Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ

Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ

Share

ክፍለ ከተማችንን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት !!

ይህ የፌስቡክ ገጽ ትክክለኛው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

This is the official page of Kolfe Keranio Communication.

03/06/2026

#አገልግሎት አሰጣጥ ቅኝት

''አገልግሎት አሰጣጥ ከተገልጋይ አንደበት በኮልፌ''

#ኮልፌ ዜና

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 26 /2018 ዓ.ም

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፦
https://linkmix.co/48811202

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 03/06/2026

ዛሬ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ውይይት አድርገናል።

በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) ላይ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ከተማችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Today, we held discussions with H.E. Stian Christensen, Ambassador of Norway to Ethiopia.

We had a productive exchange with the Ambassador on areas of mutual cooperation in preparation for the upcoming Nordic Africa EV Summit, which will be held in Ethiopia this September.
During our discussion, I emphasized that our city has developed considerable experience and capacity in successfully hosting major continental and international events and is increasingly emerging as a preferred destination for such gatherings. I assured the Ambassador that, in close collaboration with all relevant stakeholders, we will organize this summit with the highest standards of professionalism and excellence.
Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

03/06/2026

“የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል” - ኡሁሩ ኬንያታ

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር የግምገማ ውጤት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ባሳዩት ድንቅ የሆነ አፈጻጸም በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል።

“ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ በቁርጠኝነት ለመምረጥ ተሰልፈዋል፤ ይህን ታላቅ ሁነት በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ተመልክተነዋል፤ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የታዘብነው ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ሲሉ አጠቃላይ ሁኔታውን ገልጸውታል።

“ኢትዮጵያውያን ታሪክ ይሠራሉ፤ ቀኝ ገዢዎችን በጋራ ተዋግተዋል፤ ይህም በአፍሪካ ብቸኛ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል፤ የአፍሪካ የነፃነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ቀጠሮ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የምርጫውን ታማኝነት እና ዴሞክራሲያዊነት ስንከታተል ነበር ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ የሠራው ሥራ መራጮች ሳይደናገሩ ድምፅ እንዲሰጡ እንዳስቻለ አንሥተዋል።

በምርጫው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት በነጻነት ሲከታተሉ እንደነበር ጠቁመው፣ “በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለውን ታላቅ ቁርጠኝነት የታዘብንበት ነበር” ብለዋል።

03/06/2026

አዎ የኢትዮዽያ ህዝብ ሊኮራ ይገባል!!!

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 03/06/2026

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 03/06/2026

በሀገር በቀል እዉቀት ፣ በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 03/06/2026

በክፍለ ከተማው አስተዳደር የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣንና አስተማማኝ በመሆናቸው መጉላላቶችን ማስቀረት እንደተቻለ ተገልጋዮች ገለፁ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ግንቦት 26/2018ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣንና አስተማማኝ እየሆኑ በመምጣታቸው ከዚህ ቀደም የነበሩ መጉላላቶችና ቀጠሮዎችን ማስቀረት ተችሏል ሲሉ ያነጋገርናቸው ባለጉዳዮች ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የአገልግሎት ቀን የሆኑትን ረቡዕና አርብን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች የተገልጋዮችን ሀሳብ አስተያየት አነጋግሯል።

ተገልጋዮቹም በሰጡት ሀሳብ ከክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀድሞ ከነበረው አንፃር በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ በተሻለ አቀባበልና ምላሽ አገልግሎቶችን እያገኘን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ተገልጋዮቹ አክለውም ቀድሞ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች መጉላላት የበዛበት እንዲሁም ረጅም ቀጠሮ የሚሰጥበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናገኘው አገልግሎትና የመረጃ ተደራሽነት እያደገና እየተሻሻለ የመጣ በመሆኑ በጣም ጥሩና ፈጣን አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የባለጉዳይን ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚሰጠው አገልግሎት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች!

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪዎች በፅናት ለሊት ቀን ሳይል ወጥቶ በነቂስ የመረጠውን ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 02/06/2026

የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤቶችን እየተመለከተ ነው!!

እስከ እኩለ ሌሊት ተራዝሞ የተጠናቀቀውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ የድምፅ ቆጠራ ሥራው ወዲያውኑ የተጀመረ ሲሆን፣ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤቶች መለጠፍ ተጀምረዋል።

ሕዝቡም በየአካባቢው ወደሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በማምራት የተለጠፉትን ውጤቶች እየተመለከተ ነው።

በአሁኑ ወቅት በምርጫ ጣቢያዎቹ ይፋ እየተደረገ ያለውን ውጤት ኅብረተሰቡ በሰላማዊ ሁኔታ እና በከፍተኛ ጉጉት እየተከታተለ ይገኛል።

ኮልፌ ኮሙዩኒኬሽን ግንቦት 25/2018ዓ.ም

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Kolfe
Addis Ababa