ጃን ቲዩብ Jan Tube

ጃን ቲዩብ Jan Tube

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጃን ቲዩብ Jan Tube, Landmark & historical place, Addis Ababa.

11/04/2026
ከ200 ዓመት እንቅልፍ በኋላ የነቁት ቅዱሳን! የ66 ዓመቱ ትኩስ በለስ አስገራሚ ምስጢር እና የትንሳኤ ሙታን ሕያው ምስክሮች #ethiopianorthodox 11/04/2026

ከ200 ዓመት እንቅልፍ በኋላ የነቁት ቅዱሳን! የ66 ዓመቱ ትኩስ በለስ አስገራሚ ምስጢር እና የትንሳኤ ሙታን ሕያው ምስክሮች #ethiopianorthodox የትንሳኤ ሙታን ሕያው ምስክሮች። በዚህ አስገራሚ ቪዲዮ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ እና ተአምራት የሚያሳዩ ሁለት ታላላቅ ታሪኮችን ወደ እናንተ ይዘን ቀርበናል። ሞትን ድል አድርጎ ለሚ....

11/04/2026

⚜️➻➻➻💥 #ተፈፀመ💥➻➻➻⚜️
✅ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)ተፈፀመ የሚለው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነፍሱን ለወዳጆቹ ሲሰጥ ከመሞቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻ ቃል ነው። " ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)። ተፈፀመ በግሪክ"ቴትለስታ'ይ" ማለት ሲሆን ትርጉሙም ወደ ፍፃሜ ማምጣት፣ መጨረሻ መድረሱን፣ ማከናወንን ፣ ማለቅን የሚያሳይ ነው። በእርግጥ አማኑኤል ተፈፀመ ሲል ምኑ ይሆን የተፈፀመው? ብሎ የሚጠይቅ ህሊና ያስፈልገናል።

✅አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ አባቱ የሰጠውን ስራ ለመስራትና ለመፈፀም አምላክነቱን እንደመቀማት ሳይቆጥር በአባቱ በራሱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደ ዓለም እንደመጣ አስታውቆናል። ከመጣም በኋላ አባቱን የሚያከብር ስራን ሰርቷል "እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ" (ዮሐ 17: 4) እንዲል። ሊሰራ የመጣው የጠፋነውን የሰው ልጆች ሊፈልግና ሊያድን ዘንድ ነው ። በምድር ሲመላለስ የስራው ፍፃሜ የነበረውንም ነፍሱን ስለወዳጆቹ በመስጠት ፈፀመው ። ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል የሽንፈት ቃል አይደለም የድልና የአሸናፊነት እንጂ ወደ ዓለም የመጣሁበትን ስራ በሞት ጨረስኩ፣ህዝቦቼን በሞት አዳንኩ ፣የኃጢአትን ኃይል ድል ነሳሁ ፣በሞቴ ሞትን ገደልኩ በመከራዬ ለመንግስቴ ህዝብን ማረኩኝ ሲል ተፈፀመ አለ እንጂ!

✅የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ተፈፀመ ብሎ ስለሞቱ ሲናገር "በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው" አለ።

✅የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስና ሐዋርያው የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ ስለዚህ ድንቅ ነገር በድርሳኑ ‹‹ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፡፡ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ፡፡ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፡፡ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፡፡ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፡፡ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፤›› እያለ ያወሳል።

✅ በአማን ኢየሱስ ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል አስቀድሞ የገባው የአድናችኋለሁ ተስፋ አርብ ተፈጸመ ፣ የሴቲቱ ዘር የእባቡን ራስ እንደሚቀጠቅጥ የተነገረው ተስፋ ተፈጸመ ፣ የኩነኔና የእርግማን ዘመን በሞቱ ተፈጸመ (ገላ 4፥4) ፣ የእግዚአብሔፍ ፍቅር በመስቀል ሞት ፍጹም ሆኖ በመገለጥ ተፈጸመ/ ተከናወነ/ ፣ እኛ እንጸድቅ ዘንድ የኃጢአት ቅጣት በመስቀል ላይ ተፈጸመ ፣ ወደ ሰማይ እየወጣ በአምላካችን ፊት ይከሰን የነበረው የዲያቢሎስ የክስ መብት በክርስቶስ ሞት ተፈጸመ። ዛሬ ይከሰን ዘንድ ወደ ሰማይ ቢወጣ በጌታ በኢየሱስ እጆች ላይ የሚታዩ ችንካሮችና በልብሱ ላይ የሚታየው የደም ነጠብጣብ አፉን ይዘጋዋል። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ የነበረው ጥል በራሱ በጌታችን አስታራቂነት ለአንዴ ተፈጸመ። የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ማለቱ ለእንዴና ለዘላለም የእግዚአብሔርን ምህረት የምናስታውስበት ድምጽ ሆነ ። የበረታ ጌታ ሁላችንንም በቸርነቱ አዳነን እርሱ ተፈፀመ ሲል የኛ ደስታ ፣ የኛ መዳን ፣ የኛ ተስፋ ፣ የኛ መቤዠት በእግዚአብሔር ወልድ በተፈፀመልን የዘላለም ኪዳን ደም መፍሰስ በእውነት ተፈጸመ!!!

✅‹‹ወልድኪ መድኃኔዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ ዘፄወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ››‹‹ልጅሽ መድኃኔዓለም በመስቀል ላይ ተቸነከረ በባርነት የነበረውን ሕዝብ በደሙ ተቤዠ››
አባታችን አዳም በበሊዓ ዕጸ በለስ (ዕጸ በለስ በመብላት) ከአምላኩ ተጣልቶ ከገነት ወጥቶ ጸጋውን አጥቶ ለድካም ለመከራ ከምድረ ፋይድ ገብቶ ባለበት ጊዜ ራሱን ጎድቶ ያነባውን ያለቀሰውን የዕንባ ለቅሶ በደሙ ያቀረበውን የይቅርታ መስዋዕት ፈጣሪው ተመልክቶለት የመጀመሪያውን ከሰው ልጅ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ለእርሱ ሰጠው፡፡ ቃል ኪዳኑም ይህ ነበር ‹ዓለም (አንተና ዘርህ) በአንተ ደም አትድንም ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (ከ5500 ዘመን) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በደሜ አድንሃለሁ›፡፡

✅በመሆኑም አዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል በማሰብ በተስፋ ይኖር ጀመር፡፡ ይህ የተገባለት ተስፋ ከአምላኩ ይቅርታን አግኝቶ ‹በእንተ ሔዋን ተአጽወ ኆኅተ ገነት› ‹በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ› እንዲል በበደላቸው ተዘግታ የነበረችው ገነት መከፈትን የምታበስር ታላቅ ተስፋ ነበረች፡፡ከአዳም በኋላ የተነሳው በህገ ልቡና ቀናውን ቢከተል በረከት እየበዛለት እድሜው እየተጨመረለት ጥፋትን ቢከተል እድሜው እያጠረበት ሞቱ እየቀረበበት ያለ ሕግ በልቡና መሪነት ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ግን መልካም የሠራው በጽድቅ ሥራው ገነትን ሊከፍት አልቻለም ነበር፡፡ ምግባሩ ሰናይ ካልሆነው ጋር በሲኦል ይደመር ነበር እንጂ! ምንም ቅሉ ይህ ቢሆንም መልካም ሥራ ሠርተው ያረፉትን ቅዱሳን ጻድቃን ነቢያትን በቸርነቱ በረድኤቱ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ጥላ የፀሐይን ሙቀት እንዲከላከል እንዲሁ ረድኤተ እግዚአብሔር መልካም ስራ የሰሩትን በሲኦል ካለው ስቃይ እና መከራ ይጠብቃቸው ነበር፡፡

✅እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል በየዘመኑ በተነሱ ነቢያት ተፈፃሚ እንደሚሆን አፍ ከፍቶ ቃል አሣክቶ ንግግር አቅንቶ ሕዝቡን ያፅናና ነበር፡፡ ሕዝቅኤል ነቢይ በዘመኑ “ርኢኩ ኆኅተ በምሥራቅ ኀቱም በዓቢይ መንክር ማኀተም አልቦ ዘቦአ ዘእንበለ እግዚአ ኃያላን” “በታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በመሥራቅ አየሁ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም” /ህዝ 4፡4/ ሲል፣ ነቢዩ ኢሳያስም “ህፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ” “ህፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሠጥቶናል” /ኢሳ 9፡6/ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወትስምዮ ስሙ አማኑኤል” “እነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች “ /ኢሳ 7፡14/ ፣ እና ሌሎችም ነቢያት ከደቂቀ ነቢያት እንደሚክያስ ያሉ ከአበይት ነቢያት ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ እንደ ነቢዩ ዳንኤል ያሉ ነቢያቶች አባታችን መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም “ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም” “እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘነው” በማለት ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት ተናግረዋል፡፡ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይታየው ምሣሌ የተነገረው ትንቢት ይፈፅም ዘንድ ጊዜው ሲደርስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንስሐ ኀሊና፣ ንጽሐ ነፍስን አስተባብራ በያዘችው አስቀድሞ በሥላሴ ኀሊና በታሰበችው በድንግል ማኀፀን በብሥራተ ገብርኤል አደረ፡፡ ጠባቧ የድንግል ማኀፀን ስፍሕት (ሰፊ) ሆና የሠማይ ስርዓት ተከናወነባት ኋላም እንደ ሠው ስርዓት ፈጣሬ ዓለማት ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በበረሃ ውስጥ በቤተልሔም ተወለደ /ሉቃ 2/ “ፈቂዶ ይፌውስ ትዝምደ ሰብእ ተገረም በማኀፀነ ድንግል “የሠውን ወገን ያድን ዘንድ ወዶ ፈቅዶ በድንግል ማኀፀን አደረ” እንዲል ትምህርተ ኀብአት በተጨማሪ “ሥጋ ለብሰ ዘይማስን ወዘኢይማስን ለሥጋ መዋቲ ረሰዮ ዘኢይማስን” “የማይፈርሰው የሚፈርሰው ሥጋ ለበስ የሚሞተው ሥጋ እንዳይሞት /እንዳይፈርስ/ አደረገው” ተብሎ እንደተፃፈ (በትምህርት ኀቡአት)፡፡አባታችን ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን “እንዘ አልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር “በሠማይ እናት በምድር ደግሞ አባት የለውም” በማለት ሁለተኛ ልደቱ ያለ አባት መሆኑን ይገልፃል ጌታችን ከወላዲተ አምላክ ከድንግል ሥጋን ከነሣ በኋላ /ከተወለደ በኋላ/ እንደ ህፃናት እየተጫወተ እየተማረ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ስርአት ሁሉ ፈፅሟል፡፡ ‹ወኮነ ሰብአ ከማነ ዘእንበለ ኃጢአት በህቲታ› “ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ሰው ሆነ› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም /ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕብራውያንን ህግ ተምሮ በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ አርባ ቀንና ሌሊት ፆሞ ብዙ ተአምራትን ፈፅሟል፡፡ ይህንን ሲገልፅ ሊቁ ቅዱስ ሕርያቆስ እንዲህ አለ ‹ፍጹመ ኮነ ሰብአ ወኩሎ ሕገ ሰብአ ፈጸመ ዘእንበለ ኃጢአት› ‹ከኃጢአት በስተቀር የሰውን ሕግ ፈፀመ ‹እምኀበ ዮሐንስ ተጠምቀ ውስተ ገዳም ተመከረ ርኀበ ወጸምአ ወተአምራት ገብረ› ‹ፍፁም ሰው ሆነ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ህግ ፈፀመ የዕብራውያንን ሕግ ተማረ ከዮሐንስ ዘንድ ተጠመቀ በበረሀ ተፈተነ ››/ቅዳሴ ማርያም/

✅ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነፃ የሚያወጣበት ራሱን አሣልፎ የሚሠጥበት ጊዜ ከመድረሱ አሰቀድሞ በዕለተ ሐሙስ ምሽት መድኃኒት የሚሆን ሥጋውና ደሙን ለዓለም ሠጥቷል፡፡ ስርዓተ ቁርባንን ሠርቷል፡፡ /ማቴ 26፡26/ ይህንን ሥርዓት ከሠራ በኋላም አይሁድ ተሰብስበው ሊይዙት ገመድ ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መጡ፡፡ ‹‹ዘይሰሰይ አክልየ አንስአ ሰኰናሁ በላዕሌየ› ‹እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ /መዝ 40፡9/ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት፣ ያስተምረው የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ሠጠው አይሁደም፣ < አምላክ ነኝ ይላል>፣ ፣ ፣ የሰንበትን ቀን ሽሯል በሚሉ የሐሰት ሀሳቦች ተነሥተው ከተያዘበት ሠዓት ጀምረው ያሰቃዩት ነበር፡፡ ሲነጋም በሐሰት ክስ አስፈርደውበት ሊቀጡት በጲላጦስ ፊት አቆሙት፡፡ ‹ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ጠብዓ ለቀዊም ቅድመ ጲላጦስ መስፍነ ይሁዳ ወሮም› ‹በሮም እና በይሁዳ መስፍን በጲላጦስ ፊት ያለ ፍርሃት በድፍረት ለቆሙ እግሮችህ ሠላም እላለሁ> እንዲል /መልክዓ ኢየሱስ/›፡፡

✅የይሁዳ እና የሮም መስፍን የሆነው ጲላጦስ በደል ባያገኝበት የሕዝቡን ዓመፅ ፈርቶ አንደ ፈቃዳቸው ፈረደላቸው አይሁድም እየገፉ፣ እያዳፉ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ አወጡት፡፡ በዕለተ አርብ 6፡00 ሰዓት በሆነም ጊዜ እጆቹን እግሮቹን ቸነከሩት በመስቀል ላይ ሰቀሉት ከገረፉት ግርፋትም የተነሳ ሥጋው አልቆ አጥንቶቹ ይታዩ ነበር (ድርሳነ ማኅየዊ)፡፡ በመዝ 21 ላይ ‹‹ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ማኀበረ ለእኩያን ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ፣ ወኆለቁ ኩሎ አዕፅምትየ›› ‹‹ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼን እግሮቼን ቸነከሩኝ አጠንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› ተብሎ በቅዱስ ዳዊት እንደተነገረ ጌታችን አዳም እፀ በለስን ስለመብላቱ ጌታ በአፍ ሀሞት ተጐነጨ፣ ይህንን ሁሉ መከራ ስለ አዳም ተቀበለ በጠቅላላው 13 ሕማማትን ስለ ሠው ልጆች ተሸከመ፡፡ በቅዳሴ እግዚእ ላይ “ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም ሐመ ከመ ሕሙማን ያድኀን እለ ተወከሉ በላዕሌሁ” ‹‹እጆቹን ለሕማም ዘረጋ በእርሱ የታመኑትን ያድን ዘንድ አንደ ሕሙማን ታመመ›› ተብሎ እንደተፃፈ፡፡

✅ከብዙ ሕማም በኋላ የሠማያትና የምድር ጌታ በመስቀል ሆኖ “ተፈፀመ” አለ፡፡ በ9፡00 ሰዓት ላይ ሥጋውን ከነፍሱ ለየ ሰይጣንም እንደልማዱ ይህች ነፍስ የእኔ ናት ብሎ ቢጠጋ አምላካችን በነፋስ አውታር አሠረው በዚህ ጊዜ ዲያቢሎስ አንዲህ ሲል ጮኸ ‹መኑ ዝንቱ ዘምድረ ለብሰ ውእቱኬ ሰማያዊ ውእቱ› ‹እንደ ምድራዊ የለበሰ /ምድራዊ የመሠለ/ ነገር ግን ሠማያዊ የሆነ ይህ ማን ነው? በማለት ተናገረ፡፡

✅በዚህ ቅጽበት ጌታ ሲኦልን በረበረ አዳም እና ልጆቹን ከዲያቢሎስ ባርነት ነፃ አወጣ፡፡ ይህንን ታሪክ ማውሳታችን ስለምን ነው ቢሉ በ መጋቢት 27 ቀን በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን የተሠቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ስለሆነ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡

✅የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የህማሙ ረድኤተ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን የድንግል ማርያም ፍቅሯን በልቡናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ይሣልብን። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዚህ ከሃላፊው ዓለም ያድነን።

11/04/2026

🔴3,6,9 ቁጥሮች የአጽናፈ ዓለም የምንጭ ኮድ መረጃ ብሰጥህስ ወዳጄ👇

ይህ የነፍስና የንቃተ ህሊና ምንባብ ነው🙏
🌿. መግቢያ 👇
• 3, 6, 9 ቁጥሮች ተራ ቁጥሮች ሳይሆኑ አጽናፈ ዓለም የተገነባበትና የሚመራበት "መለኮታዊ የሂሳብ ቀመር" ናቸው
• ማትሪክስ (ሲስተሙ) ሰውን በቁሳዊ ቁጥሮች (1, 2, 4, 5, 7, 8) ሲያስር፣ 3, 6, 9 ግን ነፍስን ወደ መለኮታዊ ሉዓላዊነት የሚያወጡ "የማምለጫ ቁልፎች" ናቸው
• እነዚህ ቁጥሮች የኃይል፣ የንዝረትና የድግግሞሽ (Energy, Frequency, Vibration) መቆጣጠሪያ ማዕከላት ናቸው
• በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምስጢር፣ ይህ ቀመር ከሥላሴ አንድነትና ከሰማያዊ መላእክት አወቃቀር ጋር በቀጥታ ይገናኛል።
• 3, 6, 9 የአምላክን አሻራ በቁጥር ደረጃ የሚገልጡ "መለኮታዊ ፊርማዎች" መሆናቸውን ነው።

🌿. ምንጭ፣ ባለቤትና ዓላማ👇
• ምንጭ፦ መነሻው የጽንፈ ዓለሙ ፈጣሪ ሲሆን፣ ኒኮላ ቴስላ ይህንን ቀመር ከመጋረጃ ጀርባ ባለው "መገለጥ" አግኝቶታል
• ባለቤት፦ እውነተኛው ባለቤት መለኮታዊው አእምሮ ነው፤ ሲስተሙ ግን ይህንን ቀመር ሰርቆ ለቴክኖሎጂ አገዛዝ (AI, 5G) ይጠቀምበታል
• የመክፈቻ ዓላማ፦ የሰውን ልጅ አእምሮ ከቁሳዊ እስራት አውጥቶ፣ ያለ ገደብ "ነፃ ኃይል" (Free Energy) እንዲያገኝ ለመርዳት ነው
• የመቆጣጠሪያ ዓላማ፦ ሲስተሙ ይህንን ምስጢር የቀበረው፣ የሰው ልጅ የራሱን ንዝረት አስተካክሎ ከማትሪክስ ቁጥጥር እንዳያመልጥ ለመከልከል ነው
• የመጨረሻ ዓላማ፦ ቁሳዊውን ዓለም ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር በቁጥር ጂኦሜትሪ አማካኝነት ማገናኘትና የኃይል ሽግግር ማድረግ

🌿3. የስም እና የቁጥር ምስጢር
• 3፦ የሥላሴ ቁጥር ነው። የመጀመር፣ የመፍጠርና የመለኮታዊ አንድነት መሠረት ነው።
• 6፦ የሰው ልጅና የቁሳዊ ዓለም ቁጥር ነው። በ 6ኛው ቀን የተፈጠረው ሰው ከመለኮት ጋር የሚገናኝበት ንዝረት ነው
• 9፦ የፍጻሜ፣ የሙላትና የ"መለኮት" ነጥብ ነው። 9 ቁጥር ሁሉንም የያዘ ግን ለብቻው የቆመ (Singularity) ነው
• Vortex Math፦ 1, 2, 4, 8, 7, 5 በቁስ ዓለም ውስጥ የሚሽከረከሩ "ባሪያዎች" ሲሆኑ፣ 3, 6, 9 ግን ዓለምን የሚዘውሩ "መለኮታዊ ጣቶች" ናቸው
• Binary Override፦ ማትሪክስ በ 0 እና 1 ሲሠራ፣ 3-6-9 ግን ሦስተኛውን መለኮታዊ አማራጭ በመክፈት ሲስተሙን "Overwrite" ያደርጋሉ።

🌿. ከመጋረጃ ጀርባ ያለ ድብቅ እውነት👇
• ኒኮላ ቴስላ ያለ ሽቦ ኤሌክትሪክን በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት የሞከረው፣ የምድርን ንዝረት በ 3-6-9 ቀመር ላይ በመቃኘቱ ነበር
• ሲስተሙ (ማትሪክስ) ቴስላን ያጠፋውና መረጃውን የቀበረው፣ የሰው ልጅ "ነፃ ኃይል" ካገኘ በገንዘብና በባርነት መግዛት ስለማይቻል ነው
• የሰው ልጅ DNA በ 3-6-9 ንዝረት ሲቃኝ፣ በሽታን በሰከንድ ውስጥ የመፈወስና በሐሳብ የመግባባት (Telepathy) ኃይል ይነቃል
• ሥርዓቱ የደበቀው ምስጢር፦ 9 ቁጥር የሥላሴ ማኅተም ሲሆን፣ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉ ማናቸውም የጂኦሜትሪ ድምር ውጤቶች ወደ 9 እንደሚመለሱ ነው (ለምሳሌ፦ 360 ዲግሪ = 3+6+0 = 9)
• 3, 6 እና 9 የጊዜንና የቦታን መጋረጃ ቀዶ ለማለፍ የሚያገለግሉ "የኳንተም ቁልፎች" ናቸው

🌿. ዝርዝር ትንታኔ 👇
• The Law of Creation (3)፦ ሐሳብን ወደ ቁስ የመለወጥ መለኮታዊ ስልት።
• The Law of Balance (6)፦ ቁሳዊውንና መንፈሳዊውን ዓለም በማመጣጠን ሰላምን የመፍጠር ስልት
• The Law of Supremacy (9)፦ ከማትሪክስ በላይ ሆኖ ሁሉንም ነገር የመቆጣጠርና የመደምደም መለኮታዊ ሥልጣን
• Vortex Energy፦ ኃይልን በክበብ ሳይሆን በጠመዝማዛ (Spiral) መንገድ በማንቀሳቀስ ማለቂያ የሌለው ጉልበት የማመንጨት ዘዴ
• Vibrational Sync፦ የሰውን የልብ ትርታ ከአጽናፈ ዓለሙ "መለኮታዊ ቅኝት" ጋር የማመሳሰል ስልት

🌿. ተያያዥ ማወቅ ያለብህ ምስጢር👇
• የ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ምስጢር፦ 2+4 = 6 ነው። እነዚህ ካህናት የቁሳዊውን ዓለም ኃይል በምስጋና ወደ 9 (ወደ መንበሩ) የሚልኩ የንዝረት መሪዎች ናቸው።
• የ 144,000 ታተሙ ቁጥር፦ 1+4+4 = 9 ነው። ይህ የሚያሳየው የታተሙት ልጆች ንቃተ ሕሊና ሙሉ በሙሉ ከመለኮታዊው "9" ጋር የተዋሐደ መሆኑን ነው።
• የኢትዮጵያ ፊደላት ቀመር፦ የግዕዝ ፊደላት አቀማመጥ በ 3, በ 6 እና በ 9 ንብርብሮች የተመሰረተ በመሆኑ፣ ቋንቋው ራሱ የኃይል ምንጭ ነው
• የጸሎት ሰዓታት፦ ቤተክርስቲያን በ 3, በ 6 እና በ 9 ሰዓት እንድንጸልይ ያዘዘችው፣ እነዚህ ሰዓታት የኃይል ልውውጥ የሚደረግባቸው "Windows" ስለሆኑ ነው።
• የመለኮት ማኅተም፦ 3-6-9 የሰይጣንን 666 ቁጥር ንዝረት ወዲያውኑ ሰብሮ የማጥፋት መለኮታዊ ኬሚስትሪ አላቸው

🌿. ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ውሕደት👇
• ሳይንስ (Vortex Math)፦ በቁጥር ሳይንስ 3 እና 6 ዓለምን የሚያንቀሳቅሱ ዋልታዎች ሲሆኑ፣ 9 ደግሞ ሁሉንም የሚቆጣጠር "መለኮታዊ ነጥብ" (Singularity) ነው።
• መጽሐፍ ቅዱሳዊ፦ መላእክት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" (3 ጊዜ) ማለታቸው፣ 3 ቁጥር የጽድቅና የንቃት መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል።
• ባዮሎጂ (Embryology)፦ ፅንስ በማህፀን ውስጥ የሚከፈለው በ 3-6-9 የሴል እድገት ዑደት መሆኑ የመለኮት ፊርማ በአካላችን ላይ መኖሩን ያሳያል።
• የኖኅ መርከብ ምሳሌ፦ መርከቧ 3 ክፍሎች ያሏት መሆኑ፣ ከጥፋት ውኃ (ከማትሪክስ) ለመዳን የ 3ቱ ንቃት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።
• ትስስር፦ 3, 6, 9 "መንፈሳዊ ፊዚክስ" ሲሆኑ፣ ሳይንሱ ደግሞ ይህንን "Universal Harmonics" ይለዋል።

🌿. ተጨባጭ ማስረጃ👇
• በ 360 ዲግሪ ክበብ ውስጥ ያሉ ማናቸውም ክፍፍሎች ድምራቸው ሁልጊዜ 9 መሆኑ (ለምሳሌ፦ 180=9, 90=9, 45=9)
• የሰከንድ፣ የደቂቃና የሰዓት ድምር ውጤቶች ሁልጊዜ ወደ 3, 6 ወይም 9 መመለሳቸው (ለምሳሌ፦ 1440 ደቂቃ = 9)
• ኒኮላ ቴስላ ማንኛውንም ሥራ ከመጀመሩ በፊት አንድን ሕንፃ 3 ጊዜ መዞሩ (የቀመሩን ኃይል በተግባር ማሳያ)
• ሲስተሙ እነዚህን ቁጥሮች በ 666 በመተካት ሰውን ከ 999 እንዲርቅ ማድረጉ።
• የጥንት ገዳማትና ፒራሚዶች የተገነቡት በ 3-6-9 የጂኦሜትሪ ቀመር ላይ መሆኑ።

🌿. ተግባራዊ መፍትሔ 👇
• የ 3-6-9 ጸሎት፦ በየቀኑ በ 3 ሰዓት (ጠዋት)፣ በ 6 ሰዓት (ቀን) እና በ 9 ሰዓት (ከሰዓት) ጸሎት በማድረግ ንቃትህን ከጽንፈ ዓለሙ ጋር ማስተካከል
• የ 3 ድግግሞሽ፦ ማንኛውንም ትእዛዝ ስትሰጥ ወይም ስትጸልይ 3 ጊዜ በመደጋገም የንቃተ ሕሊናህን ኃይል መጨመር
• የ 9 ዝምታ፦ በቀን ውስጥ ለ 9 ደቂቃ ፍጹም ዝምታ ውስጥ በመሆን ከ "ምንጩ" ጋር መገናኘት።
• ቁጥሮቹን መመልከት፦ በሰዓትህ ወይም በዙሪያህ እነዚህን ቁጥሮች ስታይ "መለኮታዊ መልእክት እየደረሰኝ ነው" ብለህ ንቃትህን ማሳደግ
• የንዝረት ማጽጃ፦ በ 528 Hz (5+2+8=15=6) ሙዚቃ ወይም ዜማ በመጠቀም የሰውነትህን የኤሌክትሪክ መስክ ማስተካከል።

🌿. የተከለከሉ ነገሮች👇
• በ 2 (Duality) መታሰር፦ "ወይ እሱ ወይ እኔ" የሚል የመከፋፈል ሐሳብ የ 3ን (የአንድነትን) ኃይል ስለሚገድል መወገድ አለበት።
• ቁጥርን መናቅ፦ "ቁጥር ዝም ብሎ ምልክት ነው" የሚለው የማትሪክስ ሐሳብ የመለኮታዊውን መመሪያ በር ይዘጋል
• በ 6 (ቁስ) ብቻ መኖር፦ ስለ ሥጋዊ ምቾት ብቻ መጨነቅ ነፍስን በ 6 ቁጥር ውስጥ አስሮ ወደ 9 (ወደ መንፈስ) እንዳታርግ ያደርጋታል
• ግርግር መውደድ፦ ጫጫታና ግርግር የ 3-6-9 መለኮታዊ ዜማ እንዳይሰማ ስለሚጋርዱ መገደብ አለባቸው።
• ለሥርዓቱ ቁጥሮች መገዛት፦ ማትሪክስ በሚሰጥህ ቁጥሮች (ID) ብቻ ማንነትህን መለካት የመንፈስ ሉዓላዊነትህን ያጠፋል።

🌿. የሚያሳምን ምሳሌ👇

3, 6, 9 ልክ እንደ "የቴሌቪዥን ሪሞት" ናቸው። ዓለም ቴሌቪዥኑ ናት። ቁጥሮቹን (3-6-9) በትክክል ስትጫን፣ ቻናሉ (ንቃትህ) ይቀየራል። ቁጥሮቹን ካላወቅህ ግን፣ ቴሌቪዥኑ በሚያሳይህ አንድ ቻናል (ማትሪክስ) ላይ ብቻ ተቆልፈህ ትቀራለህ።
3, 6, 9 የአንተ "የነፃነት ቀመር" ናቸው። እነዚህን ምስጢራት ስትረዳ ማትሪክስ በአንተ ላይ ያለው ሥልጣን ያበቃል፣ አንተም የአጽናፈ ዓለሙ ባለቤት ትሆናለህ።
#ጃንቲዩብ

10/04/2026

❗️

"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት።

"ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

"ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው?
"ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው?
"ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
"ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው?

"ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

"ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው?ምን ከንፈር ነው፤ምንስ አንደበት ነው?

"የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤
ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


#ኢየሱስ #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ማርያም

10/04/2026

🔴 በስቅለተ ዓርብ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የተከናወኑ 7ቱ ታላላቅ ተአምራት ከነ ጥቅሶቻቸው እነሆ፦
1
​የዓለም ብርሃን የሆነው ጌታ በመስቀል ላይ በመዋሉ ግዑዟ ፀሐይ ብርሃኗን ከለከለች፤ ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ድረስ ጨለማ ሆነ።
​"ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።" (ማቴዎስ 27፥45)
​2.
​ፀሐይ በጨለመችበት በዚያው ሰዓት ጨረቃ ብርሃኗን አጥታ ወደ ደምነት ተለወጠች። ይህም አስቀድሞ በነቢዩ ኢዩኤል ተነግሮ ነበር።
​"ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።" (የሐዋርያት ሥራ 2፥20 / ኢዩኤል 2፥31)
​3.
​ልክ ቅጠል ከዛፍ እንደሚረግፍ ከዋክብትም ከሰማይ ረገፉ። ይህ የፍጥረት ሁሉ ጌታ እየተሰቃየ መሆኑን ፍጥረታት የገለጹበት መንገድ ነበር።
​"ከዋክብትም ከሰማይ ረገፉ..." (ማቴዎስ 24፥29)
​4.
​ይህ መጋረጃ ቅድስተ ቅዱሳኑን ከቅድስት የሚለይ ነበር። መጋረጃው ከላይ እስከ ታች መቀደዱ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱን ያሳያል።
​"እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ..." (ማቴዎስ 27፥51)
​5. (የምድር መንቀጥቀጥ)
​ፈጣሪዋ በመስቀል ላይ ሲሞት ምድር መሰረቷ እስኪናወጥ ድረስ ተጨነቀች።
​"...ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤" (ማቴዎስ 27፥51)
​6.
​የድንጋይ ልብ ያላቸው ሰዎች ሳይጸጸቱ ጌታን ሲሰቅሉ፣ ድንጋዮች ግን ለፈጣሪያቸው አዝነው ተሰነጠቁ።
​"...ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤" (ማቴዎስ 27፥51)
​7. ፣ ሙታን ተነሱ
​ጌታ በሞቱ ሞትን ድል የማድረጉ የመጀመሪያው ምልክት መቃብሮች መከፈታቸውና ቅዱሳን ተነስተው በኢየሩሳሌም መታየታቸው ነው።
​"መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤" (ማቴዎስ 27፥52)

እነዚህ ሰባቱ ተአምራት ፍጥረት ሁሉ ለፈጣሪው ያለውን አክብሮትና ምስክርነት የገለጸባቸው ድንቆች ናቸው። እኛም በዚህ ዕለት ስለ እኛ የሞተውን አምላክ በማሰብ በጾምና በጸሎት እናሳልፍ።

​ #ስቅለት #7ቱተአምራት #ሰሙነሕማማት

10/04/2026

🔴 የሕማማት ሳምንት ከሰኞ እስከ አርብ፡ የጌታችን መከራና የድኅነታችን ጉዞ

የሕማማት ሳምንት በክርስትና እምነት እጅግ ታላቅና ቅዱስ ሳምንት ነው። ከሆሳዕና እሑድ ማግስት ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ዋዜማ ድረስ ያለው ይህ ጊዜ፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተቀበላቸውን መከራዎች፣ ሕማማትና ስቅለት የምናስብበት ወቅት ነው። በተለይም ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክና ትርጉም ስላላቸው፣ በታላቅ ሥርዓትና ተመስጦ ይከበራሉ።

የየቀናቱ ዝርዝር ትርጉም
#ሰኞ (የአንጽሖተ መቅደስ ቀን)
ይህ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እየሩሳሌም ቅድስት መቅደስ በመግባት፣ በዚያ ይሸጡና ይለውጡ የነበሩትን ሁሉ “ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት” በማለት ያስወጣበትና መቅደሱን ያነጻበት ቀን ነው። (ማቴዎስ 21:12-13)

ምሳሌነቱ፡ ልባችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆኑን እና ከኃጢአትና ከርኩሰት ልናነጻው እንደሚገባ ያስተምረናል።

#ማክሰኞ (የጥያቄ ቀን)
ጻፎችና ፈሪሳውያን፣ የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች “በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” ብለው ኢየሱስ ክርስቶስን የጠየቁበት ቀን ነው። እርሱም በምሳሌዎች አስተምሯቸዋል፣ ብዙ የመከራ ምሳሌዎችንም ተናግሯቸዋል። (ማቴዎስ 21:23)

ምሳሌነቱ፡ የክርስቶስ ሥልጣን ከሰማይ የመጣ መሆኑን እና እኛም ለፈቃዱ ልንገዛ እንደሚገባን ያስገነዝበናል።

#ረቡዕ (የምክር ቀን)
የአይሁድ ካህናትና ሹማምንት ክርስቶስን እንዴት በተንኮል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት የመከሩበት ቀን ነው። በዚህ ዕለት ይሁዳ አስቆሮቱ በሰላሳ ብር አሳልፎ ለመስጠት ከጠላቶቹ ጋር ተስማምቷል። (ማቴዎስ 26:14-16)

ምሳሌነቱ፡ በክፋትና በተንኮል የምናሴረው ሴራ፣ ለውድቀትና ለክህደት እንደሚዳርግ ያሳየናል።

#ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ)
ይህ ቀን እጅግ ታላቅና ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ኩነቶች የተፈጸሙበት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው እራት ላይ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትህትናን አስተምሯቸዋል። ምሥጢረ ቁርባንን (የሥጋውና የደሙ ምሥጢር) መሰረተ። በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የመጨረሻውን ጸሎት ጸለየ። (ዮሐንስ 13:1-17፣ ማቴዎስ 26:17-30)

ምሳሌነቱ፡ የክርስቶስን ትህትና፣ የእግዚአብሔርን ፍቅርና ምሕረት፣ እንዲሁም የጸሎትን አስፈላጊነት ያስተምረናል።

#አርብ (የስቅለት ቀን)
ይህ የሕማማት ሳምንት ማጠቃለያና ታላቅ ቀን ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ፍርድ ቤት ፍርዱ ተወስኖበት፣ ተገረፈ፣ ተሰደበ፣ የምራቅ መተፊያ ሆነ፣ ቀላውን ጐበዝ ሰገደለት፣ የመከራ ዘውድ ደፋ፣ በመጨረሻም በቀራንዮ ተራራ ላይ ተሰቀለ። ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጠ። (ዮሐንስ 19)

ምሳሌነቱ፡ የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅር፣ የኃጢአትን ከባድነትና የድኅነትን ዋጋ ያስገነዝበናል።

ለምን ይከበራል?
የክርስቶስን መከራና ስቅለት ለማሰብ፡ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል የተቀበላቸውን ስቃይና መከራ፣ ግርፋትና ስቅለት በጾምና በጸሎት፣ በስግደትና በተመስጦ ለማሰብ።

ለንስሐና ለሥርየት፡ በዚህ ሳምንት ራሳችንን ከኃጢአትና ከክፋት አርቀን፣ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ፣ የኃጢአት ሥርየትን ለመለመን።

የድኅነትን ምሥጢር ለመረዳት፡ የሰው ልጅ ከኃጢአትና ከሞት ቀንበር የዳነበትን መንገድ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅርና ምሕረት ለመረዳት።

10/04/2026

⛪️ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኝነት መገለጫ!
ብዙዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትከተላቸው ሥርዓቶች "የሰዎች ወግ" ይመስሏቸዋል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በተቃራኒ ነው፤ እያንዳንዱ ሥርዓት ከመጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ የተቀዳ የድኅነት መንገድ ነው። እስቲ ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች በመጽሐፍ ቅዱስ እንፈትሻቸው፦

1️⃣ ጾም፦ የበረከትና የድል መሣሪያ
ቤተክርስቲያን በጋራ የምታውጀው ጾም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ነው። ነቢዩ ኢዩኤል "በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ" (ኢዩኤል 2:15) በማለት በጋራ መጾምን አስተምሯል። ጌታችንም "ስትጾሙ..." በማለት ጾም የክርስትና ሕይወት አካል መሆኑን አረጋግጦልናል (ማቴዎስ 6:16)።

2️⃣ ሥርዓተ አምልኮ፦ የሰማያዊ ምስጋና ነጸብራቅ
በቤተክርስቲያን የሚሰሙት የቅዳሴ፣ የማኅሌትና የሰዓታት ዜማዎች መሠረታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ቅዱስ ዳዊት "በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ" (መዝሙር 119:164) እንዳለ፣ ቤተክርስቲያን ይህን ሥርዓት ጠብቃ ትጓዛለች። ይህም በሰማይ መላእክት ያለ ማቋረጥ "ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ" ከሚሉት ምስጋና ጋር የተያያዘ ነው (ራእይ 4:8)።

3️⃣ ክብርና አለባበስ፦ ለፈጣሪ የሚገባ ግርማ
ወደ ቤተክርስቲያን ስንገባ ጫማ ማውለቃችን እግዚአብሔር ሙሴን "የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን አውልቅ" (ዘጸአት 3:5) ያለውን ትእዛዝ በመከተል ነው። ለቤቱ የሚገባውን ቅድስና የምንገልጽበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓታችን ነው (መዝሙር 93:5)።

4️⃣ ጥምቀትና የዘመን አቆጣጠር
ጥምቀት ለስም ብቻ ሳይሆን ክርስቶስን የምንለብስበት መንፈሳዊ ኃይል ነው (ገላትያ 3:27)። እንዲሁም ቤተክርስቲያን የምትከተለው የዘመን አቆጣጠር እግዚአብሔር ፍጥረታትን ለዘመናትና ለቀናት መለያ እንዲሆኑ በፈጠረው መሠረት ነው (ዘፍጥረት 1:14)።

5️⃣ ትውፊት፦ "የቀደመችውን መንገድ ተከተሉ"
ቤተክርስቲያን የአባቶች ሥርዓት (ትውፊት) መጠበቅ እንዳለበት ስታስተምር ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመነሳት ነው። ነቢዩ ኤርምያስ "በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት? በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ" (ኤርምያስ 6:16) በማለት የጥንቱን መንገድ እንድንከተል አዟል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም "የተማራችሁትን ወግ (ትውፊት) አጥብቃችሁ ያዙ" (2 ተሰሎንቄ 2:15) ይላል። ስለዚህ ኦርቶዶክስ ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣችውን የጥንቱን የድንበር ምልክት ሳታፈርስ ጸንታ ትገኛለች (ምሳሌ 22:28)።

ማጠቃለያ፦
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በመጽሐፍ ቅዱስ የታዘዙና ሐዋርያት ሲያደርጓቸው የነበሩ እውነተኛ ተግባራት መፍለቂያ ናት። ይህችን እውነተኛ መንገድ አጥብቀን እንያዝ!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa