እንኳን ደስ አላችሁ
የሲባ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ለሰደሬም ጭምር እንድሆን ተወሰኗል፡፡
Water head office - Legehida
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Water head office - Legehida, Government Organization, legehida, Addis Ababa.
22/01/2020
After much struggle
We are delighted to have agreed with the community to work in @010 kebele Constructing SPD.
By always participating in the community
We realized that it was possible to meet,communicate and win by dialog and discussion .
22/12/2019
This is good news for all of us with the situation of siba drinking water
Go to Home
Legehida Woreda Communication
በለገሂዳ ወረዳ የሲባና አካባቢዋ ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር
እንድፈታ ታስቦ በአማራ ድዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት በ21 ሚሊዮን ብር
በጀት ስራው መጀመሩ ይታወቃል፡፡
የድርጅቱ ጅኦሎጅስት የሆኑት አቶ አዳነ ጋርደው እንደገለፁት ከሆነ 81.5 ሜትር
ጥልቀት እንደተቆፈረና 69.5 ሜትር ላይ ፓንፑ ለሙከራ እንደገባም
አስታውቀዋል፡፡
የውሃው አቅም የሚታወቀው በ24 ሰዓታት ተሞክሮ ቢሆንም አሁን በቅድመ የ2
ስዓት ሙከራው በሰከንድ 26 ሊትር እንደሆንና ይህም ትልቅ የውሃ መጠን
እንደአለው አብራርተዋል፡፡
የለገሂዳ ወረዳ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጽ/ቤት የውሃ አቅርቦት ጂኦሎጅስት ወ/
ሪት አድማሴ አርያ በበኩሏ የቁፋሮ ስራው 40ቀናት እንደወሰደ እና ዛሬ ላይ
የውሃ አቅሙን ለማወቅ የቅድመ ሙከራ ስራ እንደተሰራና ቀሪ ስራዎች
ተከናውነው የሲባ ህዝብን የውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግራለች፡፡
የህዝቡን ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን
የገለፁት ደግሞ የውሃና መስኖ ኢነርጂ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይመር ማስረሻ
ናቸው፡፡
ሃላፊው አያይዘውም ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በክልል በጀት በ3 ደረጃዎች
የሚከናወን እንደሆነ እና የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ ቀጣይ የድዛይን ስራ
እንደተጠናቀቀ የመሰመር ዝርጋት፣የታንከር እና የማስፋፊያ ሰራዎችን
በማጠናቀቅ የንፁህ መጠጥ ውሃው ለማህበረሰቡ እንደሚደርስ ጠቁመዋል፡፡
19/12/2019
ታኅሣሥ 10 የምትመጥቀው ሳተላይት መረጃ]
ሠው ሠራሽ ሳተላይቷ ሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት ስትሆን በምሕጻረ ቃል
ETRSS-1 ትባላለች። ክብደቷ 70 ኪሎ ግራም ትመዝናለች፤ ከመሬት 700
ኪሎ ሜትር ቆይታ ላይ ነው የምትቆየው። ሳተላይቷ ብዙ ጥቅሞች ያላት ሲሆን
በተለይ ለኢትዮጵያ ብዙ መረጃዎችን በግብርናው ዘርፍ የሰብል ሁኔታ ያለበትን
ለማወቅ፣ የደን፣ የአፈር፣ የውሃ ሁኔታችንን ያሉበትን ለመረዳት፣ ለመቆጣጠር፣
በአግባቡ ሥርዓት ለማስያዝ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎችን፣ የጎርፍና የድርቅ አደጋዎችን፣ የሰደድ
እሳት አስቀድሞ ለመተንበይና ለመቆጣጠር ታስችላለች ተብሎ ይጠበቃል።
በጣም ብዙ ሳተላይቶች በሕዋ ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ
በርቀት ላይ ያሉ ጋላክሲዎችን፣ ፕላኔቶችን፣ የሚያጠኑ አስትሮኖሚ
ሳተላይቶች (Astronomical satellites)፤
ሕይወት ያላቸውን ይዘው የሚሄዱ ባዮሳተለይቶች (Biosatellites)፤
ለቴሌቭዥናችን፣ ለሬዲዮናችን፣ ለኢንተርኔታችን የሚጠቅሙ የግንኙነት
ሳተላይቶች (Communication satellites)፤
ሥነ አየርን፣ የአየር ንብረትን ወዘተርፈ አካባቢን የሚያሳውቁት (Earth
observation satellite or Earth remote sensing satellite)፤
የየሃገራቱ ሎንግቲዩድና ላቲቲዩድን በአግባቡ የሚያሳውቁ የናቪጌሽን
ሳተላይቶች (Navigational satellites)፤
ጸረ ሳተላይቶችን ማጥቃት የሚችሉ ገዳይ ሳተላይቶች (Killer
satellites)፣
የውትድርና ሳተላይቶች፣
የጂፒኤስ ሳተላይት፣
ለወታደራዊ አገልግሎት የሚጠቅም የስለላ ሳተላይቶች
(reconnaissance satellite or intelligence satellite; spy satellite)
ቴሌስኮፓችን ለማምጠቅ የሚረዳው የዲፕ ስፔስ ሳተላይትና ሌሎችም
ይገኛሉ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በ1957 ዓ.ም ሶቪየት ሕብረት ስፑትኒክ 1 የምትባለውን
የመጀመሪያውን ሠው ሠራሽ ሳተላይት ያመጠቀች ሲሆን ከዚያ በኋላ በአሁኑ ጊዜ
በሥራ ላይ 2062 የተለያዩ ሳተላይቶች በሕዋ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ
የሰው ልጅ የላካቸው ግን ከ8900 ይጠጋሉ።
ብዙዎቹን አሜሪካ፣ ሩሲያና ቻይና የላኳቸው ሲሆኑ በአፍሪካ 8 ሀገራት ደቡብ
አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ግብጽ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሞሮኮ አሁን ደግሞ
ኢትዮጵያም በ9ኛነት ተጨምራለች።
ዐርብ ታኅሣሥ 10 (December 20) በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር
12:21 ላይ የኢትዮጵያ ሳተላይት ከቻይና ትመጥቃለች። መቆጣጠሪያው
ከእንጦጦ ሲሆን ግንባታውም የተጠናቀቀና 20 ኢንጂነሮች ሥልጠናን
ወስደዋል።
የዛሬ 4000 ዓመት በነካሲዮፕያ፣ በነሴፌውስና በነአንድሮሜዳ ዘመን
ጠፈርን መመርመር የጀመረች ሀገር ታታሪ ልጆች ካሏት አሁንም የማታድግበት
ምንም ምክንያት የለም። አሁን ላለነው ይህን የሳተላይት መምጠቅ ታላቅ መነሻ
ሲሆን ወደፊት ይህንን የሳተላይት ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎ
ማምጠቂያውም ከኢትዮጵያ እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ መሠራት ያለበት ሲሆን
ሕዝቦቿ ቀንና ሌሊት ያለ ዕረፍት ለሃገሪቱ ከሠሩ በቅርቡ የማይሆንበት ምከንያት
ምንም የለም።
ምንጭ፡ አንድሮ ሜዳ
26/11/2019
A 5-year national movement to create an environment free from pollution has been announced
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Water supply, sanitation and water resource management with stakeholders
Discussions are underway in Addis Ababa.
With support from a variety of national and international partners, over 5 hundred
Work on water supply and sanitation in districts and towns
Millions of applications for the first phase of the 'Wanewash' program
Because I was able to make it accessible to citizens in rural and urban areas
It's described.
Phase 2 of the program also continued this practice by 4.4 million
Irrigation and water schemes are also planned to reach out to citizens
Energy Minister Dr. Sileshi Bekele said.
The environment that will be implemented over the next 5 years is environment-free
The National Movement to make citizens from diseases that result from impurity
He also plays a key role in the prevention of health, State Minister of Health Dr. Lidya said .
Source .EBC
09/09/2019
22/06/2019
የውሃ መስኖና ኢነርጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይመር ማስረሻ ዛሬ በ04, በ08 እና በ012 ቀበሌወች በመሄድ በሴፍትኔት በጀት የተገነቡ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡
እንድሁም እሰከዛሬ ድረስ ለሽክፍ ውሃ የመብራት ቆጣሪ ሳይገባለት መቆየቱ ይታወቃል ፡፡ነገር ግን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ባለፈው ሳምንት ወረኢሉ በመሄድ የቆጣሪውን ብር በማስከፈል እና ከስራ አስካጁ ጋር በመወያየት በዛሬው እለት ቆጣሪውን ማስገጠም ተችላል፡፡
woin amba
19/06/2019
የለገሂዳ ወረዳ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ጽ/ቤት ባስመጣቸው የአማራ ድዛይንና ቁጥጥር ቢሮ
ባለሙያወች ጋር በጋራ በመሆን ከ4/10/11-12/10/11 ድረስ ለሲባ ከተማ የንፁህ መጠጥ
ውሃ የጥናት ሰራ የሰራን ሲሆን የድዛይን ዶክመንት ሰራ ሪፖርት አልቆ የቁፋሮ ቦታ ርክብክብ
ርክብክብ ያደረግን ሲሆን የቁፋሮ ስራውም በዚህ ወር የሚጀመር ይሆናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለወይን አምባ ከተማ የሚሆን ሌላ የንፁህ መጠጥ ውሃ ቦር ሆል ከ07 ቀበሌ
ጥናት በማድረግ የድዛይን ዶክመንት በማዘጋጀት የሚሰራልን NGO በማፈላለግላይ እንገኛለን፡፡
08/06/2019
በለገሂዳ ወረዳ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ጽ/ቤት የሲባ ከተማን ማህበረሰብ የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ብንሞክርም ሳይሳካ መቆየቱ ይታወቃል ፡፡ ነገር ግን ከመቸውም በላይ ባደረግነው የጋራ ርብርብ የፕሮጀክቱ ጥናትና የመጀመሪያው ምዕራፍ የቁፋሮ ስራ በዚህ ወር እንደሚጀመር ተውቃል፡፡
በለገሂዳ ወረዳ ዉሃ መስኖና ኢነርጅ ጽ/ቤት ከወረዳው ለተውጣጡ ወጣቶች የአርቴዝያን ሰልጠና በሲባ 04 ቀበሌ ውርጌ ጎጥ እየሰለጠኑ ይገኛሉ :: ግንቦት 13 2011 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Legehida
Addis Ababa
+251
