01/06/2026
Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency
C R R S A - Civil Registration and Residency Service Agency - የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
01/06/2026
26/05/2026
የኤጀንሲው እግር ኳስ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለ
CRRSA: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የእግርኳስ ቡድን አስደናቂ ብቃት በማሳየት ወደ ግማሽ ፍጻሜ መቀላቀሉ አስታወቀ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 28 የከተማ አስተዳደርና የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች መካከል እየተካሄደ በሚገኘው "ስፖርት ለሁሉም" የታላቅ እግርኳስ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የኤጀንሲያችን የእግር ኳስ ቡድን አስደናቂ ብቃትና ተከታታይ ድሎችን በማስመዝገብ ወደ ግማሽ ፍጻሜ መግባቱን አረጋግጧል።
በኤጀንሲው የስፖርት ባለሙያ የሆኑት አቶ መኳንንት አንዷለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጤናማ የአካልና የአዕምሮ ብቃትን ከማጎናጸፍ ባለፈ በማህበራዊ ግንኙነት ላይ መተዋወቅን መቀራረብንና አብሮ መስራትን እንዲሁም እውነተኛ የቤተሰባዊነት ፍቅርን የሚያጠናክሩ ታላላቅ ድልድዮች ናቸው በማለት ገልጸዋል።
የመንግስት ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያዘወትሩና ተቋማት ከተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ በሚደረገው ዘላቂ እንቅስቃሴ ላይ ተቋማችን የራሱን አሻራ እያሳረፈ የሚገኝ ሲሆን በስፖርት የተገነባ አዕምሮ እና አካል ያለው ሰራተኛ በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ላይ እንዲሁም ለተቋማዊ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ኤጀንሲው የሰራተኞችን ጤና ለመጠበቅ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/
ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/
ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320
24/05/2026
CRRSA፡ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የሚከሰቱ ወሳኝ ኩነቶችን በመመዝገብ፣ ለሀገራዊ ፖሊሲ ቀረጻ እና ለስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት የሚሆኑ መረጃዎችን ያደራጃል።
ስለሆነም የሚከተሉትን ወሳኝ ኩነቶች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስመዝገብ እንዳለበት አውቆ በወቅቱ ማስመዝገብ አለበት፡፡
የጊዜ ገደቦች፦
ልደት (ህፃን ሲወለድ) በተወለደ በ 90 ቀናት ውስጥ
ሞት ፡ በተከሰተ በ 30 ቀናት ውስጥ ጋብቻ፣ ፍች ጉዲፈቻ እንደተፈፀመ በ 30 ቀናት ውስጥ “የሚከሰቱ ወሳኝ ኩነቶችን በወቅቱ ማስመዝገብ ዘመናዊነት ነው’’!
ቢሆንም በተሳሳተ መልኩ ያልተፃፈ ህግ እያነበቡ የተሳሳተ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን አረጋግጠናል ስለሆነም ተገልጋዮች ይህን ከተሳሳተ መረጃ ራሱን መጠበቅ አለበት በአሁኑ ወቅት ምንም ቅጣት የሌለ መሆኑን እናሳውቃለን::
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ስለ ምዝገባው ሂደት ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በነጻ የስልክ መስመር 7533 ላይ ይደውሉልን።
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et ወይም id.et
ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ (TikTok): https://www.tiktok.com/
ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/
ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Tunisia Avenue, Gulelle Subcity Woreda 8
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 12:30 |
