Ethiopian Sugar Industry Group

Ethiopian Sugar Industry Group

Share

Established as public enterprise by the Public enterprise proclamation No. 500/2022.

Established as public enterprise by the Public enterprise proclamation No. 25/1992.

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 03/06/2026

የሐዘን መግለጫ
_______________
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በምርምርና ስልጠና ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት በተመራማሪነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ቶሎሳ ታዬ ሁንዴሳ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ በተወለዱ በ33 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ማነጅመንት እና ሠራተኞች በአቶ ቶሎሳ ታዬ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!!

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 29/05/2026

የኢ.አር.ፒ እና ኤ.ኤም.ኤስ ሥርዓት አጠቃላይ ምልከታና ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ
_________________________________________
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ተግባራዊ ለማድረግ ትግበራ ምዕራፍ ላይ የደረሰው ተቋማዊ የሀብት አመራር (ኢ.አር.ፒ) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ሥርዓት (ኤ.ኤም.ኤስ) ምልከታና የከፍተኛ ማነጅመንት ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
አጠቃላይ የፕሮጀክት ምልከታና የከፍተኛ ማነጅመንት ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በንግግር የከፈቱት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ መድረኩ የፕሮጀክቱ ይፋዊ ትግበራ የመጨረሻ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በእስካሁኑ የፕሮጀክቱ ትግበራ ሒደት መሰረታዊ የሆነው የሲስተም ዲዛይን ሥራ ተጠናቆ የተለያዩ የፍተሻ እና የግምገማ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ወጥ ቻርት ኦፍ አካውንት መፍጠር፣ ኮስት ሴንተር እና አይተም ኮዲፊኬሽን፣ በተቋም ደረጃ የሚገናኙ የሥራ ሒደቶች ፕሮሰስ ማፒንግ ቀጣይ ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተቋማዊ ሀብት አመራር (ኢ.አር.ፒ) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ሥርዓት (ኤ.ኤም.ኤስ) ፕሮጀክት የመጨረሻው የትግበራ ምእራፍ ላይ መድረስ መቻሉ አስደሳች ቢሆንም ቀሪ ሥራዎች ልዩ ትኩረት የሚሹና ወሳኝ በመሆናቸው የግሩፑ ከፍተኛ የማነጅመንት አባላት ልዩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሳስበዋል፡፡
ግሩፑ ወደሥራ ለማስገባት እየሰራበት ያለው የተቋማዊ ሀብት አመራር (ኢ.አር.ፒ) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ሥርዓት (ኤ.ኤም.ኤስ) ፕሮጀክት መንግስት ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኘው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዕቅድን ለማሳካት የራሱን ድርሻ ከመወጣት አንጻር ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን በመረዳት ለፕሮጀክቱ ስኬት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠትና አስፈላጊውን ሀብት በመመደብ ወደሥራ መግባቱን ክቡር አቶ ወዮ ሮባ አስታውሰዋል፡፡
የፕሮጄክቱ ትግበራ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል የቴክኖሎጂ አልሚ ኩባንያ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና አማካሪው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አማካሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ተወካይ ናትናኤል አርጋው (ዶ/ር) ሮጀጀክቱ ያለበትን ሁኔታ ለግሩፑ ከፍተኛ ማነጅመንት አባላት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ማነጅመንት ለፕሮጀክቱ ስኬቱ ያሳየው ቁርጠኝነት የሚደነቅ እና ለሌሎች ተቋማት በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተደረገው አጠቃላይ የምክክር እና የቢዝነስ ኢንተለጀንስ እንዲሁም የሁሉም ሞጁሎች ምልከታና የማኔጅመንቱ ተጨማሪ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፕሮጀክቱ አማካሪ እና የሥርዓቱ አበልጻጊ ድርጅት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

18/05/2026

የቅጥር ማስታወቂያ
______________________
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካዎች
ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በተተኪነት አሠልጥኖ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል
_________________
ኦንላየን ማመልከቻ ቅጽ
_________________
https://forms.gle/QFToER8caBTeN8sN7

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 14/05/2026

በኦሞ ቤልት በመዝነብ ላይ የሚገኘው ከፍተኛ ዝናብ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል
______________________________
በኦሞ ቤልት ስኳር ፋብሪካዎች በመዝነብ ላይ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በልዩ ልዩ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ከማድረሱም በተጨማሪ አጠቃላይ የመሬት ዝግጅት፣ አገዳ ተከላ እና ክብካቤ ሥራዎችን እያስተጓጎለ ይገኛል፡፡
በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካዎች ከየካቲት ወር ጀምሮ በመዝነብ ላይ የሚገኘው ወቅቱን ያልጠበቀ ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በፋብሪካዎቹ የመኖሪያ መንደሮች፣ መንገዶች፣ ድልድዮች እና የመስኖ ካናሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ጎርፉ የሠራተኛ መኖሪያ መንደሮች እርስ በርስ እና ከዋና ከተማ ጋር የሚያገናኝ ዋና መንገድ መቆረጥ፣ በአብኛው የአገዳ ማሳዎች በጎርፍ ውሃ መሞላት (መዋጥ)፣ የሠራተኛ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ውሃ የመጥለቅለቅ አደጋ አስከትሏል፡፡
በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 የተመዘገበው የሜትሮሎጂ መረጃ እንደሚመለክተው በየካቲት 120.08 ሚሊ ሜትር፣ በመጋቢት 156.25 ሚሊ ሜትር፣ በሚያዚያ 275.08 ሚሊ ሜትር እና ግንቦት የመጀመሪያ ቀናት (እስከ ግንቦት 4/2018ዓ.ም) 39 ሚሊ ሜትር አማካይ ወርሃዊ መጠን ያለው ከፍተኛ ዝናብ፣ በሶስት ወር ደግሞ በድምሩ 590.41 ሚ.ሜ. የሆነ ከፍተኛ ዝናብ መመዝገቡን ያሳያል፡፡
በተመሳሳይ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ የተመዘገበው የሜትሮሎጂ መረጃ በየካቲት 47.72 ሚሊ ሜትር፣ በመጋቢት 173.58 ሚሊ ሜትር፣ በሚያዚያ 403.76 ሚሊ ሜትር እና በግንቦት የመጀመሪያ ቀናት (እስከ ግንቦት 5/2018ዓ.ም) 49.36 ሚሊ ሜትር አማካይ ወርሃዊ መጠን ያለው ከፍተኛ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሶስት ወር በድምሩ 674.42 ሚ.ሜ. መሆኑንም ያሳያል፡፡
ፋብሪካዎቹ ጎርፉ ያስከተለውን ጉዳት ከመቅረፍ ባለፈ የተለያዩ የመከላከል ሥራዎችን በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ሠራተኛውም ጎርፉ የበለጠ ጉዳት እንዳያስከትል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 11/05/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የተመራው ልዑክ በፋብሪካው ውይይት አደረገ
_________________________
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሀ ጋረደው የተመራው ልዑክ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በመገኘት ውይይት አድርጓል፡፡
ግንቦት 2 ቀን 2018ዓ.ም የተደረገው ውይይት በአካባቢው በሚገኙ አርብቶ አደሮች መካከል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩት አለመግባባቶች በኦሞ ኩራዝ በሚገኙ ስኳር ፋብሪካዎች የሚያስከትሏቸውን የጸጥታ ችግሮች መከላከል ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውይይቱ ላይ የደቡብ ኦሞ ዞን ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ፣ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ፣ የሣላማጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣ የሣላማጎ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ፣ በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት እና ፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እንዲሁም የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት እና ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ ማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በአካባቢዎቹ በአርብቶ አደሮች መካከል በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አለመግባባቶች በፋብሪካዎቹ የስኳር ልማት ሥራ ላይ ያስከተሉትንና እያስከተሉ የሚገኙትን ተግዳሮቶችን በተመለከተ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈለቀ ቶማ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሠነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ መጨረሻ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሀ ጋረደው በአካባቢው አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ፋብሪካዎቹ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሣላማጎ ወረዳ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ለመፍታት እያደረጉት የሚገኙትን ጥረቶች አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
በዋናነት ግን ኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች የሚገኝበት የሣላማጎ ወረዳ አካባቢው ሠላማዊ የኢንዱስትሪ ቀጠና እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አስገንዝበው የክልሉ መንግስት በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ በመግለጽ የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 29/04/2026

ለግሩፑ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
‎‎---------------------------------------------
ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች "የከፍተኛ አመራሩ ሚና ለጸረ ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ" በሚል ርዕስ በሥነ ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭትን መከላከል ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ሚያዚያ 21 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተሰጠውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባ ስልጠናው በሥነ ምግባር የታነጸና ታማኝ እንዲሁም አገልጋይ የሥራ መሪ በመፍጠር ረገድ የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ግሩፑ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች የውስጥ አሠራሮችን ለብልሹ አሰራሮች በማይመች መልኩ መቅረጽና የተጠያቂነት ሥርዓትን ማሻሻል ተጠቃሾች እንደነበሩ ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታውሰው ስልጠናው ተቋሙ የጀመረውን ይህንን ሙስናን የመከላከል ጥረት ያግዛል ብለዋል፡፡
ከፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስልጠናዎችን በመስጠትና ግንዛቤ በማዳበር ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚረዱ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቅሰው ሥልጠናውን የወሰዱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ባገኙት ዕውቀት በመታገዝ ለታችኛው መዋቅር አርዓያ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡
በስልጠናው ግብረ-ገብነት ለማህበረሰብ ዕድገትና ለተቋማዊ ስኬት ያለው ወሳኝ ሚና ከመዳሰሱም በተጨማሪ ተገልጋይ ተኮር የሆነና በግል ፍላጎትና በተቋማዊ ግዴታ መካከል ያለውን ልዩነት ጠብቆ የሚሄድ አመራር እንዴት መፍጠር እንደሚቻልም ታይቷል።
‎በተቋማት ሊፈጠሩ የሚችሉ የጥቅም ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከል ለአመራሩና ለሚሰራበት ተቋም ውጤታማነት ያለው ድርሻ እንዲሁ በስልጠናው ትኩረት ተደርጎበታል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተሳታፊዎች ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየር፣ ተቋሙን የበለጠ ውጤታማና ተዓማኒ በሆኑ መልኩ ለማገልገልና ሥራዎችን ለመምራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።
ስልጠናውን የሰጡት በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ ናቸው፡፡

Photos from Ethiopian Sugar Industry Group's post 28/04/2026

በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ የኢአርፒ እና የእርሻ ስራዎች አመራር ስርዓት ስልጠና መስጠት ተጀመረ
_______________________________
ተቋማዊ የሀብት አመራር (ኢ.አር.ፒ) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ሥርዓት (ኤ.ኤም.ኤስ) ስልጠና ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 ስኳር ፋብሪካ አስተግባሪ አካላት የምርት ሥራቸውን በማያስጓጉል መልኩ መስጠት ተጀምሯል፡፡
ከሁሉም የፋብሪካው ሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ 69 አስተግባሪ አካላት ከዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆየው ሥልጠና በፋብሪካው ተቋማዊ የሀብት አመራር (ERP) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ስርዓት (AMS) ለመተግበር የሚያስችል መሆኑ ታውቋል፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪጅ አቶ ሚጀና ቢቂላ ሥልጠናው በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ እንዲሁም በፋብሪካው እየተካሄደ የሚገኘውን የለውጥ ጉዞ በማዘመን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ለሠራተኞቻቸው ማካፈልና በቁርጠኝነት ወደተግባር መለወጥና እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
በግሩፑ የአይ.ሲ.ቲ መምሪያ ስራ አስፈጻሚ አቶ መሰለ እሸቱ በበኩላቸው የግሩፑ ከፍተኛ አመራር የኢ.አር.ፒ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን በቁርጠኝነት ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረጉ የዲዛይን ስራው ተጠናቆ ወደተግባር ለመግባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህ ስልጠና የተዘጋጀው የፋብሪካው አመራርና ሰራተኛ የአጠቃቀም ስልጠና ወስደው ሲስተሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስቻል ታልሞ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለውጤታማነቱ ሃላፊነት እዳለባቸው ገልጸዋል።
ተቋማዊ የሀብት አመራር (ኢ.አር.ፒ) እና የእርሻ ሥራዎች አመራር ሥርዓት (ኤ.ኤም.ኤስ) የማበልጸግ ስራውን ያከናውነው ኢትዮ ቴሌኮም የዲዛይን ስራውን እና የተለያዩ ግምገማዎችን እንዲሁም ሙከራ አከናውኖ በማጠናቀቅ ወደስልጠና መሸጋገሩ ታውቋል፡፡
ስልጠናው በመሰጠት ላይ የሚገኘው በስምንት ሞጅሎች ማለትም በእርሻ ማኔጅመንት፣ በፋብሪካ ኦፕሬሽን፣ በሰው ሐብት አስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በግዥ፣ በንብረት አስተዳደር፣ በፔሮል ዝግጅት እና በኢንቨንተሪ ማኔጅመንት ሞጁሎች ነው፡፡
ይኸው ስልጠና ከዚህ ቀደም ለዋና መስሪያ ቤት እና ለኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 አስተግባሪ አካላት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ለአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

27/04/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Mexico Square, Philips Building
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00