Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination

Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination

Share

Youth and voluntary coordination

Clique para me ajudar! 31/05/2023

Clique para me ajudar! Só falta um pouquinho para ganharmos bônus de até R$150 juntos

Clique para me ajudar!

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 30/09/2021

መስከረም 20 / 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አዲስ ለተደራጀው የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስራ ርክክብ አደረገ ።
በአዲሱ ምክር ቤት በአዲስ መልክ የተዋቀረው የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ አብረሀም ታደሰ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ጋር የሁለትዮሽ የስራ ውይይት በማድረግ የስራ ርክክብ አካሂደዋል ።
ኮሚሽነር በላይ ደጀን አዲስ ለተሾሙት የቢሮ ሀላፊ ለአቶ አብርሀም ታደሰ እንኳን ደስ አሎት በማለት መልካም የአመራርና የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል ።
የ2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የስኬታማ ዘመንና ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የ10 ዐመቱንና የ5 ዐመቱን የስፖርት ልማት ዕቅድና ፍኖተ ካርታ መሠረት በማድረግ ተቋማዊ አሰራሮችን ማጠናከር ፣ ከስፖርቱ ቤተሰቦችና ባለድርሻ አካላት ጋራ ተቀራርቦ መስራት ፣ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ #ለወጣቶች ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አመላክተዋል ።
ቢሮው የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎችን ቁልፉ ተግባር አርጎ መንቀሳቀስ የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ተከታትሎ ማስጨረስ ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ የተረጋገጠበት ወንድማማችነትና ኢትዮጵያዊነት የታየበትን ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳትፎን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ፣ የትምህርት ስልጠናና ተኪ ታዳጊዎች ላይ መረባረብ ፣እና ለሁሉም ስኬት የአመራር ዲሞክራሲያዊ ውህደትን በግልፅነት ማስቀጠል መቻል እንደሚገባ ኮሚሽነሩ በውይይታቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::
ኮሚሽነር በላይ ደጀን ጋር የሁለትዮሽ የስራ ውይይት በማድረግ የስራ ርክክብ አካሂደዋል ።
ኮሚሽነር በላይ ደጀን የማኔጅመንት አባላት ፣ ሰራተኞች ፣ የሁሉም የስፖርት ቤተሰቦች ፣ ባለድርሻ አካላትና የስፖርት ሚዲያዎችና ጋዜጠኞችን አመስግነው ፣ለነበራቸው ቆይታና ለመጣው የጋራ ውጤት ከልብ ምስጋናቸውን በማቅረብ ወደፊትም ቢሮውን ባላቸው አቅምና ዕውቀት ለመደገፍ አብሮ ለመሥራት ቃል ገብተዋል ።
ይህ ሁሉ ድጋፍ ለጋራ ለውጥ በመሆኑ በዚሁ ልክ ሁሉም አዲስ ለተሾሙት የቢሮ ሀላፊ ለአቶ አብርሃም ታደሰ አጋርነታቸውን በመስጠት ለጋራ ለውጥ ከጎናቸው እንዲቆሙ በአደራ ጭምር ጠይቀው ለቢሮው ሀላፊ መልካም የስራ ዘመንንና የስራ ስኬትን ተመኝተዋል ።
አዲሱ ተሿሚ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው ከተማችን የያዘችውን ለውጥ በሁለንተናዊ ገፅታ ወደፊት ካስኬዱ ተቋማት አንዱ ስፖርት ኮሚሽን ሲሆን ለዚህም የአመራሩ ሚና የላቀ በመሆኑ ኮሚሽነር በላይ ደጀን በቆይታቸው ለሰሩት ስራና አመራር ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የአመራር መተካካት የተሰጠን ተልዕኮ በሚገባ በመፈፀም ለውጥ ማምጣት በመሆኑ በስፖርት ዘርፍ የተሰሩ ፣ በወጣቶች ዘርፍ የተሰሩ ስኬታማ ግቦቻችንን በማስቀጠል በጋራ ደሞ አቅደን ተልዕኮአችንን ከነበረው ከፍ አድርገን በጋራ ለውጥ በማምጣት የወጣቶቻችንንና የከተማችንን ነዋሪዎች ፍላጎቶች ለሟሟላት እንሰራለን ያሉት አቶ አብርሃም ለዚህም በከተማችን በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም ለመሆን ጥሩ ስራ መሥራት ፣ መደማመጥ ፣ መከባበርና መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል ።
በርክክቡና በጋራ የስራ ውይይት ላይ ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ለአረካካቢነት የተወከሉት ተወካይ አቶ ተክሌ ዲዶን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ማኔጅመንት አባላትና ስራ አስኪያጆች በተገኙበት የስራ ርክክቡ ተከናውኗል ።
ዘገባው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው ።

28/09/2021

መስከረም18/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አብረሃም ታደሰ በከተማ አስተዳደሩ በተዋቀረው አዲሱ ሹመት መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ በመሆን በመሾማቸው እንኳን ደስ አልዎት እንኳን ደስ አለን።
መልካም የስራ ዘመን ይሁንሎት!!

26/09/2021

መስከረም 15 / 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ የመስቀል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በመልዕክታቸውም የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ በመሆኑ የመስቀል በዐልን ስናከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመተሳሰብ፣ ማዕድ በማጋራት ፣ ወገንን በመጠየቅ በአብሮነት ማሳለፍ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ለከተማችን ነዋሪዎች ፣ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣ የተቋማችን ሰራተኞችና አመራሮች በሙሉ መልካም በዓል እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አቶ አብረሃም ታደሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 24/09/2021

መስከረም 14/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ከከተማችን ለተወጣጡ ወጣቶች በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሆቴል ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

ስልጠናውም በወጣቶች ሁለንተናዊ ማንነት፣በጋራ መኖርና መስራት፣የግጭት አፈታት ዘዴዎች፣በበጎ ፈቃደኝነትና ወጣቶች በሀገራዊ ለውጥ ሂደት ውስጥ በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ከውጭ በመጡና በሙያው ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል።

በመረሃ ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ፣ከከተማችን የተወጣጡ ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 24/09/2021

የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማዋል እየተሰራ ነው

መስከረም 14/2014 ዓ.ም

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማህበረሰቡ ወደተለያዩ ተቋማት በአካል በመሄድ የሚያገኛቸውን አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን ገለፀ፡፡

ከአዲስ አበባ 121 ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ሲናሞ÷ እስከአሁን ባለው ሂደት በ45 ተቋማት 226 የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች ለምተው ከ2 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮች የተለያዩ አገልግሎቶችን እያገኙ መሆኑን አውስተዋል::

የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3 ትሪሊን ዶላር በላይ የሚያንቀሳቅሱ እንደመሆናቸው እና ለወጣቶቻችንም የስራ እድል ለመፍጠር ምቹ ስለሆኑ ከወጣቶች ጋር በማስተዋወቅ ወጣቶች እንዲጠቀሙባቸውና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችንም እንዲጠቀሙ በማድረግ ገቢ ማግኘት እንደሚችሉ ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ተናግረዋል::

በመድረኩ በቀጣይ ወጣቶቹ በየወረዳው በሚገኙ የወጣት ማዕከላት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን ለአካባቢያቸው ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲያደርጉ እና አገልግሎቶችን እንዲሰጡ መልእክት የተላለፈ ሲሆን ÷ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለፁን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 23/09/2021

መስከረም 13/2014 ዓ.ም

በመዲናችን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ከ27ሺህ 500 በላይ በጎ ፈቃደኞች ወደ ስራ ገቡ።

ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ተውጣተው በፈቃደኝነት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ከ27 ሺህ 500 በላይ ወጣቶች ከዛሬ ጀምረው ወደ ስራ ስምሪት ገብተዋል።

ወጣቶቹ በከተማዋ ላይ ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር በራሳቸው ተነሳሽነት አካባቢያቸውን ለመጠበቅ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ናቸው።

“እኔ ለከተማዬ የሰላም ዘብ ነኝ ” የሚል መሪ ቃል ያነገቡት ወጣቶቹ የከተማዋን ሰላም የተረጋገጠ ለማድረግ የስራ ስምሪቱን በወሰዱበት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማእከል ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ሌሎች የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

‘’የከተማ አስተዳድሩ የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ሃላፊ ለከተማችሁ ሰላም አለኝታ ለመሆን ፈቃደኛ ሆናችሁ የህዝባችሁን ሰላም እንዲሁም ደህንነቱን ለማረጋገጥ ስልጠና የወሰዳችሁ ተመራቂዎች ላሳያችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና ይገባችኋል’’ ብለዋል።

ጠላት ሃገርን ሰላሟን ለማናጋት በሚሯሯጥበት በዚህ ወቅት የከተማዋ ህዝብ የጸጥታ አካላትን ለመደገፍ ያሳየው ድጋፍ የሚደንቅ ነውም ብለዋል።

ዛሬ መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና ወስዳችሁ ከጸጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር ሆናችሁ የጥፋት ቅጥረኞችን እና ጸረ ሰላሞችን ለመዋጋት ደጀን ለመሆን በመነሳታችሁ እና የተሰለፋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ኮርተንባችኋልም ነው ያሉት።

አሁን ያጋጠመንን ችግር ቀዳሚ ሆነን ለመከላከል እና ከፊታችን ላለው የኢትዮጵያ የመበልጸግ ተስፋ ለመድረስ አቅምና ሰራዊት ናችሁና የተሰጣችሁን ሃላፊነት በብቃት እንደምትወጡም ባለ ሙሉ ተስፋ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

በዚህም ለቀጣዩ ትውልድ አሻራችሁን እንደምታስቀምጡ እርግጠኞች ነን ብለዋል አቶ መለስ አለሙ።

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 22/09/2021

መስከረም 12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ "ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግስት" በሚል ሀሳብ የቢሮውና የሌሎች ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በርካታ የከተማችን ወጣቶች በተገኙበት የፊርማ ስነ ስርዓት መረሃ ግብር በየካ ክ/ከተማ አካሂዷል።

በተጨማሪም ከፊታችን ባሉት ቀናት የሚከበሩትን የኢሬቻና የመስቀል በዓላትን በማስመልከት ወጣቶች አከባቢያቸውን ከጥፋት ሀይላት ነቅተው እንዲጠብቁ፣ ከፀጥታ አካላትና ከፓሊሶች ጋር በመሆን ወንጀለኞችን በማጋለጥ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንዲችሉ በመረሃ ግብሩ መልዕክት ተላልፏል።

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 17/09/2021

መስከረም 07/2014 ዓ.ም

"የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት" በሚል መሪ ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ የወጣቶች የፊርማ ስነ ስርዓት አካሄደ።

በመረሃ ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ፣ የቢሮው ም/ሀላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ፣የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጣት መለሰ አባተ እንዲሁም ከሁሉም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶችና አመራሮች ተገኝተዋል።

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 16/09/2021

መስከረም /2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብራሃም ታደሰ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ሽታ በጋራ በመሆን በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ለማስተላለፍ በወረዳ 8 እየተገነባ የሚገኘውንና ከመስቀል በዓል በፊት ግንባታው እንዲጠናቀቅ ታስቦ እየተገነቡ የሚገኙትን 68 ቤቶች አሁን የደረሰበትን ደረጃ በቦታው በመገኘት ጎብኝተዋል።

Photos from Addis Ababa Bureau of Youth & Volunteers Coordination's post 14/09/2021

መስከረም 04/2014 ዓ.ም

"እኔ ለከተማዬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መሪ ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአከባቢያቸው ሰላም የቆሙ 259 ሰልጣኞችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከሁሉም ክ/ከተሞች የተወጣጡ የከተማችን በጎ ፈቃደኞች፣የስፖርት ቤተሰቦችና እንዲሁም 32 የሚሆኑ የፖሊስ አካላት በአጠቃላይ 259 ሰልጣኞችን የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ የከንቲባዋ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በመኮንኖች ክበብ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመርቀዋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ አካዳሚ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 259 በጎፈቃደኛ ወጣቶች ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በቅርቡ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማችን ወጣቶች መከላከያ ሰራዊቱን መቀላቀል የቻሉ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት የተመረቁ ወጣቶችም በስልጠና አቅማቸውን ብቁ አርገው የሀገራችንና የከተማችንን ሰላም ለመጠበቅ ላደረጋችሁት ተሳትፎ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ።

ለሰልጣኞቹም ከከንቲባዋ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።

10/09/2021

አቶ አብረሃም ታደሰ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ የ2014 አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት፣እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመተሳሰብ፣ በአብሮነትና በወንድማማች ፍቅር አዲሱን ዓመት መቀበልና ማክበር እንዳለብንም ገልፀዋል፡፡
አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያዊያንና የከተማችን ነዋሪዎች የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የደስታ ፣የአብሮነትና የወንድማማችነት እንዲሆንልን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በአንድነት የምንቆምበት፣ ኢትዮጵያዊነትን የምናጎላበት ፣የብልጽግና ጉዞን የምናፈጥንበት፣ በጋራ የሀገራችንን ሰላም እና ልማት የምናረጋግጥበት ዘመን ይሆንልን ዘንድ አቶ አብረሃም መልካም ምኞታቸውኝ ገልጸዋል።

አቶ አብረሃም ታደሰ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ
ጳጉሜ 05 / 2013 ዓ.ም

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa