መፅሐፍት

መፅሐፍት

Share

በቅርቡ ከወጡ መፅሓፍት የተወሰዱ ፅሁፍች እና ቆየት ካሉትም፡፡፡ በተጨማሪም የመፅሀፍት ጥቆማ ያገኛሉ

09/05/2024

Shout out to my newest followers!

Photos from World Athletics's post 06/06/2023
04/06/2022

በቅርብ ቀን!

Photos from መፅሐፍት's post 29/10/2020

ግሩም ግጥም ምርጥ አገላለፅ Awtar Multimedia Haile Roots
ከአውታር ላይ እንገባበዝ

16/08/2020

ጀግና ማነው? ጅግንነትስ ምንድነው? ጀግና ምንለው ማንን ነው?

12/08/2020

.....የቀጠለ

Via Girum Solomon

ላም የጠፋበት ሰውዬ እና ልጁ
አባት ፡ እንዴ ወዴት ወዴት ነው?

ልጅ ፡ እሷን ፍለጋ! የምተርክላትን ላም ?

አባት ፡ አሄ! የት ነው ባክህ ምትፈልገው?

ልጅ፡ ሰው ፍለጋ ሲወጣ እኮ ለማግኝት ብሎ እንጂ የት እንደሆነ አያቅም። የት እንደሆነ ቢያቅማ ቀድሞውንም አልጠፋበትም ነበር።

አባት ፡ ፓ! እኔ በስንት አሉ በተባሉ ሰዎች አስፈልጌ ያላገኘኋትን አንተ ቱታና ቦቲ ስላረክ ምታገኛት መሰለህ?

ልጅ ፡ እሱ እኮ ነው ችግሩ የጠፋብህ አንተ። የፈለጉት ሌሎች። ማንያቃል ይሄኔ እኮ ፈልጉ ያልካቸው ደብቀዋት ወተትዋን እየጠጡ ይሆናል እኮ። ሌላው ስለ አለባበሴ ለጠየከኝ ያው ሽርሽር አይደለም። ፍለጋ ነው። የተመቸኝ ቦታ ብቻ አይደለም ምፈልጋት። ስለዚህ ለመንገድ እንዲመቸኝ ነው።

አባት ፡ እረ ተው ሰው ምን ይልሃል? የት ይደርሳል የተባለ ዛፍ አሉ?

ልጅ ፡ ሚገርምህ እሱ ነበር እስከዛሬ ድረስም ጠፍንጎ የያዘኝ። ዛሬ ላይ ግን አንድ የገባኝ እውነት ሰው የጠፋበት ነገር ዋጋ እንዳለው ካወቀ ለዛ ነገር መስዋት መክፈል ብዙ አያሳስበውም።

አባት ፡ አሁን እስቲ እዚህ ያንተ እኩዮች እኔን ብለው ከየት ድረስ መተው ይማራሉ አንተ ግን?

ልጅ ፡ አባዪ! እኔ እኮ ከገባኝ ቆየ። ከዛሬ ነገ አንድ ቀን መጥታ ወተትዋን ጠጣሁ እያልኩ በምናብ ሞትኩኝ እኮ። አንተም ብትሆን በፊት ትተርክበት የነበረበትን መንገድ ዘመናዊ እና ለጆሮ አማላይ ማድረጉ ላይ ነው ያተኮርከው እንጂ ላምዏን ጭራሽ እረስተሃታል።

አባት ፡ ግድ የለም በተከበርኩበት ልታዋርድኝ ነው አይደል ቆርጠ የተነሳህው?

ልጅ ፡ ክብር እኮ ‘እንዲ ነበረኝ’ በማለት ውስጥ አይደለም ያለው በመሆን ውስጥ ነው መገኛው። ደግሞስ ካሰብከው እኮ የኔ ፍለጋ መውጣት ጥቅም አለው እንጂ ጉዳት የለውም። ካገኘኋት እኔም አንተም እዲሁም የሰው ልጅ ጭምር ነው ሚከብረው። በዛላይ እስከዛሬ ምታወራው እውነት እንደነበር ማረጋገጫ ይሆንልሃል።

አባት ፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ምን ጉድ ነው የሰጠህኝ... በል እዲያ ከሆነ ነገሩ፣ በል ብቻህን አትሄድም እኔም ልብስ ቀይሬ መጣሁ።




ከባዶም ቢሆን ተነስተን ፍለጋ መውጣት ከፊታችን ያለ ምርጫ ነው። ጥቂት ልንሆን እንችላለን ግን ብቻችንን አይደለንም። እኛ ኢትዮጵያዊያኖች በድቅድቅ ጨለማ ብረሃን ይዘን እንወጣለን። ለሰው ልጅ የሚሆን ሃሳብ ከጓዳችን ዘንድ አለ።

ለበለጠ ስለነዚህ ሃሳቦች ጥልቅ ትንታኔ በመልከዓ ሃሳብ ሬዲዪ ዝግጅት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 9፡30 ይጠብቁ

12/08/2020

ልጅ - አባዬ ይሄ ምንድን ነው?
አባት - እንስራ ይባላል በድሮ ግዜ ወተት ያስቀምጡበት ነበር
ልጅ - ባዶ እኮ ነው ወተቱ የታለ ታዲይ?
አባት - አዪ ወተት ድሮ ቀረ የዛኔ ወተት ማር ማር ነበር ሚለው
አሁንማ ውተት የታለ በውሃ የቀጠነ ወተት ነው ምንጠጣው
ልጅ - አሃ! በውሃ የቀጠነ ወተት ስለሚሻል ነው?
አባት - ምን ይሻላለ፣ ወተት ቢጠፋ ነው እንጂ
ልጅ - እና ለምን አንፈልገውም?
አባት - እስቲ ተወኝ ፊልሜን ልይበት፣ ግባና የቤት ስራህን ስራ!
ልጅ - እምቢየው እኔ ማር ማር ሚለውን ወተት መጠጣት እፈልጋለሁ?
አባት - ሂድ እኮ ነው ምልህ ዋ! ቀበቶዪን እንዳልፈታ
ልጅ - እሺ በቃ ዝም እላለሁ…

ቀጣይ አለው......

የፀሐይ ግርዶሽ በላይሊበላ 22/06/2020

የፀሐይ ግርዶሽ

የፀሐይ ግርዶሽ በላይሊበላ የፀሐይ ግርዶሽ በሳይንስ እንደ ሳይንሱ ምልከታ የፀሐይ ግርዶሽ ጨረቃ በፀሐይና በመሬት መሓከል ገብታ ፀሐይን የምትጋርድበት ክስተት ነው። ይህ ደግሞ የሚ....

21/06/2020

የፀሐይ ግርዶሽ

በሳይንስ

እንደ ሳይንሱ ምልከታ የፀሐይ ግርዶሽ ጨረቃ በፀሐይና በመሬት መሓከል ገብታ ፀሐይን የምትጋርድበት ክስተት ነው። ይህ ደግሞ የሚሆነው ጠፍ ጨረቃ በምትሆንበት የለውጥ ሂድት ወቅት ነው። ይህ ወቅት ጨረቃ መሓከል ላይ ስላለችና ለፀሐይም የምትቀርብበት ወቅት ስለሆነ ፀሐይን የመጋረድ አጋጣሚው ይፈጠራል።

የፀሐይ ግርዶሽ ሦስት ዓይነት ሲሆኑ።
* ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ
* ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ
* ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ
ይባላሉ።

ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ የሚታየው ጨረቃ ሙሉ ለሙሉ ፀሐይን እንዳናይ ስትጋርደንና ሙሉ ጥቁር በሆነው ጸሊም ጥላ ውስጥ ስንሆን ነው። በዚህ ቅጽፈት ወፎች የመሸ መስሏቸው ወደ ጎጇቸው ይመለሳሉ።

ጨረቃ ፀሐይን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ሳትችል ስትቀር በጨረቃ ጠርዝ ዙሪያ ቀለበት ሠርታ ፀሐይ የምትታየን ከሆነ ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ(Annular Solar Eclipse) ይባላል። ይህ ሊሆን የሚችለው ጨረቃ ከመሬት እርቃ ባለችበትና "አፖጊ" (Apogee) ተብሎ በሚጠራው ርቀት ላይ ስትሆን ነው በዚህ ወቅት የጨረቃ ጥቁር ጥላ (ጽሊም ጽላሎት)መሬት ላይ ላያርፍ ይችላል።

የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ መጻሕፍት

ኢትዮያዊያን ስለ ፀሓይና ስለ ጨረቃ ግርዶሽ በተናገሩበት ትርጓሜ "ሚጠተ ብርሃናት" በተባለ መጽሐፋቸው ላይ ስለ ፀሐይ ግርዶሽ ጽፈዋል። በኢትዮጵያ የተከሰቱ የፀሐይ ግርዶሾችን የመመዝገብ ልምድ ነበራቸው።

ዐጼ በካፋ በነገሡ በስድስተኛው ዓመት በመስገረም ሰባት በዕለተ ሰኞ ሦስት ሰዓት ላይ ፀሐይ ጨለመች ከዋክብት ታዮ ሰው ሁሉ ታወከ፣ ለመነ፣ ፀሐይ እንደ ቀደመው በራች።

ይህ መጽሐፍ በ2011 ነው የታተመው የዛሬን ክስተት የት የት እንደሚከሱት በትትል ተጽፎ እናገኛለን

21/06/2020

🌗 ፀሐይ በእሳታማ ቀለበት ተሞሽራ በማየት በሕይወቴ ካስደሰቱኝ ዕለታት ውስጥ አንደኛው ዛሬ ነበር። በላሊበላ ጥንታዊ ቤተ መንግሥት ላይ ይህንን የሕይወት ዘመን ክስተት አይቶ ምስክር ለመሆን እጅግ ብዙ ሕዝብ በተራራው ላይ ቀድሞ ነበር የተገኘው። ሁሉም eclipse viewer አርጎ ስለነበር በጉጉት መከታተል ጀመረ። ልክ 12:45 ላይ ጨረቃ ፀሐይን መሸፈን ስትጀምር ሁሉም በአንድ ላይ በአድናቆት ጮኸ።

🌗 ከዚያም በደንብ ጨረቃ እየገባች መጋረድ ስትጀምር ተራራው መደብዘዝ ጀመረ። ከዚያም የሌሊት ወፎች ወጥተው መብረር ያዙ። ልክ 2 ሰዓት ላይ ፀሐይ እሳታማ ቀለበት ሠርታ ስትታይ በተራራው ላይ የነበረው ሕዝብ ሁሉ በጩኸትና በፉጨት ተራራውን አደበላለቀው።

🌗 ይህን እሳታማ ቀለበት ማየት የሚሰጠውን ደስታ በጽሑፍ መግለጽ አልቻልኩም። ወዲያው ከፀሐይ ግራና ቀኝ ፕላኔት ሜርኩሪና ቬኑስ ማብራት ሲጀምሩ ክስተቱ አስገራሚም አስፈሪም ነበር። በስካይ ማፕ ስመለከት ፕላኔት ጁፒተር፣ ማርስና ሳተርን ከፊት ለፊት ነበሩ።

🌗 የዘንድሮ ግርዶሽ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ መሬት፣ ሰመር ሶልስቲስ፣ ስካይ ክሮስ፣ የፍኖተ ሐሊብ ማዕከል፣ የፕላኔቶች ሁሉ መደርደር በትክክል ተገጣጥሟል። ይህ ጉዳይ ለፕላኔታችን መሬት በቅርቡ ምን ይዞ እንደሚመጣ መገመት ቢከብድም ነገር ግን የዓለምን ሁኔታ በጥንቃቄ ከዚ በኋላ መከታተል ይገባል በማለት በመላው ዓለም ያሉ ሳይንቲስቶች እየዘገቡ ነው።

🌗 ክስተቱን በፌስቡክ የቀጥታ ሥርጭት ለማስተላለፍ ምንም ኔት ባለመኖሩ የቀረጽኩትን ቪዲዮ በቅርቡ ሼር አረግላችኋለሁ።

Photos from መፅሐፍት's post 24/05/2020

ወዮ አለማያ
(አበባው መላኩ)

ዓለማያ የአወዳይ ልምላሜ
የሃረር ጠባይ ሚስጥር የፍቅር ሁሉ ፍጻሜ
አለማያ የወዳጅነት ልክ ማሳያ የመስዋዕትነት ጣሪያ
እስከመጨረሻይቱ ጠብታ እስከ ህይዎቱ ህቅታ
ወዙ ነጥፎ እስኪረታ
ዝም ነው የሱስ ውለታ
ሃረርጌ አለቀሰ እንባውም ፈሰሰ
የክፉ ቀን ጓዱን ሰርክ እያስታወሰ
ወዮ ዓለማያ የሃረር ሲሳይ
ባህርም እንደሰው ሞት ይሞታል ወይ
ማነው የገደለው ብዬ አልጠይቅ እኔ
በማን ዕጅ አለፈ ብየ አልልም እኔ
የደሙን አባላ በሃርርጌ ወዝ ላይ እያየሁኝ ባይኔ
የየዋህነቱን የታዳጊነቱን የአፍቃሪነቱን ልክ መቁጠር ቢታክትም
ርግማን ሆኖብን ባበሻ ምድር ላይ ደግ አይበረክትም
ይናገር እያሱ ከሞት ተመላሹ
ይናገር ተፈሪ በባህር ደጋሹ
በአለማያ ነገር የማይወሻሹ
ያ ሃረሩ ልቤ ያ ሃሩሩ ልቤ የተንሰፈሰፈው
ያን ኩሩ ዓለማያ የዛን ጀግና ባህር መቃብሩን ሲያየው
ከጨው ልክ ያለፈ ከሬት የመረረ እንባውን የረጨው
የዓልማያን ነገር ማትረፍ እየቻለ ቸልታው ቢቆጨው እስከመጨረሻይቱ ጠብታ
እስከ ህይወቱ ህቅታ
ወዙ ነጥፎ እስኪረታ
ዝም ነው የሱስ ውለታ
አረሱት ይሉኛል የሚያርስ ይረሳቸው
ህይወቱን ሰውቶ ህይዎት በሰጣቸው
ደረቱን በብረት ቀረደዱት አሉ
ለእፍኝ ማሽላ ማተብ በጣሽ ሁሉ
አይ የሰው ውለታ አይ የሰው ሰውነት
ምኑን ለማረሻ ምኑንስ ለብረት
እስከመጨረሻይቱ ጠብታ
እስከህይወቱ ህቅታ
ወዙ ነጥፎ እስኪረታ
መቼ እንድህ የሱስ ውለታ
አበሻ ምን ሆኗል አበሻ ታክቶታል?
ለባህር መሞቱን ዘንድሮስ ትቶታል?
"ወየውልሽ ጣና ወየው አባያታ ወየውልህ ጫሞ
ፊት ሰው ሞቶለታል ባህር ይሙት ደግሞ"
ብለው ዶለቱ አሉ ብለው መከሩ አሉ
እንግዲህ ዘራፍ በል የባህር ልጅ ሁሉ
ቀረርቶን ተላመድ ሰይፎችህ ይሳሉ
በአለማያ ይብቃ ከሰው መዋዋሉ
ወየው አለማያ የሃረር ሲሳይ
ባህርም የሰውን ሞት ይሞታል ወይ
የሱን ሞት ማን ቻለው የቱ ጎበዝ ከቶ
300 ሽ ነፍሳት ከሞት አፍ አውጥቶ
ደሙን አጠጥቶ የሱን ህይዎቱን ሰውቶ
አወይ ዓለማያ አቤት ያንተስ ነገር
አሉላ ቢሰማ ዮሃንስ ቢሰማ ቴዎድሮስ ቢሰማ
ምን ይውጠው ነበር
ምን ይውጠን ነበር
ያ ለባህር ሟቹ
ለውሃ ሰሳቹ
ባህር አሥራት ሲሆን ለሚያየው ልጆቹ
ምን ይሰማው ነበር የፈረሱ ጌታ ለደም ተሟጋቹ
መጥኔ ለሁላችን የአገር ልማድ ሻሪ
የአባት ወግን ሻሪ
ስንት ባህር ገሎ
ስንት ወንዝ አጉድሎ
ሽህ ዓመት አክባሪ
የየዋህነቱን የታዳጊነቱን የአፍቃሪነቱን ልክ መቁጠር ቢታክትም
ርግማን ሆኖብን ባበሻ ምድር ላይ ደግ አይበረክትም።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa