27/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የዒድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የትብብር እንዲሆን እንመኛለን።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Educational Assessment and Examinations Service
27/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የዒድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የትብብር እንዲሆን እንመኛለን።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
21/05/2026
ማስታወቂያ
የ2018 ትምህርት ዘመን የሪሜዲያል ፈተና እና በዓመቱ መጨረሻ የሚሠጠው የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ።
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የሚሰጥባቸው ቀናት እንደሚከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል !
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
16/05/2026
የትምህርት ምዘናና ምርምር ለትምህርት ጥራት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በላቀ ደረጃ እንዲያበረክት እየሠራ መሆኑን አገልግሎቱ ያስታወቀ ሲሆን ባለድርሻ አካላትንም አመስግኗል።
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከሚያዚያ 26 - ግንቦት 07/2018 ዓ.ም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ በ359 ትምህርት ቤቶች ስካሄድ የነበረዉ የመሠረታዊ የንባብና የስሌት (EGRA እና EGMA) ጥናትና ምርምር መረጃ በተሳካ ሁኔታ ተሰብስቦ ተጠናቋል።
ስለሆነም መረጃው በጥራት እና በታቀደው የጊዜ ገደብ ተሰብስቦ እንዲጠናቀቅ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ክቡራን የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን፣ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን፣ የወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎችን እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሰ-መምህራንንና መምህራንን ከልብ እናመሰግናለን።
የጥናት ውጤቱ መረጃው ተተንትኖ፣ ሪፖርት ተዘጋጅቶ፣ ግኝቶቹና ምክረ ሐሳቦቹም ተለይተው ሲቀርቡ በባለድርሻ አካላት ከተተቸ በኃላ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በይፋ የሚቀርብ ይሆናል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 2018 ዓ/
14/05/2026
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆነ። ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ ይችላሉ። ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት ይችላሉ። በየጊዜው የተለያዩ የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ ይሆናል። ድልድሉ የተካሄደው የተፈታኞችን ብዛት መሠረት በማድረግ ነው።
ስለሆነም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኞቹ እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን። ለትክክለኛ መረጃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማህበራዊ ሚዲያዎችን ይከታተሉ።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋር እንከላከል
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 2018 ዓ/ም
አዲስ አባባ - ኢትዮጵያ
13/05/2026
ማስታወቂያ ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
መጪ ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች ተለቋል።
ስለሆነም፡-
1.እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የተፈታኝ ተማሪው ትምህርት ቤት ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ ይጠበቅበታል።
2.በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ፣ የጾታ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
3.እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከልም ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ መያስ ይገበዋል።
4.ተፈታኞች በፈተና ወቅት ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
01/05/2026
ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ዝግጅትና አስተዳደር መሻሻል ማሳየቱ ተገለጸ።
ይህም የተገለጸው በሀገር ደረጀ የማህበራዊ ዘርፍ እምርታ ለሀገር ግንባታ በሚል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሚኒስትሮች፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የተቋማት ኃላፊዎችና የዘርፉ ምሁራን በተገኙበት መድረክ ላይ ነው።
በተለይም የፈተና ስርቆትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ተችሏል ፣ የፈተና ኩረጃ በእጅጉ እንዲቀንስ ተደርጓል፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጀን የጠበቀ የፊተና ዝግጅትና አስተዳደር እንዲኖር ተደርጓል፡ ዴጅታላይዜሽንን እውን በማድረግ ሁሉንም አገልግሎቶች በበይነ መረብና በመሶብ አንድ የአገልግሎት ማዕከል ላይ መስጠት ከመቻሉ በተጨማሪ የተወሰኑ አገልግሎቶች ራስ አገዝ(self servie ) በሆነ መንገድ መስጠት ተችሏል።
ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ፈተናዎችን 100% በበይነመረብ ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ፎቶ ከETV
✍🏼ማስታወቂያ (Remedial and Exit Exams)✍🏼
የ2018 ትምህርት ዘመን የሪሜዲያል ፕሮግራም (Remedial Program) ተማሪዎች እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምዝገባ እና መፈተኛ ቀናትን ማሳወቃችን ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት:-
1. በሚያዚያ 19/2018 ዓ/ም የጀመረው የሪሜዲያል ፕሮግራም ተፈታኞች ምዝገባ ዛሬ ሚያዚያ 23/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት የሚበቃ መሆኑን
2. የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ምዝገባ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 07/2018 ዓ/ም የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን።
ተፈታኞች በተሰጠው የምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ እንዲመዘገቡ እናሳስባለን።
ያልተመዘገበ አይፈተንም።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ለትክክለኛ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች መረጃ የአገልግሎቱን ማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን በላቀ ደረጃ እያዘመነ እንደምገኝ ተገለፀ።
በ2016 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ 29,686 በኦንላይን በተሳካ ሁኔታ ፈተና መስጠት ተችሏል። በ2017 ትምህርት ዘመን 134,609 ተፈታኞች በኦንላይን በተሳካ ሁኔታ ፈተና መስጠት ተችሏል።
ከዚህ ተሞክሮ በመነሳት በ2018 ዓ/ም ሁሉም (100%) ተፈታኞች በኦንላይን እንዲፈተኑ እየተሠራ ይገኛል።
የትምህርት መረጃ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ዲጄታላይዝ ከማድረግ ተሻግሮ ራስ አገዝ (self-selvice) እንዲሆን በማድረግ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
በተቋማዊ ቅንጅትና ትብብር የላቀ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እንተጋለን።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
24/04/2026