲ/ን ሸጋው ውቤ የስሜን ተራሮች ብ/ፓርክን መጠበቅና ማልማት የዞኑ ዋነኛ ተግባር መሆኑን እና በሁሉም ብ/ፓርክ አዋሳኝ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እየተሰራ ቢሆኑም ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለየ መንገድ ፓርኩ ካለበት ችግር እንዲወጣ ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በምክክር መድረኩም የብሔራዊ ፓርኩ የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት እንዲሁም በቀሪ 3 ወራት ሊሰሩ የሚገባቸው የትኩረት መስኮች ቀርበዋል።
በተጨማሪም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አጋር የሆነው እና በብ/ፓርኩ ላይ ሰፊ ተግባራትን እየተገበረ ያለው አፍሪካ ዋልድላይፍ ፍውንዴሽን (AWF) ያከናወናቸው ስራዎች ቀርበዋል።
የቀረቡትን ሪፖርቶች መነሻ በማድርግ ሠፊ ውይይት ተካሒዷል።
የብ/ፓርኩን ልማትና ጥበቃ ለማጠናከር ከመንግስት በተጨማሪ የአጋር አካላት ሚና በእጅጉ ወሳኝ እንደሆነ እና በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በተሳታፊዎች ተነስቷል።
እንዲሁም ሁሉም አካል ብ/ፓርኩን ከመጠበቅ አንጻር ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በመግለፅ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።
Park #
#
29/04/2026
በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከዱር እንስሳት አጠቃቀም ዘርፍ ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።
ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ይህ የተገለፀው ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኞች ጋር ባዛሬው ዕለት ገምግሟል።
በውይይቱ ባለስልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከዱር እንስሳት አጠቃቀም ዘርፍ ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።
ገቢው ከኢ-ፍጆታዊና ከፍጆታዊ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ማለትም ከዱር እንስሳት ጥናትና ምርምር፣ ከስፖርታዊ አደን፣ ከሀገር ውስጥ አደን፣ ከጥበቃ ቦታዎች ጉብኝት እና ከዱር እንስሳት ውጤቶች እንዲሁም ከህይወት ንግድ እንደሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ከተቋሙ ሪፎርም ስራዎች ረገድ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው የጋራ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱም ላይ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች፣ በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ክፍተቶች ተዳሰዋል።
26/04/2026
በስንቅሌ ቆርኬዎች መጠለያ የሚስተዋሉ ሰው ሠራሽ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡
ሚያዝያ 17/2018ዓ.ም
ስንቅሌ ቆርኬዎች መጠለያ
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን በስንቅሌ ቆርኬዎች መጠለያ የሚስተዋሉ ሰው ሠራሽ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል የምክክር መድረክ የመጠለያው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል፡፡
የምክክር መድረኩ በ2018 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት መጠለያው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተሠሩ ዋና ዋና ሥራዎች አፈጻጸም ለመገምገምና የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በርብርብ ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ለማመላከት ያለመ ነው።
ባለፉት 9 ወራት በቅንጅት የተሠሩ ሥራዎች በመጠለያው ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ባንኪ ቡደሞ ቀርቦ ውይይት የጋራ ተደርጎበታል፡፡
ህግን ለማስከበር፣ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ እና የብርቅዬውን የቆርኬ ቁጥር ለመጨመር ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸው ተገምግሟል።
እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት የሚፈልጉ የልቅ ግጦሽ፣ ወሠን ማስከበር እና ማህበራት ተጠቃሚነት በሥርዓት አለመመራት የመጠለያው ተግዳሮት ሆነው የቀጠሉ በመሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን እንደገለጹት የስንቅሌ ቆርኬዎች መጠለያ ሀገራችን በብቸኛ ባለቤትነት የምትታወቅበትና የምትኮራበት የስዌይን ቆርኬዎች መኖሪያ መሆኑን በመጥቀስ መጠለያውን በተለይም የቆርኬን ህልውና ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታ ባልነበረበት ጊዜ የገዳ ስርዓት በመጠቀም የአከባቢው ማህበረሰብ ያበረከተውን የላቀ አስተዋጽኦ በማውሳት አሁን የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በዚህ መድረክ የተፈጠረውን የአስተሳሰብ አንድነትና ቁርጠኝነት በመጠቀም መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሠጠውን ልዩ ትኩረት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን መረባረብ እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት አንስተዋል፡፡
የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ቶሎሳ በበኩላቸው ተፈጥሮ ያደለንን ሀብት የመጠበቅና ዘላቂነት ባለው መልኩ የመጠቀም ኃላፊነት አለብን ብለው በበጀት አመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት የተቀጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም እነዚህኑ ማጽናትና አሁንም ተግዳሮት ሆነው የቀጠሉ በጥበቃ ቦታው የቤት እንስሳ ስምሪት፣ የቆርኬዎች ቁጥር መቀነስ፣ በምስራቅ አዋሳኝ የሚስተዋለው ድንበር ግፍያ፣ የህብረተሰብ ተጠቃሚነትና የህግ ተከባሪነት ችግር በቅንጅት በአጭር ጊዜ ውስጥ በርብርብ እንዲፈቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በመድረኩ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ጥሪ የተደረገላቸው ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን መታየት የጀመሩ ለውጦችን ለማስቀጠልና በመድረኩ የተነሱ ቁልፍ የመጠለያው ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት የጋራ መግባባት በመድርስ የውይይት መድረኩ እስካሁን የተሠሩ ሥራዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
24/04/2026
የቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ተገመገመ፡፡
ሚያዝያ 16/2018ዓም
አዲስ አበባ
የቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ተገመገመ ፡፡ የፊዴራል ሲቪል ሰርቪሽ ኮሚሽን ሚኒስቴሩ የደረሰበትን የሪፎርም ዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም በዝርዝር አቅርቧል ፡፡
ሪፎርሙን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተሰጡ አቅጣጫዎችን ተከትሎ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የትራንስፎርሜሽንና የለውጥ ስራ አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ወርቁ ደጄኔ (ዶ/ር) ጠቁመዋል ፡፡ ሚኒስትሩና ተጠሪ ተቋማቱ ወደ ተሟላ ትግብራ መግባት እንዲቻልም ቀሪ ስራዎችን በተሰጠው ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው ገልፀዋል ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአሰራርና ከአስተሳሰብ ጋር በተገናኘ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየተጋች ያለች ሀገር መሆኗን በመግለጽ ሪፎርሙ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጠንካራና ብቁ የሆነ ተቋም ለመፍጠር በዘርፉ የሚታዩ ጉድለቶችን ማረም እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን በተጠሪ ተቋማት መዋቅር ውስጥ የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያውን እኩል ማስኬድ እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
በመድረኩ የዝግጅት ምዕራፉ የደረሰበት ደረጃ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል።
21/04/2026
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሔደ።
ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም
ኢዱጥባ
የባለስልጣን መስራያ ቤቱ የበላይ አመራሮች፤ ስራ አስፈፃሚዎችና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስር የሚገኙ ብሔራዊ ፖርክ እና የዱር እንስሳት መጠለያ ችፍ ዋርደኖች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በዋናው መስራያ ቤት የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ውይይት አካሂዷል ።
አጭር መልክት በማስተላለፍ ውይይቱን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ውይይቱ በሱፐርቪዥን ቡድኑ የተገኙ ውጤቶችን እና በአፈፃፀም ወቅት የታዩ ክፍተቶችን ለይቶ የሚፈቱበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ እና በቀጣይ በሚሠሩ ሥራዎች ዙሪያ የጋራ አቋም ይዘን የምንወጣበት የውይይት መድረክ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም አስመልክቶ በተለያዩ ቀጠናዎች በመንቀሳቀስ የመስክ ላይ ምልከታ ያደረገው የሱፐር ቪዥን ቡድን ሪፓርት ለተሳታፊዎች ቀርቧል።
በሪፖርቱም በጥበቃ ቦታዎች እየተከናወኑ ያሉ የህግ ማስከበር እንቅስቃሴዎች ፤ የጥናትና ምርምር ስራዎች፤ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ተጠቃማነት ከማሳደግ አንፃር የተከናወኑ ተግባራትን፤ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠሩ እና በቀጣይ ሊሠሩ የሚገባቸውን ስራዎች እንዲሁም ከሠው ኃይል ሙሌት ፤ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዎች ተዳሠዋል። በቀረቡት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የጋራ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የአፈፃፀም ግብረ መልሱ እንደተቋም በርካታ ስኬቶቻችንን ማሳየት የቻለ ቢሆንም የዚያንው ያህል ደግሞ ያልተሻገርናቸውን ተግዳሮቶች ማሳየት መቻሉን አውስተው በቀጣይ የጥበቃ ስራዎች በተለይ የህግ ማስከበር ሥራዎች ፣ የሰው ኃይል ሙሌት ፣ ፈጣን ምላሽ ከመስጠት፣ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን እና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ የሚቀሩን ስራዎች በርካታ በመሆናቸው በቀጣይ ትኩረት ተሠጥቶ ሊሠራ እንደማገባ ገልፀዋል ።
አቶ ኩመራ አያይዘው እለት እለት በጥበቃ ሥራዎች ላይ የሚገጥሙ ፈተናዎች በመቀነስ ፈንታ እየጨመሩ በመሆናቸው በፈተናዎቹ ከመንበርከክ ይልቅ ለሞያችን ጸንተን የመፍትሔው አካል ልንሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የተቋሙን በጀት በአግባቡ ከመጠቀም አኳያ አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ላሉ ጥበቃ ቦታዎች ትኩረት ተሠጥቶ ድጋፉ እንደሚቀጥል ገልፀው ሁሉም የስራ ኃላፊ እና የዘርፉ ባለሞያ ከጠባቂነት መንፈስ ተላቆ እና ችግርን ከማወጅ ወጥቶ የመፍትሔ አካል መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሌላ መልኩ አቶ ሠለሞን መኮንን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር በጥበቃ ቦታዎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሠፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችና የህግ ማስከበር ተግባራት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ሠለሞን አያይዘው የድጋፍና ክትትል ስራው ቀጣይነት ያለውና ውጤት የሚያመጣ መሆን አለበት ሲሉ ገልፀዋል።
17/04/2026
https://www.facebook.com/100078842288985/posts/964209149550486/
ለስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ድምፃችንን እንስጥ! 🇪🇹
የዓለም ትራቭል አዋርድ (World Travel Awards) ለ33ኛ ጊዜ በሚያካሂደው ውድድር፣ የእናት ኢትዮጵያ ኩራት የሆነው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ ‘Africa’s Leading Scenic National Park 2026’ ዘርፍ በእጩነት ቀርቧል።
ይህ ድንቅ የተፈጥሮ ሀብታችን የዓለምን ትኩረት እንዲስብ እና የቱሪዝም መዳረሻነታችን እንዲጎላ የእያንዳንዳችን ድምጽ ወሳኝ ነው።
እንዴት ድምጽ መስጠት ይቻላል?
ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.worldtravelawards.com/vote
'Register' በማድረግ ይመዝገቡ (ኢሜይልዎን ያረጋግጡ)።
ወደ 'Africa' ዝርዝር ውስጥ በመግባት 'Africa’s Leading Scenic National Park' የሚለውን ይምረጡ።
Simien Mountains National Park, Ethiopia የሚለውን በመጫን ድምጽዎን ይስጡ።
ኢትዮጵያን በጋራ እናልማ! ድምጽዎን በመስጠት ለሀገርዎ ያለዎትን ኩራት ይግለጹ።
15/04/2026
የቱሪዝም ዘርፍን ከሙስና የፀዳና አርአያ ለማድረግ የአመራሩ ሚና የማይተካ መሆኑ ተገለጸ።
ሚያዚያ 7/2018 ዓ.ም
የቱሪዝም ሚኒስቴር ከፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ ለዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች “የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ቃል የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል።
በሥልጠናው መድረክ ላይ እንደተመላከተው የቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመሆኑ ዘርፉን ከሙስና የፀዳና አርአያ ለማድረግ የአመራሩ ሚና የማይተካ መሆኑ ተገለጻል።
አመራሩ ማንኛውንም ውሳኔ ሲያሳልፍ ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥን በመከተል፣ የሕግ የበላይነትንና ተቋማዊ አሠራርን መሠረት ማድረግ እንዳለበትም ተጠቅሷል።
በተለይም ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል የጥቅም ግጭት የሚታይባቸውን ሁኔታዎች የመለየትና የማስተዳደር ክህሎት ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እንደገለጹት:- ተቋማዊ ሪፎርሞችን ውጤታማ ለማድረግና ለሀገራዊ ብልጽግና ስኬት በቆራጥነት ለመቆም የአመራሩ በሥነ-ምግባራዊ እሴቶችና በታማኝነት ላይ የተመሠረተ የውሳኔ አሰጣጥ ሚና ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
አክልውም ውሳኔዎች የሕግ የበላይነትን ያከበሩ፣ ከተቋማዊ አሠራር ጋር የተሳሰሩና ቀጣይነት ያለው የተቋም ግንባታን ታሳቢ ያደረጉ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ዙሪያ መነሻ የሥልጠና ሰነድ በዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ የቀረበ ሲሆን፣ የዘርፉ አመራሮችም ለፀረ-ሙስና ትግሉ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የሥልጠናውን ማጠቃለያ የሰጡት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፤ ሕግና ሞራል አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይም ሙስናን ለማስቀረት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማገዝ እና አሠራሮችን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ለፀረ-ሙስና ትግሉ እንቅፋት የሚሆኑ አዝማሚያዎችንና የጥቅም ግጭቶችን ለይቶ በመከላከል፣ ዘርፉን ከሙስና የፀዳና አርአያ ተቋም የማድረግ ኃላፊነት ከአመራሩ እንደሚጠበቅም አክለዋል።
በሥልጠናው ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ
11/04/2026
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንኳን ለትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
ባለስልጣን መሥሪያ ቤታችን የተፈጥሮ ሀብታችንን በጋራ እንጠብቅ እያለ በዓሉ የሰላም ፣ የመተሳሰብ እና የበረከት ይሆንላችሁ ዘንድ ይመኛል!
60 ዓመታት ለኢትዮጵያ የዱር ሕይወት!
መልካም የትንሳዔ በዓል!
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን
11/04/2026
33ኛው የአለም ትራቭል አዋርድ
የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በ ‘Africa’s Leading Scenic National Park 2026’ ዘርፍ በእጩነት አቅርቦታል።
የእያንዳንዳችን ድምጽ ዋጋ አለው!
ቀጣዮን ማስፈንጠሪያ በመጫን ድምጻችሁን ስጡ፤
👇🏻
https://www.worldtravelawards.com/vote
ኢትዮጵያን በብሔራዊ ፓርክ መዳረሻዎች ቱሪዝም መዳረሻነት ተመራጭ እንድትሆን የድርሻችሁን ተወጡ።
የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በማራኪ ተፈጥሯዊ አቀማመጡ የታደለ ውብ መዳረሻ ነው። መዳረሻቸውን በስሜን ተራሮች ላይ ያደረጉ የብርቅዬ የዱር ሕይወት መኖሪያ።
Simien Mountains National Park Office
08/04/2026
𝐋𝐞𝐬𝐬𝐨𝐧𝐬 𝐟𝐫𝐨𝐦 𝟑𝟎 𝐘𝐞𝐚𝐫𝐬 𝐨𝐟 𝐖𝐢𝐥𝐝𝐥𝐢𝐟𝐞 𝐂𝐨𝐧𝐬𝐞𝐫𝐯𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐢𝐧 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚
Mr. Kumara Wakjira, Director General of the Ethiopian Wildlife Conservation Authority, reflects on his long conservation journey in an interview with Dialogue Earth.
He has been recognized with the prestigious Tusk Conservation African Award for his outstanding contributions to wildlife conservation.
Over the past 30 years, his leadership has driven major milestones, including the global recognition for Bale Mountains National Park as UNESCO world heritage site and strengthening the management of protected areas across the country and offering renewed hope for the future of Ethiopia’s wildlife.
To read more, please use the link provided below.
Q&A: Lessons from 30 years of wildlife conservation in Ethiopia
The head of Ethiopia's wildlife authority talks to Dialogue Earth about his career highlights, and the road ahead for conservation