የፓስፖርት እድሳትን እና አዲስ ፓስፖርት ማውጣትን በሚመለከት በውስጥ መልእክት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እየደረሱን በመሆኑ ጠቅለል አድርገን ምላሽ ለመስጠት ወደናል፡፡
አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
የሚያስፈልጉት የልደት ምስክር ወረቀት እና የአገልግሎት ጊዜው ያላለቀ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ ሲሆኑ ምንም አይነት ተጨማሪ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡የሚወስደው ጊዜ ከአመለከቱ በኋላ 2 ወር፡፡
ሆኖም በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ፓስፖርት በአስቸኳይ ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዩን አስቸኳይነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ፡፡
ጉዳዩ የስራ ከሆነ ከመስሪያቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ እና የመስሪያ ቤቱ መታወቂያ
ዲቪ
የህክምና ወረቀት(ሪፈር)
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር መኖሪያ ፍቃድ
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር የስራ ፍቃድ
የኢምባሲ ቀጠሮ
ተመላላሽ መንገደኞች ሆነው ፓስፖርት ገፁ ያለቀባቸው ፓስፖርቱን ይዞ መቅረብ
የአለም አቀፍ ድርጅቶች
ጊዜ ያለው የባህረኞች መታወቂያ (ሲማንቡክ)
ሆነው የሁሉም አገልግሎቶች አከፋፈል ሁኔታ እንደአገልግሎቶ የተለያየ ነው፡፡
ለፓስፖርት እድሳት
የቀበሌ መታወቂያ እና ፓስፖርት ኮፒ
የጠፋ ፓስፖርት የቀበሌ መታወቂያ እና የፖሊስ ማስረጃ
ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ከቀረበ አገልግሎቱን የማግኘት ሙሉ መብት እንዳለው እየገለፅን በአገልግሎታችን ላይ ለሚኖራችሁ አስተያየትም ሆነ ቅሬት በውስጥ መልእክታችን (inbox) እንድታደርሱን እንጠይቃለን
FDRE Immigration Nationality And Vital Events Agency
official page of FDRE INVEA
11/09/2019
02/09/2019
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አተገባበር ላይ ለመስራት በታሰበው ዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ
ዛሬ ነሀሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከተባባሪ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመስራት ባሰበው አጠቃላይ የዳሰሳ ጥናት (comprehensive assessment) ላይ መክሯል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ላይ ዳሰሳዊ ጥናት የመስራት አስፈላጊነትን የሚያብራራ እና ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተሞክሮ የተቀመረ መወያያ ፅሁፍ እንዲሁም የፓኪስታን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ተሞክሮን የሚያሳይ ፅሁፍ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች በተወከሉ አቅራቢዎች ለውይይት የቀረበ ሲሆን የዳሰሳ ጥናቱን ምንነት እና በምን ሁኔታ ለማካሄድ እንደታሰበ የሚያመላክት ፅሁፍ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክቶር አቶ ሙጂብ ጀማል ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ የውይይት መድረኩ ከተለያዩ ተባባሪ እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲዎች የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎችን ተሳታፊ አድርጓል፡፡
19/08/2019
የኤጀንሲው ሰራተኞች በየወሩ የመስሪያ ቤታቸውን ጊቢ እና አካባቢ ሊያፀዱ ነው
የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች የስራ ቦታቸውን እና አካባቢያቸውን ነሀሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም አፅድተዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል እንዳሉት የአካባቢ ፅዳት በአንድ ቀን ብቻ የሚጠናቀቅ ተግባር ባለመሆኑ ምክንያት የኤጀንሲው አመራሮች እና ሰራተኞች በየወሩ የመስሪያ ቤቱን ጊቢ እና አካባቢ ለመፅዳት እንደተስማሙ ገልፀዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Website
Address
Infront Of Tikur Anbesa Secondary School
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:00 |
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |
