Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office

Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office

Share

 ለሴቶችና ህጻናት መብት መከበር በትጋት እንሠራለን!!

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 25/11/2022

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሴ/ህ/ማ/ጉ/ፅ/ቤት በ16/03/2015 ዓ.ም "ኑ ቡና እንጠጣ በጋራ ስለ ሴቶችና ህፃናት እናውጋ!" በሚል መሪ ቃል ስለ ህፃናትና ሴቶች ጥቃት ከህፃናት ፓርላማ ጋር ውይይት ተደረገ።

23/11/2022
Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 20/11/2022

"ምቹና ሠላማዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ህፃናት"

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 19/11/2022

"ምቹና ሰላማዊ አትዮጵያ ለሁሉም ህጻናት"በሚል ሃሳብ የአለም ህፃናት ቀን ተከብሮ ዋለ።

አራዳ ህዳር 10/2015ዓ.ም

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በሃገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታና በተለያዩ ዝግጅቶች የአለም የህጻናት ቀን ተከብሮ መዋሉን የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ሴቶች;ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ; የክ/ከተማው አመራሮች የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች; ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ማህበራት እንዲሁም የበዓሉ ባለቤት የሆኑት ህጻናት መድረኩን ታድመው በድምቀት አክብረዋል።

የክ/ከተማው ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ድሪባ ታደሰ በበዓሉ ላይ በመገኘት እንደተናገሩት ህጻናት የነገ የሃገራችን ተስፍና ኢትዮጵያን ተረክበው የሚያስቀጥሉ እንደሆኑና በአካልና በስነ-ልቦና የጎለበተ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ደግሞ በትኩረት እየተሰሩ እንደሆነ የጠቆሙ ሲሆን በተለይ የህጻናትን መብት ከማስጠበቅ ጋር ተያይዞ እንደ አስተዳደር ብዙ ተግባራት ሊሰሩ በዕቅድ ደረጃ የተያዙ እንዳሉም አያይዘው ገልጸዋል።

የህፃናት መብት ተከብሮ አካላቸውና ስነ-ልቦናቸው በተጠበቀ መልኩ ማስቀጠል የምንችልበትን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ በዓል ነው ያሉት የክ/ከተማው ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ እሱባለው የህፃናት ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ በመሆኑ በተመቻቸ መልኩ እንዲቀረጹ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዕለቱ በባህላዊ ውዝዋዜ; በጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደመ ሁኔታ ተከብሯል

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 18/11/2022

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት
በዓለም ለ33ኛ ጊዜ በአገራችን ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን ህዳር 11 ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም አፀደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር የተማሪዎች ፌስቲቫል አካሄደ ::

"ምቹና ሰላማዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ህፃናት"
ህዳር 2015 ዓ.ም
አድስ አበባ :ኢትዮጵያ

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 18/11/2022

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት
በዓለም ለ33ኛ ጊዜ በአገራችን ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን ህዳር 11 ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፓናል ዉይይት አካሄደ ::

"ምቹና ሰላማዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ህፃናት"
ህዳር 2015 ዓ.ም
አድስ አበባ :ኢትዮጵያ

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 24/06/2022

በሕጻናት ፓርላማ ምስረታና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ለህፃናት ፓርላማ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 17 2014 ዓ.ም የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የህጻናት ፓርላማ ምስረታ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ለስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት የቡድን መሪ አቶ በላይ አክሎ ሲሆኑ የአገር ተረካቢ ህጻናትን አቅማቸውን መገንባት አስፈላጊ ነው ብለዋል
ስልጠናውን የሰጡት በሴቶችና ህጻናት ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ ወይንሸት ተገኝ የህጻናት ፓርላማ ለመመስረት በወጣው ደንብ አሰራርና አደረጃጀት ቌሚ ኮሚቴ አደረጃጀት ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ስልጠነው አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የህጽናት ፓርላማ አባላትም በክረምት በጎ ፈቃድ ችግረኛ ህጻናት ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ሴቶችና ህጻናት እና የወረዳው ምክር ቤት እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል
የምክር ቤቱ ጸሐፉ አቶ ዮሐንስ ኩማ ህጻናት መብታቸው እንዲያውቁ የተሰጠው ስልጠና አበረታች መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን ለሰጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል
ሰኔ 2014 ዓ.ም.

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 14/06/2022

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በቀን 07/10/2014 ዓ/ም በህፃናት ላይ የሚፈፀም ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ለ32ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበረውን ሰኔ 9 የአፍሪካ የህፃናት ቀን ምክንያት በማድረግ የፓናል ዉይይት አካሂዷል።
በበዓሉ ላይ ፖሊሶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ሁሉም ህብረተሰብ በጋራ በመተባበር በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጋራ ልንከላከል ይገባል የሚል የጋራ ሀሳብ በመያዝ ፓናሉ ተጠናቋል"!!
ሰኔ 7/2014 ዓ/ም

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 09/06/2022

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከመስከረም አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር በቀን 02/10/2014 ዓ/ም በህፃናት ላይ የሚፈፀም ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ለ32ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበረውን ሰኔ 9 የአፍሪካ የህፃናት ቀን እጅግ በደማቅ ሁኔታ አክብሮ ዉሏል።
በበዓሉ ላይ የጥያቄና መልስ ዉድድርን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራም እየተስተናገዱ ሲሆን በዉድድሩ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች በት/ቤቱ ር/መምህር ና መምህር የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በዚህ አጋጣሚ የመስከረም አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና ይድረሳችሁ!!
"በህፃናት ላይ የሚፈፀም ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጋራ እንከላከል"!!
ሰኔ 2/10/2014ዓ/ም

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 04/06/2022

"የደግነት ጥግ"!!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ራስ አምባ ሆቴል ፊት ለፊት በታችኛው አስፓልት በኩል እጅግ ቅንና ታዋቂ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ይዞ የተቋቋመው "ሀኪም መካከለኛ ክሊኒክ " ከተቋቋመ ትንሽ ጊዜ ቢሆነውም ከተቋቋበት ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ አቅመ ደካሞች የተለያዩ የሰብዓዊነት ስራዎችን እየሠራ ያለ ድንቅ ክሊኒክ ነው።
በተጨማሪም ከቀን 25/9/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 27/9/2014 ዓ/ም ድረስ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በወረዳው ውስጥ የሚኖሩና የተለየ የጤና ችግር ያለባቸዉና ከፍለው መታከም የማይችሉ ከ65 በላይ ህፃናትን እስከ ሪፈር ድረስ ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን ተወጥተዋል።
በመሆኑም ለተደረገልን ታላቅ ድጋፍ በፅ/ቤታችን ፣ በአስተዳደሩና ድጋፍ በተደረገላቸው ህፃናት ስም ከልብ እናመሠግናለን።
"አገር የምትገነባው ለዛሬዎቹ ህፃናት በምንሰጠው ትኩረት ነው "
ግንቦት 2014 ዓ/ም

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 14/05/2022

የሕጻናት ፓርላማ ጉባኤ ተካሄደ
።።።።።።።።።።።🇪🇹🇪🇹።።።።።።።።።።።።።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ምክር ቤት ከወረዳው ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የህጻናት ፓርላማ መደበኛ ጉባኤ አካሄዱ ።

የምክር ቤቱ ጸሐፊ አቶ ዮሐንስ ኩማ በመክፈቻ ንግግራቸው ህጻናት መብታቸው ተጠብቆ ደህንነታቸው ተረጋግጦና በሃገራዊ እንዲሁም በራሳቸው ጉዳዮች ላይ ተሳታፊነታቸው ጎልብቶ እንዲታይ ምክር ቤቱ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል
የሕጻናት ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሕጻን ምስክር ወንድማገኝ የዘጠኝ ወር ሪፓርት ለአባላቱ ያቀረበ ሲሆን በተሰሩ ስራዎች እና ሊከናወኑ በሚገባው ተግባር ላይ ማብራርያ ሰጥትዋል
አባላቱም ችግረኛ ሕጻናት እንዲረዱ ፣ አካል ጉዳተኞችም ፣እንዲካተቱ ከመጠየቃቸው ባሻገር ምክር ቤቱ የግንንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በስፋት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል

Photos from Arada Sub-City Wereda 08 Women; Children and Social Affair Office's post 21/04/2022
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:29 - 23:00
Tuesday 02:30 - 23:00
Wednesday 02:30 - 23:00
Thursday 02:30 - 23:00
Friday 02:00 - 23:00