Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing

Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing, Political organisation, lideta church area, Addis Ababa.

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 05/03/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው እለት የ7ኛው ሀገራዊ እና ከተማ አቅፍ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም አካሄደ።
በመድረኩም ብልፅግና ፓርቲ ወጣቱ የሀገሪቱ የብልፅግና መሠረት መሆኑን በማመን በኢኮኖሚው ዘርፍ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ መደረጉን የተጠቁማል።
በውይይቱ ላይም የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ም/ል እና ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ጋረደው ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች የሥራ ዕድል ዋስትና በመሆን ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው። ​ብልፅግናን መምረጥ የኢትዮጵያን አንድነት ማስቀጠል፣ ሰላምን ማረጋገጥና የጀመርነውን የልማት ጉዞ ዳር ማድረስ ማለት ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎ በተጨማሪም የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት አቤል ሙሉጌታ ባለፉት አመታት በተለያዩ ደረጃዎች ለሚገኙ ወጣቶች የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት፣ ለሀገር ግንባታ የሚሆኑ ብቁ መሪዎችን የማፍራት ስራ የተከናወነ እና የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሁም በማህበራዊ ተሳትፎ ወጣቱ በሀገራዊ አንድነትና በበጎ አድራጎት ስራዎች ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲወጣ መደረጉን በመናገር ብልፅግናን መምረጥ የኢትዮጵያን አንድነት ማስቀጠል፣ ሰላምን ማረጋገጥና የጀመርነውን የልማት ጉዞ ዳር ማድረስ ማለት ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 17/02/2026

#የ130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ "የዓድዋ ድል በዳግም ዓድዋ ይጎመራል!!" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ወጣቶችና ሰፖርት ጽ/ቤት እና የብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ጋር በጋራ በመሆን "የዓድዋ ድል በዳግም ዓድዋ ይጎመራል!!" በሚል መሪ ቃል በወረዳው ከሚገኙ ወጣቶች የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

በውይይቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ወ/አረጋይ እንዳነሱት ዓድዋ ፣ የአንድነታችንና የአብሮነታችን ማሳያ፣ ጀግኖች አባቶቻችን ወራሪ ያሸነፉበት ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ጋረደው እንደገለፁት የጥቁር ህዝቦች መኩሪያ መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ታሪካዊ ዕሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ እንዲውል የወጣቱ ሚና እጅግ የጎላ መሆኑን ገልፀው ይሄን አኩሪ ድል ወጣቱ በስራ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል።

የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ረዳቱ ኪዳኔ እንደገለፁት በመጪው የካቲት 23 የሚከበረውን የ130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በድምቀት ለማክበር የታቀደ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የአድዋ ድል የጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የኢትዮጵያዊያን የአንድነት ማህተም በመሆኑ፣ ይህንን እሴት ለትውልድ ለማሻገር ማስቻል ይኖርብናል ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣት ክንፍ ሰብሰቢ ወጣት አቤል ሙሉጌታ በበኩላቸው የዓድዋ አንድነት ሊፈጠር የቻለው የዓድዋ ጀግኖች አባቶቻችን ከራሳቸው ጥቅም በፊት የሀገርና የሕዝብን ጥቅም በማስቀደማቸው እና “የኛ ጥቅም የሚረጋገጠው ሀገር ተጠብቃ ስትኖር ነው” የሚል ጠንካራ እምነት ስለነበራቸው ነው እኛ ወጣቶች ይሄንን የአባቶቻችን ታላቅ እምነትና የድል ለሀገራችን ጠንክረን በመስራት ማረጋገጥ ይኖረናል ብለዋል፤

በተያያዘም ወጣት አቤል ሙሉጌታ የወጣት ክንፍ አባላት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚኖራቸውን ሚናን በተመለከተ ማብራሪያና ገለፃ ሰጥተዋል።

የካቲት10/2018

10/02/2026

“የስንዴ ነዶ”፥ የ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ የፓርቲያችን ብልፅግና የመወዳደርያ ምልክት!

የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ነው። የስንዴ ነዶ፥ የመደመር፣ የአንድነት፣ ትብብርና የሉአላዊነት መገለጫ ነው።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 16/12/2025

" የዳበረ ዴሞክራሲ የሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው ! "

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ አመራሮች ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ክንፍ አመራሮች የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ሚናቸውን የሚያጠናክር የአሰልጣኞች ስልጠና ተጀምሯል ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ የህዝባችንን የዘመናት የዴሞክራሲ ጥያቄዎች የሚመልስ ፣ የሀገራችንን ብዝሀነት ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም የወደፊቱን ታሳቢ ያደረገ ፣ የፅንፈኝነት ፖለቲካን የሚገራ ፣ በሀሳብ የበላይነት የሚያምን የተግባቦት ፖለቲካን እየገነባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሀገራችን የዴሞክራሲ ምህዳር እየሰፋ መሆኑን የጠቃቀሱት አቶ ሞገስ የልዩነት ሀሳቦችን በማስተናገድ እና በማክበር በሀሳብ የበላይነት የሚያምን ዘመኑን የዋጀ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ብርቱ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ሁሉን አቀፍ በሆነው የብልፅግና ጉዞአችን እንዲሁም የከተማችን ተምሳሌትነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የከተማችን ወጣቶች እና ሴቶች የማይተካ ሚናቸውን እየተወጡ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ኋላቀር የፖለቲካ ባህልን በማስወገድ ፣ዴሞክራሲን በመገንባት ትውልዳዊ አሻራን ማሳረፍን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው የተገኙ ሲሆን ፤ በየደረጃው የሚገኙ የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ እና ወጣቶች ክንፍ አመራሮች የስልጠናው ተሳታፊዎች ናቸው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሚኤሳ ኤለማ "የዴሞክራሲ ባህል ምሰሶዎች " በሚል ርዕስ ስልጠናውን መስጠት ጀምረዋል።

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 25/11/2025

"በመንካባከብ ማንሰራራት"
🌲🌲🌳🌲🌳🌲🍀🌲🌳🍀☘️🌿

የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ከተማችንን ውብ ማራኪ በማድረግ የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን!!

የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመሆን ''በመንከባከብ ማንሰራራት'' በሚል ዕሳቤ የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ተወካይ፣ የልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ፣የወረዳው ጠቅላላ አመራሮችና ከየወረዳው የመጡ ወጣቶች የተሳተፉበት የችግኝ እንክብካቤ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ወረዳ 10 የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ተወካይ ሻ/ል በሻህ ንጉሴ እንደተናገሩት ችግኞችን መንከባከብና ማጽደቅ ለሀገሪችን የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ መሰረት መጣል መሆኑን ገልጸው ወጣቶች በክረምት የተተከሉ ችግኞችን ጊዜ በመስጠት ሊከባከባቸው እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

አክለውም አረንጓዴ አሻራ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ በመሆኑ በላቀ ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነትና አርዓያነት ማሳካት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የልደታ ክ/ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ተወካይ ወጣት ዘላለም ታመነ ክረምት የተከልናቸውን ችግኝ በበጋው እየተንከባከቡ እየኮተኮቱ ፅድቀት እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሚገባ በማስታወስ በክረምት የተከልናቸውን ችግኞች ተንከባክቦ ማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካል ቢሆንም በዚህ ተግባር ውስጥ የወጣቶች ሚና ትክ የሌለው እና ውጤታማ በመሆኑ ተቋሙ ይህን ተግባር በዘላቂነት እንደሚያስቀጥል ገልፀዋል።

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 06/11/2025

ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ ይገባል ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

አስተዳደሩ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላም እሴቶችን በማጎልበት ሰላምና አብሮነትን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለው ወጣቶች እነዚህን እሴቶች በማጠናከር አንድነትን፣ አብሮነትን እና መቻቻልን ሊያጠናክሩ ይገባል በማለት ገልፀዋል።

መድረኩ ወጣቶች ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀው ለትውልድ በማሸጋገር ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የክ/ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ ተናግረዋል፡፡

አቶ ቶሎሳ አክለውም ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጣቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለው ወጣቱ ለሰላም ለአብሮነትና ለአንድነት በጋራ መቆሙን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ ፣በበኩላቸው ወጣቱ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፈታት ባህልን የማዳበር ልምድ ሊያካብቱ ይገባል ብለው ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ የደርሻቸውን እንዲወጡ ለማሰቻል እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች እንደገለጹት መድረኩ ችግሮች ሲያጋጥሙ በውይይት የመፍታት ባህልን እንድናዳብር እና ሀገር በቀል የሠላምና የመቻቻል እሴቶችን ጠብቀን ለትውልድ ለማሻገር ከፍተኛ አስተዋፆ አለው ሲሉ ገልፀዋል።

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 27/10/2025

የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ 2017 ዓ/ም የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር መዝጊያና የ2018 በጀት ዓመት የበጋ በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ
ዶ/ር ሚኢሳ ኤሌሞ እንደገለጹት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላት ባሳለፍነው የክረምት መርሀ ግብር በርካታ የበጎፍቃድ ተግባራትን በመፈጸማቸው አያሌ ዜጎችን ተጠቃሚ ማረግ የቻሉበትና ከፍተኛ የመንግስት ወጪን ማዳን መቻላቸውን ገልፀዋል።የከተማዋ ወጣቶች በአጠቃላይ ተግባራት ላይ ያላቸው ተሳትፎና አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ወራት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።

የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በበኩላቸው ባሳለፍነው የክረምት ወራት በተከናወነው የበጎ ፍቃድ ተግባር ከ1 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ 400 ሚሊዮን ብር የሚገመት ተግባር መፈጸማቸውን በመግለፅ የከተማዋ ወጣቶች ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ከመወጣት አንጻር ከፍተኛ መሻሻሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ባሳለፍነው የክረምት ወራት ወጣቶች በቤት ዕድሳት፤በማዕድ ማጋራት፤በአረንጓዴአሻራ፤በደምልገሳ፤በጎነትበሆስፒታል፤በትራፊክ አገልግሎት፤በትምህርት ቤት ዕድሳትና የነጻ ትምህርት አገልግሎት በመሰማራት ከፍተኛ ተግባራት መፈጸማቸው በመግለጽ በተግባሩ አቅመ ደካማ ዜጎች መታገዛቸውንና በወጣቶች መሀል አብሮነትና መደጋገፍ መጎልበቱን ገልጸዋል።

በመድረኩ ባለፈው የክረምት በጎፍቃድ ለተከናወኑ ተግባራት ዕውቅና ሽልማት በመስጠት በቀጣይ በክንፉ አስተባባሪነት የሚከናወኑ የበጋ በጎ ፍቃድ ተግባራት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በበጋ በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ በልደታ ክፍለከተማ ወረዳ 9 የቤት ዕድሳት መርሃ ግብር ከማስጀመር በተጨማሪ ከሁሉም ክፍለከተማ የተውጣጡ ወጣቶች የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂደዋል።

Photos from Lideta Sub City Woreda 10 Prosperty Party Youth Wing's post 25/10/2025

#በስነ-ምግባር የታነፀ ወጣት ለሀገር ግንባታ ያለው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው!

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍና በወጣት ክንፍ አስተባባሪነት በስነ-ምግባር የታነፀ ወጣት ለሀገር ግንባታ" በሚል ርዕስ ለወጣቶች ክንፍ አባላት ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የወጣት ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ሳሙኤል ዋለልኝ እንዳነሱት ስነምግባር የሁሉም ነገር መነሻ መሠረት ነው ሲሉ አንስተው በስነምግባር የታነፀ ወጣት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ እጅግ የጎላ ሚና ይጫወታል ብለዋል፤

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ጋረደው እንደገለፁት ወጣትነት ኃላፊነት ካልታከለበት ለጥፋት ኃላፊነት ታክሎበት በስነምግባር ከታነፀ ደግሞ የሀገር ብልፅግና አውታር ነው ሲሉ አንስተው በአመለካከትና በተግባር የተሻለ ግንዛቤ ያለው ወጣት ለመፍጠር እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ትልቅ መሰረት ይጥላሉ ሲሉ አንስተው ፤ለሀገራችን ልማት ዕድገትና ለውጥ በስነምግባር መመራት ወሳኝ ነው ሲሉ አንስተዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ አስተባባሪ ወጣት አቤል ሙሉጌታ በበኩላቸው ስልጠናው የተዘጋጀው ወጣቱ ስነምግባር ለሀገር ሁለንተናዊ ግንባታ ወሳኝ እንደሆነ በመረዳት ሂደቱ ወጣቱ የእራሱ አሻራ እንዲያር በማሰብ ነው ሲሉ አንስተዋል

በዕለቱም በወጣቶችና ስፖርት፣በወጣት ክንፍና በወጣት ማህበር አስተባባሪት በልል ክህሎት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በተጋበዙ አሰልጣኝ ተጨማሪ ስልጠና ሰጥተዋል

ልደታ ወረዳ10 ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት15/2018ዓ.ም

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Lideta Church Area
Addis Ababa