Ministry of Agriculture - Ethiopia

Ministry of Agriculture - Ethiopia

Share

Ministry of Agriculture

Create a modern and a highly productive agricultural system that uses a more advanced technology which enables the society to get rid of poverty

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 29/05/2026

ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ለአቮካዶ ምርታማነት ዕድገት!

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ሃገራችን ከአቮካዶ ምርት የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

ይህ ፕሮግራም ከሌሎች ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ የልማት ግቦች ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተቀረፀ ሲሆን በዚህም የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የህብረተሰባችንን ኑሮ ለማሻሻል እና የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማሳደግ እንዲሁም ለአግሮ-ኢንዱስትሪ በቂ ጥሬ ዕቃ ለማቅረብ ትልቅ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተቀረፀ ነው።

በዚህም ፕሮግራሙ እየተተገበረ በሚገኝባቸው ክልሎች ያለውን አፈፃፀም በመገምገም ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከክልል ከፍተኛ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ተደርጓል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእርሻ እና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ደሳለኝ ተሻለ እንደተናገሩት፤ ይህ ፕሮግራም ሀገራችን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን ከጀመረችባቸው ዘርፎች አንደኛው ተደርጎ የሚወሰድና በግንባር ቀደምትነት ትኩረት ተሰጥቶት በመንግስት ከፍተኛ በጀት የሚሰራ ስራ ነው።

ብሔራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም ከአረንጓዴ አሻራ፣ ከሌማት ትሩፋት እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ጋር በማቆራኘት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ተደርጎ መቀረፁን አንስተው፣ ሀገራችንም ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን የውጭ ምንዛሬ፣ የስራ እድል ፈጠራና መሰል ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀና ለ15 ዓመት የሚቆይ ፕሮግራም መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር አሊ መሃመድ የአቮካዶ እሴት ሰንሰለት አለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ እይታ፣ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታና ዕድሎች እንዲሁም የሆርቲካልቸር ዘርፍ ለውጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በምግብና ስርዓተ-ምግብ ራሳችንን ለመቻል፣ ለኢንዱስትሪዎች የጥሬ እቃ አቅርቦት እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ አቮካዶ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አማካሪው ባቀረቡት ጽሁፍ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም አጠቃላይ እይታ፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና የወደፊት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች እንዲሁም ገበያ ተኮር የሆነ ክላስተር ላይ የተመሰረተ አቮካዶ ምርትን በተመለከተ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፦ ማቲዎስ ተገኝ

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

29/05/2026

"የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ" የእንስሳት መኖ ልማት ዕድገት!

#ከማምረትበላይ

-------------------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
***
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
***
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
***
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
***
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
***
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
***
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
***
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

29/05/2026

📸 የሳምንቱ የግብርና ፎቶ

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 29/05/2026

የግብርናውን ዘርፍ ለማሻገር የግብርና ሜካናይዜሽን ሚና!

****************

የግብርናውን ዘርፍ ለማሻገር በሚደረገው ርብርብ የግብርና ሜካናይዜሽን የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

መንግስት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ ምርቱን ለገበያ እስከ ማቅረብ ድረስ አርሶአደሮች የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎትን እንዲያገኙ በማድረግ ለዘርፉም ዕድገት አበክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

አርሶአደሮች በቁጠባና ብድር መልክ የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎችን የሚያገኙበት ሁኔታ በማመቻቸቱ በርካታ አርሶአደሮች እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡

የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጡ ከባህላዊ አሰራር ይልቅ በአንድ ሄክታር መሬት የሚገኘውን ምርታማነትን ለማሳደግ ፋይዳው የላቀ ነው፡፡

የአርሶአደሩን ድካም፣ ጊዜ እና የምርት ብክነት በመቀነስ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት የሚቻለው የግብርና ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ሲቻል መሆኑ እሙን ነው፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት በግብርናው ዘርፍ በሚወስዳቸው እርምጃዎች በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ ሲሆን የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ለአብነት ይጠቀሳል፡፡
የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን እንዲገጣጥሙ፣ በሂደትም ወደ ማምረት እንዲገቡ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የግብርና ሜካናይዜሽን ፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የግሉን ዘርፍ አጋርነትን በማሳደግ፣ በሀገር ውስጥ ማምረትና መገጣጠምን በመደገፍ እና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በማቋቋም የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂን ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡

የኩታ ገጠም እርሻ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ መምጣቱም ለግብርና ሜካናይዜሽን መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በመደረጉ የአርሶአደሩ የግብርና ሜካናይዜሽን አጠቃቀም እያደገ እንዲመጣ አድርጎታል፡፡

ለአብነትም በ2012 ዓ.ም 1 ሺህ 316 የነበረውን የትራክተር ቁጥር ወደ 27 ሺህ እንዲሁም የኮምባይነር ቁጥር ከ448 ወደ 8000 ማድረስ ተችሏል፡፡

አዘጋጅ፡- ዮሐንስ ደመቀ

#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
******
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 28/05/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ 5 ሚሊዮን ችግኝ ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ትልቅና ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ አለው፡፡ የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ይበልጥ ለማሳደግ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን አደጋ በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል ሲሆን የአረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ፕሮግራሙ በታቀደና በተቀናጀ መንገድ በትኩረት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች በትኩረት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኑረዲን አብደላ እንደተናገሩት፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለድሬዳዋ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።

ዘንድሮ ለሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ 5 ሚሊዮን ችግኞችን ማዘጋጀት እንደተቻለም አብራርተዋል፡፡

በተለይም የምግብ ዋስትናን ሊያረጋግጡ የሚችሉ የሚበሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት ማዘጋጀት እንደተቻለም ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ከሚተከሉ ዛፎች ውስጥ የሚበላው ድርሻ 30 በመቶ የነበረ መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት ወደ 60 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ጠቁመዋል።

በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሚገኙ በ22 የችግኝ ጣቢያዎች በመንግስትና በማህበረሰብ በጋራ የችግኝ ማፍላት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል።

አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ተክለመድህን አቻምየለህ

#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
******
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 28/05/2026

📸 በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን ሊባን ወረዳ በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ማሳ አሁናዊ ገፅታ፡፡

#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
******
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 28/05/2026

በአሲዳማነት የተጎዳ የእርሻ መሬትን በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ!

********************

የአፈር አሲዳማነት የግብርናን ምርትና ምርታማነት ከሚቀንሱ ምክንያቶች በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን የሚከሰተውም በአብዛኛው የእርሻ መሬትን ባለመንከባከብ ነው።

የአፈርን ለምነት ከሚጎዱ ነገሮች ውስጥ ዋናዎቹ የአፈር መታጠብ፣ ተረፈ ምርትን አሟጦ ከማሳ ላይ ማንሳት፣ ያለ እንክብካቤ መሬትን ደጋግሞ ማረስ፣ የሰብል ንጥረ-ነገሮችን ከአፈር ውስጥ መጨረስ እና ከምክረ ሀሳብ ውጪ የናይትሮጅን ማዳብሪያዎችን መጠቀም ናቸው።

አሲዳማ አፈርን ማከም የሚቻለው በዋናነት በግብርና ኖራ ነው፡፡ በአሲዳማነት የተጎዳውን መሬት በግብርና ኖራ አክሞ ለማልማት ባለፉት አምስት አመታት በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከግብርና ኖራ አቅርቦትና ምርት ጋር በተያያዘ በአማራ፣ ኦሮሚያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች 11 የሚሆኑ የኖራ ወፍጮዎችን በመትከል የግብርና ኖራ እየተመረተ ሲሆን ይህም በአሲዳማነት የተጎዳውን የአርሶ አደሩን የእርሻ መሬት ለማከም ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 5 የግብርና ኖራ ወፍጮዎችን ለመትከል እየተሰራ ነው።

የአሲዳማ አፈር ችግርን በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ግብርና ሚኒስቴር ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የንቀናቄ ሰነድ በማዘጋጀት ብዙ ስራዎችን የሰራ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ወደ 1.4 ቢልዮን ብር በመመደብ በክልሎች ትላልቅ ማሳዎች ላይ የግብርና ኖራን በመጠቀም አሲዳማ አፈርን የማክም ሰርቶ ማሳያዎችን በመስራት የግንዛቤ ማስጨበጫና መሰል ስልጠናዎች ከክልል እሰከ ቀበሌ ላሉ ባለሙያዎችና አመራሮች ተሰጥተዋል።

ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ባልፉት አምስት ዓመታት 103,590 ሄ/ር የእርሻ መሬትን በማከም ወደ ልማት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ከችግሩ ስፋት አንጻር ግን ብዙ መስራት ስለሚጠበቅ፣ በአሲዳማነት የተጎዳውን መሬት አክሞ ወደ ምርታማነት ለማስገባት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በቁርጠኝነት መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

አዘጋጅ፡- ካሳሁን ማለቶ
ፎቶ፡- ማቲዎስ ተገኝ
#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
******
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Photos from Ministry of Agriculture - Ethiopia's post 28/05/2026

የእንስሳት ጤናና ደህንነት አዋጅ ለእንስሳት ምርታማነት!

ሀዋሳ፣ ግንቦት 20/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ 1376/2017 ላይ ከሲዳማ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች እና ለአዋጁ አስፈጻሚ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ፣ ዝርያ ማሻሻል እና መኖ ዝግጅት ላይ መንግስት አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ሚናው የላቀ ነው ያሉት አማካሪዋ፣ ለአዋጁ ተግባራዊነት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በሲዳማ ክልል የእንስሳት ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ሚሊዮን ዮቴ በበኩላቸው እንስሳት መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላላቸው የሚሹ ፍጡራን መሆናቸውን ጠቁመው በእንስሳት አያያዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመፍታት አዋጁ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

ለግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ዝግጅት በአውሮፓ ህብረት የሚደገፈው ሪስቶር ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ የተገኙ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ህክምና ቤተ-ሙከራዎችን እንዲሁም የእንስሳት ደህንነትና ጤና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ደመቀ
ፎቶ፡ ማቲዎስ ተገኝ

#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
******
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

27/05/2026
Photos from Abiy Ahmed Ali's post 27/05/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
6234

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30