Ethiopian Health Insurance Service

Call Directions Website

Ethiopian Health Insurance Service to promote Health Insurance in Ethiopia Ethiopian Health Insurance Service

የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድኅን ህብረተሰቡ በህክምና ወጪ ምክንያት ለአልጋ ቁራኛነት እንዳይዳረግ ማድረጉ ተገለጸ20/01/2019 ዓም ኢጤመአየማኅበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን  ከተጀመረበት ጊዜ...
30/09/2026

የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድኅን ህብረተሰቡ በህክምና ወጪ ምክንያት ለአልጋ ቁራኛነት እንዳይዳረግ ማድረጉ ተገለጸ
20/01/2019 ዓም ኢጤመአ

የማኅበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እየሰጠ ባለው አጠቃላይ የአገልግሎት ዘርፍ ህብረተሰቡ ከአቅሙ በላይ በሆነ ከፍተኛ የህክምና ወጪ ምክንያት ታሞ አልጋ ላይ እንዳይቀርና ለአልጋ ቁራኛነት እንዳይዳረግ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉ ተገለጸ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የነቀምቴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተመስገን ምሬሳ ዋጭላ እንደገለጹት፤ ሥርዓቱ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን የማህበረሰብ ክፍል ከድንገተኛ የህክምና ወጪ ስጋት ነፃ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ምክትል ከንቲባው አክለው እንደገለጹት፤ በነቀምቴ ከተማ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት በይፋ ሲጀመር በዕቅድ የተያዘው ሽፋን የከተማዋን ነዋሪ 50 በመቶ ያህል አባል ማድረግ ነበር። ሆኖም ግን ከላይ እስከ ታች ባለው የመንግሥት አመራር ቁርጠኝነት፣ በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት እና ህብረተሰቡ የአገልግሎቱን አወንታዊ ውጤት በተግባር በመረዳቱ በ2018 ዓ.ም የአባላቱን ቁጥር እስከ 107 በመቶ ማድረስ ተችሏል። ይህም ዕቅድን ከመቶ በመቶ በላይ በማሳካት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬት መሆኑን አስረድተዋል።

የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ህብረተሰቡ ለድንገተኛ ህመም ከአቅም በላይ የሆነ የህክምና ወጪ ሳያወጣ፣ የነበረውን ሀብትና ንብረት ለመሸጥ ሳይገደድ ወይም አላስፈላጊ ለሆነ ብድርና ዕዳ ሳይዳረግ ሙሉ ቤተሰቡን ማከም የሚያስችለው አስተማማኝ ዋስትና ነው። አባላት ከመጀመሪያ ደረጃ የጤና ጣቢያዎች አንስቶ እስከ ከፍተኛ ሪፈራል ሆስፒታሎች ድረስ ጥራት ያለው፣ ፍትሐዊና ፈጣን የህክምና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸው የሥርዓቱን ጠቀሜታ የጎላ እንደሚያደርገው ምክትል ከንቲባው አመላክተዋል።

በሌላ በኩል በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በሚፈጠሩ የአቅርቦት ክፍተቶች፣ በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት እንዲሁም በሕብረተሰቡ በሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ላይ በየደረጃው ባለው አመራርና በቦርድ አስተዳደር በቅንጅት ወቅትታዊ ግምገማዎች እየተደረጉ አፋጣኝ መፍትሔ እየተሰጠ እንደሚገኝ አቶ ተመስገን ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሚታዩ መዋቅራዊና የአቅርቦት ክፍተቶችን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት እስከ ጤና ሚኒስቴር እና በየደረጃው ካሉ አጋር አካላት ጋር የቅርብ ውይይትና ትብብር እየተደረገ ይገኛል።

በመጨረሻም ምክትል ከንቲባው ባስተላለፉት መልእክት፤ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን በኢመደበኛው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው፤ በተመሳሳይ መልኩ መደበኛ ገቢ ያላቸውን የመንግሥትና የግል ድርጅት ሰራተኞች ተጠቃሚ የሚያደርገው የማህበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓትም በተቻለ ፍጥነት ተተግብሮ ሙሉ ዜጎችን የጤና ዋስትና ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

30/09/2026
አገልግሎቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ጋር በኦዲት ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ19/01/2019 ዓም ኢጤመአየኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከአዲስ አበባ ከነማ ፋርማሲዎ...
29/09/2026

አገልግሎቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ጋር በኦዲት ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ
19/01/2019 ዓም ኢጤመአ
የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከአዲስ አበባ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅትና ከሜድኮ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ ከመስከረም እስከ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በከነማ ፋርማሲዎች ላይ በተከናወነው የኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጠዓመ አረዶም እንደገለጹት፣ የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ መድሃኒት በማቅረብ የጤናውን ዘርፍ ግቦች በማሳካት ረገድ ትልቅ አበርክቶ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በከነማ ፋርማሲዎች ላይ በተከናወነው የኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት መደረጉ ቀደም ሲል የታዩ ክፈተቶችን ለማስተካከል ብቻ ሳይሆን በቀጣይም ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ፍትሐዊ የመድሀኒት አቅርቦትን ለማረጋገጥና አሰራሩን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ የተጀመረውን ስራ ለማጠናከር ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ብርቱካን አህመድ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 53 ከነማ ፋርማሲዎች መኖራቸውን ጠቁመው፣ ከፋርማሲዎቹ ተጠቃሚዎች መካከል 63 በመቶ በላይ የሚሆኑት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አስረድዋል።
በኦዲት ግኝቱ ላይ ውይይት መደረጉ የማስተካከያ እርምጃዎችን በፍጥነት ለመውሰድ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የጋራ አሰራርንና ትብብርን ለማጠናከርና የስጋት አስተዳደርን ለማሻሻል ትልቅ ጥቅም እንዳለው ስራ አስኪያጇ ገልጸዋል።
የአገልግሎቱ የክሌም ማነጅመንት መሪ ስራ አሰፈጻሚ ዶክተር ሀሊማ አባተ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የመድሀኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን በማሳለጥ ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ጠቁመው፣ ድርጅቱ ትክክለኛ የክሌም ጥያቄ፣ በየደረጃው የተጣራ መረጃ በማቅረብ ከአገልግሎቱ ጋር በቅንጅትና በትብብር በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይገባል ብለዋል።
በውይይት መድረኩ አጠቃላይ የጤና መድህን ስርዓት በኢትዮጵያ፣ የክሌም ማኔጅመንት መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች እንዲሁም በከነማ ፋርማሲዎች ላይ በተከናወነው የኦዲት ግኝት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት መድረኩ ተጠናቋል። "Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን 84 በመቶ ማድረሱን አስታወቀ19/01/2019 ዓም ኢጤመአበኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት ...
29/09/2026

የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን 84 በመቶ ማድረሱን አስታወቀ
19/01/2019 ዓም ኢጤመአ

በኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት በበጀት ዓመቱ አጋጥመውት የነበሩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ከዞንና ከወረዳ አመራሮች ጋር በጋራና በቅንጅት በመስራቱ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የአባላት ምጣኔን 84 በመቶ ማድረስ መቻሉን አስታወቀ።

የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፉፋ አያና እንደገለጹት፤ በክላስተር ጽሕፈት ቤቱ ሥር በሚገኙት ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የሚገኙ ወረዳዎችን አፈጻጸም መቶ በመቶ በማድረስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማስፋት ተችሏል።
ኃላፊው በሰጡት ማብራሪያ፣ በ2018 በጀት ዓመት የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላትን ቁጥር 1 ሚሊዮን አምስት ለማድረስ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቶ እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም ግን በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የተሞላበት ቅንጅታዊ ሥራ 844 ሺህ 942 አባላትን ማፍራት ተችሏል። ይህም የታቀደውን 84 በመቶ ማሳካት ያስቻለ አፈጻጸም መሆኑ ገልጻዋል።

ከአባላት ምጣኔ በተጨማሪም የነባር አባላት የዕድሳት ምጣኔ 96 በመቶ ደርሷል፤ ከአባላትና የተሰበሰበው የመዋጮ ገንዘብ መጠን 1 ቢሊዮን ብር በማድረስ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን አቶ ፉፋ አማላክተዋል፡፡

አቶ ፉፋ አያና አክለው እንደገለጹት፣ ይህ ውጤት ሊመጣ የቻለው በየደረጃው ያለው አመራር ለአገልግሎቱ መስፋፋትና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ያሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት ነው። በተጨማሪም የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎትን የፋይናንስ ዘላቂነት ለማረጋገጥና የህብረተሰቡን እንግልት ለመቀነስ በርካታ የአሰራር ማሻሻያዎች ተደርገዋል። በክላስተሩ ሥር ባሉት 254 ጤና ጣቢያዎች እና 18 ሆስፒታሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲሻሻል ከተደረጉት ሥራዎች በተጨማሪ፡ ህዝቡ ያለእንግልትና በፍጥነት አገልግሎት የሚያገኝበት አሰራር ተዘርግቷል። የፋይናንስ ዘላቂነትንና አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ዞኖች የጋራ ቋት እንዲመሰረት መደረጉን አቶ ፉፋ ገልጻዋል።

የነቀምቴ ክላስተር ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከአምናው የተሻለና የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ አልሞ መነሳቱን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፉፋ አያና ገልጸዋል። በጥብቅ የፋይናንስ ኦዲት አሰራርን በመከተል የሀብት ብክነትን ማስወገድ፤ የአሰራር ስርአቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ እና ከአባላት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) አሰራርን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፤ የቅድመ ቁርጥ ክፍያ (Capitation Payment) ማስፋፋት፡ ከዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር የህብረተሰቡን ቅሬታዎች በፍጥነትና በዘላቂነት መፍታት እንደሆነ አቶ ፉፋ ጠቁመዋል ።

በመጨረሻም በ2019 በጀት ዓመት የታቀዱትን እነዚህን ተግባራት በማሳካት ህብረተሰቡ ከጤና መድኅን አገልግሎት የሚያገኘውን ጠቀሜታ የበለጠ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አቶ ፉፋ አያና የነቀምቴ ክላስተር ጽ/ቤት ኃላፊ ገልጸዋል፡፡"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

ሆስፒታሉ የዞን ፑል አሰራር መዘርጋቱ ለአገልግሎት ቅልጥፍና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስተወቀ18/01/2019 ዓም ኦጤመአየነቀምቴ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አ...
28/09/2026

ሆስፒታሉ የዞን ፑል አሰራር መዘርጋቱ ለአገልግሎት ቅልጥፍና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስተወቀ
18/01/2019 ዓም ኦጤመአ
የነቀምቴ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አሰራርን በማሻሻል ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ማቀላጠፉ ተገለጸ።
የሆስፒታሉ የጤና መድህን አስተባባሪ አቶ ተመስገን ፈይሳ እንደገለጹት፤ የዞን ፑል አሰራር መመስረቱ ለሥራው ቅልጥፍና ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ቀደም ሲል አገልግሎት የሚሰጠው ከእያንዳንዱ ወረዳ ጋር በተናጠል ውል በመፈረም ነበር።
በምዕራብ ወለጋ 22 ወረዳዎች፣ እንዲሁም በምስራቅ ደግሞ 17 ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የነበሩ ሲሆን፣ ውል የሚታሰረው ከእነዚህ አካላት ሁሉ ጋር በመሆኑ ለአገልግሎት ክፍያ በወቅቱ ለማግኘት ከፍተኛ ፈተና ፈጥሮ ነበር። አስተባባሪው ይህንን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ውሉ ከአራት ዞኖች የጤና ጽህፈት ቤቶች ጋር ብቻ መደረጉ የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ እንደቀረፈው አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ለህክምና ባለሙያዎች የማህበራዊ ጤና መድህን መጀመሩ ለሐኪሞች ይበልጥ የሥራ ተነሳሽነትን በመፍጠሩ የተገልጋዮች እርካታ እንዲጨምር አድርጓል። በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ አገልግሎት ከሚያገኙ ተገልጋዮች መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባላት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሆስፒታሉ ከማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህኑ የሚያገኘውን ገንዘብ ለህክምና ግብአቶች ግዢ ስለሚያውለው በመርሃግብሩ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን መቻሉ ተመላክቷል። የነቀምቴ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2012 ዓ.ም. በተወሰኑ ወረዳዎች የጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት፣ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዞኖች መስፋፋት ችሏል።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

በዞኑ  የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ሽፋን 83 በመቶ መድረሱ ተገለጸ18/01/2019 ዓም ኢጤመአበምስራቅ ወለጋ ዞን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ስራ በየጊዜው ...
28/09/2026

በዞኑ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ሽፋን 83 በመቶ መድረሱ ተገለጸ
18/01/2019 ዓም ኢጤመአ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ስራ በየጊዜው እድገት በማሳየት በ2018 በጀት ዓመት 83 በመቶ ማድረስ መቻሉን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ለሜሳ እንደገለጹት፣ የጤና መድህን መርሃ ግብሩ በዞኑ በ2007 ዓመተ ምህረት በሶስት ወረዳዎች ብቻ ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት በዞኑ በሚገኙ 17ቱም ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ማዳረስ ተችሏል።

በተጨማሪም የዞኑን የጤና መድህን አሰራር ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የፑል አሰራርን በተግባር ማዋል በመቻሉ በዞኑ የሚገኙ 97 የጤና ተቋማት የህክምና አገልግሎት ክፍያን በተቀላጠፈ ሁኔታ መክፈል መቻሉን አስረድተዋል።

ዶክተር ለሜሳ አክለውም ከነቀምቴ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ጤና መድህን ክላስተር ጽህፈት ቤት ጋር እንደ አንድ ስታፍ በመቀናጀት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ለተመዘገበው አጠቃላይ ስኬት ይህ የጋራ ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

በዞኑ በተከታታይ በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ነዋሪው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንን ጠቀሜታ እየተረዳ በመምጣቱ መርሀ ግብሩ ሲጀመር ከግንዛቤ እጥረት ጋር ተያይዘው ይከሰቱ የነበሩ ችግሮች በአሁኑ ሰአት በእጅጉ መቀነሳቸውን የዞኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ጨምረው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ባስተላለፉት መልክት በጤና ተቋማት ለሚገኙ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አስተባባሪዎች በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አሰራሮች ላይ ስልጠና ቢሰጥ ይበልጥ ጥሩ መስራት እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።
"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

Address

Nifase Silke Lafto Around Gotera Pepsi , GUAVA Building
Addis Ababa
21254/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health Insurance Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share