የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication

የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication

Share

Media and communication office

Photos from የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication's post 04/02/2025

የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ 6 ወር ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡

(የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥር፡-27/2017)

የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ 6 ወር ሪፖርትና የ2017 የ2ኛው ግማሽ ዓመት የተከለሰ እቅድ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ አድርጓል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የጽ/ቤቱን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ
እናመሰግናለን፡፡
👍ፌስ ቡክ ገጽ:-👇 https://www.facebook.com/yekaworedaten
https://www.facebook.com/yekawordatencomm?mibextid=ZbWKwL
👍 ቲክቶክ👇
https://vm.tiktok.com/ZMMU4w3yE/
👍instagram👇
https://www.instagram.com/yeka_w10_communication_office?igsh=MW55aHFyeWt3Y2tmaw==
👍ኤክስ(Twitter )👇
https://pbs.twimg.com/profile_images/1621240863719395328/XIOLtkKY.jpg
👍WhatsApp 👇 https://chat.whatsapp.com/HwwqgSqr2dGD1DhYP6WeeM

Photos from የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication's post 01/01/2025

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በየካ ክፍለ ከተማ በተመረጡ ተቋማትና ወረዳዎች በስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ምልከታ ማካሄድ ጀመረ

የካ ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመንግስትና ከፓርቲ ዘርፍ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን በየካ ክፍለ ከተማ በተመረጡ ተቋማት እንዲሁም በወረዳዎች ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ምልከታ ማድረግ ጀምሯል።

ባለፉት ስድት ወራት በመንግሥት ዘርፍ እና በፓርቲ ዘርፍ ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ላይ ትኩረት ተደርጎ ምልከታው የሚካሄድ ሲሆን በዋነኝነት የዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም፣የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የተቋማት ግንባታ ስራዎች እና የቅንጅት ስራዎችን መሰረት ያደረገ ምልከታ እንደሚደረግም ተገልፃል፡፡

ምልከታው በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲሁም በወረዳዎች እንደሚካሄድ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡

Photos from የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication's post 01/01/2025

የወረዳው ምክር ቤት አስተባባሪ ኮሚቴ የወረዳውን አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ አደረገ።
****************************************
የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 23/2017

የባለ ጉዳይ ቀን በአንድ ማዕከል ቀልጣፋና የተሻለ በማድረግ የየካ ወረዳ 10 አስተዳደር ምክር ቤት አስተባባሪ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት የአገልግልግሎት አሰጣጡን ምልከታ አደረጓል በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ ምላ ጨምሮ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በየጽ/ቤታቸው በአንድ ማዕከል ተገኝተው አገልግሎት ፈላጊው ማህብረሰቡን በተሻለ ሁኔታ በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በዚሁ መሰረትም አስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቀላሉ ለመቅረፍ በሚያስችል አግባብ እየሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ በሌሎችም ተቋማት ዘንድ ተዘዋውሮ ለመመልከት እንደተቻለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ስለመሆናቸው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባደረገው ምልከታ አማካኝነት አረጋግጧል ።

30/12/2024
Photos from የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን /Yeka Woreda 10 communication's post 24/12/2024
16/12/2024

የካ ክ/ከተማ ወረዳ10 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ከሴ/ህ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ጋር ስለአረጋዉያን የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ዳሰሳ አደረገ፡፡

ታህሳስ 07/2017 የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የወረዳ 10 ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር የአረጋዉያንን አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ የወረዳ 10 ሴ/ህ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበርያ እና መከታተያ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ሊግዲ ጋር ቆይታ አድርጎ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል፡፡

የሴቶችና ህጻናት ስለአረጋዉያን የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አጻጸም የነበረው አጠቃላይ 103 አረጋዉያን በስራችን ታቅፈው ሲረዱ የነበሩ ሲሆኑ 56ቱ በቋሚነት ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸው 6ቱ በዶሮ እርባታና በጎሮ አትክልትና በተለያዩ ስራዎች ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በ2017 በጀት ዓመት ወደ 13 አረጋዉያን ከፍ በማድረግ በዶሮ እርባታ፣በጓሮ አትክልትና በተለያዩ ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ለተወሰኑ አረጋዉያን ደግሞ በካሽ በየወሩ ክፍያ በማድረግ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ሲሳይ እንደገለጹት በገንዘብ አሰባሰብ ዙርያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ለአረጋዉያን የምንረዳው ወይም ድጋፍ የምንሰበስበው ከዚህ በፊት ከመንግስት ነበር አሁን ግን በስፖንሰር ከሃበሻ ቢራ ፋብሪካና ኮርፎር ችልድረን ከሚባሉ ድርጅቶች እንዲሁም ከግለሰብ በሚሰበሰብ ገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ከወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የጽ/ቤቱን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ
እናመሰግናለን፡፡
👍ፌስ ቡክ ገጽ:-👇 https://www.facebook.com/meski.comi
https://www.facebook.com/yekawordatencomm?mibextid=ZbWKwL
👍 ቲክቶክ👇
https://vm.tiktok.com/ZMMU4w3yE/
👍instagram👇
https://www.instagram.com/yeka_w10_communication_office?igsh=MW55aHFyeWt3Y2tmaw==
👍ኤክስ(Twitter )👇
https://pbs.twimg.com/profile_images/1621240863719395328/XIOLtkKY.jpg
👍WhatsApp 👇 https://chat.whatsapp.com/HwwqgSqr2dGD1DhYP6WeeM
👍YouTube 👇
https://youtube.com/?si=Xvko7fj6ZdYFAGyE

13/12/2024

የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን በወረዳው ያጋጠመውን የወረቀት ችግር በተመለከተ ቅኝት አደረገ፡፡

(ታህሳስ 4/2017/የካ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን)

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር የወረቀት ችግር ካጋጠመው ሰነባብቷል ይሄንን በማስመልከት የወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ተዘዋውሮ የጽ/ቤቶችን የወረቀት ችግርና ስራዎችን በሃርድ መረጃ ማደራጀት ማቆማቸውን ተመልክቷል፡፡

የወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ጉዳዩን ይዞ ወደ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘመዴ ደሳለኝን "በወረዳው ያገጠመው የወረቀት ችግር ከምን የመነጨ ነው ችግሩ ከቀጠለስ የመንግስትና የተገልጋዮች መረጃ ባለመኖሩ የሚደርሰው ጉዳት የከፋ አይሆንም ወይ?ሲል ጠይቆ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

"በእርግጥም ወረዳ አስተዳደሩ ከፍተኛ የወረቀት ችግር አጋጥሞታል ለዚህም ምክንያት የሆነን ጨረታ አሸናፊው የወረቀት ዋጋ አሁን ስለጨመረ ባሸነፍኩት ዋጋ ማቅረብ አልችልም ብሏል ለዚህም ክስ ተመስርቶበት ለ 2 ዓመት በየተኛውም ተቋም በጨረታ መወዳደር እንዳይችል ታግዷል በተጨማሪም በወረዳው ያስያዘውን (ብር አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ተደርጎበታል፡፡

ሃላፊው ጨምረውም ችግሩን ለመቅረፍ 2ኛ ዙር ጨረታ ለማውጣት ሂደት ላይ መሆኑንና ለጊዜያዊ መፍትሄ ከወረዳ 10 ሚሊኒዬም ት/ቤት ከገዛን በኋላ የሚመለስ ውሰት 50 ደስታ ገቢ ተደርጎ ለጽ/ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ ወስነናል ብለዋል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የጽ/ቤቱን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ
እናመሰግናለን፡፡
👍ፌስ ቡክ ገጽ:-👇 https://www.facebook.com/meski.comi
https://www.facebook.com/yekawordatencomm?mibextid=ZbWKwL
👍 ቲክቶክ👇
https://vm.tiktok.com/ZMMU4w3yE/
👍instagram👇
https://www.instagram.com/yeka_w10_communication_office?igsh=MW55aHFyeWt3Y2tmaw==
👍ኤክስ(Twitter )👇
https://pbs.twimg.com/profile_images/1621240863719395328/XIOLtkKY.jpg
👍WhatsApp 👇 https://chat.whatsapp.com/HwwqgSqr2dGD1DhYP6WeeM
👍YouTube 👇
https://youtube.com/?si=Xvko7fj6ZdYFAGyE

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
W010