07/07/2022
ትዉልዱ ዛሬም በአረንጓዴ አሻራው ታሪክ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የመንገድ ደህንነት እና የመድን ፈንድ አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች 4ተኛው ዙር የአርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በ29/10/2014 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል ፡፡
የችግኝ ተከላውን መርሃ ግብር በይፋ ያስጀመሩት የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ ሲሆኑ በንግግራቸው እንደገለፁት የሀገር ግንባታው የትውልድ ቅብብሎሽ እንደሆነ ሁሉ ይህም ትውልድ አራተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በሀገር ግንባታው የድርሻውን እያበረከተ ታሪክም እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
በዕለቱ መርሃ ግብር 2000 ችግኞች ተተክለዋል፡፡ በቀጣይ በጋ ወራት የመኮትኮት የመንከባከብና ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በዕለቱ የትራንስፖርት ሎጅስቲክ ሚንስቴርና ተጠሪ ተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የአመቱን የመጀመሪያ ዙር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡ በቀጣይ ሀምሌ 06/ 2014 ዓም 100,000 (መቶ ሺ) ችግኞችን እንደሚተከሉ በዕለቱ የተገኙ ሚንስቴር ዴታዎች ገልፀዋል ፡፡
13/06/2022
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወጡ እስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ህጎች እና ደንቦች የተሸከርካሪ አደጋን ለመቀነስ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወጡ ተገለፀ፡፡
የመንገድ ደህንነትና የመድን ፈንድ አገልግሎት በደንብ ቁጥር 493/2014 በተሰጠውን ስልጣንና ተግባር እና አለማቀፍ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ህጎች ላይ በካፒታል ሆቴል በ6/10/20141 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር ወርክሾፕ አካሂዶል፡፡
በዕለቱን ፕሮግራም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንገድ ደህንነትና የመድን ፈንድ አገልግሎት የኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ አዲል አብዱላሂ አንደገለፁት አገልግሎቱ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር የማስተዋወቅ፣ የመንገድ ትራፊክ ደህንንነት ህጎችን የማስፈፀም እና በአለም አቀፍ ደረጃ የወጡና ሀገራችን የተስማማችበትን የመንገድ ደህንነትና የመድን ፈንድን የሚመለከቱ ስምምነቶች መተግበርና አፈፃፀማቸውን መከታታል ለመቤቱ ከተሰጡት ስልጣን ውስጥ እንደሚጠቀስ በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡
በወርክሾፑ ላይ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ማቋቋሚያ በድንብ ቁጥር 493/2014 የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በአቶ ዮናስ በለጠ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ የብሉምበርግ ኢንሼቲቭ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ለገሰ የመንገድ ደህንነት አለማቀፍ ተሞክሮዎችን በህግ አተገባበር ላይ ያሉ ክፍተቶችን እና የአደጋ መንስኤ አቅርበዋል፡፡ እንደ ሃገርም በዘርፉ በተለያያ ጊዜ የመንገድ ደህንነት የህግ መእቀፎችን ለማሻሻል በወጣው የትራፊክ ደንብ ቁጥር 208/2011 ላይ ያሉትን የትርጉም ክፍተቶችን በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርበታል፡፡
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳተፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ የአለም አቀፍ የህግ ማስከበር ሰኬትና ተሞክሮዎች ቀርበው በሃገር ደረጃ በየጊዜው ለሚደርሱ አደጋዎች የመጀመሪያው ክፍተት ህግን ማስከበር ላይ እንደሆነና በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ ትኩርት እንዲሰጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለመንገድ ትራፊክ አደጋ መቀነስ የድሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ተደርጎ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡
13/06/2022
የመንገድ ደህንነት እና የመድን ፈንድ አገልግሎት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት
አሰጣጥ እና የፈንድ አጠቃቀም ላይ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
የመንገድ ደህነንት እና የመድን ፈንድ አገልግሎት ፣የጤና ሚንስቴር፣የፌዴራል ፖሊስ ፣የክልል ፓሊስ ኮሚሽኖች፣የክልል ጤና ቢሮዎች እና የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና እና የፓሊስ ቢሮዎች የዘጠኝ ወራት የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እና የፈንድ አጠቃቀም ላይ በአዳማ ከተማ ከረዮ ሆቴል በ4/10/2014 ዓ/ም ተገመገመ፡፡
በእለቱ ፕሮግራም ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንገድ ደህንነት እና የመድን ፈንድ አገልግሎት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አዲል አብዱላሂ ሲሆኑ በንግግራቸውም የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በሆነ እና በተገቢው ሰዓት አገልግሎቱን በመስጠት የሰውን ህይወት ከሞት መታደግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመቅረፍም በተጨማሪ ከሞራል አንፃር እንደ ዜጋ ማህበራዊ ሀላፊነት መወጣት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ሁሉም ክልሎች የተሽከርካሪ አደጋ የአስቸኳይ ህክምና አገልግሎት አፈፃፀማቸውና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር እና የነበሯቸዉን ጠንካራና ደካማ ጎኖች የያዘ አፈፃፀም በሪፖርታቸው ላይ በማካተት አቅርበዋል ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደር በደረሱ አደጋዎች የሞት፣ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳቶች እና የንብረት ውድመትን በዝርዝር አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ በርካታ ሀሳቦች ተነስተው ከጤና ሚንስቴር እና ከመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ምላሽ ተሰቶባቸዉ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል ፡፡
17/05/2022
የመንገድ ደህንነት ማስጠበቅ የቁጥጥር ዘመቻ
የመንገድ ደህንነት ማስጠበቅ የቁጥጥር ዘመቻ
25/03/2022
ብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ቴክኒካል የስራ ቡድን የምስረታ ፕሮግራም በአዳማ ከተማ መጋቢት 15/01/2014 ዓ.ም ተካሄደ
……………………………… …………………………. …………………….
የመንገድ ደህንነት ቴክኒካል የስራ ቡድን ምስረታን አስመልክቶም የተከበሩ አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ደህንነት እና የመድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ኢንድራጂት ሀዛሪካ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን
አቶ ጀማሉ አባሶ በንግግራቸውም ለአንድ ሀገር ሁለተናዊ ዕድገት የመንገድ ትራንሰፖርት እየተጫወተ ያለው ሚና የላቀ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ይህ ዘርፍ ከዚህም በላይ ድርሻው የጎላ እንዳይሆን የመንገድት ትራፊክ አደጋ በዜጎች እና በሀገር ሁለተናዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በመሆኑም የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለማሰፈን የሁሉንመ አካላት ርዕብርብ የሚሻ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ ብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ቴክኒካል የስራ ቡድን ማቋቋሙ ግድ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በጋራ ዕቅድ ለማቀድ ተቀራርቦ ለመስራት እና የነቃ ተሳትፎን ለማጠናከር እንዲሁም የመንገድ ደህንነት ተግባራትን ለማሻሻል የባለሙያዎች ስብስብ መኖሩ ድርሻው የላቀ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
በመጨረሻም የተቋቋመው ብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ቴክኒካል የስራ ቡድን ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን ለማስተባበርና የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል እንዲሁም በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ለመቀነስ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ለዚህ ቴክኒካ ቡድን ምስረታ መሳካት የድርሻቸውን የተወጡ አካላትን አመስግነው ለብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ቴክኒካል የስራ ቡድን መልካም የስራ ጊዜ ይኖራቸው ዘንድ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
23/03/2022
አሉታዊ መጤ ባህሎች በወጣቶች ስብዕና ላይ በሚያስከትለው ተፅዕኖ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
------------------- ------- ------ --------
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት አሉታዊናመጤ ባህሎችና አደንዛዥ ዕፆች በወጣቶች ሰብዕና ላይ በሚያስከትለው ተፅዕኖ ዙሪያ መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም በዲባቤ ሆቴል ስልጠና ተሰጠ።
የዕለቱ ፕሮግራም በማስመልከት የተቋሙ የሴቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አያሌው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ እንኳን ለማርች 8 አደረሳቹህ ብለዋል። ወ/ሮ መሰረት አያሌው በንግግራቸው የወጣቶች ስብዕና ለመገንባት ተቋማችን ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስተር የወጣቶች ስብዕና ባለሙያ አቶ ኑረዲን ሽኩሪ ባቀረቡት ሰነድ ላይ እንደገለፁት አደንዛዥ ዕፆች የሚያስከትሉት ማህበራዊ ቀውስ እንዲሁም የጤና ጉዳት ምርታማነትን በመቀነስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ስለሚከት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከሚኒስተር መስሪያቤቱ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ማርች 8 በማስመልከት እና ተሽከርካሪና ሴቶች በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።