08/10/2026
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ " የእንጠያየቅ መድረክ" አካሄዷል
የእንጠያየቅ መድረኩ ዓላማ በማዘጋጃ ቤታዊና ተጠሪ ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣንና ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መሬት ወርዶ በማየት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የተለያዩ የፊት ለፊት መድረኮች በማዘጋጀት የነዋሪዎችን ጥያቄዎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በጋራ በትብብር በመሆን ምላሽ እያገኙ ሲሆን በቀጣይም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።
የዛሬ እንጠያየቅ መድረክ ዋና ዓላማ በማዘጋጃ ቤታዊ በሚሰጡ አገልግሎቶች በዘርፉ የነበሩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ጉድለቶችን ለማስተካከል ከህብረተሰቡ መወያየትና ግብአት ማግኘት አሰፈላጊ መሆኑን ገልፀው ይሄንኑ ወስዶ በጥንካሬ የታዩትን ለማስቀጠል በድክመት የተነሱትን ለማረም ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አበባዬ ደምሴ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ በስሩ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማስተባበር ለውጦች መምጣታቸው ገልጸው በዛሬ የእንጠያየቅ መድረክ ህብረተሰቡ የሚያገኘውን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግና በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን በመለየት ለማረም እንደሆነ ተናግረዋል።
የእንጠያየቅ መድረክ ህብረተሰቡ የሚያገኘውን አገልግሎት ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግና በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን በመለየት ለማረም አስተዋፅኦ የላቀ እንደሆነ ገልጸው ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህሉ እንዲያደርግ የተለያዩ ግንዛቤ መድረኮች በመፍጠር የተለያዩ የጽዳት ንቅናቄዎችን በማድረግ አካባቢውን ጽዱና ውብ የማድረግ ስራ መከናወናቸው በዚህም ትላልቅ ውጤቶች መታየት ችለዋል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የእንጠያየቅ መድረኩ በጋራ የህብረተሰቡን ችግሮች በመለየት ለመፍታትና ፈጣን ምላሾች ለመስጠት ሚናው ትልቅ መሆኑን ገልጸው የሚታዩ የመብራት መቆራረጥ ያረጁ ምሶሶዎች የአደጋ መንስኤ እየሆኑ ነው ቢስተካከል ፣ የመንገድ ስራዎች ፣ ከአደጋ ስጋት አንጻር ጥያቄዎች አንስተው ምላሽ ተሰጥቷል።