02/04/2026
Yeka woreda 11 Communication-የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን
ይህ በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን ህጋዊ የፌስቡክ ገፅ ነዉ!!
02/04/2026
01/04/2026
30/03/2026
ለነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ዛሬ የተሟላ እንክብካቤ እናደርጋለን!
የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን መጋቢት 21/2018
በየካ ወረዳ 11 አስተዳደር በሚገኘዉ ደጃዝማች ወንድራይድ 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የሚማሩ ህፃናት በእረፍት ሰዓታቸዉ የሚዝናኑበት የህፃናት መጨወቻ ቦታ በሚያምር ሁኔታ ተመቻችቷል።
ህፃናት ለአካላዊ ዕድገታቸዉ ምግብ እንደምፈልጉ ሁሉ ለአዕምሮ እድገትና ለተሟላ ጤና ፅዱ ፣ ዉብ እና ማራኪ የመማሪያና መጨወቻ ቦታዎች ያስፈልጋሉ።
የህፃናትን ሁሌንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ታስቦ በተሰረዉ የህፃናት መጨወቻ ቦታ በርካታ ህፃናት እየተዝናኑ ሲሆን የት/ት ቤቱ ተማሪ በመሆናቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉን መገንዘብ ችለናል።
29/03/2026
በየካ ወረዳ 11 አስተዳደር የከተማ ግብርና ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ!
የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን መጋቢት 20/2018
በወረዳዉ በስፋት እየተሰሩ ካሉት የከተማ ግብርና ስራዎች መካካል የዶሮ እርባታ፣ የአትክልት እናፍራፍሬ ልማት፣ እንስሳት እርባታ እንዲሁም የዓሳ እርባታ በተቀናጀ መልኩ እየተካሄደ ነው።
ይህም የነዋሪዎችን ገቢ ማሻሻል፣ በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ ለገበያ ማቅረብ እና የስራ እድል መፍጠር ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጨወተነው።
በአጠቃላይ ወረዳው በዘርፉ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ እያደረገ ባለዉ ክትትልና ድጋፍ አነስተኛ ቦታን በብዛት በመጠቀም በዘመናዊ የከተማ ግብርና ስራ ተሰማርተዉ ዉጤት እያመጡ ያሉ ነዋሪዎችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ተችሏል።
29/03/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ
መጋቢት 20 ቀን 2018ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎችና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በስፋት ተሳትፈዋል።
በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፤ በመዲናዋ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
አፈ ጉባኤዋ አክለውም “የህብረተሰቡን የዘመናት ጥያቄዎች መመለስ ተችሏል” ካሉ በኋላ፣ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ በበኩላቸው፣ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ስፖርት ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል።
ማህበረሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ ያሳሰቡት ኃላፊው፤ የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው፣ ስፖርት ከጤና ባለፈ ለማህበራዊ ትስስር ያለውን ሚና አጉልተዋል። ስፖርት አንድነትን፣ አብሮነትንና የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከር አኳያ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
ይህ የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ማህበረሰቡ ለጤናው ትኩረት እንዲሰጥና የስፖርት ቤተሰቡን ትስስር ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የቀጣዩን ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያዘጋጅ የቦሌ ክፍለ ከተማ የተመረጠ ሲሆን የአዘጋጅነት አርማውን ከየካ ክፍለ ከተማ ተቀብሏል።
28/03/2026
28/03/2026
ምቹ የስራ አከባቢን መፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥን ዉጤታማ ያደርጋል!
የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን መጋቢት 19/2018
በየካ ወረዳ 11 አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ለማሻሻል የቢሮ እድሳት ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ያቀላጥፋሉ ተብለዉ ከታደሱት ቢሮዎች መካካል የዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ፣የ“አንድ ማዕከል”የአገልግሎት መስጫ ቢሮ ፣ የካቢኔ መሰብሰቢያ አደራሽ፣ንግድ ጽ/ቤት የሰራተኞች ካፍቴሪያ ተጠቃሽ ናቸዉ።
ይህ ማሻሻያ ለተገልጋዩ ህዝብ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና ለአገልጋዩ ሰራተኛ የተሻለ የስራ አካባቢ
27/03/2026
በየካ ወረዳ 11 አስተዳደር ባሉት ት/ት ቤቶች የተማሪ ምገባ ፕሮግራም ተጠናክሮ ቀጥሏል
የካ ወረዳ 11 ኮሙኒኬሽን መጋቢት 18/2018
በየካ ወረዳ 11 አስተዳደር ዉስጥ የሚገኙ ት/ት ቤቶች የተማሪ ምገባ ፕሮግራሙን በተጠናክሮ ሁኔታ እየፈጸሙ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች በትምህርት ላይ የተሻለ ትኩረት እንዲያደርጉ፣ የምግብ እጥረት እንዳይገጥማቸው እና ጤናቸው እንዲጠናከር አስፈላጊ ሚና እየተጫወተ ነው።
እንደ ት/ት ቤቱ አስተዳደር ገለጻ፣ ተማሪዎች በየቀኑ የተመጣጠነ ምግብ እየተሰጣቸው ሲሆን ይህም በመጠኑ የተሻለ የመማር ችሎታ እና የመገኘት መጠን እንዲጨምር አድርጎታል።
የተማሪ ወላጆችም ፕሮግራሙ ለልጆቻቸው ትልቅ ድጋፍ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይነት እንዲጠናከር ጠይቀዋል።
በአጠቃላይ፣ የተማሪ ምገባ ፕሮግራም በትምህርት ጥራት ላይ እና በተማሪዎች ጤና ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገልጿል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Address
Addis Ababa
Addis Ababa
