03/06/2026
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
02/06/2026
ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በሕዝብ ነፃ ውሳኔና በምርጫ ሂደት ብቻ መሆኑን ያስመሰከረ ታሪካዊ ክስተት ሆኖል። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን በማጠናከር፣ የዜጎች ድምፅ የመጨረሻው ዳኛ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ነዋሪዎች ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።
02/06/2026
ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚመራውን ሕጋዊ መንግሥት ለማቋቋም ያለው ጉጉት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ትልቅ አስረጅ ሆኖ በፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተመዝግቧል።
የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።
02/06/2026
ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!
የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።
በተለይ በአዲስ አበባ ከለሊቱ ጀምሮ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።
የሀገራችን ፖለቲከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
01/06/2026
በብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታና የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሪት ፈዲላ ቢያ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው !!!
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ሉዓላዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ የምርጫ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ!