ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

Share

This is the page of Ministry of Culture and Sport of Ethiopia!

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 08/06/2026

ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ኦሮሚያ ክልል ያቀናው የድጋፍና ክትትል ቡድን ስራውን ጀመረ።

ሰኔ 01፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ኦሮሚያ ክልል ያቀናው የድጋፍና ክትትል ቡድን ዛሬ ሰኔ 01/2018ዓ.ም ስራውን ጀምሯል።

ቡድኑ ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እና ማኔጅመንት አባላት ጋር በተዘጋጀው ቼክ ሊስት እና በቀጣይ ቀናት ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በቀጣይ ቀናት በሰነድ ግምገማና በመስክ ምልከታ በታገዘ መልኩ የድጋፍና ክትትል ስራው ተጠናክሮ ይጥላል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 08/06/2026

‎ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለድጋፍና ክትትል የተሰማራው ቡድን የመግቢያ ውይይት በማድረግ ስራውን ጀመረ፤

ሰኔ 01፣ 2018ዓ.ም ታርጫ

‎ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለድጋፍና ክትትል የተሰማራው ቡድን የመግቢያ ውይይት በማድረግ ስራውን ጀምሯል።

የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ መቀመጫ በሆነችው ታርጫ ከተማ መዳረሻውን ያደረገው ቡድኑ ከአቶ ፋንታሁን ብላቴ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና ማኔጅመንት አባላት ጋር ዛሬ በሰኔ 01 ቀን 2018ዓ.ም የመግቢያ ውይይት አካሂዷል።

በ‎ውይይቱ በምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋፋት ላይ ያተኮረ አጭር ገለጻ በቡድን አስተባባሪዋ በወ/ሮ አበባ አማረ አማካኝነት ቀርቦ አጠቃላይ የቢሮው የዓመቱ አፈጻጸም በቸክሊስቱ መስረት በዝርዝር ቀርቧል። በቀረበው ዝርዝር ጉዳይ ላይ የቢሮ ኃላፊው በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

08/06/2026

ንፁህ ስፖርት ለኢትዮጵያ!
አበረታች ቅመሞችን በጋራ እንከላከል።

06/06/2026

ንፁህ ስፖርት ለኢትዮጵያ!

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 05/06/2026

የሀገራችን ስፖርት ከአበረታች ቅመሞች እንዲፀዳ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች የበኩላቸውን ድርሻ ሲወጡ ቆይተዋል:- አቶ መኮንን ይደርሳል

ግንቦት 28፣ 2018ዓ.ም አዳማ

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ እና በጋዜጠኞች የዘገባ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል የሀገራችን ስፖርት ከአበረታች ቅመሞች እንዲፀዳ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች የበኩላቸውን ድርሻ ሲወጡ እንደቆዩ ገለፁ።

ህብረተሰቡ ዶፒንግን እንዲጸየፍ እና ንጹህ የስፖርት ማህበረሰብ እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ ከፍተኛ በመሆኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።

የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል እና በዓለም አቀፍ መድረክ ውጤታማ ሆኖ ለመቀጠል በአበረታች ንጥረነገር ዙሪያ ሁሉም በየበኩሉ ያለመታከት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በስልጠናና ውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የመገናኛ ብዙሀን ባለሞያዎች ባለስልጣኑ እያሳየ ያለውን እድገት አድንቀው ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችንም አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በዚሁ መሠረት ባለስልጣኑ ከፌደራል ፖሊስ፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ጋር የጋራ አጋርነት በመፍጠር በሳይንሳዊ መንገድ የተደገፈ የትንተናና የክትትል ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመድረኩ ተነስቷል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳሬይክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ባለስልጣኑ ጥፋተኞችን ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ስልጣን እንዳለው አስታውሰዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ስፖርተኞች ከዶፒንግ ነፃ የሆነ ንጹህ ስፖርትን እንዲያራምዱ የማስተማር፣ ግንዛቤ የመፍጠርና የስነ-ባህሪ ለውጥ እንዲመጡ የማድረግ ስራዎችን ጎን ለጎን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት እና ስልጠናዎች በሳይንሳዊ ጥናት ላይ ተመስርተው በካሪኩለም መልክ እየተሰጡ መሆኑ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳሬይክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ የገለፁ ሲሆን ይህም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን አንድ እርምጃ ከፍ ያደረገ ተግባር መሆኑን አክለዋል።

በሀገር ውስጥ የዶፒንግ ምርመራ ላብራቶሪዎችን ለመክፈት ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በመድረኩ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት የአትሌት ባዮሎጂካል ፓስፖርት ላብራቶሪን ወደ ስራ ለማስገባት የማሽኖች ግዢ የተጠናቀቀ ሲሆን ቦታውም ተዘጋጅቶ የተከላ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ይህ ላብራቶሪ በቅርቡ ስራ የሚጀምር ሲሆን በቀጣይም ትልቁን ላብራቶሪ ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ባለስልጣኑ በሀገራችን ለዶፒንግ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ የሆኑ ስፖርቶችን በመለየት መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየከወነ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሁሉም ረገድ በአፍሪካ ደረጃ ተምሳሌት መሆን የሚችል ጠንካራ ተቋም እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።

በዶፒንግ ምክንያት እገዳ የተጣለባቸውን አትሌቶች ወደ ስልጠና እና ውድድር ለመመለስ የሚደረገው የማገገሚያ ሥራንም ባለስልጣኑ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል።

የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ከባለስልጣኑ ጋር ያላቸውን የሥራ ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር የተገኙ ግድፈቶችን በጥናትና በማስረጃ ለይተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመተባበር በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ እና በጋዜጠኞች የዘገባ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረው ውይይት ስኬታማ በመሆኑ በቀጣይም በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 05/06/2026

የ2018 በጀት ዓመት የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ዓመታዊ የድጋፍ እና ክትትል ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ተሰጣቸው፤

ግንቦት 28፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓመታዊ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እና ክትትል ስራ ለሚወጡ ቡድን አባላት ኦረንቴሽን ሰጥተዋል።

ሚኒስቴሩ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የውል ስምምነት ተፈራርሞ ወደ ስራ በመግባት በሴክተሩ በርካታ ስራዎች ተሰርተው አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ክብርት ሸዊት ሻንካ አንስተዋል።

ድጋፋዊ የሱፐርቪዥኑ አስፈላጊነቱን የገለፁት ክብርት ሸዊት በበጀት ዓመቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በውል ስምምነቱ መሰረት ሲከውኗቸው የነበሩ ተግባራት ምን ያህል መሬት ላይ እንዳሉ ምልከታ ማድረግ እንዲሁም ለቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅትም እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል።

የቡድን አባላት በየሄዱበት አካባቢ ፍፁም ስነ ምግባር እና መከባበር በተሞላበት፣ በእህትማማችነትና ወንድማማችነት መንፈስ ስራቸውን በመከወን የሚጠበቀውን ውጤት ይዘው እንዲመጡ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የቡድኑ አባላት ከሰኞ ሰኔ 01/2018ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ክልል በመጓዝ ስራቸውን የሚጀምሩ ሲሆን በተዘጋጁ ቼክ ሊስቶች መሰረት በሰነድ ግምገማ፣ መስክ ምልከታ፣ ቃለ ምልልስ እና በውይይት አግባብ ድጋፋዊ ክትትሉን የሚያደርጉ ይሆናል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 04/06/2026

ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የተዘጋጀው የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ኢንስትራክተርነት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ግንቦት 27፣ 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ

የሀገራችንን የባህል ስፖርቶች በሳይንሳዊ መንገድ ለማሳደግ እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታላቅ ተስፋ የተጣለበት ልዩ የባህል ስፖርቶች የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ኢንስትራክተርነት ስልጠና በዛሬው ዕለት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተሰናዳው ይህ ስልጠና ከሀገሪቱ የተወጣጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ያሳተፈ ሲሆን በዘርፉ ብቁ የሆኑ ባለሞያዎችን ወደ ኢንስትራክተርነት ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ ለሰልጣኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት የስልጠናውን አስፈላጊነት አብራርተዋል።

የባህል ስፖርቶቻችንን መነሻ እና መድረሻ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ቀርፆ መዝግቦ እና አቀናጅቶ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ የሚቻለው የአካዳሚክ ማህበረሰቡን ሚና ስናጎላ ብቻ ነው ያሉት ወ/ሮ ህይወት “መምህራኖቻችን የዚህ ስልጠና ዋነኛ ተሳታፊ መሆናቸው ስፖርቱን ከቀላል ጨዋታነት ወደ ላቀ የምርምር፣ የፅንሰ-ሀሳብ እና የስትራቴጂክ ልማት ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ይህ መድረክ የባህል ስፖርቶቻችንን በሀገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን በአህጉር ደረጃም ጭምር ተወዳዳሪ እና ተደራሽ ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቷ አክለውም ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ስልጠና መሳካት ላደረገው ትብብር እና ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት ዶ/ር መስፍን ደጀኔ በበኩላቸው ከባህላዊ ስፖርቶች ጋር የተያያዘው ይህ ስልጠና በእጅጉ ጠቃሚ በመሆኑ ስልጠናውን ያዘጋጁትን የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽንን አመስግነው ሰልጣኞችም ይህን ጠቃሚ ስልጠና በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው መምህር የሆኑት አቶ አባይ በላይሁን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር እና የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን በቅርበት አብረው የሚሰሩ ሀገር አቀፍ ተቋማት በመሆናቸው ስፖርታዊ ውጤት መመዝገቡን በመጥቀስ ስልጠናው የባህል ስፖርት እንዲያድግ እና እንዲስፋፋ ትልቅ ዋጋ ስላለው ከሰርተፍኬት ባሻገር ከስልጠና ባገኙት እውቀት በዘርፉ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አመልክተዋል፡፡

ይህ ለቀጣይ ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ስልጠና በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባር የታገዘ ሲሆን ሰልጣኝ መምህራኖች ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ ወደ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች በመመለስ አዳዲስ አሰልጣኞችን እና ዳኞችን በሰፊው የሚያፈሩበትን የኢንስትራክተርነት ሚና እንደሚረከቡ ይጠበቃል።

መርሃ-ግብሩ በሀገራችን የባህል ስፖርት ታሪክ ውስጥ በአካዳሚክ ተቋማት እና በፌዴሬሽኑ መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር እንዲሁም የስፖርቱን ፕሮፌሽናሊዝም (Professionalism) ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

Photos from ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia's post 04/06/2026

አበረታች ቅመሞችን በመከላከል የጋዜጠኞች ሚና በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ እየተካሄ ነው።

ግንቦት 27፣ 2018ዓ.ም ​አዳማ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመተባበር በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ እና በጋዜጠኞች የዘገባ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ መክፈቻ ላይ
ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት አምስት እና ስድስት ዓመታት የሀገሪቱን ስፖርት ከነበረበት የዶፒንግ ስጋት ለመታደግ እና ጠንካራ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ህብረተሰቡ ዶፒንግን እንዲጸየፍ እና ንጹህ የስፖርት ማህበረሰብ እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የሚዲያ ባለሙያዎች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

​ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰው ሃይል፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራር እና በግብዓት ራሱን በማጠናከር በአፍሪካ ደረጃ ተምሳሌት መሆን የሚችል ጠንካራ ተቋም መቋቋም መቻሉም ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የአበረታች ቅመሞችን መከላከል ትምህርትን በሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ማስገባት መቻሉ፣ ወደፊት ወደ ስፖርቱ የሚቀላቀሉ ዜጎች በቂ እውቀትና ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው ለማድረግ ባለስልጠን መስሪያ ቤቱ መስራቱንም በመልዕክቱ ተካቷል።

​የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴን ማጠናከር ያስፈለገበትን ምክንያቶች ዋና ዳይሬክተሩ በአራት ዋና አላማዎች ከፍለው አብራርተዋል።

የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል እና በዓለም አቀፍ መድረክ ውጤታማ ሆኖ ለመቀጠል ዶፒንግን ያለመታከት መከላከል እንደሚገባ፤ ካልሆነ ግን ውድድሩ የሳይንቲስቶችና የቴክኖሎጂ ባለቤቶች ብቻ ይሆናል ብለዋል።

በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ በዶፒንግ ዙሪያ የተቀመጡ ጥብቅ መስፈርቶችን ማሟላት ሲቻል ሁለተኛው ጉዳይ ሲሆን ውድድሮችና ስልጠናዎች ያለምንም አበረታች ቅመም፣ በተፈጥሯዊ ተሰጥኦ እና በሳይንሳዊ ልምምድ ላይ ብቻ የተመሰረቱ እንዲሆኑ በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጧል።

በሌላ መልኩ የስፖርትን ተዓማኒነትና ውበት መጠበቅ ስፖርት ያለ ደጋፊ ምንም በመሆኑ፣ ደጋፊው ደግሞ ንጹህ ውድድርን ስለሚሻ፤ የስፖርቱን ተዓማኒነት ጠብቆ ደጋፊው ከሜዳ እንዳይጠፋ ለማድረግ እንደሆነ ተመላክቷል።

አበረታች ቅመሞች በዜጎቻችን ላይ የሚያስከትሉት የጤና፣ ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ዜጎቻችንን ከዚህ አደጋ የመጠበቅ እና የመከላከል ትልቅ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ ቢሆንም የሚዲያ ዘርፉ በዋናነት የላቀ ድረሻ እንዳለው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

አክለውም የስፖርቱ ተዓማኒነት እንዲቀጥልና የስፖርት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የጀመሩትን የተቀናጀ ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶፒንግ እና የጋዜጠኞች የዘገባ ስነምግባር፣ የአበረታች ቅመሞች ፅንሰ ሀሳቦች፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የዶፒንግ ተፅዕኖ እና የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ በሚል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

04/06/2026

ባህላዊ ምግቦች የአንድ ሀገር የማንነት ነፀብራቆች ናቸው፤

ባህላዊ ምግቦች በተለያየ ማህበረሰብ ውስጥ እንደየአካባቢው ሁኔታና ልምድ የሚዘጋጁ የእለት ከእለት ወይም ለተለየ ፕሮግራም የሚዘጋጁ የምግብ አይነቶች ናቸው።

እነዚህ ባህላዊ ምግቦች ላይ በትኩረት በመስራት እና በማስተዋወቅ እንዲሁም በምግብ ቤቶችና ሆቴሎች የምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ በዘርፋ እየተሰራ ያለው ስራ ይበል የሚያሰኝ ነው።

ጥሩ የማብሰል እና የመመገብ ጥበብን (Gastronomy Art) በብዙ ሀገራት ትልቅ የቱሪዝም መስህብ እና የገቢ ምንጭ አድርገው ይጠቀሙታል።

በሀገራችንም በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቢሆኑም ወደ ኢንደስትሪ ለመቀየር
በትኩረት መስራት ተገቢ ነው።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa