15/05/2026
Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን
ህዝብና መንግስትን ማገናኘት፣ተጨባጭ ፣ታማኝ ወቅታዊ ፣ ቀላጣፋና ጠቃሚ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስ ነው ። (በቅንነት follow )አድርጉና እናመሰግናለን 🙏
15/05/2026
15/05/2026
''የአገልግሎት እርካታ በተግባር የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ተገልጋዮች ምስክርነት!"
የ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የሚገኘው የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎቶች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በቦታው በመገኘት ምልከታና የሕዝብ አስተያየት አሰባስቧል።
ጽ/ ቤታችን በጤና ጣቢያው ተገኝተን ከተገልጋዮች ጋር ባደረግነው ቃለ-መጠይቅ፤ ተቋሙ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አበረታችየሆኑ ውጤታማ የህክምና ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አረጋግጠናል።
በዕለቱ ያነጋገርናቸው የጤና ጣቢያው ተገልጋዮች እንደገለጹት፤ በተቋሙ ያለው የታካሚዎችና የተገልጋዮች አያያዝ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም ሕሙማን በወረፋ ሥርዓት ተራቸውን ጠብቀው ያለምንም መንገላታት የሚፈልጉትን የሕክምና አገልግሎት በአግባቡ እያገኙ መሆኑን በደስታ ገልጸዋል። በመሆኑም ይህ አርአያነት ያለው ቀልጣፋ አሠራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎታቸውን አጋርተዋል።
ጽ/ቤታችን በምልከታው እንዳረጋገጠው፤ ከቀልጣፋው የአገልግሎት አሰጣጥ ባሻገር የጤና ጣቢያው አጠቃላይ የግቢ ምቹ ሁኔታ፣ ንጽህና፣ የታካሚዎች ማረፊያ ቦታዎችና አያያዝ ለሕክምና ምቹና ሳቢ በሆነ መልኩ የተደራጀ ነው።
የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ አመራሮችና መላው የጤና ባለሙያዎች ለሕዝብ እርካታ እያሳዩት ላለው ቁርጠኝነት እያመሰገንን፣ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤትም መሰል ሕዝብ ተኮር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ወደ ማኅበረሰቡ ተደራሽ ማድረጉን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
"ለተገልጋይ እርካታ በጋራ እንሠራለን!" የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት
#ወረዳ04 #የካ
15/05/2026
የአገልግሎት አሰጣጥ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲሁ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የሚሰሩ ስራዎችው ጤታማ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
ግንቦት 7/2018 የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን
************************************
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የምክር ቤት ጽ/ቤት የዘርፍ ኮሚቴዎች ከኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት በጋራ በመሆን በህብረተሰቡ ዘንድ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ መድረኮች ማለትም በ2018 በጀት አመት በ1ኛ ዙር በእንጠየቅ መድረክ እንዲሁም በምክር ቤት ፣ በህዝብ በተለያዩ መድረኮች የተነሱ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ናየአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መፈታትናአለመፈታቸውን እንዲሁም እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ያሉበትን ደረጃ በአካል ወርዶ በመስክ ምልከታ የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል ። በምልከታው ቀደም ሲል ከተነሱ ችግሮች መካከል ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር የማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት አሰጣጥ፣የወጣቶች ናየሴቶች የስራ እድል ጥያቄ ፣የኑሮ ውድነትና የዋጋ ማረጋጋት ፤የምርት አቅርቦት ጥራት፣ ተደራሽነት፣የዋጋ ሁኔታ፣ከመሰረተ ልማት ጋረ በተያያዘ የተነሱና የሚስተዋሉ ችግሮች በውጤታማነት የተከናወኑ መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራዎች የተሰራ ሲሆን ከተነሱ ችግሮች በውጤታማነት የተሰሩ ስራዎች ቢኖርም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ና መልስ ያላገኙ ችግሮች በአጭር ጊዜ እንዲፈቱ ተቋማት ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው እና ውጤት ተኮር ክትትልና ድጋፍ እንሚደረግ ናየህዝብ እርካታ የሚያረጋግጡ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
''የህዝብ ጥያቄዎችን ለቅሞ በመያዝ ምላሽ እንዲያገኙማድረግ ቀዳሚ ስራች ነው''።
# #የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት
#ወረዳ04 #የካ
14/05/2026
በምርጫ ብቻ !
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 17:00 |
| Sunday | 08:00 - 17:00 |
