የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency

Share

@feeding agency

14/04/2025

ማሳሰቢያ
ቀን 6/8/2017 ዓ.ም

👉ውድ የኤጀንሲያችን ማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ቀደም ብሎ ሲጠቀምበት የነበረውን ማህበራዊ ሚዲያ የቀየረ በመሆኑ እና ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ማንኛውንም መረጃ የማንለቅ መሆኑን ፣ ቢለቀቅ የኤጀንሲው አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ።

የኤጀንሲውን አዲሱ ማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገፅ ከታች የተቀመጠላችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ታማኝ፣ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት የኤጀንሲውን ማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇👇👇

ፌስቡክ :https://www.facebook.com/61575251932855/posts/122094478412841731/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ቴሌግራም:https://t.me/feedingagency8

ቲክቶክ:http://tiktok.com/.agency

ዩቲዩብ:https://youtube.com/?si=QyoZiayxIloRxa5j

ኢንስታግራም:https://www.instagram.com/reel/DIXXS2EoUTA/?igsh=NTc4MTIwNjQ2YQ==

12/04/2025

ማሳሰቢያ :- ውድ የኤጀንሲው ሰራተኞች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች በቅድሚያ ለምታደርጉልን አስተያየትና ጥቆማ እያመሰገን ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተቀመጠላችህ ማስፈንጠሪያ/link አድሱን የኤጀንሲው ማህበራዊ ድረ ገፅ እየገባችሁ የቀደመ ሚናችሁን እንድትወጡ ስንል እናሳስባለን።

https://www.facebook.com/61575251932855/posts/122094478412841731/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

https://t.me/feedingagency8

https://youtube.com/?si=QyoZiayxIloRxa5j

tiktok.com/.agency

https://www.instagram.com/reel/DIXXS2EoUTA/?igsh=NTc4MTIwNjQ2YQ==

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 12/04/2025

📝ኤጀንሲው የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸም ገመገመ!!

ምገባ ኤጀንሲ -ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸም የኤጀንሲው አመራርሮች፣ አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሪፓርቱን ያቀረቡት የተቋሙ እቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ገ/ፃድቅ ኤጀንሲው በዘጠኝ ወር የሰራቸውን ዝርዝር ተግባራት በሰነድ በተደገፈ ሪፓርት አቅርበዋል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ ተቋሙ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ፣ የዕለት ጉርስ ያጡ ዜጎችን በቀን አንድ ጊዜ በተስፋ ብረሃን የምገባ ማዕከላት መመገብ፣በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ ውስጥ በሚገኙ በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ(ቁርስና ምሳ) ምገባ አገልግሎት እንዲሁም የትምህርት ግበዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው የቀረበው ሪፓርት የተሻለ አፈፃፅም የታየበት መሆኑንና በቀሩት ሶስት ወራት በልዩ ሁኔታ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በመድረኩ የኤጀንሲው ሰራተኞች በበኩላቸው የቀረበው ሪፓርት የተሻለ መሆኑን አንስተው በጥንካሬ የታዩ ስራዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክረው እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በኤጀንሲው ሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኤጀንሲው አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ማሳሰቢያ :- ውድ የኤጀንሲው ሰራተኞች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች በቅድሚያ ለምታደርጉልን አስተያየትና ጥቆማ እያመሰገን ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተቀመጠላችህ ማስፈንጠሪያ/link አድሱን የኤጀንሲው ማህበራዊ ድረ ገፅ እየገባችሁ የቀደመ ሚናችሁን እንድትወጡ ስንል እናሳስባለን።

https://www.facebook.com/61575251932855/posts/122094478412841731/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

https://t.me/feedingagency8

https://youtube.com/?si=QyoZiayxIloRxa5j

tiktok.com/.agency
"ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ"!!

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 09/04/2025

👉 የኤጀንሲው የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙ ተመዘነ፡፡

ምገባ ኤጀንሲ ፣መጋቢት 30/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ፣የፕላንና ልማት ኮሚሽን እና የከንቲባ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በምገባ ኤጀንሲ በመገኘት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት ውስጥ በአዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት በምገባ አገልግሎት እና በአግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በተስፋ ብርሀን እና በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እንዲሁም የተማሪዎች ግብዓት አቅርቦት በወጥነትና በፍትሀዊነት ተደራሽ መሆናቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ በዕቅድና በተደራጀ መንገድ እንደተሰራና የሚታዩ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ተጋለጭነት ለመቀነስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ እተሰራ መሆኑን በማስረዳት ምዘናው መከናወኑ ኤጀንሲው እያከናወነ የሚገኘውን ሰው ተኮር ተግባር ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርገው አስረድተዋል ።

የምዘና ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ጉታ እንደገለጹት ኤጀንሲው በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር በሚገባ መሰራቱን እና ውጤታማ መሆኑን በማየት በ6ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ያሉ ክፍተቶችን እየፈቱ ለመሄድ ፣ ኤጀንሲው ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚያስችል ፣ ሰነዶችን መሰረት ያደረገ ምዝና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የምዘናው ኮሚቴ ኤጀንሲው በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት በትምህርት ቤቶች፣ በተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት በምገባው ዘርፍ እና የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ስራዎች መረጃ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ በአግባቡ ተሰንደው እና ተደራጅተው የቀረቡበት አግባብ በጣም ጥሩ መሆኑን ገልጸው በምዘናው ወቅት የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ማስተካከል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

" ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ"!

08/04/2025

👉ኤጀንሲው የህይወት ክህሎት ስልጠና እንደሰጠ ገለጸ፡፡

ምገባ ኤጀንሲ ፡-መጋቢት 30/2017 ዓ/ም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት በተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል ለ165 ተመጋቢዎች የፍላጎት ልየታ እና የህይወት ክህሎት ስልጠና እንደተሰጣቸው ገልጿል፡፡

የምገባ ኤጀንሲ የምገባ ማዕከላት አገልግሎት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ጴጥሮስ በተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከል ከ37ሺ በላይ የዕለት ጉርስ የሌላቸው አረጋውያን፣አካል ጉዳተኞች፣የአእምሮ ህሙማን ፣ የሀገር ባለውለታዎች እና መሰል የማህበረሰብ ክፍሎችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ፣የህይወት ክህሎት እና የማማከር አገልግሎት መስጠት እና የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ማመቻቸት ዋንኛ ተግባሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው በ2017 በጀት ዓመት በተስፋ ብርሐን ምገባ ማዕከላት የዕለት ጉርስ የሌላቸው እና መስራት የሚችሉ 165 ተመጋቢዎችን በመለየት የህይወት የክህሎት ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ 65 ተመጋቢዎች የስራና ክህሎት ቢሮ በተለያዩ ተቋማት የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡

"ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ "!

03/04/2025

📝ኤጀንሲው የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰብ መቻሉን ገለፀ !!
ምገባ ኤጀንሲ ፡-መጋቢት 25/2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በ22ቱም ተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት ከ37ሺ በላይ የዕለት ጉርስ ከሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የ1446ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በጋራ እና በአብሮነት ለማክበር ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ሀብት ማሰባሰቡን ገልጿል፡፡

የምገባ ኤጀንሲ የፕሮጀክት ዝግጅት ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መራጊያው ተበጀ የኢዲ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ተመጋቢዎች ጋር በጋራ ለማክበር ከፌደራል ፤ከማዕከል እና ከክፍለ ከተማ ተቋማት እንዲሁም በተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት በቋሚነት ከሚመግቡ ባለ ሀብቶች ድጋፍ በመጠየቅ የበሬ፣ የበግ ፣ የፍየል ፣ የዘይት ፣የዱቄት እና ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በአይነት መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት 200 ለሚሆኑ ተመጋቢዎች የዘይት ፣የዱቄት እና 10 ለሚሆኑ ተመጋቢዎች ለእያንዳንዳቸው የአምስት አምስት ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር መካሄዱንም ተናግረዋል።

የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በየማዕከላቱ ለእምነቱ ተከታዮች የበሬ፣የበግ እና የፍየል እርድ የተከናወነ መሆኑን ገልፀው በሁሉም ምገባ ማዕከላት ሙሉ ምግብ በቡፌ ፣የመደበኛ ምገባ ዝግጅት ፣የዳቦ ና የቡና የሰረሞኒ እና ዲኮር በማዘጋጀት በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ማክበር እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም መጪው የትንሳኤ በዓልን በድምቀት ለማክበር ድጋፍ አድራጊ ተቋማትን እና ባለሀብቶችን የማነጋገር እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

"ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ"!

03/04/2025

📝ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ለከፋ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን አራጋውያንና ለሀገር ባለውለታዎች የማዕድ ማጋራት አከናውነዋል ።
ምገባ ኤጀንሲ መጋቢት 25/2017 ዓ.ም

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 01/04/2025

👉ኤጀንሲው በሰው ሃይል ዝውውርና ምደባ ዙሪያ ለሰራተኞች ግንዛቤ ሰጠ

ምገባ ኤጀንሲ መጋቢት 23 ፤2017 ዓ.ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ ልዪ የዝውውር፣ ምደባና ምጥጥን ደንብ ቁጥር 179/2017 ዙሪያ የኤጀንሲው ሰራተኞች ግንዛቤ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰው ሃይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘላለም ጌትነት እንደገለፁት በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ እየታየ ያለውን የአፈፃፀም ክፍተትና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ እና ተቋማት የተመጣጠነ የሰው ሃይል እንዲኖራቸው ፣ቀልጣፋና ጥራት ያለው ውጤታማ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር እና ስራና ሰራተኛን በማገናኘት የተቋማትን ውጤታማነት ለማሳደግ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሃይል ስምሪቱን ለማመጣጠን እንዲያስችል ከስልሳ በመቶ በላይ የሰው ሃይል ከተሟላላቸው ዝቅተኛ የሰው ሃይል ወዳላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች በልዪ ሁኔታ በማዘዋወር ወይም በመመደብ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር የከተማ አስተዳደሩ ለመንግስት ሰራተኞች ባወጣው አዋጅ 56/2010 አንቀፅ 97 ንዑስ አጥን ንቀፅ 1 ደንብ ዙሪያ ለኤጀንሲው ደጋፊ የስራ ሂደት ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በዝውውር ወይም በምደባ ሂደቱ ሰራተኛው ለሚያቀርበው ማንኛውም አይነት ተገቢነት ያለው ጥያቄ ወይም ቅሬታ ለማስተናገድ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 30/03/2025

👉1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በድምቀት ተከበረ

ምገባ ኤጀንሲ -መጋቢት 21/2017 ዓ.ም.
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሁሉም ተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት በድምቀት ማክበር ተችሏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አበቤ በተስፋ ምገባ ማዕከል ቁጥር -2 በመገኘት ከዓቅመ ደካሞች፣ ከሀገር ባለውለታዎች ጋር ማዕድ ያጋሩ ሲሆን ፣በዓሉ የሰላም፣ የደስታ ፣የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በባዕሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኤጀንሲው አመራሮች፣ የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት መጋቢ ባለሀብቶች ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራርሮች፣የኤጀንሲው ሰራተኞች በሁሉም ተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል ።

29/03/2025

👉ምገባ ኤጀንሲ -መጋቢት-20/2017ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ !! አደረሰን እያለሁ !! እያለ በዓሉ የሰላም የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል ።

በነገው ዕለትም በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ከተመጋቢዎች ጋር በጋራ በዓሉን የምናከብር መሆኑን እየገለፅኩኝ ፣ ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ሁሌም ከጎናችን ለምትሆኑት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ባለሀብቶች በኤጀንሲው እና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።

ክብርት ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 28/03/2025

👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የአፍጥር መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

ምገባ ኤጀንሲ -መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆኑ የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል ቁጥር -9 ተመጋቢዎች ጋር በጋራ በመሆን የአፍጥር ፕርግራም አከናውኗል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ስንታየሁ ማሞ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የአፍጥር ፕሮግራምን በጋራ ማክበራችን የሀይማኖት መቻቻል እና የመከባበር እሴቶችን ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነ በመግለፅ በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችም ኤጀንሲው አቅሙ በፈቀደ መጠን ከማህበረሰብ ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። አያይዘውም ለበዓል ዋዜማ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ::

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ስንታየሁ ማሞ ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ጥሩወርቅ አንዳርጌ ፣ የወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅራአዲስ አባይነህ ፣የኤጀንሲው ሰራተኞች ተገኝተዋል::

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጅንሲ-Addis Ababa City Feeding Agency's post 27/03/2025

👉የትምህርት ውጤታማነትን እያረጋገጠ ያለ ተግባር ...

ምገባ ኤጀንሲ ፡-መጋቢት 18/2017 ዓ/ም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ የደጃች በቀለ ወያ ቅድመ አንደኛ እና የተስፋ ኮከብ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ዮናስ አደራጀው በትምህርት ቤቱ 1865 ተማሪዎች በመማር ላይ እንደሚገኙ ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ የደብተርና የደንብ ልብስ ተደራሽ በማድረጉ የወላጆችን ኢኮኖሚያዊ ችግር የቀረፈ እና የመማር ማስተማሩን ስርዓት ውጤታማ ያደረገ ፣ ተማሪዎችን ከችግር እና ከሰቀቀን የታደገ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር በተማሪዎች ላይ አካላዊ ፣አእምሮዊ እና ስነ ልቦናዊ ለውጥ ያመጣ ፣ የተማሪዎችን መጠነ መድገምና የማቋረጥ ችግር የቀረፍ እንዲሁም በተማሪዎች ላይ አብሮነትን፣ፍቅርን እና መተሳሰብን እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡

የትምሀርት ቤቱ መጋቢ እናት አስተባባሪ ወ/ሮ ማርታ ግርማ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የምገባውን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት እና በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸው ፣ የምግብ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችም ምግብ በሜኑ እና በስታንዳርድ መሠረት መዘጋጀቱን በመገምገም ፤ከተማሪዎች አስተያየት በመሰብሰብ እና ግብረ መልስ በመስጠት በወቅቱ ጥራት ያለው ምግብ እንዲያቀርቡ የማድረግ ተግባር እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

"ከነዋሪዎች እፎይታ እስከ ብቁ ትውልድ ግንባታ"

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa