Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

Share

Ethiopian Press Agency is a public media enterprise operating in Ethiopia.

01/06/2026

ምርጫ የሀገር ሰርግ ነው - - ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

01/06/2026

"የኢትዮጵያ ምርጫ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው"
-ኡሁሩ ኬንያታ

+++++++++++

| የኢትዮጵያ ምርጫ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ።

ኡሁሩ ኬንያታ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከአሁን ያለው የምርጫ ሂደት ያለምንም ችግር እየተከናወነ ነው፡፡

የምርጫ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው ተከፍተዋል ዜጎች በንቃት ድምጽ እየሰጡ ነው ያሉት ኡሁሩ፤ የምርጫ ሂደቱ በታሰበው መልኩ እየተካሄደ መሆኑን መታዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው ያሉት መሪው፤ የምርጫ ቦርድ ባለው ሙያዊ ብቃት መገረማቸውንም አንስተዋል ።

ምርጫው በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መልኩ ደህንቱ በተጠበቀ መልኩ እየተካሄደ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

በዳግማዊት አበበ
++++++++++++
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #ጋዜጣ ፕላስ #በምርጫብቻ #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ #ዲሞክራሲ

01/06/2026

በምርጫ ሂደቱ ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አልታየም - ኢሰመኮ

+++++++++++++++++++++

፡ እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አለመታየቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኮሚሽኑ ቡድን በአርባምንጭና በጅማ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደትን ተመልክቷል፡፡

በዚህ ወቅት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እንዳሉት፣ ለአካል ጉዳተኞች ጭምር የተመቻቹ የምርጫ ጣቢያዎች ተመልክተዋል።

የምርጫ መስፈርቶችን ያሟላ የምርጫ ሂደትን መታዘባቸውንም ተናግረዋል።

የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና መስተጓጉል ያልታየበት መሆኑን ጠቅሰው፥ ቡድኑ እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አለመመልከቱን ገልጸዋል።

የምርጫ ታዛቢዎች እና መራጩ ዜጋ በሰዓቱ በምርጫ ጣቢያው በመገኘት ምርጫውን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ በ175 የምርጫ ክልሎችና ከ2 ሺህ 700 በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመታዘብ ሥራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በምርጫ ሂደቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በመከታተልና በድህረ ምርጫ የሚኖረውንም ሂደት በአግባቡ በመምራት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በምርጫ ሂደቱ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ በተዘጋጀው የቅሬታ መከታተያ ስርዓትም የምርጫውን ሂደት እየተከታተለ እንደሆነ አስረድተዋል።

ምርጫው ሕብረተሰቡ ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመራውን አካል በድምጹ የሚያረጋግጥበት በመሆኑ እንደሀገር ለመምረጥ የተመዘገበው ከ54 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ በመምረጥ ሕገመንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው

01/06/2026

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ነቢሀ መሀመድ አብድልሀኪም በሀላባ ምርጫ ክልል ቁጥር አንድ በሸኖ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

01/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉን ጨምሮ የቦርዱ ከፍተኛ አመራሮች የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደትን እየተከታተሉ ነው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ ማሲንጋም ከቦርዱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

01/06/2026

ከሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች መረጃዎች ይደርሱናል

01/06/2026

ሚስጥረስላሴ ታምራት፣ ከትብብር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 19፣ ኮከብ ሸማች ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን ሰጡ

01/06/2026

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች በመላ ሀገሪቱ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

++++++++++++++++++++++

| በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች በመላ ሀገሪቱ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ድምጽ የሚሰጥባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ስዓት ጀምሮ እንዲከፈቱ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ከ50 ሺህ 188 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተክፍተው ድምጽ እየተሰጣባቸው ይገኛል።

695 የምርጫ ጣቢያዎች ከ12 ስዓት በኋላ መከፈታቸውን እና 143 የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በጸጥታ ምክንያት አለመከፈታቸውን አስታውቀዋል።

የቁሳቁስ ስርጭትንም በሚመለከት በሁሉም የምርጫ ጣቢያ በትናንትናው ዕለት እስከ ምሽት 12 ስዓት አካባቢ ድረስ ተደራሽ ሆኗል ብለዋል።

የምርጫ ጣቢያውን ነጻ እና ገለልተኛ መሆኑን የሚያረጋግጡ የምርጫ ታዛቢዎች በ39 ሺህ 723 የምርጫ ጣቢያዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች ባጋጠመ የጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫው ተጀምሮ የተቋረጠባቸው ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውንም አንስተዋል።

በ41 ሺህ 978 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩ ተወካዮች መገኘታቸውንም አስታውቀዋል።

በዲጅታል የተመዘገቡ መራጮች የገጽ ቁጥር ባለመገኙቱ ረጃጅም ሰልፎች መኖቸራውን አንስተው፤ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች በመላ ሀገሪቱ ድምጻቸውን እየሰጡ ናቸው

በሄለን ወንድምነው
+++++++++++++
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #ጋዜጣፕላስ #በምርጫብቻ #ምርጫ2018 #ጋምቤላ #ኢትዮጵያ #ዲሞክራሲ

01/06/2026

“የመራጩ ህዝብ ሌሊት በነቂስ ወጥቶ መምረጥ በአገሩ ጉዳይ ላይ ያለዉን የእኔነት ስሜት የሚገልጽ ነው”
- ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

+++++++++++++

፡ የመራጩ ህዝብ በሌሊት በነቂስ ወጥቶ መምረጥ በአገሩ ጉዳይ ላይ ያለዉን የእኔነት ስሜት የሚገልጽ መሆኑን ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በምርጫ ክልል 28 በዛጎል ትምህርት ቤት አካባቢ የምርጫ ጣቢያ ተገኝቸዉ ድምጽ ሰጥተዋል።

ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል በዚሁ ወቅት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ መራጩ ህዝብ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ተሰልፎ እና ወረፋ ጠብቆ በመምረጥ ለምርጫዉ ያለዉን ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል።

የመራጩ ህዝብ በሌሊት በነቂስ ወጥቶ መምረጥ በአገሩ ጉዳይ ላይ ያለዉን የእኔነት ስሜት የሚገልጽ መሆኑን የተናገሩት ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል፣ ይህም ህዝቡ ለመምረጥ የማንም ቅስቀሳ እንደማያስፈልገዉ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርጫ አገር የምናስቀጥልበት፣የምናጸናበት እንዲሁም ዲሞክራሲ የምንለማመድበት ነዉ ያሉት ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል፣ ለአገር ዋጋ የሚከፍለዉ እና የማይከፍለዉ የሚለይበትም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

በመዓዛ ማሞ
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #ምርጫ

01/06/2026

"ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል"
- የአብን የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ከድር ይመር
++++++++++++

፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ከድር ይመር ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀም ጥሪ አቀረቡ።

በደሴ ከተማ በተወከሉበት የምርጫ ክልል ድምጽ የሰጡት አቶ ከድር፤ የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኅብረተሰቡ ይበጀናል ያለውን በካርዱ እየመረጠ እንደሆነም አብራርተዋል።

የምርጫ ሂደቱ መልካም መሆኑን ያነሱት እጩ ተወዳዳሪው ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመኾኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

https://t.me/ethpress

Address


Arat Killo/Arada Sub City
Addis Ababa
30145