Addis Ababa City Government Bureau of Justice
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa City Government Bureau of Justice, Government Organization, Mexico, Addis Ababa.
04/06/2026
የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም
04/06/2026
04/06/2026
በሴቶች መብት እና ሴቶች ላይ በሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ህግ ስርጸት እና ምክር መስጠት ዳሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮች ተሳትፈመዋል፡፡
በወቅቱ የፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቸቶ አሰፋ መብራቴ መምህራን በሴቶች መብት እና ሴቶች ላይ በሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት ህጉ ምን ይደነግጋል የሚለውን አውቆ ነገ ሃገር የሚረከቡ ተማሪዎች ባለማወቅ የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ግንዛቤ እንዲፈጥሩላቸው የተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች የስልጠናውን አላማ ለተፈለገው አላማ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በአዲስ አበባ መምራን ማህበር ተጠሪ ወይዘሮ እየሩሳሌም ብዙነህ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርጸት ዳይሬክቶሬት በነባር እና አዳዲስ ህጎች ዙሪያ ለማህበሩ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ፈጠራ መስራቱን ገልጸው በማመስገን ዛሬም የሴቶችን ጥቃት አስመልክቶ በተሰጠው ስልጠና የመምህራን ማህበር አመራሮች ለተማሪዎቻቸው ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ዐቃቢ መሰረት ጸሃይ ስልጠናውን ሲሰጡ በኢትዮጲያ ህገመንግስት አንቀጽ 35 የተደነገጉትን የሴቶች መብቶች ፣በኢትዮጲያ አሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ፣በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲሱ የመንግስት ሰራቶች አዋጅ 87/2017 ስለ ትንኮሳ እና አዎንታዊ ድጋፍ ፣በኢትዮጲያ አዲሱ የወንጀል ህግ የሴቶችን ጥቃት በተመለከተ እንዲሁም የቤተሰብ ህጉ ከአለም አቀፍ ስምነቶች ጋር በምነጻጸር የተብራራ ሲሆን ሴቶችን አስመልክቶ የተደረጉ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተወስተዋል፡፡
03/06/2026
የወርሀ ሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
03/06/2026
“የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል” - ኡሁሩ ኬንያታ
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር የግምገማ ውጤት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ባሳዩት ድንቅ የሆነ አፈጻጸም በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።
“ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ በቁርጠኝነት ለመምረጥ ተሰልፈዋል፤ ይህን ታላቅ ሁነት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ተመልክተነዋል፤ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የታዘብነው ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ሲሉ አጠቃላይ ሁኔታውን ገልጸውታል።
“ኢትዮጵያውያን ታሪክ ይሠራሉ፤ ቀኝ ገዢዎችን በጋራ ተዋግተዋል፤ ይህም በአፍሪካ ብቸኛ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፤ የአፍሪካ የነፃነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ቀጠሮ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የምርጫውን ታማኝነት እና ዴሞክራሲያዊነት ስንከታተል ነበር ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ የሠራው ሥራ መራጮች ሳይደናገሩ ድምፅ እንዲሰጡ እንዳስቻለ አንሥተዋል።
በምርጫው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት በነጻነት ሲከታተሉ እንደነበር ጠቁመው፣ “በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለውን ታላቅ ቁርጠኝነት የታዘብንበት ነበር” ብለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Mexico
Addis Ababa
15052
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |
