02/06/2026
#የተሟላ ግልጋሎት ለመሰጠት በሰሚት #
(ሲቲ ባስ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሰሚት ቅርንጫፍ የመማክርት ጉባኤ አባላት ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና በየደረጃው ካሉ የስራ መሪዎች ጋር እየተከናወኑ የሚገኙ አገልግሎቶች ምን እንደሚመስሉ ውይይትና ግምገማ ተካሄደ፡፡
የትራንስፖርት እጥረትና የአገልግሎት አሰጣጥ መስተጓጎል እንዳይፈጠር የአውቶቡሶቻችን እንቅስቃሴ በተመደቡበት መስመር የአገልግሎት አሰጣጡ ምን እንደሚመስል ተነጋግረን የመፍትሄ እቅጣጫዎችን አስቀምጠን እንወያያለን ሲሉ የመማክርት ጉባኤው ዋና ሰብሳቢ አቶ ማርቆስ ለማ ተናግረዋል።
የሰሚት ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሱ አሰፋ እንዳሉት ስራዎችን በጋራ ተነጋግሮና ተባብሮ መስራት ለኛ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል ከመማክርት ጉባኤው ጋር በርካታ ስራዎችን በመስራት ውጤት ያመጡ ክንውኖች ከመፈጠራቸው ባሻገር ለቀጣይም ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል ። አያይዘውም ቅርንጫፋችን በጋራ መኖሪያ አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ፍሰቱ ስለሚበዛ ህብረተሰቡ በጠየቀን ጥያቄ መሰረት ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ እርብርብ አድርገን ለማህበረሰቡ ምላሽ በመስጠት ማህበረሰቡም ከኛ ጋር በመሆን አብሮነታቸውን አሳይተውናል ብለዋል ።
በውይይቱ ወቅት በቅያሬ ሰአት የሚነሱ ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ክትትል በማድረግ ቁጥጥሩን በማጠናከር የትራንስፖርት ጥያቄዎቹ የተፈቱበት ሁኔታ መፈጠሩ ተነስቷል ፡፡ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጠን ለማሳለጥ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ሁሉም አካል ይገነዘባል በመሆኑም በቀጣይ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል በማለት በውይይቱ ወቅት መገባባት ላይ ተደርሷል፡፡
እንዲሁም ከመድረኩና ከቤቱ በተነሱ ሃሳቦና ጥያቄዎች መሰረት የቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደሱ አሰፋ ማብራሪያና ምልሽ ሰተዋል ፡፡ በመጨረሻም የመማክርት ጉባኤ አባላቶች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ውስጥ የተሰሩ በርካታ ስራዎችንና የሌማት ትሩፋቶችን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
30/05/2026
# አገልግሎትን ለማሻሻል ምክክር በመከኒሳ #
(ሲቲ ባስ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የመከኒሳ ቅርንጫፍ የመማክርት ጉባኤ አባላት ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና በየደረጃው ካሉ የስራ መሪዎች ጋር የአገልግሎት አሰጣጡ ምን እንደሚመስል ውይይትና ግምገማ ተካሄደ፡፡
በመከኒሳ ቅርንጫፍ የተገኘው የመማክርት ጉባኤው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ላይ አውቶቡሶቹ በተመደቡብት ቦታ መስራታቸውን የቁጥጥርና ስምሪት ሂድታቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም በአገልግሎቱ ተደራሽነት ዙሪያ ላይ ተወያይተን የመፍትሄ እቅጣጫዎችን እናስቀምጣለን ሲሉ የመማክርት ጉባኤው ዋና ሰብሳቢው አቶ ማርቆስ ለማ ተናግረዋል ።
የመከኒሳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ከልሌ እንዳሉት የኦፕሬሽን ስራ ዘርፈ ብዙና ሰፊ ሰራ በመሆኑ ክትትልና ቁጥጥር የሚፈልግ እንደሆነ ይታወቃል በኛ ቅርንጫፍ በኩል አውቶቡሶቻችንን በተመደቡበት መሰመር ላይ በጠንካራ ቁጥጥርና ስምሪት አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል ። አያይዘውም ለካፒቴኖቻችንና ለአገልግሎት ክፍያ ተቀባዮቻችን በስራው ዙሪያ ግንዛቤዎችን በመስጠት እንዲሁም የከተማውን ውበት ለመጠብቅ ንፅህናቸው የተጠበቀ ባሶችን ማሰማራት ችለናል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በውይቱም መስመሮችን በማራዘምና አዳዲስ መስመሮችን በመክፈት የማህበረሰባችንን ፍላጎት ከፍ ለማድረግና ግጋሎቱን ለማስፋት ከማገዙም ባሻገር የተሳለጠ ትራንስፖርት እንዲኖር ለማስቻል ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በቀጣይም የመማክርት ጉባኤው ጋር በጋራ በመስራቱ ጥሩ ክንውን እንደሚመጣ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ከመድረኩና ከቤቱ በተነሱ ሃሳቦና ጥያቄዎች መሰረት የቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ከልሌ ማብራሪያና ምልሽ ሰተዋል ፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
30/05/2026
ሁሌም የከተማዉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዘላቂነት ዋስትና ሆነው ያገለግላሉ።
(ግንቦት 22/ 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መጭዉን 7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የትራንስፖረት እጥረት እንደማይኖር አሳዉቋል፡፡
የኢንተለጀንት ትራንስፖርት ሲስተም ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደገፉ ገ/መድህን ሰኞ ለሚከናወነዉ ለ7ኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማችንና አጎራባች ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎቱ ለህብረተሰቡ ምቹና ዘላቂ እንዲሆን በተለመደዉ በሁሉም መስመሮቻችን መደበኛ የትራንስፖርት ስምሪት የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡
ኃላፊዉ አያይዘዉም የትራንስፖርት እንቅስቃሴዉን የሚሰጡት የኦፕሬሽን አጠቃላይ ሰራተኞቻችን ማለትም ሾፌር፤ የአገልግሎት ክፍያ ተቀባዮች፤ስምሪት እንዲሁም ቁጥጥርን ጨምሮ እንደየስራዉ ባህሪ በተቃራኒ ሽፍት ምርጫዉን ያከናዉናሉ ያሉ ሲሆን እንደየ ማህበረሰቡ እንቅስቃሴ መኪኖች ስምሪት ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
29/05/2026
# ውይይትና ምክክር ለአገልግሎት ጥራት #
(ሲቲ ባስ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሸጎሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የመማክርት ጉባኤ አባላቶች ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና አመራሮች ጋር በተሰሩ ስራዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውይይትና ግምገማ ማካሄዱ ተገለፀ ፡፡
የመግቢያ ንግግሩን ያደረጉት አቶ ማርቆስ ለማ የመማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ የመማክርት ምክክር ስናደርግ ስራዎችን በመደጋገፍና በመከታተል ድልድይ በመሆን አገልግሎትን ለመሻሻል ተደራሽ የሆነ ትራንስፖርት ለማህበረሰቡ ለማቅረብ እንዲያስችል ይረዳናል ብለዋል፡፡
የሸጎሌ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጌጤ ሃብቴ በብኩላቸው በቅድሚያ የመማክርት ጉባኤውን አመስግነው በቅርንጫፉ 84 መስመሮችን በ13 ተርሚናሎች በከፍተኛ ቁጥጥርና በተሳለጠ ስምሪት ንፅህናቸው የተጠበቀ አውቶቡሶቻችንን በማሰማራትና በከፊል ተደራሽ በመሆን የከተማዋንና የሸገር ሲቲን ጨምሮ ጥሩ ግልጋሎት እየሰጠንና የማህበረሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ትኩረት ሰጥተን እየሰራንና እያገለገልን እንገኛለን ብለዋል ። አያይዘውም በመማክርት ጉባኤውና በተቋማችን በኩል ስራውን የጋራ አድርጎ በመስራት በርካታ ለውጦች መምጣታቸው እውን ነው ብለዋል ።
በተጨማሪም ይህ ጉባኤ ለቀጣይም ከእኛ ጋር ታች ድረስ ወርዶ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ተሻጋሪ ስራዎችን በጋራ እንደምንሰራ ሙሉ እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
ስራ አስፈፃሚዋ እንዲሁም በቅርንጫፋችን በኩል ክመደበኛ እጥበት ባሻገር ቅዳሜ ቅዳሜ የቢሮ ሰራተኛውን በማስተባበርና በጥሩ ተነሳሽነት ስሜት የአውቶቡሶቻችንን ንፅህና በርብርብ በማፅዳት ፅዱና ውብ የሆኑ መኪናዎችን ለማቅረብ ጥረት በመደረጉ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል ።
በመጨረሻም የመማክርት ጉባኤ አባላቶች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ውስጥ የተሰሩ በርካታ ስራዎችንና የሌማት ትሩፋት ተግባራትን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
29/05/2026
የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ማሳደግ፣
(ግንቦት 20/ 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የማዕከልና የ5 ቅርንጫፍ ስራ አስፈጻሚዎች ፤የዘርፍ ዳይሬክተሮች ፤የከተማዉ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የክ/ከተማ ምምህራን ማህበር ተወካዮች በተገኙበት በመምህራን ትራንስፖርት አጠቃቀም ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ፡፡
አቶ አካሉ አሰፋ የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ትራስፖርት የሚፈልግ ከተማ መሆኑን ጠቅሰዉ በቀን 212 መስመሮችን ላይ ተደራሽ በመሆን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች ተቋሙ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡
አቶ አካሉ አክለዉም አዲስ አበባ መስተዳደድር በልዩ ዉሳኔ የመምህራንን ማርፈድ ለተማሪዎች እዉቀት ሽግግር ችግር እየሆነ መምጣቱን በመረዳት መምህራኖች ቀድመዉ ስራቸዉ ላይ እንዲገኙ ቅድሚያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ለተነሱ የገልግሎት አሰጣጥና አጠቃቀም ችግሮች ግንዛቤ በመፍጠር ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት ደህንነቱ የተጠበቀና ሙሉ አገልግሎት በመስጠት ገቢን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ሃላፊዉ አያይዘዉም ለተቋሙ ቀጣይነት አገልግለሎት ተጠቃሚዉ በታመኝነት መስተናገድና እዛም እዚህ የሚነሱ ስነ ምግባር ችግሮችን በማስተካከል ህዝብን ማገልገል ይገባል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለመምህራን አአዲስ አበባ የከተማ አዉቶቡስ ትልቅ እገዛ ያደረጉልን መሆኑን መሆኑን በመረዳት መምህራንም የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው ለአገልግሎቱ ችግር የሆኑትን ሁሉ በመለየት በአሰራሩ መሰረት የመጠቀም ኃላፊነት ከሁሉም ይጠበቃል ያሉ ሲሆን አንድ በመሆንና በመተባበር የተነሱ ችግሮች በሂደት ይፈታሉ ብለዋል፡፡
አቶ ደገፋ ገ/መድህን በበኩላቸዉ ለአገልግሎቱ ምቹነት ሂደቱን ጠብቆ ለችግሮች መፍትሄ እየሰጡ በመሄድ ጥሩ ስነ ምግባር መያዝና ሚዛናዊ መሆን አስፈላጊ ነዉ ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ለሚያነሳዉ ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ኃላፊነትና ግዴታን አዉቆ በመጠቀም በስነ ምግባርና በአሰራሩ መሰረት ማገልገል ወሳኝ ነዉ ብለዋል፡፡ ፡፡
በመጨረሻም በዉይይቱ ለተነሱ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች ሁሉም የስራ ሃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ በመግባባት ተጠናቋል፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
28/05/2026
# የላቀ አሰራር የተሳለጠ አገልግሎት #
(ሲቲ ባስ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም) አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በየካ ቅርንጫፍ 24 በሚገኝዕው በማናጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የመማክርት ጉባኤ ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና በየደረጃው ካሉ የስራ መሪዎች ጋር የአገልግሎት አሰጣጡ ምን እንደሚመስል ውይይት ተካሄደ፡፡
የካ ዲፖ የተገኙት የመማክርት ጉባኤው አባላትና ዋና ሰብሳቢ አቶ ማርቆስ ለማ እንዳሉት የመማክርት ጉባኤው ዋናው አላማው ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን ትራንስፖርት ተደራሽ ሆኖ ማየትና ግቡን የመታ አግልጋሎት እንዲያጠናክር ቀጣይነት ያለው ስራ በመስራት አቅጣጫዎችን በማሰቀመጥ ተጋግዘንና ተባብረን የተሳለጠ ስራ ለመስራት እንዲያግዘን በጋራ በመሆን ይህ ውይይት ውጤት ተኮር ስራ እንድንሰራ ያግዘናል ብለዋል ፡፡
የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምሩፅ ታዬ እንዳሉት በኛ ቅርንጫፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ የአፈጻጸሙም ውጤት የሁሉም ሰራተኞች ውጤት መሆኑን ገልፀው በ56 መስመሮች በዋና ዋና ተርሚናሎችና ኬላዎች ንፅህናቸው የተጠበቀ አውቶቡሶቻችንን በተጠናከረ ቁጥጥርና ስምሪት በማሰማራት ምልልሳችንን በመጨመር ለህብረተሰባችን ተደራሽ መሆን ችለናል ብለዋል ፡፡ አያይዘውም ወርክ ሾፖችንን በመጠቀም ወጪን ለመቀነስ ሞደፊኬሽኖችን በማምረት መኪናዎቻችንን ጠግነን ማውጣት የቻልንበት ሁኔታ ተፈጥሯል እንዲሁም የማህበረሰቡን ጥያቄ በመፍታት በተገቢው መንገድ ምላሽ የመስጠት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም እንደ ቅርንጫፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩና ውጤትም እያመጡ በመሆናቸው አገልግሎቶችን በማጠናከር ግስጋሴያችን ይቀጥላል ብለዋል ፡፡
እንዲሁም ከመድረኩና ከቤቱ በተነሱ ሃሳቦና ጥያቄዎች መሰረት የየካ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምሩፅ ታዬ ማብራሪያና ምልሽ ተሰቷል ፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
26/05/2026
በጥናት የታገዘ ስራን መስራት ለላቀ ለውጥ
(ሲቲ ባስ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሪክቶሬት በንብረት አስተዳደር ዙሪያ እያደረገ ያለውን ጥናት አስመልክቶ ከጥናት ቡድኑ ጋር በዛሬው እለት ግምገማ አካሄደ፡፡
ጥናቱ እየተካሄደ ያለው በስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ሲሆን ጥናቱ እየተካሄደ ያለው በመአከልና በአምስቱም ቅጽ/ቤት ነው፡፡
የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሪክቶሪት አቶ ብርሀኑ አበበ የጥናቱን አስፈላጊነት ሲገልፁ የተቋሙን የንብረት አስተዳደር በመፈተሽ ግልጸኝነትን ለማምጣት ያስችላል ብለዋል፡፡
አክለውም ጥናቱ እየተካሄደ ያለው በንብረት አስተዳደር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶች ካሉ በጥናት በመለየት ምክረ ሀሳብ ለተቋሙ ለማቅረብ በዋነኛነት አተኩሮ ይሰራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በአጠቃላይ ጥናቱ እየተካሄደ ያለው መጠይቅ በመበተንና ቃለ መጠይቅ በማድረግ እንዲሁም ለጥናት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያሟላ እንደሆነና ጥናቱ በአሁን ሰአት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነ በግምገማው ለመረዳት ተችሏል፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
26/05/2026
#የአገልግሎት-ጥራትን-በማሻሻል-የደንበኛን እርካታ-ማሳደግ
(ሲቲ ባስ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የመማክርት ጉባኤ ከቅርንጫፉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና በየደረጃው ካሉ የስራ መሪዎች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄደ፡፡
የመማክርት ጉባኤው የድርጅቱን አገልግሎት ምቹና የተሳለጠ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑን የገለፁት የመማክርት ጉባኤው ሰብሳቢ አቶ ማርቆስ ለማ የመማክርቱ እቅድ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ፣ በዘርፉ የሚነሱ ቅሬታዎችን መቀነስ፣ አገልጋይና ተገልጋንይን በማቀናጀት ድልድይ ሆኖ መስራት የሚሉ ግቦችን የያዘ ነው ብለዋል፡፡
የቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጠረፍ ማሞ እንዳሉት አገልግሎት ሰጪ እንደመሆናችን መጠን ቅርንጫፋችን 60 መስመሮችን በመሸፈን ንፅህናው የተጠበቀ አውቶቡስ በማቅረብ ለማህበረሰባችን እየሰጠን ያለውን አገልግሎት ይበልጥ በማሻሻል የስምሪት ስርዓታችንን በማስተሳሰር የተሳለጠና ተደራሽ የሆነ ትራንስፖርት እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል ፡፡
አክለውም የመማክርት ጉባኤው ትራንስፖርቱን ውጤታማ ለማድረግ እስከ ታች ድረስ ወርዶ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከእኛ ጋር አብሮ በመስራቱ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለው ብለዋል ፡፡
እንዲሁም ከመድረኩና ከቤቱ በተነሱ ሃሳብና ጥያቄዎች መሰረት የቃሊቲ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጠረፍ ማሞ ማብራሪያና ምልሽ ሰጥተዋል ፡፡
በመጨረሻም የመማክርት ጉባኤ አባላቶች በቃሊቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ውስጥ የተሰሩ በርካታ ስራዎችን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]
25/05/2026
የወርቃማ ሰኞ-ማለዳ- የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አስቀጥሏል።
(ሲቲ ባስ፤ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያካሂደዉ የአብሮነት እና የእውቀት ሽግግር መርኃ-ግብር በማዕከል የስብሰባ አዳራሽ ተከናዉኗል።
በዛሬዉ መርሃ-ግብር የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በጤና ምርመራ እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው መርሃ-ግብር ላይ የገበያ ጥናትና ገቢ ማጎልበት ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ልዑል አበበ ዳይሬክቶሬቱ ስር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራቶችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት የገበያ ጥናት ማድረግ ፤የማስታወቂያ ስራን መከታተል፤ወቅታዊ የግዥ ጥናት ማካሄድ ፤ለዉስጥና ለዉጭ የቦሎ ምርመራ ማከናወን፤የዉጭ ተሸከርካሪ ጥገና መስራት ሲሆኑ በቀጣይ የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ ማስታወቂያ የተለጠፈባቸዉ መኪኖች ጽዳት ከቅርንጫፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ቢሰራበት የሚል ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አካሉ አሰፋ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ስፖርት አለም አቀፋዊ ስለሆነ የተቋማችንን ገጽታ ማስጠራትና መገንባት ከሁሉም የሚጠበቅ ነዉ ያሉ ሲሆን በቀጣይ ሰኔ ወር ተቋማችን ለሚያዘጋጀዉ ቤተሰባዊ ስፖርት ዉድድር በተለያዩ ስፖርት አይነቶች የማዕከልና ሁሉም ቅርንጫፍ ተሳታፊ ስለሚሆን ከዘሬ ጀምሮ በጥቅማጥቅም ቢሮ በአካል በመመዝገብ ዉድድሩንም ፍቅርና መግባባት የሰፈነበት ተቋም በማድረግ ጠንካራ ዉድድር አድርገን ለዋናዉ ቡድናችን ጠንካራ ስፖርተኛ የምናገኝበት ዉድድር ይሆናል ብለዋል፡፡
23/05/2026
# ስራን ለማሳለጥ የተሻለ መማክርት #
(ሲቲ ባስ 15/09/18 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 22 በሚገኘው ዋና መ/ቤት የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ውስጥ ከመማክርት ጉባዬ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥንና እየተከናወኑ ያሉትን የስራ ሂደቶች ዙሪያ ላይ ውይይትና ግምገማ ተካሄደ ፡፡
ውይይቱን የመሩት የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙላቱ ፅጌ ሲሆኑ የዛሬው ውይይታችን የተሰሩ ስራዎችንና እየተከናወኑ ያሉትን በአገልግሎት አሰጣት ዙሪያ በእኛ በኩል ትኩረት አድረግን መከታተልና መገምግም ይገባናል ሲሊ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ከመማክርት ጉባዬ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በቀጣይ ሳምንት በጋራ በምናደርገው ውይይትና ግምገማ ጥሩ አፈፃፀም እንደምናስመዘግብ እውን ነው ብለዋል፡፡
የመማክርት ጉባዬ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዳሉት ለህብረተሰቡ እየተሰጠ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በይበልጥ ተጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይ ሳምንት ለተከታታይ 5 ቀናቶች ውሰጥ በቅርንጫፍ በኩል እየተከናወኑ ላሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን በመዳሰስ የመወያየትና የመገምገም ስራ እንደሚከናወን አቅጣጫ ተሰቶ ወደ ስራ እንደሚገባ የመማክርት ጉባዬ ስራ አስፈፃሚ አቶ ማርቆስ ለማ አሳውቀዋል ፡፡
በመጨረሻም ከኮሚቴዎቹ በተነሱ ሃሳብና ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በቀጣይ ሳምንት በጋራ በመሆን እየተከናወኑ ያሉትን የስራ እንቅስቃሴዎች የሚቃኝ መሆኑን የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙላቱ ፅጌ ገልፀዋል ፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም: https://t.me/citbus
ዩቱብ: https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]