11/06/2026
በሁሉም የሥራ ኃላፊነት ደረጃዎች ከጥቅም ግጭት እና ሙስና የጸዳ ውሳኔ መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ
ሰኔ 04 / 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለአመራሮች እና ሰራተኞች በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የጥቅም ግጭት እና ሙስናን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል የአንድ ቀን ሰልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በዚህ ወቅት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ እንሴሱ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች የሀገርን እና የህዝብን ጥቅም ባስጠበቅ መልኩ የተጣለባቸውን የሥራ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ስልጠናው የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አመራሮች እና ስራተኞች የስራ ኃላፊነታቸን በሚወጡበት ወቅት የአገልጋይነት ሥነ-ምግባር መርሆችን በማክበር ለጥቅም ግጭት ከሚዳርጉ ሁኔታዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስለመሆኑ ስራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት የሱፍ ኢብራሂም ዶ/ር ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በሁሉም የሥራ ኃላፊነት ደረጃዎች ከጥቅም ግጭት እና ሙስና የጸዳ ውሳኔ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ተከታታይነት ያለው የስብዕና ግንባታ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ የተናገሩት በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን አስተባባሪ አቶ ደረጀ ኪሮስ ሲሆኑ የአመራሩን እና የፈፃሚውን የአገልጋይነት ሥነ-ምግባር ለማጎልበት በተሰራው ሥራ ውጤት ማስመዝገብ ስለመቻሉም ገልጸዋል።
በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
11/06/2026
ከሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር የተደረገ ቆይታ
ሰኔ 04/ 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)

https://www.youtube.com/watch?v=7fv3_wxVvGs
ከሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር የተደረገ ቆይታ
ሰኔ 04 / 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
10/06/2026
የሌጀር ኢንጂን ልማት በገቢዎች ሚኒስቴር እና ክልልሎች ገቢ አሰባሰብን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ በማድረግ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት የሚስችል መሆኑ ተጠቆመ
ሰኔ 03 / 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር አሰባሰብን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የተቀናጀ የታክስ አስተዳደር ስርዓትን /Integrated Tax Administration System/ ልማት ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ ይገኛል፡፡ የዚሁ ፕሮጀክት ዋነኛ አካል የሆነው የሌጀር ኢንጂን (አጠቃላይ የግብር ከፋይ የፋይናንስ መረጀ ቋት) ልማት አሰራር ማስታወቂያ እና የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ በገቢዎች ሚኒስቴር የተቀናጀ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ማሞ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /INSA/ ጋር በትብብር የሌጀር ኢንጂን ልማት የተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም የሌጀር ኢንጂን በተለምዶ የሂሳብ/ፋይናንሻል/ ውጤትን የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የሌጀር ኢንጂን፤ የአንድ ግብር ከፋይ የምዝገባ፣ የፋይሊንግ፣ የእዳ አስተዳደር፣ የክፍያ እና ከኦዲት ጋር የተያያዙትን አጠቃላይ ዝርዝር መረጃ ማሳየት የሚችል ፕላት ፎርም እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /INSA/ ቺፍ አርክቴክት የሆኑት አቶ ሳምሶን አድማሱ የለማውን የሌጀር ኢንጂን አሰራር በዝርዝር አቅርበው ግብዓት እንዲሠጥበት ተደርጓል፡፡
በበኃይሉ ሽመልስ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
10/06/2026
አዲሱ የግብር ከፋዮች ምደባ (tax payers’ segmentation) ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል
ሰኔ 03 / 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
የ2019 በጀት ዓመት የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ ኮሚቴ ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለበላይ አመራሮች ሪፖርት አቅርቧል፡፡
በዚህ ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የምደባው ዓላማ ግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ፣ የሚኒስቴር መ/ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋት እንዲሁም የግብር ከፋዮችን አደረጃጀት ለማስፋት ታስቦ ነው ብለዋል፡፡ ይህም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጎላ ሚና እንደሚኖረው የገለጹት ሚኒስትሯ ለተግባራዊነቱም የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የዚሁ የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ ውጤት የሆነው የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርቡ ለግብር ከፋዮች አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ይሆናል።
የታክስ ከፋዮች የደረጃ ምደባ ኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ደረጄ ፋና ምደባው የተካሄደው ዓለምአቀፋዊ ተሞክሮዎችን መሠረት አድርጎ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ለግብር ከፋዮች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት የሚሰበሰበውን ገቢም ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለውም አብራርተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች ተሳትፈውበታል፡፡
በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ፡- ክፍሌ ኣዳፍሬ
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
09/06/2026
የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ
ሰኔ 02 / 2018 ዓ.ም (ገቢዎች ሚኒስቴር)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ24ኛ መደበኛ ስብሰባው የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጀ ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ረቂቅ አዋጁ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ሰብሳቢው ገልጸዋል።
ረቂቅ አዋጁ በዘርፉ ሀገራችን ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የሚያስችል ሲሆን፣ በጉምሩክ አሠራር ውስጥም ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም፣ ረቂቅ አዋጁ በሀገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደግፍ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መሆኑን የኮሚቴው ሰብሳቢ አመላክተዋል።
ረቂቅ አዋጁ በነባሩ አዋጅ ውስጥ የተደነገጉ ገደቦችን በተግባር ላይ ሲውሉ ይስተዋሉ የነበሩ የአተገባበር ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችሉ ዘንድ አስፈላጊ ድንጋጌዎችን ያካተተ መሆኑንም አንስተዋል።
አስመጪዎች በቀረጥ እና ታክስ አወሳሰን ላይ ያላቸውን አቤቱታ በማቅረብ ሂደት ያጋጥሟቸው የነበሩ የአሠራር መሰናክሎችን ለማስወገድ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ጠቁመዋል።
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፣ በረቂቅ አዋጁ ዝግጅት ወቅት የተከናወነው ሥራ አስፈላጊውን የሕግ ምርመራ እና ግምገማ ሂደት የተከተለ መሆኑን እና አዋጁም በተገቢው ሁኔታ ታይቶ እና ተገምግሞ የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
በኮንትሮባንድ ጭነት ምክንያት ተሽከርካሪ እንዲወረስ የሚያስችል ድንጋጌ ቢኖርም፣ ባለቤቱ በድርጊቱ ተሳታፊ ባልሆነበት ሁኔታ ንብረቱ ሊወረስ እንደማይገባም አንሥተዋል።
ባለቤቱ ተሽከርካሪውን አሽከርካሪ እንዲጠቀምበት በውል ሲያስረክብ፣ ታማኝና ለሕግ ተገዥ የሆነ ሹፌር መቅጠር እንዲሁም ለሚደርስ ጉዳት ወይም ሕገ-ወጥ ድርጊት ተገቢ ዋስትና መውሰድ እንዳለበት ተጠቁሟል።
ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ አዋጅ ቁጥር 1425/2018 አድርጎ በሁለት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
09/06/2026
ገቢ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል!
ሰኔ 02 / 2018 ዓ.ም ገቢዎች ሚኒስቴር

ገቢ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
09/06/2026
የ2019 ረቂቅ በጀት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ሆኖ እንዲቀርብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ
ሰኔ 02 / 2018 ዓ.ም ገቢዎች ሚኒስቴር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል።
የ2019 የፌዴራል መንግሥት በጀት የዐሥር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማት እና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊሲካል ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ፣ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች እና ዓላማዎች እንዲሁም በመንግሥት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግሥትን የፋይናንስ አቅም እና አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮ እና ኃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
በዚሁ መሠረትም ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግሥታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2 ትሪሊዮን 339 ቢሊዮን 268 ሚሊዮን 126 ሺህ 738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሦስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት) ብር በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል።
ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
08/06/2026
ቀጣሪ ድርጅቶች የወጪ መጋራትን ለማስተገበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
ሰኔ 01 / 2018 ዓ.ም ገቢዎች ሚኒስቴር
መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ቀጣሪ ድርጅቶች የወጪ መጋራትን ለማስተገበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ/1 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ትምህርት መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተግባሩ ታምሩ ጠየቁ፡፡
የወጪ መጋራት ተቀዳሚ ዓላማ የመንግስትን የፋይናንስ ጫና በመቀነስ የከፍተኛ ትምህርትን ጥራት ተደራሽነት እና ፍትሃዊነትን ማሳደግ መሆኑን የገለጹት አቶ ተግባሩ ይህም ተግባራዊ እንዲደረግ የቀጣሪ ድርጅቶች ሚና የጎላ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
ቀጣሪ ድርጅቶች ሠራተኛ ሲቀጥሩ ከየትኛው የትምህርት ተቋም ወይንም ዩኒቨርስቲ እንደተመረቀ የመጠየቅ ግዴታ፣ ከደመወዝ ላይ ቀንሶ ገቢ የማድረግ ኃላፊነት እና ስለአተገባበሩ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰው ይህንን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
06/06/2026
በጉምሩክ ኮሚሽን የቱሉ ዲምቱ ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ ስራ ተጀመረ
ግንቦት 29 / 2018 ዓ.ም ገቢዎች ሚኒስቴር
ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሚሽኑ ለአገር የሚጠቅም ሕንፃ ግንባታ እንደሚከናወን በማውሳት ግንባታው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በግንባታ ስራ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ኮሚሽነሩ በንግግራቸውም የሚገነቡት ሦስት ሕንፃዎች የቢሮ፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ የተለያዩ አገልግሎቶች እና ለአካባቢው ማሕበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ክቡር ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) የሸገር ከተማ ከንቲባ በግንባታ ማስጀመሪያው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የጉምሩክ ኮሚሽን ቱሉ ዲምቱ ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ በጥራትና እና በፍጥነት መጠናቀቅ የቅርብ ክትትል ከማድረግም በላይ ሁሉን አቀፍ ደጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ባለፉት 75 አመታት የማሕበራዊ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ውስጥ ብዙ የሰራ መሆኑን ተናግረው ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር እየሰሩ የሚገኙት የአቅም ግንባታ፣ የሲስተም ዝግጅት፣ ካርጎ ትራኪንግ ፣ የሠው ሃብት ልማት እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ መሳተፋችን የአዲስ አበባ ዩ ዩኒቨርስቲ በጉምሩክ ውስጥ አሻራ እንዲኖረን ያስችለናል ብለዋል።
ይህ ሁለገብ ሕንፃ ሁለት ባለ ስምንት እና አንድ ባለ አስር ወለል የሕንፃ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚከናወን ሲሆን በሸገር ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው የሸገር ሪል ስቴት ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሕንፃ ግንባታውን እንደሚያከናውን ታውቋል።
ገዛኸኝ መካሻ
የትናየት እንዳያፍሩ
፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
06/06/2026
ስለተጨማሪ ዕሴት ታክስ
ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ስለተጨማሪ እሴት ታክስ ለግናዛቤዎ
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.